ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በበላይ እዝ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አሣምነው ብርጌዴ ድል ቀናው::

የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ሠራሁ ባለው መረጃ መሰረት ለተልዕኮ ወደ ዕብናት በለሳና ሊቦ ከምከም የተላኩ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ሕዋሶች አሣምነው ብርጌድን ለማጥመድ አስቦ ከደብረ ታብር ከተማ ተነሥቶ መቁረጫ ቦታዎች ላይ ደፈጣ ለማድረግ ቅዠት የሆነ ከባድ ሒሳብ ሰርቶ ነበር። ነገር ግን ፈጣኖቹ የውባንተ አባተ የግብር ልጆች መረጃቸውን በሁሉም አቅጣጫ አሥፍተው መረጃን በመረጃ አጣፍተው ጠላት ሊይዘው የነበረውን የደፈጣ ቦታ ቀድመው 10:00 ይዘውታል።

ጨካኙና አውሬው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት አገር አማን ብሎ ነፍጠኞቹን በደፈጣ ሊበላ ቋምጦ ደፈጣ እይዛለሁ ያለበትን ወሳኝ ቦታ የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ልጆች በመያዝ ጠላትን የሚፈልጉበት ቦታ አሥገብተውታል።

ጠላት ደፈጣ የተጣለበት ቦታ ሰተት ብሎ ገብቷል። በዚህን ጊዜ ትንታጎቹ ነፍጠኛ ዓምሐሮች ከጠዋቱ 12:00 ጀምረው ጠላትን በቦምብና በክላሽ በጨበጣ አደባይተውታል። መብረቅ የወረደባቸው የአቢይ ዙፋን ጠባቂዎች በጭንቀት የሚይዙ የሚጨብጡትን አጥተው እግራቸው ወደመራቸው እግሬ አውጭኝ ሲሉ ሌሎቹም ደግሞ የነፍጠኞቹ የሣትራት ሆነዋል።

ከደብረ ታቦር ከተማ በ06 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ባለችው ''ሎል አፋፍ'' ላይ በተደረገ የደፈጣ ምት የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በቁጥር 16 ሲደመሰስበት፣ ከ10+ ከባድ ቁሥለኛ ሲሆንበት ፣ ቁሳዊና አካላዊ ኪሳራ ሲደርስበት የተደምሳሾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል። ደብረ ታቦር ሆሥፒታልና ጤና ጣቢያዎች በአቢይ አሕመድ ጠባቂ ቁሥለኞች ተጨናንቆ ይገኛል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን

@በ አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ : ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል ሃላፊ ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
1🙏1
ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ መምሪያ ለወራቶች የሰለጠኑ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን አስመረቀ::

ምኒልክ ዕዝ የልዩ ዘመቻ መምሪያ አሃድ ከሆኑት መካከል ለወራት የሰለጠኑ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች የዕዝ የኮርና የክፍለጦሩ አመራሮች በተገኙበትና መልክት ባስተላለፉበት ሁኔታ ተመርቀዋል::

ከፍተኛ የዕዙ አመራሮችም የተጀመረውን የፖለቲካ ትጥቅ ትግል ከግብ ለማድረስና የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ብሎም ቀጣይነት ያለው ነፃነት ለመጎናፀፍና የሃገራችን ባለቤት ለመሆን በፅናትና ቁርጠኝነት መታገል ብቻኛ አማራጭ መሆኑን ለተመራቂዎች አስገንዝበዋል::

ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን ያስመረቁት በልዩ ዘመቻ መምሪያው ስር የሆነው አሃድ ወታደራዊ አዛዥና ምክትል ወታደራዊ አዛዥ የሆኑት አርበኞችም ለተመራቂዎች መልክታቸውን አስተላልፈዋል::

የልዩ ዘመቻ ሰልጣኝ ተመራቂዎች ዛሬ የተመረቃችሁ ምኒልክ ዕዝ የልዩ ዘመቻ እንደስማችሁ ልዩ ሰልጣኝ ተመራቂዎች ለበርካታ ወራት ፀሀዩን: ብርዱን: ቁሩን በርካታ ውጣውረዱ ሳይበግራችሁ ባልተመቻቸ ሁኔታ ተቋቁማችሁ ለዚህች ልዩ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ የናንተ ስልጠና ለየት የሚያደርገው ያኔ በጣት በምንቆጠረበት ጊዜ ሳይሆን አሁን በሺዎች ብሎም በሚልዮኖች በትጥቅም ይሁን በሰው ኃይል አቅማችን እንዲሁም የማድረግ አቅማችን ትልቅ የስኬት ጫፍ ላይ ባለንበት ጊዜ መቀላቀላችሁ በተጨማሪም  የዚህን አንባገነን ስርዓት ግፍ በደል እና ሰቆቃ አድራሽነት ማንም ሳይጎተጉታችሁ እያንዳንዳችሁ ቤት አንኳኩቶ የገባ በመሆኑ ያለማንም ቀስቃሽ በቃኝ አሻፈረኝ ብላችሁ ይህን ትልቅ የትጥቅ ትግል የተቀላቀላችሁ መሆኑ ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ለየት ያደርገዋል።

እንሰባሰባለን : እንደራጃለን : እንሰለጥናለን: እንታጠቃለን : ተዋግተን ይህን አንባገነን ፀረ_አማራ ስርዓት ከትክሻችን ላይ አሽቀንጥረን እንጥላለን።

የአማራ ተጋድሎ አካሄድ እና መስመር:-
👉 የተጋድሏችን
መነሻ:-የአማራ ህልውና አደጋ ነው።
መዳረሻው:- አደጋውን ቀልብሶ ህዝቡን ከባርነት አውጥቶ ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር የሃገሪቱን በትረ ስልጣን መልሶ መቆጣጠር ነው::
👉የተጋድሎው ርዮት አማራ ብሔርተኝነት ነው!
👉የተጋድሎው አካሄድ የትጥቅ ትግል ነው!
👉የአማራ ብሔርተኝነት የህልውናችን ዘላለማዊ ዋስትናም ነው!
👉የአማራ ብሎም ኢትዮጵያ ህልውና በሀገር መስራቹ በታላቁ አማራና በተባባሪ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ትብብር ዳግም ይፀናል።እናሸንፋለን!

በመቀጠልም የዚህ ስርዓት አካሄድና የህዝባችን ግፍና ሰቆቃ ለኛ ብቻ ሳይሆን እንደአማራ አማራን ለማጥፋት እየተሄደበት ያለው እርቀት  መላው ዓለም እየተረዳው ያለ ሀቅ ነው  ።እሄ ሆኖ ሳለ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ያልገባችሁ በተለያየ የፀጥታ ዘርፍ በመከላከያ :በፌደራል :ፖሊስ :በአድማ ብተናና ብሎም ሚኒሻ ውስጥ ሆናችሁ ስርዓቱን እያገለገላችሁ ያላችሁ ትውልደ አማራውያን በሙሉ በቃኝ በማለት የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ህዝባችሁን ከባርነት ቀንበር ነፃ ታወጡት ዘንድ ታላቅ የተጋድሎ ጥሪየን አስተላልፋለሁ።

በመጨረሻም አማራ በወርቃማ ልጆቹ መስዋትነት አራሱን ነፃ ያወጣል እናሸንፋለን።መ/አለቃ ግርማው አብየ
የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ የክፍለ ጦር አዛዥ

ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ተመራቂዎች   እንኳን ለዚች ቀን በሰላም አደረሳችሁ
ከዚህ በመቀጠል ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ እንኳን ለዚች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

ተመራቂወች የአማራ ህዝብ የተቃጣበት የማንነት ተኮር ጥቃት ከመገደል ወደ መከላከል ከመከላከል ወደ ሺምቅ ከሺምቅ ወደ ማጥቃት ገብተናል።

ሰለዚህ የአማራ ህዝብ መዳኛው መሰልጠን  መታጠቅ እንዲሁም በአድነት ቁመን  የአማራን ህዝብ የታወጀበትን ዘር ማጥፋት  በአድነት በመተባበር ወደፊት እንሄዳለን::

አንድነት ሃይል ነው በአንድነታችን የማንሻገረው ወንዝ የማንወጣው ተራራ የማንወርደው ቁልቁለት የለም:: እኛ አማራዎች ጀምረን ያልጨረስነው ትግል የለም:: ምክንያቱም  የአባቶቻችን ልጆች ነን የአማራን ህዝብ ለማዳን እስካሁን መሰዋትነት እየከፈሉ የመጡ ጎዶቻችነን  ትግል የማስቀጠል ግዴታችንን እደምንወጣ አልጠራጠርም:: አማራ ያሸንፋል!   ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አርበኛ አሻግሬ ሙሉ /ቦምበኛው/

ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
@አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
1🙏1
ጭና የጠላት መቀበሪያ ሁና ቀጥላለች!!

ዛሬ ጥር 03/2018 ዓ.ም በዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ የአረመኔው ዓብይ አህመድ ራሱን ጥምር ጦር ሃይል ብሎ የሚጠራው ሰራዊት የንፁሃን ወገኖቻችን ለመዝረፍ በተሰማራበት አፋብኃ በላይ ዕዝ የራስ አሞራው 3ኛ ኮር የደጃች አያሌው ብሩ ክ/ጦር የተሳካ ጥቃት ሰንዝሮበታል።

ከ13 በላይ የጥምር ወራሪው ሀይል ዓባላት እሰከ ወዲያኛው ሲሸኙ ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛ ሁኗል። ከፊሎቹ በዳባት መድሃኒያለም ሲቀበሩ ቀሪዎቹ ወደ ደባርቅ ከተማ ተወስደዋል።

አፋብኃ በላይ ዕዝ
ጥር 03/2018 ዓ.ም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
🙏21
ዋግሹም ብርጌድ በሆድ አድር ሚኒሻ እና ፖሊስ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመዉሰድ ድል ተጎናፀፈ!!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ዋግሹም ብርጌድ አማራነታቸዉን በምስር ወጥ በሸጡ ፖሊስ እና ሚኒሻ ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ።

መነሻዉን ዋግህምራ ዞን ድሃና ወረዳ አምደ ወርቅ አድርጎ ዋግሹም ብርጌድን አፍናለሁ ብሎ ቢመጣም ጀግኖቹ የሃይሉ ከበደ ልጆች አባም አቦ ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ ሲቀጠቅጡት ዉለዋል።

ዉጊያዉም ዛሬ ማለትም ጥር 3/2018 ዓ.ም ከ ጧቱ 2:00 - 8:30 የፈጀ ሲሆን በዚህም 20 ሚኒሻ እና ፖሊስ እስከወዲያኛዉ ሲሸኝ 15 የሚሆኑ ባንዳዎችን ምርኮ ማድረግ የተቻለ ሲሆን 37 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ተማርከዋል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
🙏2
የተማረኩ የደቡብ ወሎ ዞን ሰላም አስከባሪዎች እና ፓራ ኮማንዶዎች ወደ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሀድሶ ማዕከል ገቢ ተደረጉ!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ወግድ እና ከላላ ወረዳ ውስጥ ባለፉት ቀናት በሰራው ኦፕሬሽን በርካታ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን መንገድ መሪዎቹ የሆኑት የደቡብ ወሎ ዞን ሰላም አስከባሪዎች እና ፓራ ኮማንዶዎች ተማርከዋል:: ፋኖን እናጠፋለን ብለው ከጠላት አብረው ሌት ተቀን ንፁሀን ወገኖቻችንን ሲገድሉ እና ሲያስገድሉ ከርመው በስተመጨረሻ እጃችን ላይ ወድቀዋል:: እነዚህ የደቡብ ወሎ ዞን ሰላም አስከባሪዎች እና ፓራ ኮማንዶዎች አሁን ላይ የተሀድሶ ስልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን በስልጠናው መሀል አስተያየታቸውን የለገሱት በጥቅሉ የተናገሩት እስካሁን በሄዱበት መንገድ እና በፈፀሙት ድርጊት እጅጉን እንደተፀፀቱ ነው::

ምርኮኞቹ በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሀድሶ ማዕከል የሚሰጣቸውን ስልጠና እንዳጠናቀቁ ወደ ማህበረሰቡ ይመለሳሉ ተብሏል:: ፋሽስቱ አብይ አህመድ አማራን በአማራ ለማስመታት የሚያደርገው ጥረት አካል የሆነውን ፕሮጀክት ለማሳካት ደፋ ቀና የምትሉ የፀጥታ ኃይል አባላት በአስቸኳይ ከህዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ ሲል ኮሩ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ይህን ጥሪ ባለመቀበል ከጠላት ጎን የተሰለፉት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል::


መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏2