ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የልደት በዓልን አስመልክቶ ከ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ የተሰጠ የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክት!!

በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ለፃዲቁ ንጉስ ቅዱስ ላሊበላ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

የጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ተስፋ እውነት መሆን የጀመረበት፣ ቃለ መለኮት ሰው የሆነበት፣ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ድህነት ይሆን ዘንድ ወደ ምድር የመጣበት የመጀመሪያዋ የምስራች (ወንጌል) ናት፡፡

ልደቱም ለነቢያት የትንቢታቸው እውነት፣ ለሰባሰገል የፍለጋቸው ግኝት፣ ለእረኞቹ የእምነታቸው ንፅህና፣ ለመላእክትና ለሰው ልጆች ህብረ ዝማሬ፣ ለዓለም ሁሉ ድህነት የሆነበት ታላቅ በዓል ነው፡፡ በመወለዱም የጥንት ጠላታችንን የዲያቢሎስን ቀንበር ከጫንቃችን አነሳልን፤ በሞት ጥላ ሥር ለነበርን ሁሉ ብርሃንን አሳየን።

አማኑኤል በልደቱና በሞቱ ከጨለማው ገዥ ባርነት አርነት ያወጣን በዋጋ የተገዛን ህዝቦች ብንሆንም የጨለማው ገዥ አምሳያዎች ዛሬም በምድራዊ ህይዎታችን የአፓርታይድ ቀንበር ጭነውብናል።

ከትውልዱ ሁሉ ፋኖ አስተዋለ፤በእሱና በወገኑ ላይ የተጫነብንን የሞት ቀንበር ለመሰባበር ተሰለፈ። የፋኖ ትግል ለአማራው ብሎም ለመላው የሃገራችን ህዝብ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀ፣ ከአፓርታይዱና ከሰልቃጩ አገዛዝ የፍዳ ቀንበር፣ ሰቆቃ፣ ግድያ፣ከስርዓት ሰራሽ ርሃብና ድህነት፣ ከአፈና፣ ከእገታ፣ ከአፈሳ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት የመፍረስ አደጋ መትረፊያ መንገድ አድርገው የሚጠብቁት፣ እራሱን ለዚያ ያጨ እና የሚበቃት ትግል ነው፡፡

የጀመርነውን የህልውና ትግል በአጠረ ጊዜ በድል አድራጊነት ለማጠናቀቅ አቅደን እየሠራን ሲሆን በዚህም አመርቂ ርምጃዎችን እየተጓዝን እንገኛለን። ትግሉን በአጭር ጊዜ በመቋጨት አገዛዙ በተለይም በሴቶች፣ በህፃናትና በአረጋውያን ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ፣ እንግልትና ጦርነት ወለድ መታወክን ታሪክ አድርጎ ወደ ሰላማዊ ህይዎት ለማሸጋገር የሁሉንም የህልውና ትግሉ ባለድርሻ አካላትን (የፋኖንና የሲቪል ማህበረሰባችንን) ተሳትፎንና ትኩረትን ይሻል።

በአራቱ ጠቅላይ ግዛቶች ለምትገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች እንዲሁም ለአማራ ህዝብ እና ለህልውና ትግሉ ደጋፊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!

የሚከተሉትን ሁለት ጥሪዎች ላቀርብ እወዳለሁ!

1ኛ/ በአራቱም ጠቅላይ ግዛት ለምትገኙ የፋኖ አደረጃጀት ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ ፡-

ከልደት በዓል እንደምንረዳው ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመነ ፍዳን ለማሳለፍ ወደዚች ምድር መምጣትና ዝቅ ብሎ ክብሩን አውርዶ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ መለኮትን እና ሥጋን አንድ እንዳደረገ ቅዱሱ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ በመወለዱም የምድራችን የመከራ ዘመን ማብቂያ መጀመሪያ ያሳየን ተስፋ ነበር፡፡ እኛም በሁሉም ጠቅላይ ግዛቶች የምንገኝ ከፍተኛ የፋኖ አመራር የህዝባችን የፍዳ ዘመን ማብቂያ
ማብሰሪያና በዘላቂነት ዋስትና የሚሰጠውን አንድ አማራዊ ድርጅት መውለድ ዐብይ ተግባር መሆኑን አውቀን በፍጥነት አንድነቱን እንውለድ ስል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡

አንድነት ማንም ሰርቶ የሚሰጠን ስጦታ
አይደለም፤ አንድነት ጥረትን ይጠይቃል፤ የእውነት የህዝብ ፍቅርን ይጠይቃል፤ የእውነት ለህዝብ መቆምን ይጠይቃል፤ የእውነት እንደ ኢየሱስ ዝቅ ማለትን ይጠይቃል፤ የእውነት መስዋዕት መሆንን ይጠይቃል፤

አንድነት የዓላማ ፅናት ይጠይቃል፤ አንድነት የዓላማ ጥራት ይጠይቃል፤ በመሆኑም የህዝባችንን የፍዳ ዘመን ለማሳጠር፣ የመከራ ቀንበሩን በፍጥነት ለመስበር ሁላችንም ለአንድነት ቅን እንሁን፤ እራሳችንን ዝቅ እናድርግ፤እንተማመን፤ እንተባበር፤ የጋራ ግባችንን እናስቀምጥ፤ ችግራችንን የቱ ጋር እንዳለ አብረን እንፈልግ፤ በጋራም ፈትተን አንድ ሆነን ይህንን ተስፋ የተጣለበትን ትግል እና ለድል ተጠባቂ የሆነውን ትግላችንን የምናሳካበት የድላችንን የመጨረሻውን መጀመሪያ ተስፋው አድርጎ ለሚጠብቀን ህዝብ እንድናበስር ስል ጥሪ አቀርባለሁ።

2ኛ/ ለመላው የአማራ ህዝብ እና ለመላው የፋኖ አደረጃጀት ደጋፊዎች፦

ሁላችንም ልናውቀው የሚገባን ለውጥ የሁላችንም ተሳትፎና ሥራ ውጤት መሆኑን ነው፡፡ ፋኖ የትግሉ ፊትአውራሪ ቢሆንም ብቸኛ የትግሉ ባለቤት አይደለም፤ በየትኛም ቦታ የሚገኝ የዚህ ትግል ደጋፊ አማራ የትግሉ ባለቤት ነው፤ ለፋኖ ትግል እውቅና የምትሰጡ እና ድጋፍ የምታደርጉ በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የትግሉ ባለቤት ናችሁ ብለን እናምናለን።

በትግል ባለቤትነት ከተማመንን አንድ አማራዊ ድርጅት ለመፍጠር ለሚደረገው ትግል ሁሉም የትግሉ ባለቤት የድርሻውን መወጣት አለበትም ብለን እናምናለን፡፡ ይህም ማለት አንድ መሆን አይችሉም ከሚል ተስፋ አስቆራጭ ንግግር ጀምሮ እስከ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ ከሚል በሃገራችን የተቃዋሚ ጎራው ታሪክ ትልቅ ኪሳራ ሲያደርስ ከነበረው አስተሳሰብ እንደ ህዝብ መላቀቅ አለብን፡፡ አድነት የተወሰኑ አካላት ሰርተው የሚያለብሱን ሳይሆን አብረን የምንገነባው አንድ አማራዊ ቤት ነው፡፡ በመሆኑም የህልውና ትግላችን ባለድርሻ ሁሉ እንደ ትግል ባለቤት ግድፈቶችን የሚያመላከት፣ አጥፊዎችን የሚገስጽ፣ ተራማጆችንና ሃቀኞችን የሚተባበር እና አብሮ
የሚሰራ የትግሉ ጠባቂ መሆን መጀመር አለበት ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአገዛዙን እድሜ የሚወስነው የእኛ ጥንካሬ ነው። የጥንካሬያችን መሰረቱ አንድነታችን ነው። ወሎ ብቻውን ምን ያደርጋል? ጎጃም ሲጨመር ይጠነክራል፤ ሸዋ ሲታከል ላይበጠስ ይገመዳል፤ ጎንደር ሲጨመር አንድነታችን አንበሳ ያስራል፡፡ አንድነት የድላችን ቁልፍ ነው፤ ለዚህ ነው የመላው አማራ አባት ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ አንድ ሁኑ ብሎ የድላችንን ቁልፍ የነገረን፤ አንድ ሁኑ እንደተባልን አንድ እንሁን እያልኩ አማራዊ ጥሪየን እያቀርብኩ በዓሉን ለምታከብሩ የሰው ልጆች ሁሉ በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡

መልካም የገና (የልደት) በዓል!!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ!!
2
የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ታጋይ (አባልና አመራር) ፣ የትግላችን ደጋፊዎቻችን ፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ ፣አደረሰን!

ልደት (የገና በዓል) ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሶስትነቱ ሳይጎድልበት ፣አንድነቱ ሳይጨምርበት፣ የሰው ዘርን በሙሉ ሊያድን በድንቅ ምስጢሩና በማይመረመር ጥበቡ ከዙፋኑ ዝቅ ብሎ በበጎች ግርግም ከአንዲት ብላቴና የተወለደበትን ድንቅ ዕለት የምናስታውስበት ቀን ነው። ለመዳናችን ሲል ባሳለፋቸው መከራዎች ለሰው ልጅ ያለውን የመጨረሻውን የፍቅር ጥግ አሳይቶናል::

አምላካችን ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እንዳሳየን ምሳሌ ለህዝባችሁና ለወገናችሁ ያላችሁ ፍቅር ገዷችሁ በዱር በገደሉ የአማራን ህልውና ለማረጋገጥና የሰው ልጆች መብት ሁሉ ይከበር ዘንድ ጠላትን እየተፋለማችሁ ላላችሁ የአማራ ፋኖ ሰራዊትና እና አመራሮች እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ::

በመጨረሻም በዓሉን ስናከብር የፋኖ ሰራዊትና አመራር ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እንዲሆን እያሳሰብሁ ህዝባችን ያለው ከሌለው ጋር በመጋራት ያከብር ዘንድ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ!

በድጋሜ መልካም የልደት በዓል ይሁንላችሁ ይሁንልን።
አዲስ ትውልድ፣ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
29/04/2018 ዓ/ም

©፻ አለቃ አበበ ሰውመሆን
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
የፋኖ ድምፅ የሆነው አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ በመላው አለም ለምትገኙ ዉድ የክርስትና እምነት ተከታይ አድማጭ ተመልካቾች መልካም የልደት/ገና በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል::

ያለፍርድ በየእስር ቤቱ የምትንገላቱ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች : ለነፃነት በዱር በገደሉ የምትዋደቁ የፋኖ አባላት እና በዚህ ሂደት የክብር መስዋእትነት ለተቀበሉ ቤተሰቦች መልካም በዓል ለማለት ይወዳል::
ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ : ያለፍርድ በእስር ቤት
ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል/አፋብኃ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

በመከራና በፈተና ውስጥ ሆነህ ለነገ በተስፋ እየታገልክ ላለኸው የአማራ ህዝብ ሆይ!
ለህልውና ብሎም ለሃገርና ለህዝብ ደህንነት በተጋድሎ ላይ ያላችሁ የፋኖ ሰራዊት አባላት ሆይ!
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፅናት አደረሳችሁ።

ዛሬ በከባድ ፈተና መካከል ብንሆንም፣  አንድነታችንና የሰውነት ክብራችንን ጠብቀን የማይረሳ አኩሪ ተጋድሎ እያደረግን እንገኛለን።

"ገና" የሚያስታውሰንን የተስፋ ብርሃን በልባችን ይዘን የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ ሙሉ በመሉ ተቀልብሶ፣ ነፃነቱ እስከሚረጋገጥ ድረስ እና የሃገሩ ኢትዮጵያ ባለቤት እስኪሆን ድረስ የጀመርነውን ትግል ወጥ በሆነ አማራዊ አንድነት አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እየገለፅን፣ ለአማራ ህዝብ እና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን፣ ለፋኖ ሰራዊት በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፤ ገና የተስፋ መልእክቱ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ)
ሰበር ዜና/UPDATE !

የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ አሃዶች እና ከአፋህድ የተለያዩ አሃዶች በጥምረት የወረዳ ከተሞችን ጨምሮ የፋሽስቱ አገዛዝ የጦር ተሽከርካሪዎችን በርካታ ተተኳሽ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲሁም በርካታ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቶችን በመማረክ ታላቅ ድል መጎናፀፋቸው ይታወቃል::

አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በሶስት ኮሮች ማለትም ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ ልጅ እያሱ ኮር እና የደጋው መብረቅ ኮር፣ እንዲሁም የዕዙ ልዩ ዘመቻ አሃድ በሆነችው በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ እና ከአፋህድ የተለያዩ አሃዶች በጥምረት ደቡብና ምዕራብ ወሎ ቤተ-አማራ ቀጠናዎች ላይ ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ በተመሳሳይ ሰዓት በተጀመረው ማጥቃት በርካታ ወታደራዊ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናጽፏል::

በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ አሃዶች እና አፋህድ የተለያዩ አሃዶች ጥምረት ነፃ የወጡ የቤተ-አማራ የወረዳ እና ታዳጊ ከተሞች፦

•ጃማ ከለላና ልጓማ እንዲሁም ደብረዘይት ከተሞች በአፋህድ አሃዶች እና አፋብኃ ንጉስ ሚካኤል ኮር ጥምረት
•ለገሂዳ ገነቴ እና ሳይንት ደንሳ ከተማ ንጉስ ሚካኤል ኮር
•ተንታ አጅባር ልጅ እያሱ ኮር እና የደጋው መብረቅ ኮር እንዲሁም ልዩ ዘመቻ በላጎ ሻለቃ

በዚህም የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ከባድ ማጥቃት የወረዳ ከተሞችን ጨምሮ በርካታ የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች ከተተኳሽ ጋር እና የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ተማርከዋል::

ተጠናክሮ በቀጠለው ተጋድሎ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር በትናትናው ዕለት ያስመዘገባቸውን ድልች እንደደረሱን ይፋ እንደምናደር መግለፃችን የሚታወቅ ሲሆን በዚህም፦

•25 ክላሽ
•10710 የክላሽ ተተኳሽ
•3 ወታደራዊ መገናኛ
•ጠላት ለበዓል ያዘጋጃቸው አራት በሬዎች ተማርከዋል::
•አምስት ሚሊሻዎች ሲማረኩ አጠቃላይ ከ59 በላይ ጥምር ጠላት ሲደመሰስ የፖሊስ ኮማንደሩን ጨምሮ ከ37 በላይ ቆስለዋል::

ተጠናክሮ በቀጠለው ተጋድሎ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክ/ጦር ታህሳስ 28ለ29/2018 ዓ.ም አጥቢያ በክፍለጦሩ ም/ዘመቻ በአርበኛ እሸቱ በላይ ፊት አውራሪነት ከክፍለጦሩ ስበርና መብረቅ ሻለቃዎች የተውጣጡ አናብስቶችና የክፍለጦር ቃኝ አባላት ጉጉፍቱ፣ካቤና ሰኞ ገበያ ወደ ጠላት ካምፕ ዘልቆ በመግባት ሶስቱንም ታዳጊ ከተሞች የተቆጣጠሩ ሲሆን ጥላት አንድም ጥይት ሳያፈነዳ በየአቅጣጫው እግሬ አውጭኝ ያለ ሲሆን እስከ ንጋት ሰኞ ገበያንና ጉጉፍቶ ከተማ ለቀጣይ ኦፕሬሽን ያመች ዘንድ መሰራት ያለበትን ወታደራዊ ስራ ጨርሰው ሲወጡ ካቤ ከተማ አሁንም በአናብስቶቹ የጎፍ ክፍለ ጦር ቁጥጥር ስር ትገኛለች::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም
ሰባት የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት አባላቶች ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ::

የብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት 11ኛ ዕዝ 104ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ አሃድ የሆኑ ሰባት አባሎች ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::

ፋሽስቱን አገዛዝ ብልፅግና አውደ ውጊያን ጨምሮ በብዙ የጦር ግንባሮች የማፈራረሱ ሁለንተናዊ ተጋድሎ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሰራዊቱን የማፍረሱ ተግባር ደግሞ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበበት ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም
🙏21