YANGO PRO ETHIOPIA
መኪናዎን ለYango አጋሮች በማከራየት በወር እስከ 60000 ብር ያግኙ:: ከእርሶ የሚጠበቀው መኪናዎን ለኛ ማከራየት ነው እርሶም በየወሩ ቋሚ መግኘት ይጀምራሉ:: የገቢ አይነት ፡ 1. ለነዳጅ መኪና እስከ 50000 ብር 2. ኤሌክትሪክ መኪና እስከ 60000 ብር መስፈርቶቹም ፡ 1. መኪናዎ Code 3 ወይም Code 1 ከሆነ እና 2. ሙሉ ኢንሹራንስ ሊኖረው ይገባል ከላይ የተዘረዘረውን…
የሁለት ወረዳ አመራሮች ላይ ጥቃት ተፈፀመ! በጥቃቱ አጃቢዎቻቸው ሲገደሉ አመራሮች ክፉኛ ቆስለዋል::
በትናንት በስቲያው የገነቴ ከተማ አቅራቢያ የደፈጣ ጥቃት የብልጽግና ቁልፍ አመራሮች መመታታቸው ዛሬ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጤና ተቋም ከተገኘ ምንጭ ማረጋገጥ ተችሏል::
ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ወደ ወግዲ እና መካነሰላም አቅጣጫ ሲጓዙ በነበሩ የወረዳ አመራሮች ላይ ከትናንት በስቲያ ማለትም ታህሳስ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ በርካታ ጠላት ተመቷል:: የቦረና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገበያው በቀለ ጭንቅላቱ ላይ ክፉኛ መቁሰሉ የታወቀ ሲሆን የቦረና ወረዳ ሰላም እና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው ስዩም ጭምር ወገቡ ላይ ከባድ ጉዳት እንዳስተናገደ ተረጋግጧል:: የወረዳው ብልጽግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱሮህማን ደረሰ ደግሞ የግለሰብ ቤት ውስጥ ገብቶ ተደብቆ ሊተርፍ ችሏል::
ከዚህ በተጨማሪ የወግድ ወረዳ የብልጽግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሀመድ ግዛውም መቁሰሉ ታውቋል ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ይመር ሁሴን ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ገልጿል:: በኮሎኔል ጠጁ ሙላቴ የሚመራው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ተኛ ክፍለ ጦር እና አድማ ብተና ከሰላም አስከባሪዎች ጋር በመሆን የእጀባ ስራ እሰራለሁ ብሎ ዙሪያውን ቢያንዣብብም እንኳን የወረዳ አመራሮችን ሊያተርፍ ራሱ የጥይት እራት ሆኗል::
የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ (ሸዋንግዛው ካሣ) ሻለቃ ፋኖዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 33 የጠላት ኃይል ያቆሰሉ ሲሆን 13 ጠላት ደምስሰዋል:: በሰሞኑ ውጊያ ተተኳሽ እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ወደ ፋኖ ገቢ ሆኗል::
የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ አለልኝ ተሰማ የወረዳ አመራር መምታት ኮሎኔል ከመደምሰስ ጋር እኩል ነው ምክንያቱም ዋና አስገዳዮቻችን የወረዳ አመራሮች ናቸው ያለ ሲሆን በአመራሮች ላይ የምንወስደው እርምጃ ወደፊትም የሚቀጥል ይሆናል ብሏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

🙏1
ረሃብና ጥሙ ጊዜ አይሰጥም!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅና በእርዳታ አቅርቦት ችግር ከፍተኛ ረሃብ መከሰቱንና በመድኃኒት እጦት ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን መገንዘብ ችለናል። ችግሩ ከሰሞኑ በይፋ ይነገር እንጂ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በተመሳሳይ ኹኔታ በሰቆቃ የሚያሳልፉ በርካታ ወገኖቻችን መኖራቸው ይታወቃል። በተለይ በስደተኞች መጠለያ ያሉ፣ በድርቅ ምክንያት ማምረት ያልቻሉ፣ በአጠቃላይ ክልሉ እጅግ አውዳሚ ከኾነ ጦርነት ማግስት ውስጥ መገኘቱና መሰል ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች ችግሮች መፈጠራቸው አይቀሬ በመኾኑ ቅድመ ጥንቃቄና ሰብዓዊ ቀውሶች ሲከሰቱ አፋጣኝ መድረሻ የመፍትሔ አማራጮች ማስቀመጥና ከቁጥጥር ውጭ ከመኾናቸው በፊት መድረስ ይገባ ነበር።
አኹን ላይ በተለይ ሕፃፅ በሚባለው መጠለያ ጣቢያ ያሉ ዜጎች በረሃብና መድኃኒት እጦት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው በመኾኑ መላው ኢትዮጵያውያን ተረባርበው የዕለት ጉርሳቸውንና በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን ኹኔታ መፍጠር የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ኾኖ አግኝተነዋል።
በትግራይ ያለውን እጅግ የባሰበትና ጊዜ የማይሰጠውን ኹኔታ አነሳን እንጂ ችግሩ በአማራ ክልል ባሉ እንደ ደብረ ብርሃን፣ ጃራ፣... መጠለያ ያሉ ወገኖቻችን በመኖርና በመሞት መሐል ኾነው ቀናቸውን እንደሚገፉ ይታወቃል።
ስለኾነም፣
1. በውጭም በውስጥም ያሉ ኢትዮጵያውያን በሚቻለው አቅም ኹሉ ተረባርቦ በረሃብና መድኃኒት እጦት የሚሰቃዩ ወገኖቻችንን እንዲታደጋቸው፣ በዘላቂነትም እንዲያቋቁማቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን።
2. ዓለምአቀፍና ረጂ ተቋማት ለእነዚኽ በከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ ላሉ ዜጎች አፋጣኝ እርዳታና ዘላቂ መቋቋሚያ ፕሮጀክቶችን እንዲተገብሩ ተማጽኗችንን እናቀርባለን።
3. የፌዴራል መንግሥትና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እነዚኽን ወገኖች የፖለቲካ ቁማር መያዣ ከማድረግ እንዲቆጠቡ፣ እርዳታዎችን በቀናነት እንዲያሳልጡ እንዲኹም ወደዳግም ግጭት ከሚገፋ አባባሽ ምክንያቶች እንዲቆጠቡ በአደራ ጭምር እናሳስባለን።
በመጨረሻም እናት ፓርቲ ለእነዚኽ በሰቆቃ ላሉ ወግኖቻችን ለመድረስ በሚደረገው ርብርብ ከዚኽ ቀደም ስናደርግ እንደቆየነው የድርሻችንን እንደምንወጣ ለማሳወቅ እንወዳለን።
እናት ፓርቲ
ታኅሣስ 15/2018 ዓ/ም

❤1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ አበጀ ጥበቡ ብርጌድ ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ድቾ ቀበሌ ሻሽበር ከተማ ላይ ታላቅ ጀብዱ ፈፀመ።
የበረሀዋ ፈርጥ አፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ አበጀ ጥበቡ ብርጌድ በትናንትናው እለት ማለትም ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም ከንጋት 12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7:00 ሰዓት ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ገዳ ኮማንዶ፣ ኮሬ ነጌኛ፣ ጋቻና ሲርና፣ ሚሊሻ ና ፖሊስ ጋር ባደረገችው ተጋድሎ ታላቅ ጀብድ መፈፀም ችላለች።
በተጋድሎውም 66 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ቁጥሩ ለመቁጠር የሚያዳግት ቁስለኛ በማድረግ ሶስት ምሽጎችን በማስለቀቅ ተራራ ላይ ሰቅላ ቁም ስቅሉን ስታሳየው ውላለች።
ሙሉለሙሉ ይደመስሱኛል በማለት ጭንቀት ውስጥ የገባው የሺመልስ ግብስብ ሃይል በተለያዩ አቅጣጫዎች ባደረገው የድረሱልኝ ጥሪ ከቱሉጋና፣ከጊዳ አያና ከወረዳው ማለት ነው ፣ ከጉትን እንድሁም ከኡኬ ና ከነቀምት ያለየለለ ኃይሉን አሟጦ ሲመጣ ወደኋላ ሲያፈገፍጉለት የፈሪ በትር ሆድ ይገትር እንድሉ የሁሌም ተግባሩ የሆነው የኦሮሙማው ስርዓት ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊቱ እንደደረሰ ቤት ማቃጠል፣ ንብረት ማውደም ና በመዝረፍ በርካታ ሰዎችን በማፈናቀል ግፍ ፈፅመዋል። አሁንም የነውር መገለጫው የሆነውን ተግባሩን እሰከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ቤት በማቃጠል ላይ ነው ።
የጠላት ምሽግ የተሰበረባቸው ቦታዎች
1) ስላሴ ሰፈር
2) ጎጃም ሰፈር
3) ቀበሌ
4) ረጋሳ ፎቅ ናቸው።
በትናንቱ ጦርነት ከ200 በላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ሲደመሰስ ቀሪውን መከላከያ ደርሶ ታድጎታል። ጦርነቱን ወለጋ ምድር ላይ የሚንቀሳቀሰው የወለጋ ፋኖ ቢዛሞ በዝቅተኛ መስዋትነት ከፍተኛ ድል አስመዝግበዋል።
ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የኦሮሚያ ልዩ ኮማንዶ(ገዳ ኮማንዶ) መከላከያ ደርሶ ከታደገው በኋላ ቤቶችን አቃጥሏል : አካባቢው ላይ አሁንም ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል ጎሳየ የተባለው የመከላከያ አዛዥ ወደ ቦታው ተጨማሪ ሀይል እንዲገባለት የበላይ አመራሮቹን እዬተማጸነ ሲገኝ የኦሮሚያ ልዩ ኮማንዶዎች አስክሬንና ቁስለኛ በአስር ጎማ በሲኖና በኦራል እዬተጫነ ወደ አንገር ጉትን ከተማ እዬተጋዘ ይገኛል።
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን
@የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ
አበጀ ጥበቡ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት ፋኖ ብርሌው ስብሀት

❤1🙏1
በስቦ ማስከዳት ወታደራዊ ስልት የአብይ እና የብርኃኑ ጁላ ጦር እየፈራረሰ ነው::
በደጋ ዳሞት ወረዳ ከ23ኛ ክፍለ ጦር በቀን 15/04/2018 ዓ.ም ሁለት መሰረታዊ ወታደር እያንዳንዳቸው ጥቁር ክላሽ በመያዝ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋ ዳሞት ሻለቃን ተቀላቅለዋል::
እነሱም
1ኛ) መሰረታዊ ወታደር አድነው እንየው ...1ኛ ሬጅመንት ሻምበል 3 ጥቁር ክላሽ እና 91ጥይት
2ኛ) መሰረታዊ ወታደር ንግሩ ደመቀ..... 1ኛ ሬጅመንት ሻምበል 3 ጥቁር ክላሽ እና 110 ጥይት በመያዝ ተቀላቀለዋል::
በተያያዘ ከጠዋቱ 1:00 አካባቢ ፈረስ ቤት ከተማ አናብስቶቹ የደጋ ዳሞት ሻለቃ ወደ ከተማ በመግባት በቴክኒክና ሙያ አካባቢ በተቀመጠው የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በቁጥር ያልታወቀ ሙት እና ቁስለኛ በማድረግ ያለምንም መስዋትነት ቀጠናውን ለቀው ወጥተዋል::
አዲስ ትውልድ : አዲስ ተስፋ : አዲስ አስተሳሰብ

👍1🙏1
ለከበባ የመጣው የጠላት ጦር በደፈጣ ተመታ‼️
መነሻውን ከደብረብርሃን ከተማ በማድረግ በከተማው ቅርብ ርቀት ላይ ባለው ባሶ ወረዳ ወደ ዋዩ ቀበሌ የወገንን ጦር ለመክበብ በሁለት አቅጣጫ ሌሊት የተንቀሳቀሰ ሲሆን መረጃው ቀድሞ የደረሰው የጣይቱ ክፍለጦር የሶስተኛ ሻለቃ ውስን ሀይል ደፈጣ በማድረግ ለከበባ የመጣውን ጠላት በመክበብ አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ወደመጣበት እንዲፈረጥጥ አድርገውታል።
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለጦር የሶስተኛ ሻለቃ አናብስቶች የመጣውን ጠላት ከ5 በላይ የሚሆን የብልፅግናን ሰራዊት በቦንብ አጋይተው ከ7 በላይ የሚሆንን የጠላት ሀይል ከባድ ቁስለኛ በማድረግ ለከበባ የመጣውን ጠላት ቀለበት ውስጥ አስገብተው ቀጥቅጠው ወደ መጣበት ጉድጓዱ መልሰውታል።
ክብርና ሞገሰሰ ለትግሉ ሰማዕታት!!!
ድል ለአማራ ፋኖ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
@ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት

ሻለቃ አብዬ ተፈራ
ብዙ ጀግኖችን ያፈራው ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ከሚተማመንባቸው መካከል ጀግና እሳት ተራምዶ ጉሮሮ የሚጨብጥ አያሌ ጀብዶችን የፈፀመው ርር ያለው የእሳት ወላፈን ሻለቃ አብዬ ተፈራ ልቡን አምኖ የመነነው ታማኝ የአማራ ልጅ ክበርልን!!
የነ ደርምስ ልጅ የጎንደሬ በጋሻው ክንድ ጎንደር ከተማ፣ወገራ፣ደንቢያ፣በለሳ፣ኪንፋዝ፣አርማጭሆ፣ወልቃይት ጠገዴ፣ደጎማ ማክሰኝት፣አይባና ስሁር እንዴት ውሎ አደረ?
ታማኝ፣ደፋር፣ቀና ህዝባዊ አገልጋይ ታጋያችን አብዬ ተፈራ በቀጠናው አንተና ጓዶችህ እየሰራችሁ ላላችሁት ስራ ታሪክ ሁሌም ይዘክራችኋል።
በተለይ ከጓዶቻችሁ ሻምበል ሙሉሰው፣ወርቁ ዘገየ፣ደመላሽ ስመኝ እና ገብርዬ ጌታሁን እና ሌሎች ጋር ተናባችሁ እንደተለመደው ታሪክ ስሩ።
የሰረገው የሞፈሪያት ካሚል የጎንደር ከተማ ኮሚቴ አናግሩት አነጋግሩት።
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

👍2❤1🙏1
ጀኔራል ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እና ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በጥምረት ከ105 በላይ የአገዛዙን ሰራዊት በመደምሰስና ከ80 በላይ በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፀፉ!
ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ጄኔራል ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እና ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በጥምረት ባደረጉት ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በጠላት ላይ የበላይነትን በመቀዳጀት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደው ከባድ ትንቅንቅ የጠላት ኃይል በአምስት አቅጣጫ ማለትም ከአስ ከተማ በደጋው ወደ ጭማው አቅጣጫ፣ከአስከተማ ቁልቋል ጊዮርጊስ አቅጣጫ፣ከብልባላ ላልኪው ኩራዝባይ አቅጣጫ፣ከይምርሐ አዲስ አለም ሽልም ድንጋይ አቅጣጫ እና ከዶቅሳ ወደ ወይሎ አቅጣጫ አስፍቶ የመጣውን የጠላት ኃይል ቀድሞ መረጃው የደረሳቸው የክፍለ ጦሮቹ ወታደራዊ መረጃ ክፍሎች ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ቀድሞ በማስያዝ አዲስ አለም ፋጭላ ተራራ የሚገኙ አራት ምሽጎችን በመስበር ጠላት በመጣበት ሁሉም አቅጣጫ የሽንፈት ካባ ተከናንቧል።
ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅና ተጋድሎ ከ105 በላይ የብርሐኑ ጁላ አገር አፍራሽ አራዊት ሰራዊት ሲደመሰስ ከ80 በላይ ቁስለኛውን ይዞ ወደ ላልኪው ከተማ ፈርጥጧል።
በዚህም የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና አራዊት ሰራዊት የአማራ ህዝብ ላይ የግፍ እና የበቀል አፈሙዙን ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎች ላይ በማዞር ዲዝ ባዕለ እግዚአብሔር ላይ ሦስት የንፁሃንን ቤት ሲያቃጥል ኩራዝባይ ላይ አምስት የአርሶ አደሮችን የእህል ክምር በሞርተር ቅምቡላ አቃጥሏል። በዚህ ግፍ ያልረካው የአገዛዙ ምስለኔ ዘውማርያም ቀበሌ ሲገባ አንድ የአምስት ልጆች አባትን እና አንዲት የሁለት ልጆች እናትን በክላሽ ረሽኗል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
@የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

❤2🙏1