ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ጀኔራል ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እና ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በጥምረት ከ105 በላይ የአገዛዙን ሰራዊት በመደምሰስና ከ80 በላይ በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፀፉ!

ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ጄኔራል ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እና ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በጥምረት ባደረጉት ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በጠላት ላይ የበላይነትን በመቀዳጀት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደው ከባድ ትንቅንቅ የጠላት ኃይል በአምስት አቅጣጫ ማለትም ከአስ ከተማ በደጋው ወደ ጭማው አቅጣጫ፣ከአስከተማ ቁልቋል ጊዮርጊስ አቅጣጫ፣ከብልባላ ላልኪው ኩራዝባይ አቅጣጫ፣ከይምርሐ አዲስ አለም ሽልም ድንጋይ አቅጣጫ እና ከዶቅሳ ወደ ወይሎ አቅጣጫ አስፍቶ የመጣውን የጠላት ኃይል ቀድሞ መረጃው የደረሳቸው የክፍለ ጦሮቹ ወታደራዊ መረጃ ክፍሎች ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ቀድሞ በማስያዝ አዲስ አለም ፋጭላ ተራራ የሚገኙ አራት ምሽጎችን በመስበር ጠላት በመጣበት ሁሉም አቅጣጫ የሽንፈት ካባ ተከናንቧል።

ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅና ተጋድሎ ከ105 በላይ የብርሐኑ ጁላ አገር አፍራሽ አራዊት ሰራዊት ሲደመሰስ ከ80 በላይ ቁስለኛውን ይዞ ወደ ላልኪው ከተማ ፈርጥጧል።

በዚህም የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና አራዊት ሰራዊት የአማራ ህዝብ ላይ የግፍ እና የበቀል አፈሙዙን ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎች ላይ በማዞር ዲዝ ባዕለ እግዚአብሔር ላይ ሦስት የንፁሃንን ቤት ሲያቃጥል ኩራዝባይ ላይ አምስት የአርሶ አደሮችን የእህል ክምር በሞርተር ቅምቡላ አቃጥሏል። በዚህ ግፍ ያልረካው የአገዛዙ ምስለኔ ዘውማርያም ቀበሌ ሲገባ አንድ የአምስት ልጆች አባትን እና አንዲት የሁለት ልጆች እናትን በክላሽ ረሽኗል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

@የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
2🙏1
‌‎በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለ ማርያም ማሞ ክ/ጦር ተደጋጋሚ ኦፕሬሽን የተደናገጠው የብልጽግና ሰራዊት በደመ ነብስ የሞርተር ቅንቡላ ወዳገኘበት ሲወረውር ዋለ።

‎በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ተደጋጋሚ ኦፕሬሽን ተስፋ የቆረጠው የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት በደመ ነብስ በሚወረውረው የሞርተር ቅንቡላ የንሀሃን ቤት እና ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው::

‎ተስፋ የቆረጠው የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ከሰፈረበት ካምፕ ሳይወጣ የኃይለ ማርያም ማሞ ክ/ጦር ቦጋለ ሻለቃን አገኛለሁ በማለት በሚወረውረው የሞርተር ቅንቡላ በአካባቢው በሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የቤት እንሰሳት እና ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት ደርሷል::

‎የብልጽግና ሰራዊት የኃይለ ማርያም ማሞ ክ/ጦር ቦጋለ ሻለቃ ጎርፎ በተባለ ቦታ ምሽግ ይዟል ብሎ በመደናገጥ የሞርተር ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነ ከውስጥ የመረጃ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል::

‎በዚህም የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን በተፈጸመ የሞርተር ጥቃት በቄስ ከለላው ይረዱ መኖሪያ ቤት ተኝቶ የነበረ ህጻን ላይ የአካል ጉዳት ሲደደርስ በመክበቢያ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ_ክርሥቲያን በረንዳ ላይ በወደቀ ቅንቡላ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ አካል ጉዳት ደርሶበታል::

‎በተጨማሪም በፍረሀት ቆፈን የአብይ አህመድ መከላከያ በዘፈቀደ የወረወረው የሞርተር ቅንቡላ በአቶ ነጋሽ ተፈረዴ ቤት አካባቢ ወድቆ በልጆቹ እና በቤት እንሰሳት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል::

‎መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ ይታገሱ ጌታሁን ነው።

" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"

@‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
    
በዳባት ዙሪያ ውጊያ ጠላ*ት ከባድ ኪ*ሳ*ራ ደረሰበት!!

  ዘራይ ክ/ጦርና ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦሮች የተወጣጡ ሸጋው ውበትና ይታየው ብርጌዶች በዳባት ከተማ ዙሪያ ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም የአርሶ አደር የጦር መሳሪያ ለመዝረፍ ተሰማርቶ የነበረን የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በመፋለም ባደረሱበት ብርቱ ክንድ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።

በዚህ ትንቅንቅ *የተ*ደ*መ*ሰ*ሰ  31 :ቁስለኛ 55 : የተ*ማ*ረ*ከ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ 16 ሆኖ ተመዝግቧል::

    ከ4ኛ ደጃዝማች  ኮር ዘራይ ሸጋው ብርጌድ ከ5ኛ ዳ/ቴዎድሮስ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ይታየው ብርጌድ በዳባት ዙሪያ በተለይም ቀረሃ በተባለ ቦታ የዓብይ ፋሽስታዊ ሰራዊትን በመምታት ቀሪው ነብሱን ለማትረፍ ወደ ዳባት ሸሽቶ መግባቱ ይታወቃል።

  ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

@አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ህ/ግንኙነት መምሪያ
የድል ዜና!

የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በዛሬው ዕለትም በጠላት ላይ ታላቅ ድልን ተጎናጽፏል።

የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በዛሬው ዕለትም በጠላት ላይ  ታላቅ ድልን ተጎናጽፏል።

ዘራፊና ጨፍጫፊ የሆነው የብልጽግና ወራሪ ሠራዊት ከሞት የተረፈ ግብስብስ ሠራዊቱን በመያዝ ወደ ማርዘነብ ታዳጊ ከተማ ባቀናበት ጀግኖቹ የ14ኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት ማለትም የአንበሳ ደቦሎቹ የቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎች፣ ነበልባሎቹ የክፍለ ጦሩ ኮማንዶዎችና የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር አባላት

በሌሊት በመግባት ጠላትን በእሳት ሰይፋቸው ሲቀስፉት አርፍደዋል።
በጠላት ዙ-23 የታገዘው ውጊያ በጀግኖቹ የፋኖ ሠራዊት አባላት የጨበጣ ተኩስ የበላይነት የታየበት ሲሆን በጠላት ላይ በርካታ ኪሳራን አድርሷል።

እንደ አበደ ውሻ እዚህም እዚያም እየተክለፈለፈ፤ ያገኘው ሁሉ የሚገርፈው የታሪካውያን ጠላቶቻችን ቀኝ እጅ የሆነው የብልጽግና ወራሪ ሠራዊት የጀግኖቹን ምድር እንደዋዛ የሚረግጣት አልሆነም፤ ስም አጠራሩ የጠላትን ልቡና በሚያርበደብደውና ብልት ለይቶ በሚመታው ጀግና ሠራዊታችን የእሳት በትር እየተገረፈ ምድሪቷ   ብልት ለይቶ በሚመታው ጀግና ሠራዊታችን የእሳት በትር እየተገረፈ ምድሪቷ ገሃነም ሆናበት እንደ እሳት እራት እርር ኩምትር እያለ ቀርቷል።
በሌሊት በተጀመረው ውጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል የተቀጠቀጠ ሲሆን ጠላት አስከሬኑንና ቁስለኛውን ሲጎትት ውሏል

በውጊያውም አንድ አይሱዙ  አስከሬን ተነስቷል፣ 3 አምቡላንስና03 ፓትሮል ቁስለኛ የተነሳ ሲሆን ከዚህም መካከል 3 አምቡላንስ ቁስለኛ ሆስፒታል ገብቷል፤ ሶስት ፓትሮል ቁስለኛ ደግሞ በራሱ (በጠላት) ካምፕ ለመታከም ገብቷል።

ድል ለአማራ ፋኖ!
ክብር ለሰማዕታቱ!

@ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት!​
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት የተጋድሎ ውሎ

ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም

_______፩

አፋብኃ ቴዎድሮስ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር የጠላት ሀይልን እየደመሰሰው ይገኛል።

ዳጋዳሞት ፈረስቤት ከተማ የመሸገው ጡትና ምላስ ቆራጩ የብርሃኑ ጁላ ወራሪ ሀይል ወደ ሰቀላና የተለያዬ የገጠር ክፍሎች ለመንቀሳቀስ ቢሞክርም በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር በደጋዳሞት ሻለቃ አከርካሪውን ተሰብሮ ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ ፈርጥጧል። ክንደ ነበልባሎቹ 99ኛ ክ/ጦር ደጋዳሞት ሻለቃ እግር በግር በመከተል በትናንትናው ዕለት በቀን 15/04/2018 ፈረስ ቤት ከተማ ዘልቀው በመግባት የጠላትን ሀይል መውጫ መግቢያ ሲያሳጡት የዋሉ ሲሆን በርካታ የጠላት ሀይልም ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።

_____፪

ወንበር አስጠባቂው ሠራት በደፈጣ ተመታ።

ቀን 16/04/2018 ዓ/ም አፋብኀ ምዕ/አ/ቀ/ ቴዎድሮስ -እዝ 105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር ተወርዋሪ ኮማዶ ሀይል አረመኔ ሰራዊት ላይ የተሣካ የደፈጣ ጥቃት ፈጽማለች።

የአብይ አህመድ አሊ ዙፋን አስጠባቂ ሠራዊት ከዲላሞ ወደ ዝህቭስት ሬሽን ለማቀበል በሚንቀሳቀስበት ወቅት ዳግሳ አቦ ተብሎ ከሚጠራ ቦታ መብረቃዊ ጥቃት ደርሶበታል።በጥቃቱም 17 አረመኔ ሰራዊት ሲገደሉ፣ ቀሪውን መንጋ ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
_______፫

የ109 ኮር 88ኛ ክ/ጦሯ 2ኛ ሻለቃ ለ3ኛ ጊዜ የጠላትን የወረራ ዕቅድ ቀልብሳ መምታት ችላለች።

መነሻውን ከወምበርማዋ ሽንዲ ከተማ ያደረገው የአብይ አህመድ ዘር ጨፍጫፊ /Genocider/ ቅጥረኛ ሠረዊት የአርሶአደሩን ንብረት ለመዝረፍ ከንጋቱ 10 ሠዓት አካባቢ ጀምሮ ወደ አንከሻ ጎጉሳዋ ድንጉሻ ቀበሌ ተንቀሳቅሷል። አይበገሬዋ 2ኛ ሻለቃም የጠላትን የእንቅስቃሴ መረጃ አጤና ገዢ ወታደራዊ ቦታ ላይ በማድፈጥ ብርቱ ክንዷን አቅምሳ በመጣበት መንገድ አሯሩጣ መልሳዋለች። የአርሶ አደሩን ንብረት ለመዝረፍ የቋመጠው የጠላት ሀይል ለ3ኛ ጊዜ የተነኮሰ ሲሆን ዛሬም እነደዚ በፊቱ የወገንን ምት መቋቋም የተሳነው ጠላት ሙትና ቁስለኛውን አንጠልጥሎ ቀጠናውን በንፋስ ፍጥነት እግሬ አውጭኝ በማለት ፈርጥጧል።

_______፬

ለሁለት ቀናት እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ያደረገው 206ኛ ኮር በተለያዩ ግምባሮች ድል ተቀናጅቷል

በትናትናው እለት መነሻውን ከደብረ ማርቆስ ያደረገ የጠላት ኃይል በሁለት አቅጣጫ ወደ ጮቄ ተራራ ለመውጣት ሲንቀሳቀስ የ206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ የፀድ ላይ ባደረገችው ትንቅንቅ ከ30 በላይ የአረመኔውን ሰራዊት በመደምሰስ እቅዱን በማክሸፍ ተዘርግቶ የነበረውን የጠላት ኃይል እሮብ ገበያ ከተማ እንዲሰባሰብ አድርገዋለች። ጠላት ባልጠበቀው ሁኔታ ከኋላው በደረሰበት ጥቃት ወደ ፊት መራመድ ተስኖት አስክሬኑን በፔንፔ የታገዘ ውጊያ ከፍቶ ሲለቃቅም አምሽቷል።

በእሮብ ገበያ ከተማ ተሰባስቦ ያደረው ጠላት ኃይሉን አቀናጅቶ ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በነብረ ገደል ወለቄ ለማጥቃት የተንቀሳቀሰ ሲሆን ከንጋቱ ጀምሮ 24ኛ ክ/ጦር ስናን አባ ጅሜ ሻለቃ በአደረገችው እልህ አስጨራሽ የእጅ በእጅ ፍልሚያ ጠላትን እያብከነከነች መልሳዋለች።

ተደጋጋሚ ድል በማስመዝገብ የጠላትን አስክሬን ያነባበረችው ስናን አባ ጅሜ ሻለቃ የ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር የተውጣጣ ኃይል በመደምሰስ ጠላት መሽጎባቸው የነበሩ 4 ቦታዎች ላይ አስክሬኑን ቀብሮ እንዲመለስ አድርገዋለች።

ሰራዊቱን እያዝረከረከ የሚሮጠው የአረመኔው ሰራዊት በዛሬው እለት በጅምላ የቀበራቸውን ሰራዊቱን ማህበረሰቡ በመረባረብ ከእርሻ መሬቶች እያወጣ የተለየ መቃብር ቦታ አዘጋጅቶ እየቀበራቸው ይገኛል።

በተያያዘ የድል ዜና 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ፣ልዩ ኮማንዶዎችና የቀስተ ደመና ሻለቃ በመቀናጀት ከሌሊቱ 11:00 ጀምሮ በደብረ ኤልያስ ወረዳ ማርዘነብ ቀበሌ በመሸገው የአረመኔው ሰራዊት ላይ በፈፀሙት የከበባ ጥቃት ጠላትን በተኛበት ድባቅ መተውታል።

ሰዓታትን በወሰደው ድንገተኛ ማጥቃት በተኛበት የተቀጠቀጠው የአረመኔው ሰራዊት ከደብረ ኤልያስ ከተማ በዙ-23 የታገዘ ኃይል በመጨመር አንድ አይሲዙ አስክሬን፣3 አምቡላንስ እና 3 ፓትሮል ቁስለኛ በማንሳት ወደ ደብረ ኤልያስ ተመልሷል።

የጠላትን አሰላለፍ እና እቅድ በማጥናት ከፍተኛ ድል እየተቀናጀ የሚገኘው 206ኛ ኮር ፣በጃማ፣ በወለቄ፣በማርዘነብ፣በፀድ ባደረገው ፍልሚያ ከ165 በላይ የጠላት ኃይል መደምሰሱ ተረጋግጧል።

____
መብረቁ የጠላት እራስ ምታትሁኖ ቀጥሏል።

ከሰዴ ወረዳ በሌሊት በተለያዩ አቅጣጫ በመዉጣት ወደ አፍቀራ ቀበሌ ወጦ የነበረዉ የጠላት ሀይልን የ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር እየቀጠቀጠ በመመለስ ቄሳጤ ማሪያም የምትባል ቦታ ላይ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 7:00 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ የሆነ ትንቅንቅ በማድረግ በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ተችሏል በተደረገው ማጥቃት የጠላት ሀይል የመከላከያ አመራሮች ጨምሮ ከ11 በላይ አስክሬን መነሳቱን በርካታ ቁስለኛ ሲጎጎዝ እንደነበር ከአካባቢው ባሉ ነዋሪወች ማረጋገጥ ተችሏል።

የፋኖን ሀይልን መቋቋም ያቃተዉ የጠላት ሀይል ሰዴ ወረዳ ከተማ ላይ በመሆን የአዲስ አለም ቀበሌ የ1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ተቋምን በሞርተር በመደብደብ አዉድሟል።

_______፮
ስቦ ማስከዳት የአብይ እና የብርኃኑ ጁላ ጦር እየፈራረሰ ነው በደጋ ዳሞት ወረዳ ከ23ኛ ክፍለ ጦር በቀን 15/04/2018 ዓ.ም ሁለት መሰረታዊ ወታደር እያንዳንዳቸው ጥቁር ክላሽ በመያዝ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋ ዳሞት ሻለቃን ተቀላቅለዋል ::
1ኛ . መሰረታዊ ወታደር አድነው እንየው
...1ኛ ሬጅመንት ሻምበል 3 ጥቁር ክላሽ እና 91ጥይት
2ኛ.መሰረታዊ ወታደር ንግሩ ደመቀ
..... 1ኛ ሬጅመንት ሻምበል 3 ጥቁር ክላሽ እና 110 ጥይት በመያዝ ተቀላቀለዋል ::
በተያያዘ ከጠዋቱ 1:00 አካባቢ ፈረስ ቤት ከተማ አናብስቶቹ የደጋ ዳሞት ሻለቃ ወደ ከተማ በመግባት በቴክኒክና ሙያ አካባቢ በተቀመጠው የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በቁጥር ያልታወቀ ሙት እና ቁስለኛ በማድረግ ያለምንም መስዋትነት ቀጠናውን ለቀው ወጥተዋል።

______፯

በቢቸና ከተማ 04 ቀበሌ የባጃጅሹፊሮች በአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።

በቢቸና ከተማ የሚገኘው የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በፋኖ ምት ተስፋ በመቁረጥ ንፁሀን አማራዎች ላይ አፈሙዝ በማዞር ንፁሀንን በመግደል አረመኔዊ ተግባሩን እያሳየ ይገኛል።

የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1:15 3(ሶስት) የባጃጅ ሹፊሮች ላይ በመተኮስ በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል እና ከባድ ቁስለኛ በማድርግ የንፁሀን ባጃጆችን አቃጥሏል።
1ኛ. ወጣት ምናሉ መርከቡ ይባላል የትውልድ ቦታው ሸበል በረንታ ሶሃ ተፋሰስ ቀበሌ ልዩ ቦታ ደንሲት መረዛምባ ተወላጅ ሲሆን በቢቸና ከተማ ኪዳነምህረት ሰፈር ከተማ የባጃጅ ሹፊር እየሰራ የግል ህይወቱን እየመራ ይገኝ ነበር። በመሆኑም በቢቸና ከተማ ንፁሀን በመረሸን እና በመዝረፍ የሚታወቀው የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ከምሽቱ 1:15 ቢቸና ከተማ ዲዲሱ አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ከእነ ባጃጁ አቃጥለውታል።

2ኛ. ሞገስ አስቻለ ቢቸና ከተማ ተወላጅ ቢቸና የመጀመረያ ደረጃ ሆሲፒታል ህክምና እያገኘ መሆኑ ተረጋግጦል።

3ኛ. (ይወግ) ዳዱሽ የወግ የተባለ ወጣት በቢቸና ከተማ 02 ቀበሌ አቡየ ሰፈር ተወላጅ ከጓዶቹ ጋር የባጃጅ ስራቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው እየሄዱ በአለበት ሰዓት የአገዛዙ ሰራዊት ዲዲሱ ሰፈር አልመው በተኮሱት ተኩስ ቢቸና የመጀመረያ ደረጃ ሆሲፒታል የገባ ቢሆንም ዶክተሮቹ ከባድ የአጥንት መሰበር ጉዳት እንዳለበት በማሳወቅ ከአቅማቸው ውጭ መሆኑን በማሳወቅ ደ/ማርቆስ ከተማ እሪፈር ተብሎ መሄዱ ተረጋግጦል። ወጣት ደድሸው በቢቸና ከተማ በሚደርጉ ስብሰባዎች በቢቸና ከተማ እየተፈፀሙ የነበሩ ግፎችን ይናገር እንደነበር በዚህም አገዛዙ በመከታተል እርምጃ እንተወደበት ተረጋግጦል።

4ኛ.በባጃጁ ላይ አብሮ ይጎዝ የነበር ንፁሀን ቁስለኛ መሆኑ ተረጋግጦል።

5ኛ.ወጣት ውዱ ይበልጣል እነማይ ወረዳ ቅድስጌ ቀበሌ ተወላጅ የባጃጅ ሹፊር ሲሆን ሰውነቱን በዱላ፣በአፈሙዝ በመደብደብ እና በመቀጥቀጥ በሰውነቱ ላይ አካላዊ ጉዳት በማድርስ ታስሮ ይገኛል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስአስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
፩ኛ ኮር
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
ታሕሣሥ 16/2018ዓ.ም

✔️ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች በጋራ መቀመጫውን ግንዳ ጠመም ከተማ አድርጎ የነበረው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሻውን ግንዳ ጠመም በማድረግ ወደ ማሕደረ ማርያም ከተማ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ሠዓት የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር መተሬ ወንዝ በወሰደው የደፈጣ መብረቃዊ ምት ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል። ከቀኑ 9:00 በደፈጣ የጀመረው ውጊያ አድማሱን አሥፍቶ ወደ መደበኛ ውጊያ ተቀይሯል። በዚህ ውጊያ የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦርን አግዘዋል። በዚህ ውጊያ ጠላት ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊ፣ አካላዊና ሞራላዊ ኪሳራ ደርሶበታል።
ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎችም፦ ጨባ መንደር፣ ናዳ፣ ዕማ ወተት ጊዎርጊሥ፣ ዳዋ መድኃኒዓለም፣ ክሬቸር፣ ማሕደረ ማርያም፣ መተሬና ሌሎች ቦታዎች ናቸው።

በዚህ ውጊያ የአራዊት ሠራዊቱ ዕቅድ ከሽፎበታል።


ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን👊
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
ፋኖ አረጋ አንሙት
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ትግላችን እስከ ቀራኒዮ ነው!! አርበኛ ሸጋ
የልጅ እያሱ ኮር አሃዶች በጥምረት አምባሰል ላይ በበርካታ ግንባሮች ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::

ልጅ እያሱ ኮር በሁሉም የአምባሰል አካባቢዎች በበርካታ ግንባር የብልፅግናዉ አራዊት ሰራዊት የፋኖን ይዞታዎች እቆጣጠራለሁ በሚል ቅዥት የማጥቃት እንቅስቃሴ እያደረገ ያለ ሲሆን በልጅ እያሱ ኮር ስር የሚገኙት ክፍለ ጦሮች ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ አድርገው በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ወደመጣበት መልሰው ድል አስመዝግበዋል::

ምኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክ/ጦር ከጊሸን ወደ ደልባ እና ጅጎዶ ለመቀሳቀስና ለመቆጣጠር አስቦ የማጥቃት ውጊያ ቢከፍትም በመከላከል ብሎም መልሶ ማጥቃት በማድረግ ድባቅ መተዉ ወደ መጣበት እንድመለስ አድርገዉታል።

በሌላኛው ግንባር መነሻዉን ከውጫሌ ከተማና ከማርየ ያደረገ ጠላት ያለ ያለለ ሃይሉን ተጠቅሞ ወደ ድብል በምድር በመካናይዝድ ታንክና መድፍ ታግዞ በሰማይ በአየር ሃይል ድሮን ታግዞ ማጥቃት ቢያደርግም በ24ኛ ክፍለ ጦር ድብል ላይ እየተመታ ይገኛል::

እንድሁም በትናትናዉ ዕለት ማለትም ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም የልጅ እያሱ ኮር የኮር ቃኝ በወርጊሳ ከተማ ደፈጣ በመጣል ከመርሳ ወደ ዉጫሌ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱን እያጓጓዘ ባለበት በደፈጣ ዉጊያ የአገዛዙን ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል አስመዝግበዋል::

መዳረሻዉ ድልና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበር ክንዳችን!
አፋብኃ ምኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር
ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
የድል ዜና!

የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በዛሬው ዕለትም በጠላት ላይ ታላቅ ድልን ተጎናጸፈ።

የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በዛሬው ዕለትም በጠላት ላይ  ታላቅ ድልን ተጎናጽፏል።

ዘራፊና ጨፍጫፊ የሆነው የብልጽግና ወራሪ ሠራዊት ከሞት የተረፈ ግብስብስ ሠራዊቱን በመያዝ ወደ ማርዘነብ ታዳጊ ከተማ ባቀናበት ጀግኖቹ የ14ኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት ማለትም የአንበሳ ደቦሎቹ የቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎች፣ ነበልባሎቹ የክፍለ ጦሩ ኮማንዶዎችና የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር አባላት በሌሊት በመግባት ጠላትን በእሳት ሰይፋቸው ሲቀስፉት አርፍደዋል።

በጠላት ዙ-23 የታገዘው ውጊያ በጀግኖቹ የፋኖ ሠራዊት አባላት የጨበጣ ተኩስ የበላይነት የታየበት ሲሆን በጠላት ላይ በርካታ ኪሳራን አድርሷል።

እንደ አበደ ውሻ እዚህም እዚያም እየተክለፈለፈ፤ ያገኘው ሁሉ የሚገርፈው የታሪካውያን ጠላቶቻችን ቀኝ እጅ የሆነው የብልጽግና ወራሪ ሠራዊት የጀግኖቹን ምድር እንደዋዛ የሚረግጣት አልሆነም፤ ስም አጠራሩ የጠላትን ልቡና በሚያርበደብደውና ብልት ለይቶ በሚመታው ጀግና ሠራዊታችን የእሳት በትር እየተገረፈ ምድሪቷ ገሃነም ሆናበት እንደ እሳት እራት እርር ኩምትር እያለ ቀረ እንጅ።

በሌሊት በተጀመረው ውጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል የተቀጠቀጠ ሲሆን ጠላት አስከሬኑንና ቁስለኛውን ሲጎትት ውሏል።

በውጊያውም
➠ አንድ አይሱዙ  አስከሬን ተነስቷል፣
➠ 03 አምቡላንስና 03 ፓትሮል ቁስለኛ የተነሳ ሲሆን ከዚህም መካከል 03 አምቡላንስ ቁስለኛ ሆስፒታል ገብቷል፤ ሶስት ፓትሮል ቁስለኛ ደግሞ በራሱ (በጠላት) ካምፕ ለመታከም ገብቷል።

ድል ለአማራ ፋኖ!
ክብር ለሰማዕታቱ!

@ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት!​
🙏1
ኢሕአፓ የአማራ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቀ::

በማንነታቸው ብቻ በግፍ እስር ላይ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች በአስቸኳይ እንደፈቱ ኢሕአፓ ጠይቋል::

የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ሚስጥረሥላሴ ታምራት እና የኢሕአፓ ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ይስሀቅ ወልዳይ በዛሬው ዕለት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እና የማንነት እስረኞችን ጎብኝተዋል።

በዚህም ለአመታት በግፍ እስር ላይ የሚገኙትን ዮሀንስ ቧያለው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ክርስቲያን ታደለ፣ ሲሳይ አውግቼው(ረ/ፕ)፣ ቴዎድሮስ ኃይለማርያም (ዶ/ር)፣ ወንድወሰን አሰፋ(ዶ/ር)፣ ጫኔ ከበደ (ዶ/ር)እና ካሳ ተሻገርን (ዶ/ር) ጠይቀዋል።

እነዚህ በስም የተጠቀሱትም ሆነ ስማቸው ያልተገለጹ የፖለቲካ፣ የማንነት እና የህሊና እስረኞች ለሀገር እና ለወገን እየከፈሉ ያለው ዋጋ እጅግ ከባድ ነው።

ኢሕአፓ ለፖለቲካ እና ለማንነት እስረኞቹ ያለውን ጽኑ አጋርነት እየገለጸ መንግስት በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታቸውም ያሳስባል።

የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችና ዓለም ዓቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብም የግፍ እስር እንዲቆም መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ዋጋ እየከፈሉለት ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከእነርሱም ሆነ ከቤተሰባቸው ጎን በመቆም ውግንናውን በተግባር ሊያሳያቸው ይገባል ስንል ጥሪ እናቀርባለን።

Via - ኢሕአፓ
👍1