ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የነውረኛው ብልፅግና አገዛዝ ወታደሮች በጣና ሐይቅ ከሚገኙ በርካታ ቅዱሳን ስፍራዎች መካከል አንዱ በሆነው በዳጋ እስቲፋኖስ ገዳም ላይ ዛሬ ታስሳስ 25/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በዲሽቃና በብሬን የታገዘ ተኩስ ከፍተውበት አርፍደዋል።

ደናግላን መነኮሳትን መድፈር እና መግደል፣ ገዳማትን ጨምሮ አብያተ ክርስቲያናትን በድሮንና በሌሎች ከባባድ መሣሪያዎች ማውደምና ማርከስ ሁነኛ መገለጫው የሆነው የብልፅግና ስልጣን አስጠባቂው መከላከያ ሰራዊት፡ የበአዴን ሎሌ በሆኑት በአድማ ብተናና ሚኒሻ አባላት እየተመራ ነው ዛሬ ከንጋት ጀምሮ ተኩስ የከፈተው ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።

ይህ ፀረ አማራ፣ ፀረ ሐይማኖትና ፀረ ሰላም የሆነው የአገዛዙ ሠራዊት፡ ሰሞኑን ደቅ እና አካባቢው ላይ በመግባት በገዳማውያን ላይ ድብደባና ዘረፋ ሲፈፅም የሰነበተ ሲሆን፡ ዛሬ ደግሞ በዳጋ እስጢፋኖስ ላይ ወረራ ከፍቷል ነው ያሉት ምንጮቻችን።

የገዳሙ አባቶች "ቦታው የጸሎት ቦታ በመሆኑ የጦር መሣሪያ ይዞ መግባት አይቻልም" በሚል ለመከልከል ቢሞክሩም፡ ሐይማኖታዊ ስፍራዎችንና እሴቶችን ማውደም እና ማርከስ ልዩ መገለጫው የሆነው የአገዛዙ ኃይል፡ "ለምን ተናገራችሁኝ" በሚል የዘፈቀደ ተኩስ ከፍቶባቸዋል።

@መረብ ሚዲያ
የአብይ አህመድ ባህር ኃይል በጀግኖች የ102ኛ ኮር አባላት በደረሰበት ከባድ ምት ከእነ ጀልባው ጣና ውስጥ ሰጠመ።

ነገሩ እንዲህ ነው
አብይ አህመድ እና ቄስ ሞገሴ ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳምን ለመጎብኘት በተዘጋጁበት በዚህ ሰዓት ያን የቀይ ባህር ተንሳፋፊ ፣ ያንን የባህር ላይ ፋልኮን ሐይላቸውን ከባህርዳር ጊዮርጊስ በብዙ ጀልባዎች ጭነው ወደ ደቅ ደሴት እና ወደ ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳማት ይልካሉ።

ይህንን መረጃ የሰሙት ጀግኖች የ102ኛ ኮር የ11ኛ ክፍለጦር አባላት ( የባህርዳር ልጆች ) ደቅ ደሴት ላይ የተወሰኑ የቡድን መሳሪያዎችን ብቻ በመያዝ ይጠብቋቸዋል።
ከዚያም በጀልባ እየተግተለተለ ወደ ደሴቱ ለአሰሳ የመጣውን የባህር ኃይል ኮማንዶ በብሬን ጥይት ግንባር ግንባሩን በማለት ይደመስሱታል።

በዚህ ውጊያ :-
1) 2 ጀልባ ሙሉ የባህር ኃይል ኮማንዶ ብዛቱ በግምት ከ80 - 100 የሚደርስ ጣና ሐይቅ ውስጥ ሰጥሟል።

2) ከ15 - 20 የሚደርሱት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።

በጣም አስገራሚው ነገር ከውጊያው በኋላ አንድ የቀድሞው የጣናው መብረቅ አባል " ያን ሁሉ ጥርጥር ክላሽ ይዘውት ሰመጡ " ማለቱ በአባላቱ ዘንድ የዕለቱ ፀፀት ተብሎ ተመዝግቧል ።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስአስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
  
   ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

@አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
          
1
የአደረጃጀት ዜና

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ አሰራሩን እያዘመነ ይገኛል።

በቅርቡ ዓለማቀፋዊ መስፈርት ያሟላ ወታደራዊ አደረጃጅት በዕዝ፥ በኮር፥ በክ/ጦር እና በሬጅመንት በማደራጀት በየግንባሩ ድል እየተቀዳጀ ይገኛል።

በዛሬዉ ዕለትም በቀድሞዉ የክ/ጦር አደረጃጅት የ1ኛ ክ/ጦር አካል የነበሩትን ባ/ዳር ብርጌድ፥ ጣናዉ መብረቅ ብርጌድ፥ አንሙት ያዛቸዉ ብርጌድ እና ኮ/ሎ ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድን በማወሃድ የዕዝ፥ የኮር፥ የብርጌድ፣ የሻለቃ እና የሻምበል አመራሮች በተገኙበት የአመራር እንዲሁም በከፊል የሰራዊት ፕወዛ በማደረግ 11ኛ እና 22ኛ ክ/ጦር በሚል ስያሜ ክጦሮችን በማደራጀት የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በመስጠት አጠናቋል።

ትግላችን መሰረቱን አለት ላይ በማቆም ማገር እና ጣሪያዉን አዋቅሮ በመጨረስ የአማራ ህዝብን ከፈፅሞ ጥፋት እያደነ ለኢትዮጵያውያን ተስፋ በመሆን ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።

አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳስብ ፣ አዲስ ተስፋ!!

ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉም!!

@ዘውዳለም አዱኛው
በቴዎድሮስ እዝ የ102ኛ ኮር ሰብሳቢ
1
ሰበር ዜና

ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ አሳምነዉ ክፍለጦር ጀግኖች ዙ-23ቱን እስከ ኦራሉ ሲያቃጥሉ በርካታ ያገዛዙ ሰራዊት ደግሞ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል::

ከወልድያ ከተማ በመነሳት በግዳጅ በሰበሰበው በርካታ ተሳቢ : አይሱዙና ኤፍኤስአር እንዲሁም ወታደራዊ ኦራል ሎጅስቲክ ጭኖ በዙ-23 : ድሽቃና በርካታ እግረኛ ወታደሮች ታጅቦ ወደሳንቃ አቅጣጫ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሃይል በአሳምነው ክፍለጦር ነበልባል የፋኖ አባላቱ አቀባበል ተደርጎለታል::

ከአፊኬር ወደሳንቃ መግቢያ ዘንዶጅራት የተባለ ልዩ ቦታ ላይ በተወደበት የደፈጣ ጥቃትም ዙ-23 የጫነ ወታደራዊ ኦራል ሙሉለሙሉ ተቃጥሏል: በርካታ ሰራዊቱም ሙትና ቁስለኛ መደረጉን መረጃው ደርሶናል::

የተጠናከረ ዝርዝር መረጃውን ከእዙ ህዝብ ግንኙነት ይዘን የምንመለስ ይሆናል
1👍1
ሰበር ዜና!

ምኒልክ ዕዝ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዙ23 በአር ፒ ጂ ያቃጠለበትንና ያወደመበትን ድል ተጎናፀፈ::

አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነው ወልድያ ከተማ ዙሪያ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ የፋሽስቱ አገዛዝ ዙ23 ልዩ ስሙ ዘንዶ ጅራት የተባለ ቦታ ላይ በአር ፒ ጂ በማቃጠልና በማውደም ብሎም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦር እና የዞብል አምባ ክፍለ ጦር ቃኝ ወልድያ ዙሪያ ከጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ እና ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ቀጠና ላይ በመዝጋት ባጠቃላይ የተጠቀሱት አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ባጠቃላይ አሳምነው ክፍለጦር የዞብል አምባ ክፍለጦር ቃኝን ጨምሮ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ መግቢያ ድረስ ከፍተኛ አመራሮችን ጭምር የማረኩበትን በርካታ ድሎች ሲያስመዘግቡ ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ላይ በመዝጋትና ተጨማሪ የጠላት ሃይል እገዛ እንዳያደርግ በማድረግ የጠላትን ግንኙነት በማቋረጥ ለተገኘው ድል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል::

ማስታወሻ፦ ውጊያው አሁንም ተጠናክሮ ስለቀጠለ የተማረከ ጠላት እና ንብረት በዝርዝርና በማስረጃ ይዘን እንመጣለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

@አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም
4
ፋኖ ሰላዮችን ለምን ይገድላል?

ድሮን ሲዘንብብን፣ በጅምላ ስንቀበር፣ እኅቶቻችንና እናቶቻችን ሲደፈሩና ጡታቸው ሲቆረጥ፣ ተቋማት ሲወድሙ አላዘኑልንም ድምፅም አልሆኑንም። ሙሉ የሀገሪቱ ጦር ሲዘምትብን ማንም ምን አላለም። ተፈጥሯዊ መብታችንን ተጠቅመን ራሳችንን ስንከላከል ግን እንደ ሀገር አፍራሽ እንደ እምቢተኛ እንቆጠራለን። የጠላት ተልእኮ ተሸካሚን ስንቀጣ፣ ጥቁር አማራውን ለሆዱ ብቻ የሚያስበውን አማራ ስንቀጣ የቅጣት ዓይነት ይመርጡልናል ይባሱንም በደላቸውን ንጹሕ አድርገው ይዘግቡታል።

ሕዝባችን ዓለም ላይ ያልተደረገ ግፍ ሲፈጸምበት እንዳላዩ አልፈው እኛ መቅጣት ስንጀምር ስለ ሰብአዊነት ይሰብኩናል ይከሱናል። ምርኮኛ አቀማጥሎ የሚይዝ ፋኖ ሰብአዊነትን ተግብሮ የሚኖር እንጅ ያለ አግባብ አይገድልም አይዘርፍም። እንደ ጦርነት ሕግ ይገጥማል ያሸንፋል ይማርካል ይደመስሳል። ሰላይን ይቀጣል። አንዳንንዶች የፋኖ ደጋፊ ነን የሚሉና የሦስተኛ ረድፍ የብልጽግና ደጋፊዎች ሳይቀር መሃል ሠፋሪነታቸውን መደበቅ ተስኗቸው በፋኖ የትግልና የሕዝብ አስተዳደር ብሎም የፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ የእናውቅላችኋለን ጨኸት ያሰማሉ። እነዚህ ፋኖም ብልጽግናም ካሸነፉ በሰላም እንኖራለን የሚሉ ወላዋዮችና በሕዝብ ላይ ቁማር የሚይዙ ናቸው።

ሰሞኑን ስለሚወራው ጉዳይም አርበኛ አስረስ፡ "ስለላ ላይ ተሰማርተዋል" በማለት የሚከስሷቸውን ሴቶች "እንደ ተዋጊ ኃይል" እንደሚቆጥሯቸው ተናግሯል። "በሕገ ደንባችን መሠረት ለጠላት ስለላ ሥራ ሲሠራ የተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የሞት ቅጣት እርምጃ እንደምንወስድ፣ ሌላም አካባቢ ተመሳሳይ እርምጃዎችን እንደምንወስድ ይታወቃል" ብሏል።

በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች ላይ ግድያን መፈጸም እንደ የጦር ወንጀል ድርጊት ሊቆጠር የሚችል ስለመሆኑ ከቢቢሲ ጥያቄ የቀረበለት የፋኖ አመራሩ አስረስ "በምርኮ የተያዘ ሰው፤ በተኩስ ልውውጥ መሃል በፈቃደኝነት እጁን የሰጠ ሰው ሲሆን ነው። ይሄኛው ግን በልዩ ሁኔታ የስለላ ሥራ ሲሠሩ ስለሆነ በቁጥጥር ስር ዋሉት፤ በሕገ ደንባችን መሠረት እንደ ምርኮኛ የሚያዙ አይደሉም" የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

©ብላክ ላዬን ሚዲያ
5
የአብይ አህመድ አገዛዝ 17 ንፁሃንን በግፍ ጨ*ፈጨፈ::

ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም አዮ ጓጉሳ ወረዳ እሁዲት የመሸገው የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ጨፍጨ*ፊ ፀረ አማራ ሠራዊት ከምሽቱ 11 ሠዓት አካባቢ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109 ኮር የ88ኛ ክ/ጦሯን ቃኝና ማህንዲስ ሻለቃን (6ኛ ሻለቃን) ለማፈን እንቅስቃሴ ያደርጋል። ታድያ መረጃው የደረሳት ሻለቃዋ ጠላትን በደፈጣ መምታት ችላ ከ8 በላይ አቁስላ ከ10 በላይ ቅጥረኛ ጨፍጫፊውን ወደ ማይመለስበት ሽኝታዋለች።

ያልጠበቀው የምት ውርጅብኝ የገጠመው ይህ ፀረ አማራ ቡድን ወደ ኋላ ተመልሶ አዮ ቀበሌ በመግባት 16 ንፁሃን ወጣቶችን ከመዝናኛ ቦታ እና ከስራ ቦታቸው ሠብስቦ በግፍ እረሽኗል።

ስርዓቱ ፋኖን ለማጥፍት የአማራ ህዝብ ማጥፍት እንደ ወታደራዊ ስልት እየተጠቀመ ያለ እና አማራን መዝረፍ፣ መግደል፣ ሐብት ንብረት ማውደም፣ ፆታ እና እድሜ ሳይለይ በቡድን መድፈርን እንደ ተጨማሪ የጦር ስልት አድርጎ እየተጠቀመ ያለ ከኢትዮጵያ ባህል ያፈነገጠ የባዕድ ተልዕኮ አንግቦ ሁለ ገብ ጦርነት የከፈተ አለማቀፉን የጦር ህግን የማይቀበል የጦር ወንጀለኛ የሆነ አሸባሪ ኃይል ነው::

በግፍ ከተረሸኑት መሃከል:-
1. ዳዊት ቀናው
2. ተውስል ምሬ
3. ብርሃኑ አረጋ
4. ክንዱ ታደሰ
5. እንዳለ ተስፉ
6. ሽኩር ጋሻው
7. አህመድ ሁሴን
8. አውላቸው አለነ
9. ትግስቱ ጌታቸው
10. ቸኮለ አስራደ
11. ምንባለ ቢተው እና 6 የቀን ስራ የሚሰሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ይገኙበታል።

ይህ ግፈኛ ፀረ አማራ ቡድን አስከሬን አላስነሳም ያለ ሲሆን ወንድሞቻችሁ ናቸው የገደሉን እኛም እናንተን እንገላለን እያለ እንደረሸናቸው ማረጋገጥ ተችሏል። ቡድኑ ሌላ ተጨማሪ ከ10 በላይ ንፁሃን ወጣቶችን አግቶ ወደ እሁዲት ወስዷል።

ይህ አሸባሪ ስርዓት ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም ሌሊት ከቡራፈር ቀበሌ 6 እና ከሻምብላ ቀበሌ 2 በድምሩ 10 አ/አደሮችን አግቶ መሰወሩ ይታወሳል።

ለሞቱት ነፍሳቸውን ይማር : ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!!

109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም
ላስታ አሳምነዉ ኮር በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ በርካታ ድሎችን ተጎናፀፈ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር ክንፍ የሆኑት እሸት ክፍለ ጦር እና ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በጥምረት በመሆን ከላሊበላ ጋሻና-ከጋሸና ላሊበላ በሁለት አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰ የነበረን የአገዛዙ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ሲቀጡት ተፈራ ማሞ ክ/ጦር ደግሞ መነሻዉን አይና ከተማ አደርጎ ወደ ቅዱስ ሐርቤ እየተንቀሳቀሰ የነበረን ግትልትል ሰራዊት እንደ ቃሪያ ሲያራግፉት ዉለዋል።

ምላሱ ብቻ የቀረዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ በአፈ- ቀላጤዎቹ በኩል "ፋኖን ከምደረ ገፅ አጥፍቻለሁ" የሚል የዉሸት ፕሮፖጋንዳ ለገና በዓል ወደ ላሊበላ ከተማ ለሚመጡ እንግዶች ለማስረፅ የተለያዬ የክልል እና የዞን ሆድ አደር ካቢኒዎችን ይዞ በመምጣት ላይ እያለ በዛሬዉ ዕለት ማለትም በቀን 26/2018 ዓ.ም በእሸት ክፍለ ጦር እና በነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ ሲገርፍ ዉሎ ያሰበዉን ሳያሳካ ወደየመጣበት ተመልሷል።

ወጊያዉም ከንጋቱ 11:00-6:00 የዋለ ሲሆን በዚህም ብዛት ያለዉ የነፍስ ወከፍ መሳርያዎች ሲማረኩ ከ30 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት በእሸት ክ/ጦር እና በነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ ሲደመሰሱ ከወደ ቅዱስ ሐርቤም በተፈራ ማሞ ክ/ጦር ሲገረፍ ዉሎ ሙትና ቁስለኛ ሁኖ ወደ አይና ከተማ ተመልሷል።

ዉጊያን በበላይነት የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳመነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ የመራዉ ሲሆን አርበኛዉም "በደመቀ ሁኔታ ታህሳስ 29 የሚከበረዉ የገና በዓል አገዛዙ ከሚያስበዉ በላይ እኛ እንዲከበርልን እንፈልጋለን ነገር ግን በዚህ በዓል የብልፅግና አፈቀላጤ ሰለ አማራ ትግልም ሆነ ሰለ አማራ ፋኖ የዉሸት ፕሮፖጋንዳ እሚያሰራጩ ከሆነ እኛ በአቅራቢያዉ እስካለን ድረስ እርምጃ እንወስዳለን ብሏል"።

መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን ነው::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም
1