ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ነበልባሉ ፎገራ ክፍለ ጦር ክርሥትያን ታደለ ብርጌድ ድል ቀናው::

የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሻውን ከሊቦ ከምከሙ አዲሥ ዘመን አድርጎ በአምቦ ሜዳ፣ ቦረን መሥክና ርብ ካናልን በመጠቀም ወደ ፎገራዋ ወጠምብ ቀበሌ በመንቀሳቀስ የገበሬዎችን(አርሶ አደሮችን) የግል መሣሪያ ለመንጠቅ ገብቶ ነበር። ነገር ግን በነፍጠኛው ''ነበልባሉ ፎገራ'' ክፍለ ጦር አሃድ በሆኑት ''ክርሥትያን ታደለ'' ብርጌድ ከቀኑ 4:00 ጀምሮ እሥከ 11:00 ወጠምብ ቀበሌ ላይ ውጊያ ተከፍቶበታል። ወጠምብ ሚካኤል የጀመረው ውጊያ ወደ ሙርና፣ አማኑኤል፣ አውሥኮድ ካምፕ፣ ጎጃሞች ሚካኤል እና ጎንደር በር ተሥፋፍቶ ውሏል።

በዚህ ውጊያ 13 የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት(መከላከያ) ሲደመሰስ፣ 7 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ ቁሥለኛ ሆነዋል። በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የሞራል፣ የቁሥና የአካል ኪሳራ ደርሶበታል።

የአገዛዙ ቅጥረኛ የሆነው መከላከያ፥ የአማራ አርሶ አደሮችን የግል መሣሪያ የማሥወረድ ዕቅዱም ከሽፎ፣ ኪሳራውን ለመቀነሥ ከተለያዬ መዳረሻ ያሉ መከላከያዎችን የድረሱልኝ ተማጽኖ ሲያሰማም አምሽቷል።

የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት የሚፈጽመውን የግል ትጥቅ የማሥወረድ አቢያዊ ተልዕኮ መላው ዓምሐራ በአንድ እሥትንፋሥ ወግድ ማለት አለበት። አማራ የሆነ ሁሉ በዚህ የሕልውና ትግል መሣሪያውን አገልግሎት ላይ እንዲያውል የመጭውን ኦሮሙማ አውሬያዊ ድርጊት ለሕዝቡ ግንዛቤ መፍጠር የግድ ይላል። በሬህን ሸጠህ፣ እህልህን አቅንተህና መሬትህን ሸጠህ የገዛኸውን መሣሪያ ሊያሥወርድህ ለሚመጣ ነውረኛ የኦሮሙማ አገዛዝ ምላሽህ እምቢ መሆን አለበት።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን👊

@አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
5👍2
ሰበር ዜና

ስርቆትና ዝርፊያ ምግባሩ ያደረገው የአገዛዙ አረመኔ ሰራዊት የህዝብን ባንክ ዘረፋ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጄር ጀኔራል ውባተ አባተ አንደኛ ኮር የጉና ክፍለጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ምግባሩ ስርቆትና ዝርፊያ የሆነው የአገዛዙ ጡት ቆራጭ አረመኔ ሰራዊት የአርሶ አደሩን ሀብትና ንብረት ፣ መሳሪያ እና ትጥቅ መዝረፍ ፣ መቀማት ፣ ማቃጠል ስራ አድርጎ ይዞታል። ባለፋት 24 ሰዓታት ብቻ በእስቴ ወረዳ መካነየሱስ ከተማ ከ90 በላይ ንፁሀን ዜጎችን የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ ፣ ከፋኖ ጋር ትሰራላችሁ በማለት እንደማዳበሪያ መጋዘን ውስጥ በማጎር እየደበደበና እያሰቃያቸው ሲሆን በተጨማሪም ፋርጣ ወረዳ አለም ሳጋ አካባቢ የነበሩ አርሶ አደሮችን ወደ ደብረታቦር ከተማ እየደበደበ ወስዶ አስሯቸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ አንዳቤት ወረዳ ጃራ ገዶ ከተማ የሚገኘውንና የህዝብ ሀብት የሆነውን አባይ ባንክ 6,347,000(ስድስት ሚሊየን ሶስት መቶ አርባ ሰባት ሺ ) ብር እና የባንኩን መገልገያ ቁሳቁሶች በሃይል የቻለውን በመጫን የቀረውን ሙሉ በሙሉ በማውደም ወደ ወለሽ ከተማ ተመልሷል።

የአገዛዙ ቅልብ ሀይል ሰሞኑን በሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ የቁርጥ ቀን ልጆች የሚደርስበትን ምት መቋቋም ሲያቅተው በሌሊት በመንቀሳቀስ የበቀል ዱላውን ንፁሀንን በመግደልና በማሰር እንዲሁም ሀብትና ንብረታቸውን በማውደም አማራ ላይ ያለውን ጥላቻና ሁለተናዊ ማጥፋት ዘመቻ እያሳየን በመሆኑ ማንኛውም ማህበረሰብ እራሱን እንዲከላከል እና ከፋኖ ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ እናስተላልፋለን ።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!!

@አርበኛ መ/ር ያሄድ ደገፋው
የጉና ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
👍1
የነውረኛው ብልፅግና አገዛዝ ወታደሮች በጣና ሐይቅ ከሚገኙ በርካታ ቅዱሳን ስፍራዎች መካከል አንዱ በሆነው በዳጋ እስቲፋኖስ ገዳም ላይ ዛሬ ታስሳስ 25/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በዲሽቃና በብሬን የታገዘ ተኩስ ከፍተውበት አርፍደዋል።

ደናግላን መነኮሳትን መድፈር እና መግደል፣ ገዳማትን ጨምሮ አብያተ ክርስቲያናትን በድሮንና በሌሎች ከባባድ መሣሪያዎች ማውደምና ማርከስ ሁነኛ መገለጫው የሆነው የብልፅግና ስልጣን አስጠባቂው መከላከያ ሰራዊት፡ የበአዴን ሎሌ በሆኑት በአድማ ብተናና ሚኒሻ አባላት እየተመራ ነው ዛሬ ከንጋት ጀምሮ ተኩስ የከፈተው ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።

ይህ ፀረ አማራ፣ ፀረ ሐይማኖትና ፀረ ሰላም የሆነው የአገዛዙ ሠራዊት፡ ሰሞኑን ደቅ እና አካባቢው ላይ በመግባት በገዳማውያን ላይ ድብደባና ዘረፋ ሲፈፅም የሰነበተ ሲሆን፡ ዛሬ ደግሞ በዳጋ እስጢፋኖስ ላይ ወረራ ከፍቷል ነው ያሉት ምንጮቻችን።

የገዳሙ አባቶች "ቦታው የጸሎት ቦታ በመሆኑ የጦር መሣሪያ ይዞ መግባት አይቻልም" በሚል ለመከልከል ቢሞክሩም፡ ሐይማኖታዊ ስፍራዎችንና እሴቶችን ማውደም እና ማርከስ ልዩ መገለጫው የሆነው የአገዛዙ ኃይል፡ "ለምን ተናገራችሁኝ" በሚል የዘፈቀደ ተኩስ ከፍቶባቸዋል።

@መረብ ሚዲያ
የአብይ አህመድ ባህር ኃይል በጀግኖች የ102ኛ ኮር አባላት በደረሰበት ከባድ ምት ከእነ ጀልባው ጣና ውስጥ ሰጠመ።

ነገሩ እንዲህ ነው
አብይ አህመድ እና ቄስ ሞገሴ ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳምን ለመጎብኘት በተዘጋጁበት በዚህ ሰዓት ያን የቀይ ባህር ተንሳፋፊ ፣ ያንን የባህር ላይ ፋልኮን ሐይላቸውን ከባህርዳር ጊዮርጊስ በብዙ ጀልባዎች ጭነው ወደ ደቅ ደሴት እና ወደ ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳማት ይልካሉ።

ይህንን መረጃ የሰሙት ጀግኖች የ102ኛ ኮር የ11ኛ ክፍለጦር አባላት ( የባህርዳር ልጆች ) ደቅ ደሴት ላይ የተወሰኑ የቡድን መሳሪያዎችን ብቻ በመያዝ ይጠብቋቸዋል።
ከዚያም በጀልባ እየተግተለተለ ወደ ደሴቱ ለአሰሳ የመጣውን የባህር ኃይል ኮማንዶ በብሬን ጥይት ግንባር ግንባሩን በማለት ይደመስሱታል።

በዚህ ውጊያ :-
1) 2 ጀልባ ሙሉ የባህር ኃይል ኮማንዶ ብዛቱ በግምት ከ80 - 100 የሚደርስ ጣና ሐይቅ ውስጥ ሰጥሟል።

2) ከ15 - 20 የሚደርሱት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።

በጣም አስገራሚው ነገር ከውጊያው በኋላ አንድ የቀድሞው የጣናው መብረቅ አባል " ያን ሁሉ ጥርጥር ክላሽ ይዘውት ሰመጡ " ማለቱ በአባላቱ ዘንድ የዕለቱ ፀፀት ተብሎ ተመዝግቧል ።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስአስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
  
   ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

@አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
          
1
የአደረጃጀት ዜና

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ አሰራሩን እያዘመነ ይገኛል።

በቅርቡ ዓለማቀፋዊ መስፈርት ያሟላ ወታደራዊ አደረጃጅት በዕዝ፥ በኮር፥ በክ/ጦር እና በሬጅመንት በማደራጀት በየግንባሩ ድል እየተቀዳጀ ይገኛል።

በዛሬዉ ዕለትም በቀድሞዉ የክ/ጦር አደረጃጅት የ1ኛ ክ/ጦር አካል የነበሩትን ባ/ዳር ብርጌድ፥ ጣናዉ መብረቅ ብርጌድ፥ አንሙት ያዛቸዉ ብርጌድ እና ኮ/ሎ ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድን በማወሃድ የዕዝ፥ የኮር፥ የብርጌድ፣ የሻለቃ እና የሻምበል አመራሮች በተገኙበት የአመራር እንዲሁም በከፊል የሰራዊት ፕወዛ በማደረግ 11ኛ እና 22ኛ ክ/ጦር በሚል ስያሜ ክጦሮችን በማደራጀት የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በመስጠት አጠናቋል።

ትግላችን መሰረቱን አለት ላይ በማቆም ማገር እና ጣሪያዉን አዋቅሮ በመጨረስ የአማራ ህዝብን ከፈፅሞ ጥፋት እያደነ ለኢትዮጵያውያን ተስፋ በመሆን ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።

አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳስብ ፣ አዲስ ተስፋ!!

ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉም!!

@ዘውዳለም አዱኛው
በቴዎድሮስ እዝ የ102ኛ ኮር ሰብሳቢ
1
ሰበር ዜና

ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ አሳምነዉ ክፍለጦር ጀግኖች ዙ-23ቱን እስከ ኦራሉ ሲያቃጥሉ በርካታ ያገዛዙ ሰራዊት ደግሞ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል::

ከወልድያ ከተማ በመነሳት በግዳጅ በሰበሰበው በርካታ ተሳቢ : አይሱዙና ኤፍኤስአር እንዲሁም ወታደራዊ ኦራል ሎጅስቲክ ጭኖ በዙ-23 : ድሽቃና በርካታ እግረኛ ወታደሮች ታጅቦ ወደሳንቃ አቅጣጫ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሃይል በአሳምነው ክፍለጦር ነበልባል የፋኖ አባላቱ አቀባበል ተደርጎለታል::

ከአፊኬር ወደሳንቃ መግቢያ ዘንዶጅራት የተባለ ልዩ ቦታ ላይ በተወደበት የደፈጣ ጥቃትም ዙ-23 የጫነ ወታደራዊ ኦራል ሙሉለሙሉ ተቃጥሏል: በርካታ ሰራዊቱም ሙትና ቁስለኛ መደረጉን መረጃው ደርሶናል::

የተጠናከረ ዝርዝር መረጃውን ከእዙ ህዝብ ግንኙነት ይዘን የምንመለስ ይሆናል
1👍1
ሰበር ዜና!

ምኒልክ ዕዝ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዙ23 በአር ፒ ጂ ያቃጠለበትንና ያወደመበትን ድል ተጎናፀፈ::

አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነው ወልድያ ከተማ ዙሪያ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ የፋሽስቱ አገዛዝ ዙ23 ልዩ ስሙ ዘንዶ ጅራት የተባለ ቦታ ላይ በአር ፒ ጂ በማቃጠልና በማውደም ብሎም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦር እና የዞብል አምባ ክፍለ ጦር ቃኝ ወልድያ ዙሪያ ከጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ እና ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ቀጠና ላይ በመዝጋት ባጠቃላይ የተጠቀሱት አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ባጠቃላይ አሳምነው ክፍለጦር የዞብል አምባ ክፍለጦር ቃኝን ጨምሮ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ መግቢያ ድረስ ከፍተኛ አመራሮችን ጭምር የማረኩበትን በርካታ ድሎች ሲያስመዘግቡ ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ላይ በመዝጋትና ተጨማሪ የጠላት ሃይል እገዛ እንዳያደርግ በማድረግ የጠላትን ግንኙነት በማቋረጥ ለተገኘው ድል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል::

ማስታወሻ፦ ውጊያው አሁንም ተጠናክሮ ስለቀጠለ የተማረከ ጠላት እና ንብረት በዝርዝርና በማስረጃ ይዘን እንመጣለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

@አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም
4