ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር የድል ዜና

ፋኖ ደብረሲና ከተማን ተቆጣጠረ ‼️

ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የመሀመድ ቢሆነኝ ኮር ከአፄ አምደ ፂዮን ኮር ከተወጣጡ የክፍለጦር ውስን ሻለቆች የብልፅግናውን አየር ወለድ ኮማንዶ ክፍለጦር እንዲሁም ሪፐብሊካን ወደሚገኝበት ጣርማበር ፣ ደበረሲና እና በአርማኒያ ከተሞች ዘልቀው በመግባት የተቀናጀ ጥቃት ሲፈፅሙ፣ ደብረሲና ከተማ የገባው ጀግናው የፋኖ ሰራዊት በቦርቸሌ ካምፕ ላይ የመሸገውን የጠላት አየር ወለድ ኮማንዶ ክፍለጦርን ሙሉ በሙሉ ደምስሷል::

ጠላት በቀጠናው ያሰማራው ተጨማሪ የ105ኛ ኢሊት ፎርስ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ ታላቅ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

አናብስቶቹ ደብረሲና ከተማን ተቆጣጥረው የአገዛዙን ጦር ከደመሰሱ በኋላ የማረኩትን ማርከው ከስትራጂክ ጠቀሜታ አንፃር ከተማውን ለቀው ጀግኖቹ በክብር ወደምሽጋቸው ተመልሰዋል ።

በዛሬው ልዩ የተቀናጀ ኦፕሬሽን የአምባገነኑ ስርዓት ዙፋን አስጠባቂ ኢሊት ፎርስ አከርካሪውን የተመታ ሲሆን በእግረኛ ሰራዊት የተሸነፈው ብልፅግና ሰሞኑን የራሱን ምርኮኞች ጨምሮ በንፁሀን ወገኖቻችን ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት በግፍ የተጨፈጨፉትን የወገኖቻችንን ደም ሳይውል ሳያድር ጠላት ባለበት የሸዋ ሶስት (3) ከተሞች ዘልቆ በመግባት በድል ተመልሷል።

ወገቡ ተመቶ፣ እራሱ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ በሸዋ ተራሮች ላይ የአሞራ ቀለብ የሆነው የአገዛዙ ሰራዊት ምላሱ ብቻ በቀረው የብልፅግናው ተከፋይ የሚዲያ ሚሊሾቹ አማካኝነት ሰሞኑን ፋኖን እያፀዳሁ እየደመሰስኩ ነው ቢልም በዛሬው እለት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በወሰደው መልሶ ማጥቃትና ቆረጣ በተገኘው ድል መላው ሰራዊታችን እና ሰሞኑን በግፍ በተገደሉ ንፁሀን ወገኖች ምክነያት ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ የገባው ህዝባችን ከዚህ በላይ ተከታታይ ስራዎች ሰርተን የምናሳይ መሆኑን እየገለፅን ህዝባችን እስከዛሬ ሲያደርገው እደነበረው ከልጆቹ ጋር ተሰልፎ የስረዓቱን እድሜ እዲያሳጥር መልዕክት እናስተላልፋለን !! 

ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታ !!
ድል ለአማራ ፋኖ !!    
ድል ለአማራ ህዝብ !!
           
@ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
1
"እየዘፈኑ ድህነት እያለቀሱ ክብረት"

በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስባቸው ከደሴ ከተማ በስተምዕራብ በሚገኙ 11 ወረዳዎች ውስጥ የሰርግ ጥሎሽ አምስት ሺህ ብር ብቻ እንድሆን መወሰኑና በያዝነው ዓመት መባቻ ላይ መመሪያ ማውጣቱ ይታወቃል:: የመመሪያውን ተፈፃሚነት ይከታተል ዘንድ ኮሩ በየወረዳዎች የመደበው ግብረኃይል የሰበሰበው መረጃ እንደሚያስረዳው ህዝባችን ራሱ ያፀደቀውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ያልቻለበት ሁኔታ ተፈጥሯል:: ወይ መቶ ወይ መተው እየተባለ እስከ መቶ ሺህ ብር ድረስ ጥሎሽ በመጣል ገደብ የለሽ እና ድሀን አግላይ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን ደርሰንበታል:: ሰርግ ምስለት እየዘፈኑ ክስረት ሆኗል:: አላማውንም እየሳተ ነው!

በምድር በሰማይ እሳት እየነደደበት ያለው ህዝባችን በጦርነቱ ከደረሰበት የኢኮኖሚ ድቀት እና የማህበራዊ እረፍት እጦት በተጨማሪ በእንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ የሆኑ ባህላዊ ክዋኔዎች አሉ:: ከእነዚህ ባህላዊ አሰራሮች አንዱ የሆነው በተጋነነ ድግስ የሚከወን የሰርግ ስነ ስርዓት ነው:: ለሰርግ ብቻ ሳይሆን ለተዝካር እና ሰደቃ ያለ የሌለን ጥሪት አሟጦ የመደገስ ውሳኔ ከሀይማኖት ባሻገር ባህላዊ እየሆነ ነው:: ሐይማኖቶች በሚፈቅዱት መሰረት ተብቃቅቶ ህይወትን መምራትና አላስፈላጊ ወጭዎችን መቀነስ ተገቢ ስለሆነ ይህን ለማድረግ ይቻል ዘንድ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በሰርግ ዙሪያ መመሪያ አውጥቷል:: ይህ መመሪያ የሚደነግገው የሰርግ ጥሎሽ ከ 5 ሺህ ብር መብለጥ እንደሌለበት ነው::

መመሪያውን ተላልፎ የሚገኝ አካል 10 ሺህ ብር የሚቀጣ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከ5 ሺህ በላይ የከፈለው ገንዘብም ለፋኖ ገቢ ይሆናል:: ይህ ማለት አንድ ግለሰብ ለሰርግ ጥሎሽ በሚል 100 ሺህ ብር ቢከፍል 95 ሺህ ብር ለፋኖ ገቢ ሲሆን 5 ሺህ የሚሆነው ብር ደግሞ ለሴት አባት ይደርሳል ማለት ነው:: 10 ሺህ ብር ከፋይ የሚቀጣው ለህግ ጥሰቱ ማስተካከያ እርምጃ በማስፈለጉ መሆኑን ህዝባችን ከወዲሁ እንድገነዘብ ስንል ለማስታወስ እንወዳለን::

ስለዚህ ከዛሬው እለት ማለትም ከታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሰርግ ጥሎሽ 5 ሺህ ብር ሲሆን ከዚህ ቀደም ሌላ የገንዘብ መጠን ተጠይቀው የተወሰነ ፐርሰንት ከፍለው የነበሩት ደግሞ በውላቸው መሰረት ቀሪውን እንድከፍሉ ይገደዳሉ:: ከዛሬ ጀምሮ የሚፈፀሙ  የጥሎሽ ስምምነቶች ጣራ ግን 5 ሺህ ብር ብቻ መሆኑ ይታወቅልን ሲል የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ ሻለቃ አብነው ታደሰ አሳስቧል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
4
የህዝቡን አንድነት በማፅናት አስተማማኝ የህዝብ ደጀንነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስታወቀ።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ በመልሶ ማደራጀት ትግበራው የህዝብን አስተዳደር የፀጥታና የፍትህ ጥያቄዎችን በመመለስ አስተማማኝ የህዝብ ደጀንነትን እንዲያረጋግጥ ታስቦ በአዲስ የተዋቀረው ጊዚያዊ መንግስት በ206ኛ ኮር ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች አገልግሎት በመጀመር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

በ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ከጠላት ነፃ በወጡ ሁሉም ቀበሌዎች የአስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት የፍትህና ህግ አገልግሎት፣ ፀጥታ፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በማከናወን ከህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በፍጥነት ምላሽ በመስጠት አመርቂ ለውጥ እያስመዘገበ መሆኑን የወረዳው ጊዚያዊ መንግስት ገልጿል።

የህዝብን አስተማማኝ ደጀንነት በማረጋገጥ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ጊዚያዊ መንግስቱ የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት የአካባቢያቸውን ሰላም በማረጋገጥ እንደቻሉ በማውሳት የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ድርጅታዊ ግዳጅ ከመደበኛ ሰራዊቱ ጎን ተሰልፈው እንደሚወጡም አረጋግጧል።

በመልሶ ማደራጀት ትግበራው ባንዳዎችን በማፅዳት የሰራዊቱን የህዝቡንና የትግሉን ደህንነት በማስጠበቅ የጠላትን እረጅም እጅ እየቆረጠ የሚገኘው 206ኛ ኮር ለደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች፣ በህግና እና ስነ-ስርዓት  እንዲሁም በጊዚአዊ መንግስት መመሪያዎች ላይ ከ14ኛ ክ/ጦር አመራሮች ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጧል።

የድርጅቱን ህግ እና ደንብ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የፀደቁ መመሪያዎች ላይ ስልጠና የተሰጣቸው የወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች ህዝቡን ለማስተዳደርና የድርጅታችንን ህግና ደንብ ለማስፈፀም በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ተናግረዋል ።

አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!

@የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ለክፍለ ጦር አመራሮችና ለሰራዊት አባሎች ፖለቲካዊ ስልጠና ሰጠ::

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ለተከታታይ ሶስት ቀናት አጠቃላይ ለክፍለጦር፣ ለሻለሻለቃ አመራሮችና አጠቃላይ ለሰራዊቱ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የአብይ አህመድ አገዛዝ ወሮበላው የኦሮምማው ስብስብ አማራን ለማጥፋት በተለያዩ የአማራ ግዛቶችና ከአማራ ግዛቶች ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት እያደርገ መሆኑን አለም የሚያቀው ሀቅ ነው።

ሆኖም ይህን የብልፅግና ፋሽስታዊ ስርዐት የአማራ ልጆች በነበልባል ክንዳቸው እየተፋለሙትና እየመከቱ የበላይነታቸው እየወሰዱ ይገኛል። ስለሆነም የአሳምነው አናብስቶች ከትግሉ ጎን ለጎን በተለያዩ ለሰራዊት ፖለቲካዊ ስልጠና ማለትም፦

*የሰራዊት ስነምግባር እና ስነስረዓት መወሰኛ ደንብ
*ጓዳዊ ዝምደና
*ባህል እና ጨዋነት
*ድርጅትና የድርጅት ምንነት
*የአማራ ህዝብ ምንነት እና *የገጠሙት ፈተናወች እና ያደረጋቸው ተጋድሎወች
*ፋኖነት እና መገለጫ ባህሪያት በሚሉ
አርዕስቶች ላይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ ኢያሱ ሙሉጌታ ፣ የአሳምነው ዕዝ ህግ ክፍል ሀላፊ አርበኛ ተስፋዬ ገስጥ እና የአሳምነው ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ሻለቃ ሞገስ ለማ በመሆን ከትምህርት እና ስልጠና መምሪያ  በተሰጠው ዕቅድ መሰረት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ክር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር  የሻለቃ አመራሮች እና ለሰራዊት አባላት  በበቂ ሁኔታ ስልጠና በመስጠት አመርቂ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

በስልጠናውም የተገኙት የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር አመራሮችና የሻለቃ አመራር አባላት በስልጠናው የአማራን የሞኖር ነፃነት በቅርቡ እንዲሚያበስሩ እርግጠኛ እየሆኑ ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሚሰጣቸውን ማነኛውምንም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው

"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"

@የፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
1
ሰበር ዜና

የሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን የ6ኛ ዕዝ 501ኛ ኮር 52ኛ ሻለቃ 12 አባላትን የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ተቀብሏቸዋል።

እነዚህ የሰራዊት አባላት ከ3 ዓመት በላይ የውትድርና ልምድ ያላቸው ሲሆን በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን የዘር ማፅዳት ወንጀል በመቃወም የአማራ ህዝብ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ተቀላቅለዋል።

@አሻራ
3
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ፊውታራሪ ክ/ጦ

በትናንትናው እለት ታህሳስ 22/2018 የአገዛዙ ጥምር ሀይል መነሻውን ምዕራብ ጎንደር የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ከተማ ነጋዴ ባህር በማድረግ አርሶአደሩን ትጥቅ ለማስፈታትና የፋኖ ቤተሰብ፣የፋኖ ደጋፊ በሚል አጀንዳ በሰበባ ሰበቡ ለመዝረፍ እና ጀኖሳይድ ለመፈፀም ወደ ጃኖላ ማርያም እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን ነበልባሎቹ የመይሳው ካሳ ልጆች የፊውታራሪ ክ/ጦ ታጠቅ ብርጌድ 2ኛ ሻለቃ በአርበኛ ባበይ በሬ እየተመራ ቀድሞ መረጃውን በመከታተል አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፤ ጠላት ወደ ቀጠናው ከገባ በኃላ ሙት ወረዳ ላይ ከበባ በማድረግ አይቀጡ ቅጣት ተቀጦ የድረሱልኝ ጥሪ እየቀባጠረ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ እየተዝረከረከ ያሰበውን ሰይጣናዊ ተግባር አንዳችም ነገር ማይደርግ ሳይችል አፍሮና ተቀጥቅጦ ወደ መጣበት ሊመለስ ችሏል።

በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
ሙት = 22
ቁስለኛ = 13
የተማረከ 1 ሚኒሻ እስከ ሙሉ ትጥቁ እና 7 የነፍስ ወከፍ ክላሽ

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ታህሳስ 23/2018
5
አየሩ በጥይት ባሩድ ተሞልቶ፣ ሰማይ ምድሩ በከባድ መሣሪያ ተኩስ እየታረሰ... ምድር ቃጤ በሆነችበት ውጊያ መኃል...ጀግኖቹ በዚህ መልኩ ይጨቃጨቃሉ👉

👉"ክንዳለም ተረጋጋ...አንተ ወደ ኋላ ሁን፡ እኔ ቀድሜ ምሽጉን ልስበር። ከወደኩም አንተ ታነሳኛለህ"

👉"አይሆንም። እኔ ነኝ መቅደም ያለብኝ። እኔ ከወደኩ ታነሳኛለህ እንጂ...አንተ ስትወድቅ ባይኔ ማየት አልፈልግም"

👉"አይሆንም ብያለሁ ክንዴ።እኔ ነኝ ከፊት የምገባው"

👉 " ተናግሬያለው ክንዳለም።እኔ ነኝ ቀድሜህ የምገባው። አንተ ወደ ኋላ ሁን"

ይሄንን ስሜት ልትረዳው የምትችለው አማራ ሆነህ ከምሽግ ስትውል ብቻ ነው።

"ሀገራቸው ጥራሪ ከወትወት ማዶ፡
አነባባሪ የጠላት ክምር፣ የሬ*ሣ ነዶ"
የተባለላቸው የጥራሪ አናብስቱ ...የጠላት አስከሬንን አነባብረው፣ አቆላልፈው ጥለው ስለ አማራ ሕዝብ ሲሉ ክቡር መስዋዕትነትን ከተቀበሉ ሁለትና ሦስት ወራት ተቆጥረዋል።

የልጅ አዋቂዎቹ፣ አንድነት ናፋቂዎቹ....ልባም ክትት ያሉ ጀግኖች።
ይህ ትግል እነዚህን አበባ በመሰሉ ቆራጥ ወጣቶች የነፍስ ግብር የፀና ነው።

ግን አንድነት ይሻል።

ወጥ የሆነ አደረጃጀት፣ አማራዊ አንድ ቤት ካልተሰራ፡ የነዚህና ስለሕዝብ ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የገበሩ ጀግኖች አጥንት ትውልዱን እሾህ ሆኖ ይወጋዋል።

አንድነት?...አንድነት?...አንድነት?...አንድነት?...

@መረብ ሚዲያ
የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር ለበርካታ ወራቶች ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር ለሁለተኛ ዙር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን በርካታ ልዩ ኮማንዶዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::

ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም ለወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ስነ-ስርዓት ተመርቀዋል። በምርቃቱ ላይ የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ተመራቂ ኮማንዶዎችን የእንኳን ደስ አላችሁ መልካም ምኞት ሲገልፁ፤ በሌላ መልኩ የአማራን ህዝብ በታማኝነት እንዲያገለግሉ ታሪካዊ ሃላፊነት የተሰጣቸዉ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ ተመራቂዎቹ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ባግባቡ ተሸክመው ህዝባቸውን ከገባበት ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ እንደሚታደጉ ቃል ገብተዋል::

ስለሆነም በሰላሳ ክላሽ የተጀመረው የአማራ ፋኖ ትግል በአሁኑ ሰዓት ላይ ከእግረኛ ሰልጣኝ እስከ ልዩ ኮማንዶ ሰልጣኝ ብሎም ተመራቂ ፋኖዎችን የማብቃትና የማምረት እንቅስቃሴውን ለአማራ ህዝብ አኩሪና የማንነት ግዳጅም ጭምር ሲሆን ለፋሽስቱ ስርዓት ደግሞ የሞት ደብዳቤን ከመዳፉ ላይ የማስቀመጥ ያክል መሆኑን በተግባር የታየበት ወሳኝ ድል ነው::

ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

@አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
1