ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሁለት ክፍለከተሞች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲደረግ ዋለ።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኘው አፄ-ዘርዓያዕቆብ ክ/ፍለከተማ ጎሸባዶ ቀበሌ አዋሳኝ በሆነው መጥቆሪያ ቀበሌ እና ወርቅገር ጉር ገብርኤል በተባለ ቦታ እና በእቴጌ ጣይቱ ክ/ከተማ ሳሪያ አዋሳኝ በሆነው ዘንዶጉርና በዞ በተባሉ ቀበሌዎች ከጥዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ከጡት ቆራጩ አብይ አህመድ ኃይል ጋር ከፈተኛ ትንቅንቅ በማድርግ ድልን እየተጎናፀፈች ትገኛለች።

የአረመኔው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ጥምር ጦር ብሎ በሚጠራው መከላከያ፤ሚኒሻና አድማ መከላከያ ከአማራው አብራክ በወጡ የባንዳ ስብስብ እየተመራ ከደብር ብርሃን መነሻውን ያደርገው በሁለት ግንባር በጎሽባዶ አራዳ መጥቆሪያ ውጊያ በመክፈት እንዲሁም በካሲማ በዞ አቅጣጫ መነሻውን ከኩየለሽ በማድረግ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ሶስተኛ ሻለቃ አናብስቶች ጋር በአደረገው አውደ ውጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሲሆን በሚገርም ሁኔታ የአሳምነውን አናብስቶች ብትር መቋቋም ያቃተው የአብይ አህመድ ኃይል ወደ ኃላ ማፈግፈግ እያደረገ ባለበት ሰዓት ለምን ወደ ኃላ ታፈገፍጋለህ ግጠም በማለት የአብይ አህመድ መከላከያ፣አድማ መከላከል እና የሚኒሻ ኃይል እርስ በእርስ በዲሽቃ በተጋዘ ውጊያ እየተገዳዳለ ይገኛል።

መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው።

አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ጥር 5/2018 ዓ.ም
👍2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የኮሩ ተወርዋሪ ልዩ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠና የወሰዱ አባላት ተመረቁ።

በዛሬው እለት ጥር 5/2018 ከመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የሰራዊት አባላት ውስጥ ለመጀመሪያ ዙር በልዩ ስልጠና የተመለመሉ በአግባቡ ለወራት ሲሰጥ የቆየውን ሁሉን አቀፍ ስልጠና በማጠናቀቅ በዛሬው እለት የኮሩ አመራር ባሉበት ምርቃቱ ተካሂዷል።

በአርበኛ ማንዴላ እያዩ ሰብሳቢነት የሚመራው ይህ ኮር በተሻለ ሁኔታ ግዳጆችን ለመፈፀምና እዝ እና ሰንሰለትን የጠበቀ ድርጅታዊ መርህን ያከበረ ፅናት ያለው ተሻጋሪ ሰራዊት ከማፍራት አንፃር ስልጠናን አማረጭ በማድረግ የተለያዩ ግዳጆችን ከመፈፀም ባሻገር በዙር ሁሉንም ሰራዊት ለማብቃት አቅዶ እየሰራ መሆኑን አፅኖት በማድረግ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በተሳካ ሁኔታ መቋጨት ተችሏል። ቀጣይ ይሄን ስልጠና ያልወሰዱ የኮሩ የሰራዊት አባላት በጀት እየተመቻቸ ስልጠናው እንደሚቀጥል አንድ የእቅድ አካል ሆኖ ተግባራዊነቱ እውን ይሆናል።

በዚህ የምርቃን ስነ ስርአት የተገኙ የኮር አመራሮች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ከማስተላለፍ ባሻገር የብልፅግና የማፊያ ስርአት በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ሁሉን አቀፍ የህልውና ጥቃት ምን ያህል ዘግናኝ እንደሆነ በመግለፅ፤ ይሄን ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ከአማራ ህዝብ ትክሻ ለማውረድ የተደራጀና ስልጡን አዋቂ የፋኖ ሰራዊት በመገንባት ረገድ ብዙ ማቀድና መታገል በመጨረሻም አሸናፊ በመሆን ሰዋዊ ስርአትን እውን ማድረግ ተገቢ እንደሆነ እና በፍትህና በነፃነት እጦት ለዘመናት የተገፋውን ወገናችን ነፍጥ አንግበን ሁለንተናዊ ፍትህን ፍለጋ ከወጣን ከሁለት አመት ተኩል በላይ እየታገልን እውነተኛ መርህን በማፅደቅ ድርጅታዊ መዋቅርን እያሳደግን ከፍታዎችን እየወጣን እንገኛለን። ስለዚህ ማሸነፋችን እውን ነው ፤ በአላማ ፅናት የተፈተነ ታጋይና መሪ የትግሉን ፍሬ ይበላል።የህዝባችንና የተሰው ጓዶቻችን ቃል ኪዳን እውን እናደርጋለን እና መሰል መልእክቶች በጊዜው ተላልፈዋል።

ይሄነን ስልጠና ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው ድረስ በመከታተል አስፈላጊውን አይነት የስልጠና ፕሮግራም በማዘጋጀት እና በመከታተል የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ዲ/ን እስጢፋኖስ ሙላት የአንበሳውን ድርሻ ሲወስድ ወታደራዊ ስልጠናዎችን በመስጠት ደግሞ አርበኛ 50 አለቃ ደስታው ሙላት ፣ አርበኛ 10 አለቃ አማንኤል አለባቸው እና አርበኛ ዮናስ ወልዴ በመተጋገዝ ስልጠናውን በጥራት አጠናቀዋል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳች!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥር 5/2018
👍1
አፋብኃ በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ባደረገው ትቅንቅ የተማረከ የአገዛዙ ሃይል እና ተተኳሽ
🙏1
ሰበር መረጃ - የወልድያ ዙሪያ ትንቅንቅ | ደረሳዎች ላይ ያነጣጠረው የውጫሌው አፈሳ | የደብረብርሃንና ጎንደር ዙሪያ አውደውጊያ
🙏1
ካላኮርማ ክፍለ ጦር ጉባላፍቶ እና ራያ ቆቦ ወረዳ በሁለት ግንባር ከባድ ውጊያ በማካሄድ ድል አስመዘገቡ::

ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጥር 5/2018 ዓ.ም ጦር ጉባላፍቶ ወረዳ በቅሎ ማነቂያ እና ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ በሁለት ግንባሮች ከባድ ውጊያ በማካሄድ በርካታ ጥምር ዙፋን ጠባቂ አገር አፍራሽ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

ካላኮርማ ክፍለ ጦር 2ኛ እና 3ኛ ሻለቃ ከእንጃፋት ወንዳች ኩልመስክና ድልብ የመጣንና በቅሎ ማነቂያን ይዞ ወደ ቃሊም ማጥቃት ያደረገን ጠላት ባግባቡ መክተው በመዋልና በርካታ ሰራዊቱን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ምሽግ ያደረገውን በቅሎ ማነቂያ ከተማና ዙሪያውን በማስለቀቅ ወታደራዊ ገዥ መሬት መቆናጠጥም ችለዋል::

በሌላኛው ግንባር ካላኮርማ ክፍለ ጦር 1ኛ እና 4ኛ ሻለቃ እንዲሁም የ5ኛ ሻለቃ ቃኝ ጥር 5/2018 ዓ.ም ቀትር አካባቢ ጀምሮ ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በርካታ የፋሽስቱ አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ላይ ከባድ ጥቃት በማድረስ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዝግበዋል::

በዚህም የምስራቅ አማራ ኮር ሁለቱ ካላኮርማ ክፍለ ጦር በሁለት ግንባሮች ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ቃሊምና ወልድያ ዙሪያ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ ካደረጉት ከምስራቅ አማራ ኮር አንድ አሃዶች ጋር የተናበበና የተቀናጀ ሚዛን ጠባቂ ግዳጅ በመፈፀም አመርቂ ድል አስመዝቧል::

የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን በግፍ ረሽኗል:: መረጃውን በዝርዝር ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ይሆናል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 5/2018 ዓ.ም
👍2
ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ወልድያ ዙሪያ እና ቃሊም በመካናይዝድና በድሮን የታገዘ የጠላት ሃይል ጋር ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::

​የሐውጃኖ ክፍለ ጦር ጥር 5/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ ከአሳምነው ክፍለ ጦር ጋር በመጣመር ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ በጠላት ላይ የተለመደውን ገድላቸውን በመፈፀም ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል::

የአብይ አህመድ የዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በድሮን፣ በመድፍ፣ በታንክና በሞርታር ታግዞ የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት የሐውጃኖ አንበሶች በላቀ ወታደራዊ ጥበብ መክተው በማክሸፍና ከባድ መልሶ ማጥቃት በማድረግ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

​ጥር 5/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 የተጀመረውና እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ለ13 ሰዓታት ያህል ያለማቋረጥ ሲካሄድ የዋለውና ጠላት በመቶዎች ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ በሆነበት እጅግ ከባድ ፍልሚያ በሐውጃኖ ክፍለ ጦር ሙሉ የበላይነት ተጠናቋል።

በታሪካዊው የአውደ ውጊያ ግንባር ጀግናው የሐውጃኖ ክፍለ ጦር በአርበኛ ካሳ አበበ እና በምክትሉ አርበኛ ደሳለኝ መራጊያው እየተመራ ከምስራቅ አማራ ኮር አንዱ መንትያው አሳምነው ክፍለ ጦር ጋር ጎን ለጎን ተሰልፎ በቃሊም ሚጦ በኩል ባደረገው ከባድ ማጥቃት፣ በከፍተኛ ዘመናዊ ትጥቅ የታገዘውን የጠላት ኃይል በከበባ ውስጥ አስገብቶ እንደ ቅጠል አርግፎት ውሏል::

​በዚህ ታሪካዊ ፍልሚያ የተገኙ ድሎች፦
👉​የሰው ኃይል ኪሳራ፦ በጠላት ወገን ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ተመዝግቧል። በሐውጃኖ ክፍለ ጦር እና አሳምነው ክፍለ ጦር ጥምረት በመቶዎች የሚቆጠር ጠላት ሙትና ቁስለኛ ብሎም ምርኮኛ ሆኗል::

​የተማረኩ ትጥቆች፦
👉​ 8 ክላሽ
👉​1100 የሚደርስ የተለያየ አይነት ተተኳሽ
👉20 የክላሽ ካዝና
👉5 የሞርተር ቁንቡላ
👉የሰው ሃይል ሙሉ ዶክሜንት

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 5/2018 ዓ.ም
1🙏1
የራያ ቆቦ ወርቄ የአገዛዙ ሚሊሻዎች በራያ ሮቢት ሶስት በመግደልና አምስት በማቁሰል ስምንት ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን በግፍ ጨፈጨፉ::

የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና አገዛዝ ጋር በመወገን የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙ ያሉት የራያ ወርቄ ሚሊሻዎች በትናትናው ዕለት ጥር 5/2018 ዓ.ም ከብልፅግና መከላከያ ጋር ሆነው ካላኮርማ ክፍለ ጦር ጋር ባደረጉት ውጊያ በደረሰባቸው ከባድ ሽንፈት ሸሽተው ወደ ሮቢት ከተማ በመግባት ስምንት ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን በጥይት ጨፍጭፈዋል::

በነፃነት ታጋዩ ፋኖ ሲሸነፉ ፈሪ ሁሌም አህያውን ትቶ ዳውላውን ነውና እነዚህ ህዝቡ በአደባባይ የሚያውቃቸውና ነገን በተስፋ እየጠበቀ በፍፁም ትግስት የያዛቸው ህዝብን ከህዝብ የማፋጀት አላማ ያነገቡ የወርቄ ታጣቂዎች ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ገብተው ንፁሃንን በግፍ ሲጨፈጭፉ አገዛዙም የሚፈልገው ድርጊት በመሆኑ በዝምታ ማየትን መርጧል::

እነዚህ ፀረ-አማራ ታጣቂዎች ስራቸው የሚመዘዘው ከኦህዴድ ብልፅግና ሲሆን የተሰጣቸውን ሃይማኖትን መሰረት አድርጎ ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት አላማ አንግበው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ንፁሃን ያልታጠቁ አማራዎችን በግፍ እየጨፈጨፉ ቀጥለዋል::

በዚህም በትናትናው ዕለት ጥር 5/2018 ዓ.ም ራያ ቆቦ ሮቢት አቶ ሽመልስ ሲሳይ የተባለ ጋሪ እየገፋ በቀን ስራ የሚተዳደር ግለሰብ እና ሁለት ወንድና ሴት (ትግስት እና አያሌው መለሰ) የተባሉ የሆቴል አስተናጋጆችን በጥይት ደብድበው ሲገድሉ አምስት ተጨማሪ በማቁሰል ባጠቃላይ ስምንት ንፁሃን ያልታጠቁ አማራዎች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል::

ከዚህ ግፍ በተጫማሪም ፀረ-አማራ ሚሊሻዎቹ ሮቢት ከተማ የተለያዩ ሱቆችንና የንግድ ቦታዎችን ንብረት ዘርፈው መሄዳቸውን ከከተማው ነዋሪዎች ለማረጋገጥ ችለናል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 6/2018 ዓ.ም
🙏1
በመካነሰላም ግንባር የ45ተኛ ክፍለ ጦር አንድ ቲም የሚሆኑ አባላት ተደመሰሱ!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ሰራዊት ሰሞኑን ለተከታታይ ቀናት በተደረገ ግምገማ መሰረት የአመራር ሪፎርም ከተደረገለት በኃላ በትናንትናው እለት በመካነሰላም ግንባር ድል ቀንቶታል:: ከመካነሰላም ከተማ በመነሳት ወደ ሰኞ ገበያ አቅጣጫ ተንቀሳቅሶ በወገን ኃይል ላይ ጉዳት ለማድረስ ተኩስ የከፈተውን ጠላት በመልሶ ማጥቃት ጉዳት ያደረሱበት የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር 1ኛ ጥላሁን ፈንታው ሻለቃ እና 2ተኛ ጌታሰው አስረስ ሻለቃ ፋኖዎች አንድ ቲም የሚሆኑ ወታደሮችን ሲደመስሱ 3 አቁስለዋል::

ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ ስንደው ገዜ እና የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ ኮማንዶ ጀንበሩ ጌታቸው በመሩት በትናንቱ ኦፕሬሽን ያልታሰበ ጉዳት የደረሰበት የጠላት ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ ተደናግጦ ስለነበር የወረዳው ካቢኔ አባላት ጭምር ከተማይቱን ለቀው ሜዳ ላይ ማደራቸው ተርጋግጧል:: የተደመሰሱ አባላቱን አስከሬን በ3 አምቡላንስ ጭኖ መካነሰላም ከተማ ወደሚገኘው ጁኒየር ትምህርት ቤት የወሰደው ጠላት ጁኒየር ትምህርት ቤትን ካምፕ አድርጎት መክረሙ አንሶት እንደ መካነ-መቃብር እየተጠቀመው መሆኑ ይታወቃል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም
1🙏1
በአውደ ውጊያ በፋኖ የተሸነፈው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ቃሊም ዙሪያ የድሮን ጥቃት በመፈፀም ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን ጨፈጨፈ::

ጥር 5/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ 13 ሰዓት በፈጀ ከባድ ውጊያ በርካታ እግረኛ ሰራዊቱ በከበባ የተመታበት ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከወልድያ ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘው ቃሊም ከተማ ዙሪያ ስድስት ጊዜ የድሮን ጥቃት በመፈፀም ንፁሃን ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ አማራዎችን ህይወት ቀጥፏል:: የተወሰኑትም ቀላልና ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ በእንስሳቶች እንዲሁም ቤትና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል::

በድሮን ጥቃቱ አንድ የቤተክርስቲያን ጠባቂ አባትን ጨምሮ የሌሎችም ህይወት ሲያልፍ ቀላልና ከባድ ቁስለኞችም መኖራቸውን ለማረጋገጥ ችለናል:: ሌሎች ንፁሃኖችም ከወልድያ ከተማ በሚወነጨፍ መድፍ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ቀላልና ከባድ ቁስለኛ የሆኑም አሉ:: መድፉ በእንስሳቶችና በቤት ንብረት ላይም ከባድ ጉዳት አድርሷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 6/2018 ዓ.ም
👍1🙏1