ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከወደ አርሲ የእገታ መረጃ‼️

  በአርሲ ዞን አቦምሳ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ በሚገኘው ልዩ ስሙ "ሞፈር ግቢ" በተሰኘ ስፍራ ላይ 6 አማራ ኦርቶዶክሳውያን (ንፁሃን ዜጎች) ታግተው ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስደዋል ።

  በአርሲ ዞን አቦምሳ ከተማ በቅርብ እርቀት በሚገኘው "ሞፈር ግቢ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ፤ በቀን 16/04/2018 ዓ.ም ከአሰኮ ወረዳ ሰንጎ ቀበሌ ለቅሶ ደርሰው ፒካፕ መኪና እያሽከረከሩ ወደ ናዝሪት ከተማ ሲጓዙ የነበሩ 6 ንፁሃን ዜጎች - አማራ ኦርቶዶክሳውያን ታግተው ወደ አልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን የታጋች ቤተሰቦች መረጃውን አድርሰውናል ።

ይህ አማራ ኦርቶዶክሱን ማረደና በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል እንዲሁም ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቅ...ግፈኛው፣ ዘራፊው፣ ገዳዩ የጥምር ቡድን እነኝህንም ንፁሃን ዜጎች አግቶ ከወሰደ በኋላ ለያንዳንዳቸው #አንድ_አንድ_ሚሊዮን_ብር ጠይቋል ። መረጃውን ያደረሱን የታጋች ቤተሰቦች እንዲህ ሲሉም ተደምጠዋል "ይህ መፍትሄ የታጣለት የማንነት ተኮር ግድያ፣ ዘረፋና እገታ...ዛሬም እንደቀጠለ ነው፤ ይሄው ቤተሰቦቻችን አግተው ከወሰዱ በኋላ ስልክ በመደወል እስከ 1 ሚለዮን ብር ክፍሉ አልበለዚያው እንገድላቸዋለን በማለት እያስፈራሩን ይገኛሉ ፥ ገንዘቡን ብንከፍልም ስለመለቀቃቸው ምንም አይነት ዋስትና የለንም፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ገንዘብ እየተቀበሉ ብዙ አማራ ኦርቶዶክሳውያንን ገድለዋል" በማለት ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

© በጋዜጠኛ፡ አበባየሁ ሰይፈ
💔21
በደብረብርሃን መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሚቀርበውን ድጋፍ ለማደናቀፍና ፖለቲካዊ መልክ ለማስያዝ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በጽኑ እንቃወማለን---መኢአድ
👍1
ቀናቶችን በወሰደው ተጋድሎ ባለሽርጡ ክፍለጦር በመደበኛ ውጊያ እና ደፈጣ ጥቃት አመርቂ ድሎችን አስመዘገበ::

ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ፋጂ በተባለ ቦታ ማዕረጉ በውል ያልታወቀ የስራዐቱ ወታደር ከፍተኛ አመራር ከጊራና ወደ ፋጂ ሲንቀሳቀስ በተያዘ የተጠና ደፈጣ ጥቃት ከነ ፖትሮሉ እና ከአጀቢዎቹ ጋር በመደምሰስ ድል ተጎናፀፈ።

በእብሪትና ትቢት ተሞልቶ የመጣውን የአብይ አህመድ ጭራቅ ሰራዊት በሀብሩ ወረዳ ፋጂ በተባለ ቦታ በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት አንድ ጓድ የስርዐቱ ሀይሎችን በመደምሰስ እና ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ባንዳ የስርዐቱን ወንበር ጠባቂ ሀይሎችን ማቁሰልና መበተን ተችሏል።

ዛሬ ታህሳስ 18/2018 አ.ም ከቀኑ 11:30 በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት አመራሩን ከነተሽከርካሪው በመደምሰስና በማውደም አመራሩን ለማሳለፍ ግራና ቀኝ ቦታ ይዘው የነበሩትን የስርዐቱን ወታደር ጭምር በመደምሰሰና በማቁሰል የጥላትን ቅጥረኛ ሰራዊት ወደ መሬት በግስላዎቹ ነፍጥ እየተፈለፈለ የረገፈ ሲሆን፤ ከፊቱ የሚነጠፈውን ጓዱን የተመለከተ ጥላት ለተዎሰነ ሰዓት ባለበት ቁሞ መሸሻውን ቢያማትርም ግስላው ፋኖ ወደ ፊት በማጥቃት"አንድ ጥይት ለአንድ ጥላት" በሚል የአማራ ብሂል ለአንድ ጥላት በአንድ ጥይት ግንባር ግባሩን ተመቷል።

በርካታ ሙት እና ቁስለኛ ያስተናገደው የአብይ አህመድ ሰራዊት የሞራል ውድቀት፤የቁስ ክስረትን በማስተናገድ፣እና የደረሰበትን ብትር መቋቋም ሲያቅተው ሁለት ንፁሀኖችን በዘፈቀደ ተኩስ በመግደል የዘወትር ግብሩንና አቅዶት የመጣውን የጥፋት ተልዕኮ ሳያሳካ ወደ መጣበት ወደ ጊራና ከተማ መመለስ ተችሏል።አገዛዙ ክፉኛ የቆሰለውን ሰራዊቱን በአንቡላንሶች ወደ ጊራና ጤና ጣቢያ ሲያጓጊዝ አምሽቷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ቀናቶችን በወሰደው የመርሳ እና የአምባሰል ዙሪያ ተጋድሎ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ንጋት 12:00 ከውጫሌ ከተማ እና አምባሰል ዙሪያ ሮቢት አካባቢ በርካታ ሃይሉን ይዞ ወደ አበት ማጥቃት ያደረገ ጠላት ጋር ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ በጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ድል አስመዝግበዋል::

ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በአጠቃላይ ባለፉት አንድ ሳምንት ተከታታይ ቀናቶች ያለማቋረጥ ተጋድሎ በማድረግ ጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት በማድረስ ብሎም የነፍስወከፍ ክላሾችን ጨምሮ በርከት ያሉ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማርከው ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ደምሌ መኮነን
ታህሳስ 18/2081 ዓ/ም
3🙏1
በዣሬው እለት ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ/ም
በደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ከአርገቢያ ወደ ሜጮ በሚጓዝ የጭነት ኦባማ አይሱዙ መኪና ላዬ የነበሩ ተሳፊሪዎች በአገዛዙ ጨፍጫፊ ሃይል ጥቃት ተፈፀመባቸው::

ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ላይ የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ በሻለቃ አክሊሉ መሪነት መከላከያ ሰራዊት የአማራን ዘር መጥፋት ተልኮውን ንፁሀን ላይ አረመናዊ የሆነ ተግባሩን ፈፅሟል:: የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያና ነፍሰ ጡር የሆነችውን መቅደስ ፀሀየ ወደ ስራ ቦታዋ እየተጓዘች እያለ በደረሰባት ጥቃት በሞት እና በህይዎት መካከል ሁና ባህር ዳር ፈለገ ህይዎት ሆስፒታል ገብታለች።

በተጨማሪም 2 አርሶ አደሮች ሲሳይ ፈንታ እና እንዳልካቸው ማሩ የተባሉት በአብይ አህመድ ዙፋን ጠበቂ ሰራዊት በደረሰባቸው አሰቃቂ የመረሸን እርምጃ ለጊዚው ቢተርፉም ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደው በተመሳሰይ ባህር ዳር ፈለገ ህይዎት ሆስፒታል ገብተዋል።

@አፋብኀ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር : ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦርህ/ግ ሃላፊ ፍቅሩ ባየ
መብረቅ ክፍለ ጦር በምዕራብ ወሎ ግንባር ወግድ ወረዳ ውስጥ ፓራ ኮማንዶዎች እና የፓሊስ አባላት በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

ትናንት ለዛሬ ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም አጥቢያ የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ከወግድ ከተማ 17 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ለሚ ተብላ በምትጠራው ታዳጊ ከተማ ውስጥ ካቢ የተባለ ስፍራ ላይ የፋሽስቱ አብይ አህመድ ወንበር ጠባቂዎች ክፉኛ የተመቱ ሲሆን 3 ፓሊሶች እና 10 ፓራ ኮማንዶዎች በድምሩ 13 የጠላት ኃይል አባላት ተደምስሰዋል::

ንስሮቹ በሰሩት በሌሊቱ ኦፕሬሽን ከ5 በላይ ፓራ ኮማንዶዎች ቁስለኛ ሲሆኑ 22 የሚሆኑት ደግሞ ወደ ሽነት ገደል ገብተዋል:: ገደል ከገቡት መካከል በርካቶች በህይወት መትረፍ እንዳልቻሉም ለማረጋገጥ ተችሏል::

የአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ 105ኛ ክፍለ ጦር ኮማንዶዎች ለሚ የሚገኘውን ፓራ ኮማንዶ እና ፖሊስ ለማትረፍ ከወግድ ወረዳ ተንቀሳቅሰው የነበረ ቢሆንም መብረቆቹ መንገድን በእሳት ስላጠሩት ጠላት ምንም ማድረግ ሳይችል ቀርቷል::

ከመብረቅ ክፍለ ጦር ሰራዊት መካከል 1ኛ (አዳነ ሀብትነው) ሻለቃ እና ከ2ተኛ (ደምሰው ጎጡ) ሻለቃ የተውጣጡ አሃዶች ሌሊቱን የፈፀሙት የጦር ሜዳ ጀብዱን ተከትሎ ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ስለገጠመው በቅጥረኝነት ከያዛቸው ተዋጊዎቹ መካከል ከሌሊቱ መዓት የተረፉት ተስፋ ቆርጠው በየ ገጠር ቀበሌዎች ተበትነዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
@አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
2🙏1
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት የተጋድሎ ው
_
__፩
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ ድል ተቀዳጅቷል ።

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ 109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር ጡት ቆራጭ ጨፍጫፊውና አረመኔውን የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት እንደቅጠል ሲያራግፈው ውሏል።
በቀን 18/04/2018 ዓ.ም መነሻውን ከገነት አቦ ፣ከጂጋ እና ከፍኖተሰላም ያደረገው የጠላት ሀይል ማክሰኝን ላይ በ3 አቅጣጫ ዙ 23 ጨምሮ ያለ የሌለ ሀይሉን ይዞ ለመግባት ቢሞክርም ክንደ ነበልባሉ የ77ኛ ክፍለጦር ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት እሰከ 10:00 ሰአት 6ተኛ ሬጂመንት/ቃኝና መሀንዲስ / ፣3ተኛ ሬጂመንት፣1ኛ ሬጂመንት፣5ኛ ሬጅመንት እና ሌሎች የሬጅመንት አባላት በመቀናጀት የመጣውን ጨፍጫፊ ጡት ቆራጭ ሰራዊትን
እያጨደ ሲከምረው ውሏል።

አማራን ከምድረገፅ አጠፋለሁ ብሎ ያቀደው ይህ አረመኔ ስረአት በክንደ ነበልባሎች የ77ኛ ክፍለጦር አናብስቶች ከጥዋቱ12:00-10:00 በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሻምበል አዛዡና መቶ መሪዎችን ጨምሮ ከ40 በላይ የጠላትን ሀይል ደምስሰውታል። ወደ አናብስቶቹ 77ኛ ክ/ጦር ምሽግ ዘሎ የገባው የጠላት ሀይል መውጫ አጥቶ የድረሱልኝ ሲቃ ሲያሰማ ውሏል። ከበባ ውስጥ የገባውን የጠላት ሀይል ለማስለቀቅ ከጅጋ ተጨማሪ ሀይል ወደ ማክሰኝን ለማስገባት ቢሞክርም በደፈጣ ስፔሻሊስቶች ሻለቃ 1 ቀደፈጣ መብረቃዊ ጥቃት የተሰነዘረበት ሲሆን ጠላት ያሰበው ዕቅድ ሳይሳካለት ቀርቷል።

የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው ጨፍጫፊው የጠላት ሀይል ግማሹን አስከሬን ቀብሮ ሌላውን ትቶ ጨለማውን ተገን አድርጎ በሦስት መኪና ቁስለኛውን ጭኖ ወደ ጅጋ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። በዛሬው ዕለት የአካባቢው ማህበረሰብ የጠላትን አስከሬን እያነሳ እየቀበረ ይገኛል።
-በዕለቱ ከ40 በላይ የጠላት ሀይል ተደምስሷል
-ሦስት መኪና የጠላት ሀይል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል
-በርካታ የነፍስወከፍ መሳሪያና ተተኳሽ ተማርኳል
የዕለቱ አውደውጊያ በክንደ ነበልባሎቹ በ77ኛ ክ/ጦር የበላይነት የተጠናቀቀ ሲሆን ማክሰኝን ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ውስጥ ትገኛለች
_
__፪

የመከላከያ ኦፕሬተሩ እና የሞርተር ኦፒው ፋኖን ተቀላቅለዋል ደ

የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን በዛሬው እለት ሙሉ ጥቃቸውን በመያዝ ወደ ፋኖን ተቀላቅለዋል።

1ኛ 10 አለቃ ሰለሞን አለምነው 6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 25 ክፍለ ጦር 6ኛ ሬጅመንት የሞርተር ኦፒ
2ኛ 10 አለቃ ደሳለኝ አባይ አፕሬተር 602ኛ ኮር 25ኛ ክፍለጦር 6ኛ ሬጅመንት ሲሆኑ በዛሬው እለት ፋኖን ተቀላቅለዋል።

____
"ህግ የማስከበር እርምጃው እንደቀጠለ ነው"!!

➛የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ስር የነበሩ የድርጅቱን ወቅታዊ የአደረጃጀት የጦር ፕወዛ በማስመልከት #ቃልኪዳን_ሊቁ ከ64 ክፍለ ጦር በማፈንገጥ በእነማይ ወረዳ ስር-እየሱስ ቀበሌ እና ደጀን ወረዳ ቆሰቆስ ቀበሌ ተቀምጠው የአካባቢው ማህበረሰብን የሚዘርፎ፣ ወጣት ሴቶችን አስገድደው የሚደፍሩ፣ በእነማይ ወረዳ ሁለት አምባ ዲቢሳ እና ማንቆርቆሪያ/አንስላል ቀበሌ የጭነት እና የህዝብ መኪኖችን ሹፊሮችን ተሳፋሪዎችን በማስቆም ለግል ጥቅማቸው እየዘረፉ የሚገኙ ግለሰቦችን በ64ኛ ክፍለ ጦር ህግ ማስከበር ዘመቻ በቁጥጥር ስር እያወሉ ይገኛሉ።

ከእነዚህ የአፈንጋጭ ኃይሎች ውስጥ:-
1ኛ. ዘራፊ መልካሙ አየለ
2ኛ. ዘራፊ ማስተዋል አሠፋ
3ኛ. ዘራፊ ታዴ ዳምጤ የተባሉ ግለሰቦች በእነማይ ወረዳ ማንቆርቆሪያ ቀበሌ ሲዘርፉ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል

➛በእነማይ ወረዳ እድገት በአንድነት ቀበሌ ልዩ ቦታው የዳጓት ለአፈንጋጭ ኃይሉ መረጃ ይሰጥ የነበረ ግለሰቦች እና አፈንጋጮች በ64ኛ ክፍለ ጦር የህግ ማስከበር ዘመቻ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር ውሏል ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

ከእነዚህም ውስጥ:-
1ኛ. ገብሬ ካሰቸው
2ኛ. ሸገው ላቃቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።

➛በ64ኛ ክፍለ ጦር የፋኖ አባላትን የውሸት ትርክት በመስበክ የክፍለ ጦሩን የጦር ፕወዛ እና የተለያዩ ምክንያቶች በማስመልከት ወደ አፈንጋጩ ቡድን ገብተው የነበሩ ግለሰቦች ውስጥ:-
1ኛ. ፋኖ ይሁን ጤነው እና
2ኛ. ፋኖ ሀብታሙ እንደግ አፈንጋጮችን በመታኮስ 64ኛ ክፍለ ጦር ጥሪ ተቀብሎ በሰላም እጅ ሰጥቷል።

በ64ኛ ክፍለ ጦር የግል ጥቅማቸውን ለማሳካት ከጠላት ተልኮ በመቀበል የሚሰሩ ግለሰቦች በአካባቢው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍል አስገድደው ገንዘብ እንዲያግዝ በማድእግ እና አንዳንድ የፋኖ አባላት ቤተሰብ ለመጠየቅ እንደተንቀሳቀሱ የፋኖ አባላትን በአፈሙዝ በመደብደብ እና በማስገደድ የአፈንጋጭ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ አድርገዋል። ከእነዚህም ውስጥ:-
1ኛ. ፋኖ ጌቴ አሻግሬ
2ኛ. ፋኖ ከባዱ ሰናይ
3ኛ. ፋኖ ትዋቸው ዳኜ ሲሆኑ ትዋቸው ዳኜ የ64ኛ ክፍለ ጦር አባል የነበር ቢሆንም እጁን በጥይት በመምታት ህክምና እንዳያገኝ አድርገውት በህክምና እጦት ምክንያት በአፈንጋጭ ቡድኑ እየተሰቃየ ይገኛል።

➛በሌላ መረጃ ከ64ኛ ክፍለ ጦር ከጠላት ተልዕኮ በመቀበል በእነማይ ወረዳ ስር-እየሱስ ቀበሌ እና ደጀን ወረዳ ቆሰቆስ ቀበሌ መቀመጫቸው አርገው የአካባቢውን ማህበረሰብ ሲያሰቃዩ ከነበሩት አፈንጋጮች ውስጥ:-
1ኛ. አብረሀም ፍቃዱ የተባለ ግለሰብ የአገዛዙን ተልኮ ተቀብለው በ64ኛ ክፍለ ጦሩ የቆዩ ቢሆንም የክፍለ ጦሩን የጦር ፕወዛ ምክኛት በማድርግ ከክፍለ ጦሩ በማፈገጥ ቆሰቆስ ከሚገኘው የአፈጋጭ ኃይል ጋር በመሆን የአገዛዙን ተልኮ ተቀብሎ ሲሰራ የቆዩ ቢሆንም ተልኮውን ጨርሶ የትመን 01 ቀበሌ ከሚገኘው የጠላት ኃይል መግባቱ ተረጋግጦል።

➛ከጠላት ተልኮ ተቀብለው በዝርፊያ የተሰማሩ በእነማይ ወረዳ ስር እየሱስ፣ የትመን፣ ዘብች እና አካባቢው ቀበሌ የአካባቢው ማህበረሰብ የሚዘርፍ ማህበረሰቡን የሚያንጋጥጡ ጋጥ ወጥ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና በቁጥጥር ስር የማዋል ዘመቻዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስአስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

@አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
1👍1
#ዜና_ወለጋ - 19 ሰው ተገድሏል!

በምሥራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ፣ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ እና በደጋ ጅጊ ከተማ 01 ቀበሌ ከታኅሣስ 14 ቀን 2018 ጀመሮ 19(አሥራ ዘጠኝ) ሰዎች ተገድለዋል።

ትናንት ቅዳሜ ያገኘናቸው 2 ሰዎች በጢሻ ተጥለው በስለት ተወጋግተው የተገደሉ ናቸው የሚሉት ነዋሪዎች ሌሎች እንዲኹ የተሰወሩ ግለሰቦችንም በፍለጋ እያገኙ እንደኾነ ነግረውናል። ልዩ ኃይሉ ከበባ አድርጎ እስከ አኹን ባለው ቆጠራ ብቻ 562 (መኖሪያ ቤት፣ የእህል መጋዘንና መጠጥ ቤቶች) ተቃጥለዋል፣ 29 ሞተር ሳይክል፣ 3 ባጃጅ፣ 1 በቆሎ መፈልፈያ ኮምባይነር ተቃጥሏል። የሚፈልገውን አፍኖ እየጫነ ይወስዳል፣ የቀረውን በማንአለብኝነት ይገድላል ብለዋል።

ፓርቲያችን በመንግሥታዊ መዋቅር እንዲኽ በግልጽ ግፍ መፈጸሙ ያውም በተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ ድምጽ እየተሰማ መደረጉ እጅግ ያሳዘነን ተግባር ነው። የማን አለብኝነት ድርጊቱንም በጽኑ እናወግዛለን።

መንግሥት በዓላማና በሥውር የሚፈጽመው ደባ በመኾኑ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጭፍጨፋውን እንዲያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ታኅሣስ ፲፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ሰበር ዜና!!

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ምርጥ ሥብሥብ
ታሕሣሥ 19/2018ዓ.ም

በሰማዕቱ አርበኛ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ሥም የተሰየመው ፩ኛ ኮር 04 ብሬኖችን፣ ክላሾችንና ብዛት ያለው ተተኳሽ ከጠላት ማርኳል።
ይህ ድል የተገኘው ከ04ቱም ክፍለ ጦሮች በተውጣጣ ዕንቁ የተዋጊ ስብስብ ነው።

ተጨማሪ የተማረከ ተተኳሽን በቁጥር፣ የተማረከ ነፍሥ ወከፍና ቡድን መማሪያዎችን በቁጥር እንዲሁም በጠላት ላይ የደረሰውን ድምሰሳና ቁሳዊ ኪሣራ በቁጥር እናሥቀምጣለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
2🙏1