ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
#ዜና_ወለጋ - 19 ሰው ተገድሏል!

በምሥራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ፣ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ እና በደጋ ጅጊ ከተማ 01 ቀበሌ ከታኅሣስ 14 ቀን 2018 ጀመሮ 19(አሥራ ዘጠኝ) ሰዎች ተገድለዋል።

ትናንት ቅዳሜ ያገኘናቸው 2 ሰዎች በጢሻ ተጥለው በስለት ተወጋግተው የተገደሉ ናቸው የሚሉት ነዋሪዎች ሌሎች እንዲኹ የተሰወሩ ግለሰቦችንም በፍለጋ እያገኙ እንደኾነ ነግረውናል። ልዩ ኃይሉ ከበባ አድርጎ እስከ አኹን ባለው ቆጠራ ብቻ 562 (መኖሪያ ቤት፣ የእህል መጋዘንና መጠጥ ቤቶች) ተቃጥለዋል፣ 29 ሞተር ሳይክል፣ 3 ባጃጅ፣ 1 በቆሎ መፈልፈያ ኮምባይነር ተቃጥሏል። የሚፈልገውን አፍኖ እየጫነ ይወስዳል፣ የቀረውን በማንአለብኝነት ይገድላል ብለዋል።

ፓርቲያችን በመንግሥታዊ መዋቅር እንዲኽ በግልጽ ግፍ መፈጸሙ ያውም በተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ ድምጽ እየተሰማ መደረጉ እጅግ ያሳዘነን ተግባር ነው። የማን አለብኝነት ድርጊቱንም በጽኑ እናወግዛለን።

መንግሥት በዓላማና በሥውር የሚፈጽመው ደባ በመኾኑ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጭፍጨፋውን እንዲያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ታኅሣስ ፲፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ሰበር ዜና!!

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ምርጥ ሥብሥብ
ታሕሣሥ 19/2018ዓ.ም

በሰማዕቱ አርበኛ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ሥም የተሰየመው ፩ኛ ኮር 04 ብሬኖችን፣ ክላሾችንና ብዛት ያለው ተተኳሽ ከጠላት ማርኳል።
ይህ ድል የተገኘው ከ04ቱም ክፍለ ጦሮች በተውጣጣ ዕንቁ የተዋጊ ስብስብ ነው።

ተጨማሪ የተማረከ ተተኳሽን በቁጥር፣ የተማረከ ነፍሥ ወከፍና ቡድን መማሪያዎችን በቁጥር እንዲሁም በጠላት ላይ የደረሰውን ድምሰሳና ቁሳዊ ኪሣራ በቁጥር እናሥቀምጣለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
2🙏1
ሰበር ዜና!

የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች ዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ ሁለት የጠላት ምሽግ በመስበርና በርካታ ሃይሉን በመደምሰስ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::

የምኒልክ ዕዝ ደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች ታህሳስ 20/2018 ዓ/ም የዳውንት ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ኩርባ ከተማ ዘልቀው በመግባት ሁለት  ምሽግ ሲሰበር፤በምሽጉ የነበሩት የጥላት ሰራዊቶችም ተደምስሰዋል።

ከማለዳው 12:00 ላይ የተጀመረው የተጠና ኦፕሬሽን ጤና ጣቢያ ምሽግና ከፖሊስ ጣቢያ እስከ መድሃኒአለም ያለውን ምሽግ በመስበር የጥላት ሰራዊት በምሽጉ እዳለ ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ ተደምስሷል።

የተደመሰሱ የጥላት ሰራዊቶች ቁጥራቸው ለጊዜው በወል ያልታወቀ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ አስከሬን እዳያነሳ የብልፅግና ሰራዊት ከልክሏል። የውሸት ፕሮፖጋንዳውን ለአብይ ወንበር ሲባል የሚደመሰሱ ጥምር የጠላት ሃይል አሰከሬን ማህበረሰቡ እዳያቅ እና በተደመሰሱ ሰራዊቱ ፕሮፖጋንዳ ለመስራት ሲባል የአካባቢው ማህበረሰብ በተሰበሩት ሁለት ምሽጎች አካባቢ እዳይቀሳቀስ ተደርጎ ፋሽስቱ አስከሬኑን እያጋዘ ይገኛል።

በርካታው ወደ አምላኩ የተሸኘው የአረጋ ከበደ ሰራዊት የሆኑት ሚኒሻና ፖሊሶች ሲሆኑ፤ አዳራሽ አካባቢ እና ጤና ጣቢያ ባለው ምሽግ የሽመልስ አብደሳ ሰራዊቶችም ተደምስሰዋል።የሚኒሾችና የፖሊሶች አስከሬን በወረዳው ውስጥ ወደዬ ቀበሊያቸው እየተከፋፈለ ይገኛል። ቁስለኞች በኩርባ ጤና ጣቢያ ውስጥ "ዋይ ዋይ" እያሉ ሆስፒታሉን ሞልተውታል።

የኮሩ አሃዶችም በተጠና ኦፕሬሽን ተቀሳቅሰው አስፈላጊውን ውጤት የተገኘ ሲሆን ከነ አረጋ ከበደ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ማግስት መራርና ጠንካራ ጥቃትን በፋሽስቱ ሰራዊት ላይ  መፈፀሙ፤ በህይዎት በተረፉ የጥላት ሰራዊትና ካቢኔዎች ደግሞ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ሆነው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግም ተችሏል።ያልነጠፈ የኮሩ የድል ግስጋሴው ለወገን ኩራት ለጥላት ሞትን እያጎናፀፈ ቀጥሏል!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር 
ህ/ግንኙነት ክፍል
🙏1
ምኒልክ ዕዝ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በከፍተኛ እና በየደረጃው ባሉ የድርጅቱ አመራሮች የተመሩ የህዝብ አስተዳደር መዋቅሩን የሚያጠናክሩ በርካታ ህዝባዊ ውይይቶች እየተደረጉ ይገኛሉ::

ምኒልክ ዕዝ በተጋድሎው ነፃ ያወጣቸው ቀጠናዎች ላይ በድርጅት አመራሮቹ የተመሩ በርካታ ውይይቶች እየተደረጉ ሲሆን ከህዝቡ የሚመጡ አስተያየቶችንና ፍላጎቶችን መሰረት ያደረገ መመሪያ ጭምር በማውረድ የህዝብ አስተዳደር መዋቅሩን እያጠናከረ ይገኛል::

በዚህም ከህዝቡ ጋር በሚደረጉ ሰፊ ውይይቶች በፋኖ የሚመራው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ያለበትን ትልቅ ደረጃ ለህዝቡ የማስረዳትና የማስገንዘብ ብሎም ህዝቡ ደጀንነቱን እስከ ድልና ነፃነት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጭምር በመነጋገር የጋራ አቋም ተወስዶበታል::

*ምስል ራያ ቆቦ ቆባ ንዑስ ወረዳ

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
@አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
"በእነርሱ ውስጥ የሞቱት በእኛ ውስጥ ህያዋን ናቸው"

    በቀን 18/04/2018ዓ.ም በአገዛዙ በደረሰው ጥቃትና በደረሰው ጉዳት ትልቅ አባታችንን ጨምሮ ባጣናቸው ወንድሞቻችንን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን ተስፋዬ መካሻ ሀብተወልድ ግፋወሰን ዕድሜ ያልበገረው ቅን እና ጀግና አባት ነበር።

ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትግል ሜዳ ሲመጣ ወደ ትውልድ ቀዬው መርሐቤቴ በመግባት መሬት ላይ ያለውን የኃይል አሰላለፍ በሚገባ የራሱን ጥናት ሰራ። በወቅቱ በሸዋ ላይ የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ኃይሎች በሶስት መዋቅር ስር የነበሩ ናቸው። ይኼንን መመልከቱ ከምንም ነገር በፊት እና በላይ አንድነት ላይ መስራት እንዳለበት ስላስገነዘበው ለዚህም እጅግ ከባድ የሆነውን የሸዋ መልክዓምድር በጠንካራ ወታደራዊ ዲሲፕሊን በኖረበት ወታደራዊ የአካል ብቃት የነበሩትን ልዩነቶች ደግሞ በአስተዋይ የአባትነት መንፈሱ በመጠቀም ለአንድነቱ የሚጠበቅበትን ለመወጣት እንቅስቃሴውን ጀመረ። በመርሐቤቴ ከአንድ አማራ ፋኖ ጋር ያደረገውን ውይይት ተከትሎ ወደ ይፋት በመጓዝ ከአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት በሸዋ ጋር በመድገም በመቀጠል በዚያው በይፋት ከሚገኘው የአማራ ፋኖ ነፃ ህዝብ ንቅናቄ ዋና መሪ አርበኛ እና ደራሲ አሰግድ መኮንን ጋር በማድረግ የሸዋን የአንድነት ጉዞ ጀመረው። በመቀጠል በሸዋ ላይ እጅግ ረጅም እና ጥልቅ ውይይት በማመቻቸት የአቅሙን የተወጣው ጋሽ ተስፋዬ በየወቅቱ ይፈጠሩ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት የሽምግልና ወጉን በመወጣት ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆየ።

"ደክሞት አይቆምም የሸዋ ፈረስ
ከአንኮበር ዘልቆ ሀማሴን ድረስ" እንዲል ዜመኛው በሸዋ መወሰን ያልበቃው ጋሽ ተስፋዬ መሰል ወንድሞቹን በመያዝ የአማራን አንድነት ለማምጣት በዚያ በክረምት ወራት ታላቁ የአባይ ወንዝ እንኳን የሚሻገረውን በሩቅ የሚያየውን በሚያስፈራበት ወቅት ወደ ጎጃም በመሻገር በመቀጠልም ወደ ወሎ እና ጎንደር በመሄድ የአማራን አንድነት ለማምጣት ማንም ያልቻለውን ችሎ አሳይቷል። የምን ጊዜም ምኞቱ የነበረው፤ የዘወትር ጸሎቱ የነበረው "የአማራን አንድነት ሳላይ እንዳልሞት" የሚለውን ቃሉን ነፍሱን በማይፀፅታት መንገድ ኖሮታል።

ጋሽ ተስፋዬ ሌሎች ሊኖራቸው የሚያልሙትን የቅንጦት ህይወት በመተው ከሀገር ውጭ የነበራቸውን ኑሮ እና ቢዝነስ ከአማራ ህዝብ ህልውና አንፃር ምንም እንዳልሆነ በማመን ይኼንን ትግል ከተቀላቀሉ ወዲያ ለአንድ አባት እጅግ ከባድ የሆነው ልጅን የማጣት መከራ በዕድሜያቸው ማባሪያ ጊዜ ደረሰባቸው። ይኽንን መከራ ተሸክመው የአባትነት ፍቅራቸው የጫነባቸውን ሀዘን ለነፃነት ባለቸው ፍቅር መክተው ቆይተዋል።

ባለፈው አንድ ዓመት የነበራቸው ጊዜ ለአንድ ይኼን ሁሉ መስዋዕትነት ለከፈለ አባት የማይገባ ቢሆንም ሁሉንም ተቋቁመው እስከ ትናንትናዋ ሌሊት ከትግል ሜዳው ሳይወጡ ኖረው አገዛዙ ባደረሰው የድሮን ጥቃት ትናንት የህይወታቸው ምዕራፍ ከነሙሉ ታማኝነታቸው በመስዋዕትነት ተቋጭቷል።

የጋሽ ተስፋዬ ህይወትም ሆነ መስዋዕትነት የአንድ ግለሰብ ኑሮ እና ፍፃሜ ሳይሆን የአማራ አባቶች ህልም፤ ፍላጎት፤ ቁጭት፤ አላማ፤ ወግ፤ ክብር የሚነበብበት መፅሐፍ ነው። የአማራ አባቶችን የአማራ አያቶችን ከሞቀ ጎጇቸው አውጥቶ ከልጅ ልጆቻቸው ጋር የሚያታግላቸው በገዛ ሀገራቸው የታወጀባቸው የሞት አዋጅ ነው። የሚቀለበሰውም አባቶቻችን አውግተውን ሰምተን፤ ከትበውልን አንብበን፤ ባገኘነው ታሪክ እና መንገድ ብቻ ሳይሆን ኖረው አሳይተውን በዘረጉት የዘለዓለማዊ ህያውነት መንገድ ጭምር ነው።

  በትናትናው እለት አገዛዙ ባደረሰው የድሮን ጥቃት ንፁሃንን ጨምሮ የተሰው ወንድሞቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን መግለፅ እንወዳለን።

የስኬት ክብደቱ
የምቾት አይነቱ
የነገ ውበቱ
ባሻው ቋት ቢለካ በምንም ቢሰፈር
ባሻው ቃል ቢነገር :
ጀግና ልጅ አትወልድም
አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር!

ክብር ለተሰዉት!
ድል ለአማራ ህዝብ!
💔1
የምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ የድርጅትና የኮር አመራሮች በተለያዩ ቀጠናዎች የሰራዊት አደረጃጀትና አጠቃላይ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ግንባታ እየሰጡ ይገኛሉ::

በዚህም በቅርቡ የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጥልቅ ግምገማና ውይይት በማድረግ የአመራር ጥገና ያደረገው የምስራቅ አማራ ኮር አንዱ ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ሰራዊትን በተለያዩ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ መሰረታዊ የሚባል ግንባታ ሰጥተዋል::

ከፍተኛ አመራሮቹ ትኩረት ያደረጉባቸው ነጥበችም የሚከተሉት ናቸው፦

1ኛ.የድርጅቱን ቀጠናዊ ትስስር እና ፖለቲካዊ ግንባታ 
     በአርበኛ አበበ ቀዮ

2ኛ.የሲቪል አስተዳደር መዋቅር  
አስፈላጊነት እና ዘመናዊ የሰራዊት አደረጃጀትና ውህደትን በተመለከተ
በአርበኛ አሰፋ መሰለ (አሳምነው)

3ኛ.ስለ ድርጅቱ አሁናዊ ቁመና እና አንድነትን እንድሁም አጋርነትና ትብብርን በተመለከተ 
በአርበኛ እስራኤል እሸቴ

4ኛ.የወታደራዊ አቅም ግንባታ
በአርበኛ ደባሽ መምሬ (አባ ነጋ)

እነዚህን እና ሌሎች ቀጠናዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮችን ጭምር በመዳሰስና በማንሳት ለሰራዊቱ ግንባታና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ሰርተዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
1🙏1
"ህዝቤን ለሚጨፈጭፈው ሰራዊት አባል ሁኘ የወገኔን እልቂት ማየት አሞኛል" ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ

በመከላከያ ሰራዊት የሪፐብሊካን ኃይል ሜንቴናስ መምሪያ ቡድን መሪ እና በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ automotive engineering የድግሪ ምሩቅ፣ በወታደራዊ ክፍል የ25ኛ ክ/ጦር አባልና በውትድርና አለም ለ14 ዓመት በማገልገል የእረጅም አመት ልምድ ያለው ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮርን ተቀላቅሏል።

የአረመኔው ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አውጆ ከተንቀሳቀሰ ጊዜ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከጀነራል  እስከ ተራ እግረኛ ወታደር ድረስ በእየጊዜው እየከዱ ትግሉን የተቀላቀሉ ሲሆን ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ ከሪፐብሊካን ኃይል ሜንቴናስ መምሪያ በመውጣት ለአማራ ህዝብ ነፃነት የሚዋደቀውን የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮርን ተቀላቅሏል።

የመከላከያ ሰራዊት ከተቋቋመለት ሀገራዊ ተልዕኮ በተቃራኒው በእራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት በመክፈት ኢትዮጵያን ለመበታተን ቆርጦ ተነስቷል ያለው ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ ሰራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር ከማስጠበቅ ይልቅ በመላ ሀገሪቱ ሰፈር ለሰፈር እየዞረ ህዝብን መጨፍጨፍና መግደል ተቀዳሚ ተግባሩ አድርጎታል ሲል ተናግሯል። ከተራ አባል እስከ ከፍተኛ የጦር አመራሮች በአንድ ብሔር የበላይነት የተቋቋመው የመከላከያ ሰራዊት ለግለሰቦች ስልጣን እና የብልፅግና ዘብ ሁኖ ከመቆም ያለፈ አላማውን የዘነጋ የኢትዮጽያን ህዝብ ባገኘበት ሁሉ የሚገድል የሚያሳድና የሚዘርፍ ወንበዴ ቡድን እየሆነ መምጣቱን አክሎ ገልጿል።

ከ5 አመታት በፊት የነበረው የሰራዊቱ አሰላለፍ ተቀይሮ በየ ሰፈሩ ምሽግ ቆፍሮ ውሎ የሚያድረው የሰራዊት አባላቱ በግዳጅ እየታፈሰ ሰልጥኖ የተመረቀና የተሰለፈለትን አላማ ጠንቅቆ የማያውቅ በመሆኑ በህዝብ ላይ እያደረ ያለው እልቂት በኢትዮጽያ ታሪክ ተፈፅሞ የማያውቅ ነው ሲል ሰራዊቱ ህዝብ ጠል እንዲሆ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አመላክቷል።

የአማራን ህዝብ በኃይል ለማንበርከክና መንግስታዊ የዘ ፍጅትን ተቀብሎ በሙሉ ኃይሉ ጭፍጨፋ እያደረገ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ሙሉ ሰራዊቱን በክልሉ አስገብቶ ከድሮን እስከ እግረኛ ሰራዊት እያደረሰ ያለው የዘር ጭፍጨፋ በወገኔ ላይ ከፍተኛ እልቂት ተፈፅሟል ያለ ሲሆን ህዝቤን ለሚገድለው ሰራዊት አባል ሁኘ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ እረፍት ስለነሳኝ ከወንድሞቸ ጋር ለመታገል 206ኛ ኮርን ከአዲስ አበባ መጥቸ ተቀላቅያለሁ ብሏል።

"ከራስ በፊት ለህዝብ" የሚለው የተቋሙ እሴት ተንዶ ሰራዊቱ ህፃናትን፣ሴቶችንና እናቶችን በመድፈር፣ንፁሀንን በመግደል እና በመረሸን፣የወንድን ልጅ ብልት፣የሴትን ልጅ ጡት በመቁረጥ የራሱን ህዝብ በማዋረድ እጅግ አረመኒያዊ ተግባሩን ያለ እርህራሔ እየፈፀመ ይገኛል ብሏል። የአማራ ህዝብ በፋኖነት ተደራጅቶ ሊያጠፋው የመጣውን ኃይል መታገል ፍትሐዊ ነው የሚለው ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ የመከላከያ ሰራዊት በሁሉም የኢትዮጽያ ህዝብ የተጠላ ህዝባዊ ድጋፍ የሌለው ከህዝብ የተነጠለ ኃይል መሆኑን በአይኔ ተመልክቻለው ያለ ሲሆን የአማራ ህዝብ ለመከላከያ አይደለም ድጋፍ ለመስጠት ይቅርና የሰራዊቱን ዩኒፎርም ማየት እንደሚጠየፍ ጠቁሟል።

በመጨረሻም ትግሉን ከተቀላቀለ ቀናትን ያሳለፈው ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ የፋኖ ሰራዊት በአጭር ጊዚያት ያስመዘገበው ድል ፣ የአላማ ጥናት፣ የትጥቅ ሁኔታ ፣ ጠንካራ አደረጃጀትና የማይቋረጥ የህዝብ ድጋፍ ያለው መሆኑ እንዳስደነቀው ጠቁሞ የመከላከያ ሰራዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ በሻለቃ ሊኖረው የሚገባ 480 ያላነሰ የሰው ኃይል በሚደርስበት ምት እና የሰራዊት ኩብለላ ወደ 180 የሰው ኃይል በማሽቆልቆል እየተበታተነ መምጣቱን አክሎ ገልጿል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳብ! አዲስ ተስፋ!
@አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
🙏1
የስርዓቱ ታማኝ ዘብ ከሆነው መከላከያ በመረጃና ደህንነት ስራ የተሰማራው ደህንነት በፋኖ ቁጥጥር ስር ዋለ።

አበበ አዛናው የተባለው የ74ኛ ክ/ጦር አባሉ በመረጃነት ልዩ ስልጠና ተሰጥቶት በተለያዩ ቦታዎች ሲሰራ የቆየ ሲሆን በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ በመቄት የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች እና በደቡብ ጎንደር ጋይንት ጨጨሆ አካባቢ በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች ቅንጅት በደብረዘቢጥ በቁጥጥር ስር መዋል ችሏል።

የመረጃ አቅሙ እያደገ የመጣው የቀጠናው የፋኖ ኃይል በክትትል ይዞ ባደረገው ማጣራት ባንዳው የመከላከያ መረጃና ደህንነት ሰው የሆነው አበበ አዛናው ፋኖን እና የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቶት ወደ ስራ መሰማራቱን ገልጾ ስርዓቱ በአማራ ሕዝብ ላይ ለሚያደርሰው ሁለተናዊ ግፍ ተባባሪ ነበርኩም ብሏል።

በሌላ በኩል በእጃችን በርካታ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ አካላትን ይዘናል ያለው በቀጠናው የተቋቋመው የጋራ ግብረኃይል የኦሮሙማውን ስርዓት ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት በብቁ ቁመና ላይ እንገኛለን ያለ ሲሆን አሁንም በባንዳነት የተሰማራችሁ የአገዛዙ ፈረሶች ልብ ግዙ ሲል አሳስቧል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
@አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
🙏1