ቆቦ ከተማ መሬት ወረራ ላይ የተሰማሩት የብልፅግና ካድሬዎች ዘረፋቸው በተጨባጭ ማስረጃ ተጋለጠ!
ምኒልክ ዕዝ ባለፉት ጊዜያቶች በመመሪያ የተደገፈ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥበት የኖረውና አገዛዙ በሰፊው ተሰማርቶበት ያለው የመሬት ወረራና ዘረፋ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ የህዝብ ሃብት የሆነው ሁለገብ አዳራሽ የፋኖን መመሪያ በመጣስ አቶ ደጀኔ መንገሻ የተባለ ግለሰብ አረብ አገር ለሚኖር ወንድሙ 100000000 (አንድ መቶ ሚሊየን) ብር እንደገዛው ለማወቅና ለማረጋገጥ ችለናል::
አዳራሹ የተሸጠበት የገንዘብ መጠን ከፍ ያለ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች የገለፁ ቢሆንም ይፋ ከሆነው ከዚህ 100000000 (አንድ መቶ ሚሊየን) ብር ገንዘብ ውስጥ 80000000 (ሰማኒያ ሚሊየን) ብሩን ገቢዎችና ሌሎች ቢሮዎች የሚያውቁት ሲሆን 20000000 (ሃያ ሚሊየን) ብሩ በየደረጃው ላሉ የብልፅግና ካድሬዎችና ለደላላ የተሰጠ ገንዘብ ነው:: መጠኑ ያልተገለፀ ገንዘብም በየደረጃው ላሉ የመከላከያ አመራሮች እንደተሰጠ ለማወቅ ችለናል::
ቆቦ ከተማን ጨምሮ በራያ ቆቦ ህዝብ ሃብት እንደተገነባና በደርግ ዘመን ውድቀት ተጀምሮ በኢህአዴግ ዘመን መባቻ 1984 ዓ.ም እንደተጠናቀቀና አገልግሎት እንደጀመረ የሚነገረው ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ ዛሬ ላይ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ "የአማራን ህዝብ በአማራ ህዝብ ሃብት" በሚል መርህ መሰረት መሬት ሽጦ በሚገዛው ጦር መሳሪያና ተተኳሽ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ላለው ፋሽስታዊ አገዛዝ መጠቀሚያ ሆኗል::
በዚህም ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በፋኖ ትግል ተንኮታኩቶ የገንዘብ አቅሙም ሊጠገን በማይችል ሁኔታ የወደቀ ሲሆን ይህንን የገንዘብ ችግሩን ለመፍታት በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች ላይ የመሬት ወረራና ዘረፋ እየፈፀመ በህገወጥ ጨረታና ሌሎች መንገዶች እየሸጠ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም የህዝብ ሃብት የሆነውን ቆቦ ሁለገብ አዳራሽን ሸጠው ገንዘብ የተከፋፈሉና በሰውና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠባቸው የቆቦ ከተማ እና የሰሜን ወሎ ዞን አመራሮች የሚከተሉት ናቸው፦
1.አቶ ከድር ሙስጠፋ ---- የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ሃላፊ 1000000 (አንድ ሚሊየን) ብር
-ሻምበል እንዳየነው በተባለ ግለሰብ 1 ሚሊየን ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
2.አቶ ሃይለአብ ወንድሙ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ 6000000 (ስድስት ሚሊየን) ብር
-ንጉስ አያሌው ጌታሁን በተባለ ግለሰብ 2.5 ሚሊየን እና እስጢፋኖስ እምሩ ዘለቀ በተባለ ግለሰብ 2.5 ሚሊየን እና 1 ሚሊየን በድምሩ 3.5 ሚሊየን ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
3.አቶ ይርጋ ወዳጆ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ፅ/ቤት ሃላፊ 6200000 (ስድስት ሚሊየን ሁለት መቶ ሽ) ብር
-ሙሉ ታከለ ገ/ስላሴ በተባለች ግለሰብ 5.3 ሚሊየን ብር እና መቅደስ መለሰ ይመር በተባች ግለሰብ 9 መቶ ሽ ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኞች ከስር በማስረጃነት ተያይዘዋል::
4.ዶ/ር አዲሱ ወዳጆ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር መሬት አስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ 1000000 (አንድ ሚሊየን) ብር
-መሳይነሽ ደጀን ተገኘ በተባለች ግለሰብ 1 ሚሊየን ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
5.አቶ አበበ ይመር ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፅ/ቤት ሃላፊ 200000 (ሁለት መቶ ሽ) ብር
-ሁለት መቶ ሽ ብር በግል አካውንቱ በስሙ የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
6.አቶ ሙለታ መሃመድ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የመሬት ልማት ባንክ ቡድን መሪ 150000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሽ) ብር
-አንድ መቶ ሃምሳ ሽ ብር በግል አካውንቱ በስሙ የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
7.አቶ ሃይለማርያም አትክልት ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ፅ/ቤት ም/ሃላፊ 100000 (አንድ መቶ ሽ) ብር
-ደሳለ ፈንታው መንገሻ በተባለ ግለሰብ መቶ ሽ ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
8.ቦታውን ያሻሻጠው ደላላ ወይም ግለሰብ 5350000 (አምስት ሚሊየን ሶስት መቶ ሃምሳ ሽ) ብር
በአጠቃላይ ለፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ካድሬዎች 14650000 (አስራ አራት ሚሊየን ስድስት መቶ ሃምሳ ሽ) ብር የተሰጠ ሲሆን 5350000 (አምስት ሚሊየን ሶስት መቶ ሃምሳ ሽ) ብር የህዝብን ሃብት ደላላ ሆኖ ላሻሻጠው ግለሰብ የተሰጠ ገንዘብ ነው::
በመጨረሻም የአማራ ህዝብ ሆይ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ነውና ብሂሉ ግፈኞች ተመቸን ብለው በጉልበት ሃብትህን ተቀራምተው ታንክና መድፍ ጄትና ድሮን ታጥቀውበት ብሎም ለአራዊት ሰራዊታቸው ደመወዝ እየከፈሉበት መልሰው አንተው ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙበት እንደሆነ አለም ያወቀው ሐቅ ነውና በትግልህ ነፃነትህን በነፃነትህ ፍትህና ርትዕን ትጎናፀፍ ዘንድ ዛሬም መልክታችንን እናስተላልፋለን!
በመጨረሻም ግፈኞች መሬቱን ተሸክመውት የትም አይሄዱምና "የህዝብ ሃብት ጊዜውን ጠብቆ የህዝብ ነው!" የሚለው መመሪያችን እንደተጠበቀ መሆኑን እየገለፅን ህዝባችን ከግፈኞችና ይሄ ጊዜ የማያልፍና የማይነጋ ከመሰላቸው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰዎች ህገወጥ መሬት ባለመግዛት ራሳችሁን ከክስረት ብሎም ከጥፋትና ተጠያቂነት እንድትታደጉ ስንል ለማሳሰብ እንወዳለን!
ማስታወሻ፦ በሌሎች የቤተ-አማራ አካባቢዎችም ላይ ያሉ የመሬት ወረራና ዘረፋዎች በጥብቅ ክትትላችን ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ ሲሆን ማስረጃዎች እንደደረሱን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ይሆናል!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም

💔2
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት የተጋድሎ ውሎ
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር በተለያዩ ግንባሮች በዛሬው ዕለት ባደረገው ተጋድሎ 27 ክላሽ ማርኳል።
ከአምበር ከተማ በመነሳት ወደ ጃማ ከተማ በማቅናት ላይ በነበረ የጠላት ኃይል ላይ የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስና ደጃች ተድላ ጓሉ ሻለቃ በፈፀሙት የማጥቃት ውጊያ ጠላትን ከምድር ደባልቀው 27 ክላሽ ፣በርካታ ካዘና፣የደረት ትጥቅና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ቁሳቁስ ማርከዋል።
ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀትር 6:00 ስዓት በወሰደው ጠንካራ ውጊያ ጠላትን ያጋደሙት የ206ኛ ኮር አሃዶች 45 በላይ ጠላት የደመሰሱ ሲሆን ከ22 በላይ የጠላት ኃይል ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
የአረመኔው ሰራዊት፣አድማ ብተና እና ሚኒሻ በታጨደበት ውጊያ ጠላትን ቅስም በመስበር አስደናቂ ጀብድ የፈፀመው 34ኛ ክ/ጦር ተደጋጋሚ ድል ያስመዘገበ ጠንካራ ክ/ጦር ሲሆን በዚህ ስዓት 15 የጠላት ከባድ ቁስለኞች በጫካ ወድቀው እንደሚገኙ ታውቋል።
በተያያዘ ውጊያ 206ኛ ኮር የ14 ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ ከሻለቆች ጋር በመቀናጀት ከደብረ ኤልያስ ተነስቶ ወደ ማርዘነብ ከተማ ሲንቀሳቀስ በፈፀሙት ፈጣን ማጥቃት ጠላትላይ ከፍተኛ ኪሳራ በማድረስ እንዲመለስ ማድረግ ተችሏል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

🙏2
YANGO PRO ETHIOPIA
መኪናዎን ለYango አጋሮች በማከራየት በወር እስከ 60000 ብር ያግኙ:: ከእርሶ የሚጠበቀው መኪናዎን ለኛ ማከራየት ነው እርሶም በየወሩ ቋሚ መግኘት ይጀምራሉ:: የገቢ አይነት ፡ 1. ለነዳጅ መኪና እስከ 50000 ብር 2. ኤሌክትሪክ መኪና እስከ 60000 ብር መስፈርቶቹም ፡ 1. መኪናዎ Code 3 ወይም Code 1 ከሆነ እና 2. ሙሉ ኢንሹራንስ ሊኖረው ይገባል ከላይ የተዘረዘረውን…
የሁለት ወረዳ አመራሮች ላይ ጥቃት ተፈፀመ! በጥቃቱ አጃቢዎቻቸው ሲገደሉ አመራሮች ክፉኛ ቆስለዋል::
በትናንት በስቲያው የገነቴ ከተማ አቅራቢያ የደፈጣ ጥቃት የብልጽግና ቁልፍ አመራሮች መመታታቸው ዛሬ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጤና ተቋም ከተገኘ ምንጭ ማረጋገጥ ተችሏል::
ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ወደ ወግዲ እና መካነሰላም አቅጣጫ ሲጓዙ በነበሩ የወረዳ አመራሮች ላይ ከትናንት በስቲያ ማለትም ታህሳስ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ በርካታ ጠላት ተመቷል:: የቦረና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገበያው በቀለ ጭንቅላቱ ላይ ክፉኛ መቁሰሉ የታወቀ ሲሆን የቦረና ወረዳ ሰላም እና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው ስዩም ጭምር ወገቡ ላይ ከባድ ጉዳት እንዳስተናገደ ተረጋግጧል:: የወረዳው ብልጽግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱሮህማን ደረሰ ደግሞ የግለሰብ ቤት ውስጥ ገብቶ ተደብቆ ሊተርፍ ችሏል::
ከዚህ በተጨማሪ የወግድ ወረዳ የብልጽግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሀመድ ግዛውም መቁሰሉ ታውቋል ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ይመር ሁሴን ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ገልጿል:: በኮሎኔል ጠጁ ሙላቴ የሚመራው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ተኛ ክፍለ ጦር እና አድማ ብተና ከሰላም አስከባሪዎች ጋር በመሆን የእጀባ ስራ እሰራለሁ ብሎ ዙሪያውን ቢያንዣብብም እንኳን የወረዳ አመራሮችን ሊያተርፍ ራሱ የጥይት እራት ሆኗል::
የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ (ሸዋንግዛው ካሣ) ሻለቃ ፋኖዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 33 የጠላት ኃይል ያቆሰሉ ሲሆን 13 ጠላት ደምስሰዋል:: በሰሞኑ ውጊያ ተተኳሽ እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ወደ ፋኖ ገቢ ሆኗል::
የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ አለልኝ ተሰማ የወረዳ አመራር መምታት ኮሎኔል ከመደምሰስ ጋር እኩል ነው ምክንያቱም ዋና አስገዳዮቻችን የወረዳ አመራሮች ናቸው ያለ ሲሆን በአመራሮች ላይ የምንወስደው እርምጃ ወደፊትም የሚቀጥል ይሆናል ብሏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

🙏1
ረሃብና ጥሙ ጊዜ አይሰጥም!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅና በእርዳታ አቅርቦት ችግር ከፍተኛ ረሃብ መከሰቱንና በመድኃኒት እጦት ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን መገንዘብ ችለናል። ችግሩ ከሰሞኑ በይፋ ይነገር እንጂ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በተመሳሳይ ኹኔታ በሰቆቃ የሚያሳልፉ በርካታ ወገኖቻችን መኖራቸው ይታወቃል። በተለይ በስደተኞች መጠለያ ያሉ፣ በድርቅ ምክንያት ማምረት ያልቻሉ፣ በአጠቃላይ ክልሉ እጅግ አውዳሚ ከኾነ ጦርነት ማግስት ውስጥ መገኘቱና መሰል ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች ችግሮች መፈጠራቸው አይቀሬ በመኾኑ ቅድመ ጥንቃቄና ሰብዓዊ ቀውሶች ሲከሰቱ አፋጣኝ መድረሻ የመፍትሔ አማራጮች ማስቀመጥና ከቁጥጥር ውጭ ከመኾናቸው በፊት መድረስ ይገባ ነበር።
አኹን ላይ በተለይ ሕፃፅ በሚባለው መጠለያ ጣቢያ ያሉ ዜጎች በረሃብና መድኃኒት እጦት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው በመኾኑ መላው ኢትዮጵያውያን ተረባርበው የዕለት ጉርሳቸውንና በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን ኹኔታ መፍጠር የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ኾኖ አግኝተነዋል።
በትግራይ ያለውን እጅግ የባሰበትና ጊዜ የማይሰጠውን ኹኔታ አነሳን እንጂ ችግሩ በአማራ ክልል ባሉ እንደ ደብረ ብርሃን፣ ጃራ፣... መጠለያ ያሉ ወገኖቻችን በመኖርና በመሞት መሐል ኾነው ቀናቸውን እንደሚገፉ ይታወቃል።
ስለኾነም፣
1. በውጭም በውስጥም ያሉ ኢትዮጵያውያን በሚቻለው አቅም ኹሉ ተረባርቦ በረሃብና መድኃኒት እጦት የሚሰቃዩ ወገኖቻችንን እንዲታደጋቸው፣ በዘላቂነትም እንዲያቋቁማቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን።
2. ዓለምአቀፍና ረጂ ተቋማት ለእነዚኽ በከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ ላሉ ዜጎች አፋጣኝ እርዳታና ዘላቂ መቋቋሚያ ፕሮጀክቶችን እንዲተገብሩ ተማጽኗችንን እናቀርባለን።
3. የፌዴራል መንግሥትና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እነዚኽን ወገኖች የፖለቲካ ቁማር መያዣ ከማድረግ እንዲቆጠቡ፣ እርዳታዎችን በቀናነት እንዲያሳልጡ እንዲኹም ወደዳግም ግጭት ከሚገፋ አባባሽ ምክንያቶች እንዲቆጠቡ በአደራ ጭምር እናሳስባለን።
በመጨረሻም እናት ፓርቲ ለእነዚኽ በሰቆቃ ላሉ ወግኖቻችን ለመድረስ በሚደረገው ርብርብ ከዚኽ ቀደም ስናደርግ እንደቆየነው የድርሻችንን እንደምንወጣ ለማሳወቅ እንወዳለን።
እናት ፓርቲ
ታኅሣስ 15/2018 ዓ/ም

❤1