ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር ዜና

የሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን የ6ኛ ዕዝ 501ኛ ኮር 52ኛ ሻለቃ 12 አባላትን የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ተቀብሏቸዋል።

እነዚህ የሰራዊት አባላት ከ3 ዓመት በላይ የውትድርና ልምድ ያላቸው ሲሆን በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን የዘር ማፅዳት ወንጀል በመቃወም የአማራ ህዝብ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ተቀላቅለዋል።

@አሻራ
3
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ፊውታራሪ ክ/ጦ

በትናንትናው እለት ታህሳስ 22/2018 የአገዛዙ ጥምር ሀይል መነሻውን ምዕራብ ጎንደር የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ከተማ ነጋዴ ባህር በማድረግ አርሶአደሩን ትጥቅ ለማስፈታትና የፋኖ ቤተሰብ፣የፋኖ ደጋፊ በሚል አጀንዳ በሰበባ ሰበቡ ለመዝረፍ እና ጀኖሳይድ ለመፈፀም ወደ ጃኖላ ማርያም እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን ነበልባሎቹ የመይሳው ካሳ ልጆች የፊውታራሪ ክ/ጦ ታጠቅ ብርጌድ 2ኛ ሻለቃ በአርበኛ ባበይ በሬ እየተመራ ቀድሞ መረጃውን በመከታተል አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፤ ጠላት ወደ ቀጠናው ከገባ በኃላ ሙት ወረዳ ላይ ከበባ በማድረግ አይቀጡ ቅጣት ተቀጦ የድረሱልኝ ጥሪ እየቀባጠረ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ እየተዝረከረከ ያሰበውን ሰይጣናዊ ተግባር አንዳችም ነገር ማይደርግ ሳይችል አፍሮና ተቀጥቅጦ ወደ መጣበት ሊመለስ ችሏል።

በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
ሙት = 22
ቁስለኛ = 13
የተማረከ 1 ሚኒሻ እስከ ሙሉ ትጥቁ እና 7 የነፍስ ወከፍ ክላሽ

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ታህሳስ 23/2018
5
አየሩ በጥይት ባሩድ ተሞልቶ፣ ሰማይ ምድሩ በከባድ መሣሪያ ተኩስ እየታረሰ... ምድር ቃጤ በሆነችበት ውጊያ መኃል...ጀግኖቹ በዚህ መልኩ ይጨቃጨቃሉ👉

👉"ክንዳለም ተረጋጋ...አንተ ወደ ኋላ ሁን፡ እኔ ቀድሜ ምሽጉን ልስበር። ከወደኩም አንተ ታነሳኛለህ"

👉"አይሆንም። እኔ ነኝ መቅደም ያለብኝ። እኔ ከወደኩ ታነሳኛለህ እንጂ...አንተ ስትወድቅ ባይኔ ማየት አልፈልግም"

👉"አይሆንም ብያለሁ ክንዴ።እኔ ነኝ ከፊት የምገባው"

👉 " ተናግሬያለው ክንዳለም።እኔ ነኝ ቀድሜህ የምገባው። አንተ ወደ ኋላ ሁን"

ይሄንን ስሜት ልትረዳው የምትችለው አማራ ሆነህ ከምሽግ ስትውል ብቻ ነው።

"ሀገራቸው ጥራሪ ከወትወት ማዶ፡
አነባባሪ የጠላት ክምር፣ የሬ*ሣ ነዶ"
የተባለላቸው የጥራሪ አናብስቱ ...የጠላት አስከሬንን አነባብረው፣ አቆላልፈው ጥለው ስለ አማራ ሕዝብ ሲሉ ክቡር መስዋዕትነትን ከተቀበሉ ሁለትና ሦስት ወራት ተቆጥረዋል።

የልጅ አዋቂዎቹ፣ አንድነት ናፋቂዎቹ....ልባም ክትት ያሉ ጀግኖች።
ይህ ትግል እነዚህን አበባ በመሰሉ ቆራጥ ወጣቶች የነፍስ ግብር የፀና ነው።

ግን አንድነት ይሻል።

ወጥ የሆነ አደረጃጀት፣ አማራዊ አንድ ቤት ካልተሰራ፡ የነዚህና ስለሕዝብ ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የገበሩ ጀግኖች አጥንት ትውልዱን እሾህ ሆኖ ይወጋዋል።

አንድነት?...አንድነት?...አንድነት?...አንድነት?...

@መረብ ሚዲያ
የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር ለበርካታ ወራቶች ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር ለሁለተኛ ዙር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን በርካታ ልዩ ኮማንዶዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::

ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም ለወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ስነ-ስርዓት ተመርቀዋል። በምርቃቱ ላይ የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ተመራቂ ኮማንዶዎችን የእንኳን ደስ አላችሁ መልካም ምኞት ሲገልፁ፤ በሌላ መልኩ የአማራን ህዝብ በታማኝነት እንዲያገለግሉ ታሪካዊ ሃላፊነት የተሰጣቸዉ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ ተመራቂዎቹ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ባግባቡ ተሸክመው ህዝባቸውን ከገባበት ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ እንደሚታደጉ ቃል ገብተዋል::

ስለሆነም በሰላሳ ክላሽ የተጀመረው የአማራ ፋኖ ትግል በአሁኑ ሰዓት ላይ ከእግረኛ ሰልጣኝ እስከ ልዩ ኮማንዶ ሰልጣኝ ብሎም ተመራቂ ፋኖዎችን የማብቃትና የማምረት እንቅስቃሴውን ለአማራ ህዝብ አኩሪና የማንነት ግዳጅም ጭምር ሲሆን ለፋሽስቱ ስርዓት ደግሞ የሞት ደብዳቤን ከመዳፉ ላይ የማስቀመጥ ያክል መሆኑን በተግባር የታየበት ወሳኝ ድል ነው::

ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

@አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
1
ሰበር ዜና!

ብልፅግና መግለጫውን አንብቦ ሳይጨርስ ማርቆስ ዙሪያ ላይ ተዓምር ተሰርቷል።

ሞት አፈሬው 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ከሌሊቱ 11:30 ጀምሮ ባደረገው ትንቅንቅ የሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን ሰራዊት አመድ በማልበስ
1 ሞርተር
1 ዲሽቃ
4 ብሬን
ስናይፐርን ጨምሮ ለቁጥር የሚከብድ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ማርኳል።

ለስድስት ቀናት ተንኳቶ ከደብረ ማርቆስ ተነስቶ ወደ ጮቄ ተራራ ለመውጣት በተንቀሳቀሰው የአረመኔው ሰራዊት ላይ የተቀናጀ ውጊያ የከፈተው 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ጠላትን በመረፍረፍ ታሪክ ሰርቷል።

የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር አሃዶች በዕሮቡ ገበያ በመግባት የጠላትን ኃይል በማዛባት ግዳጇን በብቃት መወጣቷም ታውቋል።

ዝርዝር መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ

የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ባዬ ደስታ
4
ሰበር ዜና!

አምባጊወርጊስ ከተማ  ላይ ፋኖን ከድተው ምህረት በገቡ ከሀዲዎች ላይ የማያዳግም  እርምጃ ተወሰደ!

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር  አሀድ የሆነው  የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጋር በህቡዕ ሲሰራ የነበረው የሚኒሻ አባል በወገራ ወረዳ  በፋኖ ስም ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ሲዘርፋና ሲያግቱ ቆይተው በተጀመረው የፋኖ ማፅዳት ዘመቻ ምክንያት ወደ አባታቸው ብልፅግና ጉያ በምረሽ ስም ተሸሽገው  በእየ አዳራሹ  ሲቀባጥሩና ሲለፈልፋ  የነበሩ ካሀዲዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ።
 
በህብረተሰቡ መብትና ጥቅም ፣  በክፍለ ጦሩ ክብርና አላማው  የማይደራደረው  ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ  ጦር ሰርጎ ገቦችን በህቡዕ በማዘጋጀት ርምጃዎችን መውሰድ ጀምሯል።

የሚኒሻ አባሉ  ሰዓቱ አሁን ነው በማለት  ትናንት  ተህሳስ 23/2018 ዓ/ም ምሽት አንድ ሰዓት ላይ  ሁለቱን  ምረሽ ገቢዎችን  በሞት ቀንድሾ ወደ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በሰላም ተቀላቅሏል።

ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በቀጠናው ህዝብን በመዝረፍና በማገት ከአገዛዙ ሀይሎች ጋር በመናበብና በመቀናጀት ሲሰሩ ቆይተው ምረሽ በገቡ የአማራ አረሞች  ላይ በአምባጊወርጊስ ፣ በጎንደር እና በማክሰኝት ከተሞች ላይ ተመሳሳይ እርምጃዎችን  ለመውሰድ ተዘጋጅቷል ።

  ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!

በአርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
 
2
ሰበር ዜና!

የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል ሚጦ ዙሪያ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  ድባቅ ተመትቶ ተመለሰ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር  ጎንደሬ በጋሻው  ክፍለ ጦር  አጥናፋ ብርጌድ  እና የቴውድሮስ ብርጌድ አንድ ሻለቃን በማቀናጀት የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ማርየ አድማሱ ታህሳስ 23/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ  ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት  ሰዓት ድረስ  በወገራ ወረዳ ሚጦ ቀበሌ ዙሪያ ባደረጉት አውደ  ውጊያ የአገዛዙ ቅልብ ሀይል አስራ አንዱን በሙት አጥቶ ሁለት  ፖትሮል መኪና ቁስለኛውን ታቅፎ ገደብየ ከተማ ገብቷል ።

የአገዛዙ ወንበር  አስጠባቂ  ሰራዊት ሰሞኑን ወደ ጎንደሬ በጋሻው ቀጠና በሌሊት በመንቀሳቀስ የአርሶ አደሩን ሀብትና ንብረት የፋኖ ቤተሰብ፣ የፋኖ  ደጋፊ፣  የፋኖ አርሶ አደር አደረጃጀት ናቹህ በማለት  የጦር መሳሪያቸውን ለመዝረፍና  ቤታቸውን  ለማቃጠል  ከብታቸውን ለመንዳት የሞከረ ቢሆንም  የጎንደሬ በጋሻው  አባላት  ከፍተኛ  መከላከልና ማጥቃት ገጥሞት እየተመታና እየተዋረደ ይገኛል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!

በአርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
  ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም
2
ሰበር ዜና!

ፍፁም ጓዳዊነት የማያውቀው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ሰላሳ አስከሬኑን ጥሎ በሸሸበት ውጊያ ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

የብልፅግና ሰራዊት 30 አስከሬኑን ጥሎ በሸሸበት ፍልሚያ አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር1 የባለሽርጡ ክፍለ ጦር ከ40 በላይ የጠላትን ሃይል በመደምሰስ እና ከ12 በላይ የሚሆነውን በማቁሰል እንዲሁም ከ10 በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

የምስራቅ አማራ ኮር አንዱ ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር ዛሬ ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 7:30 ድረስ በቀጠለው አውደ ውጊያ ከመርሳና ከጊራና በመነሳት ወደ ፋጂ የተንቀሳቀሰውን የስርዐቱን ቅጥረኛ ሰራዊት በመደምሰስና በማቁሰል እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ጠላት ከጊራና ከተማ በስተምስራቅ በኩል ያሉ የፋኖ ቀጠናዎችን ለማጥቃትና ከቻለም ለመቆጣጠር አቅዶ በብዙ ግንባሮች ማለዳ በጀመረው ውጊያ የዋርካው ልጆች ባደረጉት ከባድ መከላከልና መልሶ ማጥቃት በርካታ የጠላትን ሃይል በመደምሰስና በማቁሰል ብሎም በርካታ ተቸኳሽና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ወደ ጊራና ከተማ የሸኙት ሲሆን 30 አስከሬኑንም ሳያነሳ እግሬ አውጭኝ ብሎ ለመሽሽ ተገዷል::

በተጋድሎው በምርኮ የተገኙ ድሎች፦

•10 ጥቁር ክላሽ
•1500 የክላሽ ተተኳሽ
•780 የብሬን ተተኳሽ
•25 የደረት እና 7 የወገብ ትጥቅ
. 13 F1 ቦንቦች
. 3200 የድሽቃ ተተኳሽ

በአጠቃላይ ምኒልክ ዕዝ በተጋድሎው በባለሽርጡ ክፍለጦር አማካኝነት 10 ጥቁር ክላሽ እንዲሁም ከ5480 በላይ ተተኳሽና የእጅ ቦምቦችን እና የወገብና የደረት ትጥቆችን ጨምሮ በርካታ ንብረቶችን አግኝቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
2