ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ስናን ወረዳ : ጮቄ : እጅ የሰጠ የጠላት ሃይል
እጅግ አስደማሚ ሰበር ዜና

የአገዛዙ 25ኛ ክ/ጦር በጎጃም ምድር ሙሉ ለሙሉ ተደመሰሰች። የፋኖ 206ኛ ኮር ደግሞ የድሉ ባለቤት ነው::

የአረመኔው ሰራዊት በተጠና መልኩ የ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 25ኛ/32ኛ/57ኛ ክፍለጦሮችን በማሰማራት ወደጮቄ ተራራ ለመውጣት ባደረገው እንቅስቃሴ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ታህሳስ 24እና 25 ባደረገው ትንቅንቅ የአረመኔው ሰራዊት 25ኛ ክፍለ/ጦር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሳለች።

የመልሶ ማደራጀት ተግባሩን ለማደናቀፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን በመጨረሻም በእነ ሞት አይፈሬዎች ምድር ጎጃም ድባቅ ተመቷል።

ለሶስት ቀናት በወሰደው ምርኮኛ እና ትጥቅ የመልቀም ሒደቱ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን 206ኛ ኮር 3 ዲሽቃ : 2 ሞርተር : 8 ብሬን :5 ስናይፐር : 230 ክላሽ ሲማረክ 2 መቶ አለቃዎችን ጨምሮ 61 የአረመኔው ሰራዊት ተማርከዋል ፣ 2 ሻለቃ አዛዦች ፣ 5(አምስት) መቶ አለቃዎች እና 420 የአረመኔው ሰራዊት ተደምስሰው ከ137 በላይ የጠላት ኃይል ቁስለኛ ሁነዋል።

32ኛ/57ኛ እና 25ኛ ክ/ጦርን አቀናጅቶ ማጥቃት ለማድረግ አቅዶ የነበረው የጀነራል ሶፊያ ማህመድ 602ኛ ኮር በቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ከፍተኛ ምት አርፎበት በየጫካው ሲለቀም ውሏል። የደረሰበትን ምት መቋቋም አቅቶት ብትንትኑ የወጣው የአረመኔው ሰራዊት 4ኛውን ዲሽቃ በ109ኛ ኮር የተማረከ ሲሆን ማህበረሰቡ ለሶስት ቀናት የጠላትን አስክሬን እየሰበሰበ እየቀበረ ይገኛል።

አንድም አስክሬን ሳያነሳ ብትንትኑ ወጥቶ በየጫካው ወድቆ እየተገኘ የሚገኘው የሜጄር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን 25ኛ ክ/ጦር እስከ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ 618 የሰው ኃይሉ ከጥቅም ውጭ ሁኗል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!

@የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
https://t.me/gfmn21
4🥰1
የአማራ ጠላት ወዳለበት ቦታ ሁሉ እንተኩሳለን !!

የነፃነት ጥሙን በደሙ ከቆረጠው ትውልድ ጋር የገጠመው አብይ አህመድ በየ ቀኑ እና በየ አውደ ግንባሩ የሚደርስበት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ የነገ ዕጣ ፋንታውን ፍንትው አድርጎ እያሳየ ነው።

አንዳንድ አካባቢዎችን በመምረጥ ጭፍጨፋ ሲያደርግ የነበረው አብይ ሞት በቃን በማለት በሰላማዊ መንገድ የተቃወመው አማራ ላይ ብሔራዊ ሞት በማወጅ በመላው ሐገሪቱ የሚገኘውን አማራን መግደል ፣ ማፈናቀል ፣ ማሰር ፣ የእምነት ተቋሙን እና ሐብት ንብረቱን ማውደም እና መዝረፍ ህጋዊ ሆኗል የሚል የምክር ቤት አዋጅ በማስለፈፍ ነበር በይፋ ከአማራ ጋር ወደ ጦርነት የገባው።

ትውልዱም ብሔራዊ ሞት ያወጀብንን ስርዓት ሳንገረስስ መቆም የለም በማለት በየአካባቢው የገባውን ወራሪ እየደመሰሰ ያመጣውን መሳሪያ እየማረከ ቀጥሏል።

መሰባሰብ ፣ መደራጀት ፣ መሰልጠን ፣ መታጠቅ ፣ መደምሰስ እና መማረክ በአዲሱ ትውልድ የተጀመረ ወርቃማ የትግል ምሰሶ በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ምስል :- ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ በ206ኛ ኮር የ24ኛ ክፍለጦር በስናን የማረካቸው የጠላት ሰራዊት አባላት ናቸው ።
https://t.me/gfmn21
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሰሜን አማራ በላይ ዘለቀ ወታደራዊ አዛዥና የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል አርበኛ ሳሙኤል ባለድል በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ።

ትግሉ በጠሩት ታጋዮች እንጅ በበዙት አይሆንም
https://t.me/gfmn21
1
በላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በተወሰደበት የማያዳግም እርምጃ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር፣በእሸት ክፍለ ጦርና በነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በላስታና ቡግና ሰንሰለታማ ተራሮች ሲቀጠቀጥ የዋለው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጦር በደረሰበት ሽንፈት ምላሽ ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ።

መነሻውን ከአይና ቡግና አድርጎ 05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ) ላይ ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም ንጋት አጥቢያ 12:00 ሰዓት እስከ ቀትር 8:00 ሰዓት ውጊያ የከፈተው የአገዛዙ ሰራዊት በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድና ሦስተኛና አራተኛ ሻለቃዎች በአይቆፍር ጨረሆና ሆዛ ሜዳ አቅጣጫ የመጣውን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል፤በአውደ ውጊያው 35 የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ30 በላይ ቁስለኛውን በአምቡላንስና ፓትሮል እየለቀመ ተመልሷል እንዲሁም ሰባት አባላቱ የአማራን ህዝብ አንወጋም በማለት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል።

በዚህም የተበሳጨው የጁላ ሰራዊት ቡግና ወረዳ የ08 ቀበሌ ንብ ዋርካና የ05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ)ን ህዝብ በመድፍ፣በአየር መቃወሚያ(ዙ-23) እና በሞርታር-120 ሲጨፈጭፍ ውሏል፤በዚህ ጭፍጨፋ ሦስት ንፁሃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ አራት የአርሶ አደር ቤቶች በዙ-23 ሲቃጠሉ ተጨማሪ ዘጠኝ ንፁሃን በከባድ ሁኔታ ቆስለው ህይወታቸው በህክምና እየተጠበቀ ይገኛል።

በጭፍጨፋው በከባድ መሳሪያ አንዲት የ60 ዓመት መነኩሴና የ15 ዓመት ልጃገረድ ለገና በዓልና ለንጉስ ላልይበላ ልደት ክብረ በዓል ወደ ላስታ ላሊበላ ይጓዙ የነበሩ እና ቅዱስ ሐርቤ ሚኒቃባ መንደር ከእናቷ ማዘል ላይ የነበረች እታቱ ሞላ ወዳይ የተባለች ህፃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ የህፃኗ እናትም ለህይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ:-
1ኛ. ደስታ ዋጋዬ የ28 ዓመት እናትና ልጆቿ መሰረት አበባው የ7 ዓመት ህፃን እንዲሁም ትዕግስት አበባው የ4 ዓመት ህፃን
2ኛ. ሐይማኖት ደማሙ የተባለች የ22 ዓመት ልጃገረድ
3ኛ. ወጋየሁ ባዬ የተባለች የ38 ዓመት እናት
4ኛ. እማሆይ አይቼሽ መልኬ የተባሉ የ75 ዓመት አዛውንት
5ኛ. መንበር አበባው የተባለ የ8 ዓመት ህፃን
6ኛ. ባየች ባዬ የተባለች የ28 ዓመት ወይዘሮ
7ኛ. ቄስ ካሳ ነጋሽ የተባሉ የ78 ዓመት የሐይማኖት አባት ቤተ-ክርስቲያን አገልግለው ሲወጡ እንዲሁም ህዝቡና አገልጋዩ በቅዱስ ሐርቤ ደብር ነዓኩቶልአብ ቤተ-ክርስቲያን እሁድ ሰንበትን እያከበረ በሚገኝበት በቤተ-ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እንዳሉ በከባድ መሳሪያ ቆስለዋል ቤተ-ክርስቲያኑም ጉዳት አስተናግዷል።

በተያያዘም እሸት ክፍለ ጦርና ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ ከላሊበላ ድብኮ ቀጠና በወሰዱበት የማያዳግም እርምጃ የአገዛዙ ሰራዊት በአፀፋው ንፁሃን ላይ መድፍ በመተኮስ ድብኮ ቀጠና ሁለት የአርሶ አደር ቤቶችን ያቃጠለ ሲሆን ስድስት ከብቶችም ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 26/ 2018 ዓ.ም
https://t.me/gfmn21
ሰበር የድል ዜና

በወልድያ ዙሪያ በየደረገው ትንቅንቅ ከወደመው አየር መቃወሚያ በተጨማሪ ዋና አዛዡና በርካታ አመራሮች ተማረኩ::

ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦር ወልድያ ከተማ ዙሪያ ባደረጉት ተጋድሎ የጠላትን አየር መቃወሚያ (ዙ23) ከማቃጠልና ከማውደም በተጨማሪ በርካታ ድሎችን ማስመዝገባቸውን መግለፃችን የሚታወቅ ነው::

በዚህም አሳምነው ክፍለ ጦር አንድ ሻለቃ የጠላት ሰራዊት በሙት በቁስለኛና በምርኮ ከጥቅም ውጭ ያደረጉ ሲሆን አየር መቃወሚያ (ዙ23) አዛዡንና ሌሎች አመራሮችን ጨምሮ 15 የጠላት ሰራዊት ማርከዋል:: በተጨማሪም አንድ ብሬን፣ 25 የነፍስ ወከፍ ክላሽ፣ አንድ ሽጉጥ፣ ሶስት መገናኛ ሬዲዮ፣ 5250 የክላሽ ተተኳሽ፣ 2500 የብሬን ተተኳሽ፣ 47 ወታደራዊ ሻንጣ እና 33 የወገብ ትጥቅ ብሎም ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማርከዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም
https://t.me/gfmn21
1
በላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በተወሰደበት የማያዳግም እርምጃ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር፣በእሸት ክፍለ ጦርና በነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በላስታና ቡግና ሰንሰለታማ ተራሮች ሲቀጠቀጥ የዋለው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጦር በደረሰበት ሽንፈት ምላሽ ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ።

መነሻውን ከአይና ቡግና አድርጎ 05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ) ላይ ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም ንጋት አጥቢያ 12:00 ሰዓት እስከ ቀትር 8:00 ሰዓት ውጊያ የከፈተው የአገዛዙ ሰራዊት በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድና ሦስተኛና አራተኛ ሻለቃዎች በአይቆፍር ጨረሆና ሆዛ ሜዳ አቅጣጫ የመጣውን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል፤በአውደ ውጊያው 35 የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ30 በላይ ቁስለኛውን በአምቡላንስና ፓትሮል እየለቀመ ተመልሷል እንዲሁም ሰባት አባላቱ የአማራን ህዝብ አንወጋም በማለት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል።

በዚህም የተበሳጨው የጁላ ሰራዊት ቡግና ወረዳ የ08 ቀበሌ ንብ ዋርካና የ05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ)ን ህዝብ በመድፍ፣በአየር መቃወሚያ(ዙ-23) እና በሞርታር-120 ሲጨፈጭፍ ውሏል፤በዚህ ጭፍጨፋ ሦስት ንፁሃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ አራት የአርሶ አደር ቤቶች በዙ-23 ሲቃጠሉ ተጨማሪ ዘጠኝ ንፁሃን በከባድ ሁኔታ ቆስለው ህይወታቸው በህክምና እየተጠበቀ ይገኛል።

በጭፍጨፋው በከባድ መሳሪያ አንዲት የ60 ዓመት መነኩሴና የ15 ዓመት ልጃገረድ ለገና በዓልና ለንጉስ ላልይበላ ልደት ክብረ በዓል ወደ ላስታ ላሊበላ ይጓዙ የነበሩ እና ቅዱስ ሐርቤ ሚኒቃባ መንደር ከእናቷ ማዘል ላይ የነበረች እታቱ ሞላ ወዳይ የተባለች ህፃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ የህፃኗ እናትም ለህይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ:-
1ኛ. ደስታ ዋጋዬ የ28 ዓመት እናትና ልጆቿ መሰረት አበባው የ7 ዓመት ህፃን እንዲሁም ትዕግስት አበባው የ4 ዓመት ህፃን
2ኛ. ሐይማኖት ደማሙ የተባለች የ22 ዓመት ልጃገረድ
3ኛ. ወጋየሁ ባዬ የተባለች የ38 ዓመት እናት
4ኛ. እማሆይ አይቼሽ መልኬ የተባሉ የ75 ዓመት አዛውንት
5ኛ. መንበር አበባው የተባለ የ8 ዓመት ህፃን
6ኛ. ባየች ባዬ የተባለች የ28 ዓመት ወይዘሮ
7ኛ. ቄስ ካሳ ነጋሽ የተባሉ የ78 ዓመት የሐይማኖት አባት ቤተ-ክርስቲያን አገልግለው ሲወጡ እንዲሁም ህዝቡና አገልጋዩ በቅዱስ ሐርቤ ደብር ነዓኩቶልአብ ቤተ-ክርስቲያን እሁድ ሰንበትን እያከበረ በሚገኝበት በቤተ-ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እንዳሉ በከባድ መሳሪያ ቆስለዋል ቤተ-ክርስቲያኑም ጉዳት አስተናግዷል።

በተያያዘም እሸት ክፍለ ጦርና ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ ከላሊበላ ድብኮ ቀጠና በወሰዱበት የማያዳግም እርምጃ የአገዛዙ ሰራዊት በአፀፋው ንፁሃን ላይ መድፍ በመተኮስ ድብኮ ቀጠና ሁለት የአርሶ አደር ቤቶችን ያቃጠለ ሲሆን ስድስት ከብቶችም ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 26/ 2018 ዓ.ም
https://t.me/gfmn21
1
አገዛዙ ፋኖ በፈፀመበት የላውንቸር ጥቃት የአየር መቃዎሚያው ከነ ኦራሉ መውደሙን ተከትሎ በሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አላሙዲን ስታዲየም ባጠመደው ጄነራል መድፍ የወልድያ ዙሪያ አከባቢዎች ላይ የዘፈቀደ ጥቃት ሲፈፅም አድሯል።

ከወልድያ ጥቁር ውሀ በቅርብ ርቀት ቃሊም መገንጠያ አከባቢ ልዩ ቦታው ዘንዶ ጅራት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ትናንት ታህሳስ 25/2018 ዓ/ም ፋኖ በፈፀመው የላውንቸር ጥቃት አንድ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አየር መቃዎሚያ ተጠምዶ እስከነበረበት ወታደራዊ ኦራል ተመቶ ሙሉ በሙሉ በእሳት ጋይቶ መውደሙን መረብ ሚዲያ በምስል አስደግፎ በትናንት ምሽት ዜና እወጃው መዘገቡ ይታወቃል።

ከወደ ፋኖ በተከፈተበት መብረቃዊ ጥቃት የአየር መቃዎሚያው ከነ ኦራሉ የወደመበትና በርካታ ወታደሮቹ የተገደሉበት ብሎም የተማረኩበት አገዛዙ፡ በወልድያ ከተማ ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን ስታዲየም ባጠመደው ጄነራል መድፍ ከወልድያ እስከ ቃሊም የሚገኙ አከባቢዎች ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ አምሽቶ አድሯል።

ከትናንት ታህሳስ 25/2018 ዓ/ም እኩለ ቀን ጀምሮ ከወልድያ በቅርብ ርቀት የሚገኙ አከባቢዎች ማለትም አፍሪኬር፣ አላ ገዶ፣ ሚጦ፣  ጃርሳ፣ ቃሊምና ቃሊም መገንጠያ እንዲሁም ዘንዶ ጅራት በተባሉ አከባቢዎች ላይ የዘፈቀደ የጄነራል መድፍ ድብደባ መፈፀሙን የመረብ ሚዲያ የቀጠናው ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።

በዚህም የማሽላ አዝመራ እየሰበሰቡ የነበሩ አርሶ አደሮች በከባድ መሣሪያ ተመተው ወደ ሕክምና የተወሰዱ ሲሆን፡ ከእነሱ መካከልም ሕይወታቸው ያለፈ መኖራቸው ታውቋል።

ከፋኖ ጋር ጠንከር ያለ ውጊያ አካሄዶ ድል ማድረግ የማይችለው አገዛዙ፡ በየአውደ ውጊያው ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ ኪሳራ በገጠመው ቁጥር፡ አቅመ ደካሞችን ሰብስቦ በጅምላ በመረሸን፣ ህፃናትና ነፍሰጡር ሴቶችን በመግደል እንዲሁም የልጃገረዶችን ጡት በመቁረጥና የታዳጊዎችን ብልት በመስለብ የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ በተደጋጋሚ አሳይቷል።

እነዚህ የነውረኛው ስርዓት ተላላኪ የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ፡ ከዓመት በፊት ላሊበላ ዙሪያ በነበረ ውጊያ ከወደ ፋኖ የተሰነዘረባቸውን ጥቃት መቋቋም አቅቷቸው በመሸሽ ላይ ሳሉ አንድ ማሽላ የሚጠብቅ የ10 ዓመት ታዳጊ ልጅ አግኝተው፡ ታዳጊው ይዟት በነበረችው ትንሽየ ጥልቆ(ስለታማ መሳሪያ) ብልቱን ከትክተው እንደሰለቡት የአሁኑ የመረብ ዘጋቢዎች፡ የያኔው "የአማራ ድምፅ ሚዲያ" ባልደረቦች በወቅቱ ዘግበውት ነበር።

የመከላከያ ሰራዊት አዛዦቹ "የጠላት ቤተሰቦችን ብልት መስለብና ጡት መቁረጥን የገዳ ስርዓት ያዛል" ሲሉ ምላሽ ይሰጣሉ።

እነዚህ ኃይሎች ትናንት ወልድያ ዙሪያ ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸው የዘፈቀደ የመድፍ ድብደባ በመፈፀም የበቀል ዱላቸውን በንፁኋኖች ላይ አሳርፈዋል።

በተጨማሪም ይሄው ነውረኛና አቅመቢስ አገዛዝ፡በወልድያ ከተማ ወደ ጥቁር ውሀ መውጫ ጉቦ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የሚገኙ ነዋሪዎችን "ማርፈጃውን ዙ23ና ሬሽን ጭኜ ስንቀሳቀስ አይታችሁ መረጃ ለፋኖ ሰታችሁ አስመትታችሁኛል" በሚል በየሰፈሩ ያገኛቸው ንፁኋኖችን መደብደቡንና አንዳንዶቹንም አፍኖ መውሰዱን የአይን እማኞች ለመረብ ሚዲያ ተናግረዋል።

በወልድያ ከተማ በተለይ ዳርቻማ አከባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች፡ በከተማዋ ዙሪያ ውጊያ በተደረገ ቁጥር "እናንተ ናችሁ የምታስጠቁን" በሚል በመከላከያ ሰራዊት ከባድ ግፍ ይፈፀምባቸዋል።

በዚህ ምክኒያት በከተማዋ ማር ማቀነባበሪያ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ(ጎንደር በር ኬላ ዙሪያ) የሚገኙ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን እየለቀቁ ወደ መኃል ከተማዋ ቤት ተከራይተው ለመኖር ተገደዋል።

ከሼሁ ስታዲየም ቀጥሎ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ሁለተኛ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ማር ማቀነባበሪያው ሰፈር ይገኛል።

@መረብ ሚዲያ