ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከእያንዳንዱ ሚዲያዎች በስተጀርባ ረጃጅም የሴራ ፖለቲካ እጆች እንዳሉ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን...?

አሁን ላይ የአማራ ፋኖን ትግል ደጋፊ፣ዘጋቢና አጋዥ መስለው የተቋቋሙ ሚዲያዎች መስራቾቻቸውን፣የቦርድ አባሎቻቸውንና ስራ አስኪያጆቻቸውን ታውቋቸው ይሁን? በዋናነት የሳተላይትና ዩ ቱብ ቤዝድ (satellite&youtube based) ሚዲያዎች፣አልፎ አልፎ ከማኀበራዊ ትስስር አውታሮች ደግሞ ፌስቡክና ቲክታክ (facebook& tiktok) ላይ ውለው የሚያድሩትን ግለሰቦችና ቡድኖች ከጀርባ ያላቸውን ፍላጎት የአማራ ህዝብ ይረዳው ይሆን?

በተለይ በአማራ ህዝብ የሕልውና ትግል ስም የሳተላይትና ዩቱብ ሚዲያ ከፍተው እርስ በእርስ ሲያጋድሉ የሚውሉትን የሚዲያ ባለቤቶች፣የቦርድ አባላት፣ዋናና ምክትል ስራ አስኪያጆች ማንነት፣ምንነት፣ፖለቲካዊ ፍላጎት፣የት አገራት እንደሚኖሩ፣የቤተሰብ ሁናቴ፣የግል ስራ፣ሐይማኖት፣ለአገዛዙ ያላቸው አጠቃላይ ሁኔታ፣የፋኖን ትግል የሚያዩበት መነፀር፣ የግል ስብዕናቸውና የጀርባ ታሪካቸው ወዘተ... ይታዎቅ ይሁን?? አይመስለኝም።

ምድር ላይ የሚታገሉ ሃቀኛ የፋኖ አመራሮችን፣ፋኖዎችን፣ ትግሉን የሚያግዙ አካላትን፣ተቋማትን፣ድርጅቶችንና በአጠቃላይ የትግሉ አስኳል የሆኑ አካላትን መሬት ላይ በስመ ፋኖ አገዛዙ ካሰማሯቸው የይስሙላ ታጣቂዎችና የፋኖ አመራሮች "ነን" ባዮች ጋራ ተናበው እንዴት እንደሚያጠቁ ተገልጦላችሁ ይሆን??

ከአንድ ዓመት ተኩል ቀደም ብሎ በቀድሞ አጠራሩ የ "አማራ ፋኖ በጎጃም" (አፋጎ) ከእኔ ጋራ ግጭት ውስጥ እንዲገባ፣ አስቀድመው፣ በእኔ ላይ ከፍተኛ የጥላቻ ቅስቀሳ፣በሬ ወለድ ስም ማጥፋት(defamation)፣ የስብዕና ግድያ (character assassination)፣መልካም ስምና ዝናዬን (Good name and reputation) በማጥፋት በገዛ ጦራችን ከበባ እንዲፈፀምብን ከፍ ሲል ደግሞ የህይወት መሰዋዕትነት በማስከፈል ጎጃም ላይ ታሪካዊ ስህተት እንዲሰራ ሲቀሰቀሱ የነበሩ ሚዲያዎችና ቧልተኞቻቸው ዛሬ ላይ የት እንዳሉ ታውቁ ይሆን?እነ ማ እንደሆኑ ልብ ብላችሁ ይሆን?

ያኔ በእኛ ላይ ከውስጥም ከውጭም ሲዘምቱ የነበሩት ራሳቸውን ፍፁም የትግሉ አራማጅ፣ተቆርቋሪ፣አዳኝ፣መሪና አለኝታ አስመስለው ነበረ። በአንፃሩ እኛን ደግሞ የትግሉ ስጋቶች አድርገው በመቀስቀስ እንድንወገር ሲያቧልቱ ነበረ። በጣም አስቂኙ ጉዳይ ግን እነዚህ በውስጥም በውጭም በሚዲያ፣ በጋዜጠኛ፣በቃል አቀባይና በፖለቲከኛ ስም በእኛ ላይ በሀሰት ሲዘምቱ የነበሩት አገዛዙን በዋናነት የብአዴንን መዋቅር አንገት ለአንገት ተናንቀን ካፈረስነው በኋላ እጃቸውን እየጎተትን ከባርነትም ከፍራቻም ነፃ ያወጣናቸው አንጊዎች መሆናቸው ነው።ዛሬ ደግሞ መፅናት አቅቷቸው እየተንጠባጠቡ ወትሮም ከባርነት ተጎትተው ወደ ወጡበት ስፍራ እየተመለሱ ነው።  በዚህ አጋጣሚ እጅግ በጣም ጥቂት በሐቅ የሚታገሉና የሚያታግሉ ሚዲያዎችና በለሙያዎቻቸውን አልዘነጋንም።

ለማንኛውም እኛ ሐቀኞች ከነ ሐቃችን እስከ ቀራኒዮ የሕልውና አደጋ ውስጥ ለገባው ህዝባችን ያለማዎላዎል ፀንተን እንታገላለን።

በጋዜጠኛ፣በፋኖ፣በአርበኛ፣በካፒቴን ..ወዘተ...ስሞች እየዘለሉ ለአገዛዙ ቢገብሩ እንዳይደንቃችሁ። የፀኑ፣የሚፀኑና የሚያፀኑ ዝም ያሉ ጀግና ታጋይ ልጆች ስላሏችሁ።

በቀጣይ የሚዲያና የጋዜጠኛ ሚና በትግሉ ምን መሆን አለበት? ምንድን ነውስ? ዛሬ ላይ እዚህም አዛም የምናያቸው ጋዜጠኞች ወይስ ደላሎች የሚሉትን እናነሳለን።

እንፅና!!!

@ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው - የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የሚድያ እና ዝግጅት መምሪያ ኃላፊ
3
የምኒልክ ዕዝን ክንድ መቋቋም ያቃተው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከተግባር ይልቅ "ውሸት"ን ትልቅ የአውደ ውጊያ ግንባር ካደረገው አመታቶች የተቆጠሩ ሲሆን ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሎበት በምታዩት መልኩ በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስም የሃሰት መግለጫ እያወጣ ይገኛል::

እኛም እንላለን እናንተም በውሸታችሁ ቀጥሉ እኛም በሐቀኛ ተግባራችን! በያዝናቸው አመርቂ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ድሎቻችን ታጅበን ለመጨረሻው ግብ ድልና ነፃነታችን እየታገልን እንገኛለን::

ግፈኞች ሆይ ጦራችሁም ወሬያችሁም አይፈታንም:: አላማችንን ላፍታም ቢሆን አያደናቅፈውም!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 5/2018 ዓ.ም
በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ተወርዋሪዎችን አስመረቀ!!

በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የኮሩ ተወርዋሪ ልዩ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠና የወሰዱ አባላት ተመረቁ።

ጥር 5/2018 ከመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የሰራዊት አባላት ውስጥ ለመጀመሪያ ዙር በልዩ ስልጠና የተመለመሉ እና በአግባቡ ለወራት የሰለጠኑ የቆየውን ሁሉን አቀፍ ስልጠና በማጠናቀቅ በዛሬው እለት የኮሩ አመራር ባሉበት የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተከናውኗ።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳች!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
3🙏1
በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሁለት ክፍለከተሞች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲደረግ ዋለ።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኘው አፄ-ዘርዓያዕቆብ ክ/ፍለከተማ ጎሸባዶ ቀበሌ አዋሳኝ በሆነው መጥቆሪያ ቀበሌ እና ወርቅገር ጉር ገብርኤል በተባለ ቦታ እና በእቴጌ ጣይቱ ክ/ከተማ ሳሪያ አዋሳኝ በሆነው ዘንዶጉርና በዞ በተባሉ ቀበሌዎች ከጥዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ከጡት ቆራጩ አብይ አህመድ ኃይል ጋር ከፈተኛ ትንቅንቅ በማድርግ ድልን እየተጎናፀፈች ትገኛለች።

የአረመኔው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ጥምር ጦር ብሎ በሚጠራው መከላከያ፤ሚኒሻና አድማ መከላከያ ከአማራው አብራክ በወጡ የባንዳ ስብስብ እየተመራ ከደብር ብርሃን መነሻውን ያደርገው በሁለት ግንባር በጎሽባዶ አራዳ መጥቆሪያ ውጊያ በመክፈት እንዲሁም በካሲማ በዞ አቅጣጫ መነሻውን ከኩየለሽ በማድረግ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ሶስተኛ ሻለቃ አናብስቶች ጋር በአደረገው አውደ ውጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሲሆን በሚገርም ሁኔታ የአሳምነውን አናብስቶች ብትር መቋቋም ያቃተው የአብይ አህመድ ኃይል ወደ ኃላ ማፈግፈግ እያደረገ ባለበት ሰዓት ለምን ወደ ኃላ ታፈገፍጋለህ ግጠም በማለት የአብይ አህመድ መከላከያ፣አድማ መከላከል እና የሚኒሻ ኃይል እርስ በእርስ በዲሽቃ በተጋዘ ውጊያ እየተገዳዳለ ይገኛል።

መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው።

አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ጥር 5/2018 ዓ.ም
👍2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የኮሩ ተወርዋሪ ልዩ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠና የወሰዱ አባላት ተመረቁ።

በዛሬው እለት ጥር 5/2018 ከመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የሰራዊት አባላት ውስጥ ለመጀመሪያ ዙር በልዩ ስልጠና የተመለመሉ በአግባቡ ለወራት ሲሰጥ የቆየውን ሁሉን አቀፍ ስልጠና በማጠናቀቅ በዛሬው እለት የኮሩ አመራር ባሉበት ምርቃቱ ተካሂዷል።

በአርበኛ ማንዴላ እያዩ ሰብሳቢነት የሚመራው ይህ ኮር በተሻለ ሁኔታ ግዳጆችን ለመፈፀምና እዝ እና ሰንሰለትን የጠበቀ ድርጅታዊ መርህን ያከበረ ፅናት ያለው ተሻጋሪ ሰራዊት ከማፍራት አንፃር ስልጠናን አማረጭ በማድረግ የተለያዩ ግዳጆችን ከመፈፀም ባሻገር በዙር ሁሉንም ሰራዊት ለማብቃት አቅዶ እየሰራ መሆኑን አፅኖት በማድረግ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በተሳካ ሁኔታ መቋጨት ተችሏል። ቀጣይ ይሄን ስልጠና ያልወሰዱ የኮሩ የሰራዊት አባላት በጀት እየተመቻቸ ስልጠናው እንደሚቀጥል አንድ የእቅድ አካል ሆኖ ተግባራዊነቱ እውን ይሆናል።

በዚህ የምርቃን ስነ ስርአት የተገኙ የኮር አመራሮች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ከማስተላለፍ ባሻገር የብልፅግና የማፊያ ስርአት በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ሁሉን አቀፍ የህልውና ጥቃት ምን ያህል ዘግናኝ እንደሆነ በመግለፅ፤ ይሄን ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ከአማራ ህዝብ ትክሻ ለማውረድ የተደራጀና ስልጡን አዋቂ የፋኖ ሰራዊት በመገንባት ረገድ ብዙ ማቀድና መታገል በመጨረሻም አሸናፊ በመሆን ሰዋዊ ስርአትን እውን ማድረግ ተገቢ እንደሆነ እና በፍትህና በነፃነት እጦት ለዘመናት የተገፋውን ወገናችን ነፍጥ አንግበን ሁለንተናዊ ፍትህን ፍለጋ ከወጣን ከሁለት አመት ተኩል በላይ እየታገልን እውነተኛ መርህን በማፅደቅ ድርጅታዊ መዋቅርን እያሳደግን ከፍታዎችን እየወጣን እንገኛለን። ስለዚህ ማሸነፋችን እውን ነው ፤ በአላማ ፅናት የተፈተነ ታጋይና መሪ የትግሉን ፍሬ ይበላል።የህዝባችንና የተሰው ጓዶቻችን ቃል ኪዳን እውን እናደርጋለን እና መሰል መልእክቶች በጊዜው ተላልፈዋል።

ይሄነን ስልጠና ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው ድረስ በመከታተል አስፈላጊውን አይነት የስልጠና ፕሮግራም በማዘጋጀት እና በመከታተል የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ዲ/ን እስጢፋኖስ ሙላት የአንበሳውን ድርሻ ሲወስድ ወታደራዊ ስልጠናዎችን በመስጠት ደግሞ አርበኛ 50 አለቃ ደስታው ሙላት ፣ አርበኛ 10 አለቃ አማንኤል አለባቸው እና አርበኛ ዮናስ ወልዴ በመተጋገዝ ስልጠናውን በጥራት አጠናቀዋል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳች!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥር 5/2018
👍1
አፋብኃ በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ባደረገው ትቅንቅ የተማረከ የአገዛዙ ሃይል እና ተተኳሽ
🙏1
ሰበር መረጃ - የወልድያ ዙሪያ ትንቅንቅ | ደረሳዎች ላይ ያነጣጠረው የውጫሌው አፈሳ | የደብረብርሃንና ጎንደር ዙሪያ አውደውጊያ
🙏1
ካላኮርማ ክፍለ ጦር ጉባላፍቶ እና ራያ ቆቦ ወረዳ በሁለት ግንባር ከባድ ውጊያ በማካሄድ ድል አስመዘገቡ::

ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጥር 5/2018 ዓ.ም ጦር ጉባላፍቶ ወረዳ በቅሎ ማነቂያ እና ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ በሁለት ግንባሮች ከባድ ውጊያ በማካሄድ በርካታ ጥምር ዙፋን ጠባቂ አገር አፍራሽ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

ካላኮርማ ክፍለ ጦር 2ኛ እና 3ኛ ሻለቃ ከእንጃፋት ወንዳች ኩልመስክና ድልብ የመጣንና በቅሎ ማነቂያን ይዞ ወደ ቃሊም ማጥቃት ያደረገን ጠላት ባግባቡ መክተው በመዋልና በርካታ ሰራዊቱን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ምሽግ ያደረገውን በቅሎ ማነቂያ ከተማና ዙሪያውን በማስለቀቅ ወታደራዊ ገዥ መሬት መቆናጠጥም ችለዋል::

በሌላኛው ግንባር ካላኮርማ ክፍለ ጦር 1ኛ እና 4ኛ ሻለቃ እንዲሁም የ5ኛ ሻለቃ ቃኝ ጥር 5/2018 ዓ.ም ቀትር አካባቢ ጀምሮ ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በርካታ የፋሽስቱ አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ላይ ከባድ ጥቃት በማድረስ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዝግበዋል::

በዚህም የምስራቅ አማራ ኮር ሁለቱ ካላኮርማ ክፍለ ጦር በሁለት ግንባሮች ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ቃሊምና ወልድያ ዙሪያ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ ካደረጉት ከምስራቅ አማራ ኮር አንድ አሃዶች ጋር የተናበበና የተቀናጀ ሚዛን ጠባቂ ግዳጅ በመፈፀም አመርቂ ድል አስመዝቧል::

የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን በግፍ ረሽኗል:: መረጃውን በዝርዝር ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ይሆናል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 5/2018 ዓ.ም
👍2