ምኒልክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ወረዳ እና ኩታበር ወረዳ ባደረጉት ተጋድሎ አራት ቀበሌዎችን ተቆጣጠሩ::
በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ዛሬ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ በደቡብ ወሎ ደሴ ዙርያ ወረዳና ኩታበር ወረዳ ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል::
በተጋድሎዉም በጠላት ይዞታ የነበሩ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል። ነጻ የወጡት ከተሞች አያታ፣ፋላ ፣ጽድ ገበያ፣ አጥንት መስበርያ የተባሉ ከተሞች ሲሆኑ በተጋድሎዉም የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ መከላከያ፣አድማ ብተና እና ሚሊሻ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ኪሳራ አስተናግደው ሙትና ቁስለኛቸውን ይዘው ወደ ደሴ ፈርጥጠዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም

❤1🙏1
ለህዝብ ደህንነት ሲባል መንገድ ዝግ መሆኑን ስለማሳወቅ‼️
═════════❁✿ ❁══════============
አፋብሓ ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድራቸው ቀጨናዎች የህዝብን ደንነት ለመጠበቅ ሲባል መንገድ የተዘጋ ስለመሆኑ ማሳወቅ፣
በሆዱ ተገዝቶ የአብይ አህመድ አሊን ወንበር ለመጠበቅ የሚዝረከረከው የጠላት ሀይል ፋኖን ዘራፊ ነው ለማስባል ፋኖ መሣይ ብልጽግናዎችን በማደራጀት ሹፌሮቻችንን እና ህዝባችንን እያገላታ መሆኑን ደርሰንበታል።
በመሆኑም ህዝባችንን እና ሹፌሮቻችንን ከነዚህ ወንበዴዎች ዘረፋና ግድያ መከላከል ያመች ዘንድ ከነገ 13/04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መንገዶች ማለትም፦
1.ከባህር ዳር ጭንባ ቁንዝላ ደለጎ
2.ከዱርቤቴ ዝህብስት ወገዳ
3.ከዱርቤቴ ሀሙሲት ማማላ
4.ከዱርቤቴ _ቀደምት ላሊበላ ልሁዲ መንገዶች
ዝግ እንደሆኑ ማሳወቅ እንወዳለን ።ህዝባችንም በነዚህ ዘራፊ አካላት ላይ እርምጃ ወስደን ፣በማስተካከል በፍጥነት ክፍት ስለምናደርግ፣ እንደወትሮው ሁሉ በትግስት እንድትጠብቁን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።
ማሳስቢያ፦ ይህንን መልክት ጥሶ እገዳ በተጣለባቸው መንገዶች ሲንቀሳቀስ ለሚደርስበት ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱን እራሱ ባለቤቱ የሚወስድ መሆኑን በድጋሜ እናሳውቃለን።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️
የፋብሀ ምዕ/አ/ቀ/ቴዎድሮስ-ዕዝ
የ105ኛ ኮር 55ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

❤1👍1🙏1
የአገዛዙ ኃይሎች በጎንደር ሻሁራ ከተማና አፀደማርያም አከባቢ በፈፀሙት ጥቃት ሁለት ታዳጊዎች ተገደሉ!
በእረኝነት ላይ የነበሩ የ10 ዓመት እና የ15 ዓመት ታዳጊዎች ናቸው በጥቃቱ የተገደሉት።
ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማና አፀደማርያም ቀበሌ ሰፍረው የሚገኙት የፀረ አማራው ብልፅግና አገዛዝ ወታደሮች ታህሳስ 11/2018 ዓ/ም በከፈቱት የዘፈቀደ የሞርተር እና የድሽቃ ተኩስ፡ በከብት እረኝነት ላይ የነበሩ ሁለት ታዳጊዎች መገደላቸውን ከአከባቢው ነዋሪዎች ለማረጋገጥ ተችሏል።
ንፁኋንን በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ቆራርጦ መግደል፣ የዘፈቀደ ተኩስ በመክፈት ህፃናትና ነፍሰጡር እናቶችን ሳይቀር መረሸን፣ ታዳጊ ሴቶችን መድፈር፣ ሐይማኖታዊ ስፍራዎችን ማርከስ ልዩ መገለጫቸው የሆነው የአገዛዙ ወታደሮች፡ በፈፀሙት የሞርተርና የድሽቃ ጥቃት፡ ምስጋናው አቤ የተባለ በከብት እረኝነት ላይ የነበረ የ15 ዓመት ታዳጊ እና ሌላ አንድ የ10 ዓመት ታዳጊ ተገድለዋል ነው ያሉት መረጃውን ያደረሱን የአከባቢው ነዋሪዎች።
በተጨማሪም በዚኸው የከባድ መሣሪያ ጥቃት የንፁኋን መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ነው የተነገረው።
የአገዛዙ ኃይሎች በቀጠናው ከፋኖ ጋር ውጊያ አድርገው ሽንፈት በገጠማቸው ቁጥር ሲሸሹ በመንገድ ላይ የሚያገኟቸው ንፁኋኖች ላይ ከሚፈፅሙት ግድያ በተጨማሪ፡ የዘፈቀደ የከባድ መሣሪያ ድብደባ በማካሄድ በእረኝነት፣ ሰብል በመሰብሰብና በመኖሪያ ቤታቸው የነበሩ ንፁኋኖችን ገድለዋል፡ በርካታ ሀብት ንብረትም አውድመዋል።
@መረብ ሚዲያ

❤2🙏1
በአርበኛ ሸጋ ጌታቸዉ የሚመራ የዕዝ አመራር ለክፍለ ጦር አመራሮች ለብርጌድ አመራሮች ለሻለቃ አመራሮች የማጥራት ስልጠና ሲሰጥ የቆየዉ በቀን12/4/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ
ሰበር የድል ዜና
64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ በደፈጣ ጥቃት ወረጎ እና አካባቢው ቀበሌ ታሪክ ሰርቷል።
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ማህበረሰቡን በመልሶ ማደራጀት የሰለጠነ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት እና በመገንባት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ እያደራጀ ባለው ግዙፍ ኃይል ስጋት ውስጥ የገባው የአገዛዙ ተቅበዝባዥ ኃይል በቀጠናው የሚገኘው የፋኖ አባላትን ለማጥቃት በየዕዱኃ ከተማ መሽጎ ከሚገኘውን የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ጨለማን ተገን በማድረግ በቁጥቋጥ ቀበሌ የፋኖ አባላትን ለማጥቃት ምክሮ ሳይሳካለት ቀርቷል።
በቁጥቋጥ ቀበሌ የገባውን የአገዛዙ አረመኔ ሰራዊትን ድጋፉ ለማድረግ ከየዕዱውኃ ከተማ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ተጨማሪ ኃይል በመያዝ በጉዞ ላይ የነበሩ በአንድ ፖትሮል እና በአንድ ላንድ ክሎዘር አመራር እና አባላት የጫነ ተሽከረካሪ በጉዞ ላይ እንዳሉ #በወረጓ እና አካባቢው ቀበሌ ልዩ ቦታው #ደረቅ_ወንዝ በተባለ ቦታ 64ኛ ክፍለጦር 5ኛ ሬጅመንት በወሰደው የደፈጣ ጥቃት በፖትሮል ላይ የነበሩ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አመራር እና አባላት ሙት እና ቁስለኛ አድርጓል።
በሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ ወደ ቁጥቋጥ ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ በተሰራው የደፈጣ ጥቃት ከተደመሰሱት የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላት ውስጥ:-
ሻምበል ሰለሞን የሻለቃ (ሬጅመንት )አዛዡ እና አንድ ጋንታ መሪ ፓትሮል ላይ እንዳሉ ተመተው የሞቱ : 1 ሚሊሻ እና 4 የመከላከያ አባላት ከባድ ቁስለኛ ሆነው ሆስፒታል የገቡ
ሆሲፒታል ከገቡት አምስቱ ቁስለኞች ውስጥ ሚሊሻውን ጨምሮ 2ቱ የመከላከያ አባላት መሞታቸውን አረጋግጠናል። የቀሩትም የመትረፍ እድል እንደሌላቸው ከውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ተሰምቷል።
አንድ ፖትሮል እና አንድ ላንድ ክሎዘር ተሽከረካሪ በደፈጣ ጥቃቱ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
@ፋኖ ይበልጣል ጌቴ
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት

👍2🙏1
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ወታደሮች ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ልዩ ስሙ ለሚበር የተባለ ቦታ ላይ የስምንት አመት ህፃን ደፍረው ባሰቃቂ ሁኔታ ገደሉ::
በተጨማሪም አገዛዙ ቤተ-አማራ በብዙ አካባቢዎች የምነት ግጭት ለመፍጠርም እየሰራ ነው:: ሰራዊት አዝምቶ መማር ማስተማርንም እያወከ ይገኛል::
በአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው ፋሽስቱ ብልፅግና ወታደሮች በደቡብ ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ልዩ ስሙ ለሚበር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ እንዲት የስምንት ዓመት ህፃን ደፍረው ባሰቃቂ ሁኔታ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ይህንን ግፍ ለህዝብ ብታሰሙ እንገላችኋለን በማለትና በማስፈራራት ጉዳዩ ለሚዲያ እንዳይደርስ ታፍኖ መሰንበቱን ለማረጋገጥ ችለናል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም ህዳር ወር አካባቢ መካነ ሰላም ላይ እንዲት የቄስ ሚስት እና ነፍሰ ጡር እናትን ጨምሮ ሶስት ሴቶች በአገዛዙ ወታደሮች ተገደው በግፍ የደፈሩ መሆኑን በወቅቱ ይፋ ያደረግን መሆኑ ይታወቃል::
የፋሽስቱ ፀረ አማራው የአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት በተደጋጋሚ ከሚፈፀመው የአማራ ግፍና በደል አንዱ የአማራን ህዝብ ከትምህርት ከበታ ውጭ ማድረግ ሲሆን ሰሞኑን ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም በመካነ ሰላም ወረዳ 017 ቀበሌ ት/ቤት ከረፋዱ 4:00 ተማሪዎች እየተማሩ ባሉበት ሰዓት በርቀት በዲሸቃ ት/ቤቱን ሲደብድብ የዋለ ሲሆን ተማሪዎቹ እና መምህራንም ህይወታቸውን ለማትረፍ ተበትነዋል ትምህርት ቤቱንም አውድሟል::
ይህ ድርጊት ሲፈፀም በአካባቢው ምንም አይነት የፋኖ ሃይል ያልነበረ ሲሆን በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ ተማሪዎችን ያላከበረና ትኩረት ያልሰጠ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ የተለመደ ተግባር መሆኑን ለመረዳት ችለናል::
በሌላ በኩል ጀምበር የጠለቀችበት አገዛዙ በመካነ ሰላም ዙሪያ በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ አሁንም ፖለቲካውን ወደ ሀይማኖት ግጭትና እርስ በርስ መጠፋፋት ለመቀየር አበክሮ እየሰራ መሆኑንና ካድሬዎቹ በየ እምነት ተቋማቱ እየሄዱ ይህንን ፕሮፖጋንዳ ሲሰብኩ እንደሚውሉ አብረው የነበሩ እማኞች መረጃውን እያደረሱን ይገኛሉ::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም

❤1💔1
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት የተጋድሎ ውሎ
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
______፩
የበረሃው ቋያ 66ኛ ክ/ጦር ከጃሂማላ ቅርብ ርቀት ሰሌን ውሃ ላይ ድል ተቀዳጀ።
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ በቀን 13/04/2018 ዓ.ም በሰሩት አስደናቂ ኦፕሬሽን የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ሎሌዎችን ድባቅ በመምታት ተደጋጋሚ ጀብድ ፈፅመዋል።
የበሰበሰው አገዛዝ ሰራዊቱን በየጊዜዉ እየገበረ ስልጣኑን ለማራዘም እየተፍጨረጨረ ቢገኝም ከሽንፈት ግን አልዳነም። ይሁንና በዛሬዉ አዉደ ዉጊያ ጠላት ወደ ጃሂማላ ቀጠና ለሁለተኛ ጊዜ ለመግባት ሲሞክር ሰሌን ዉሃ ከተባ ቦታ ላይ በደረሰበት ከባድ ምት ከ34 በላይ ሰራዊቱ ተደምስሶበታል። እንዲሁም ከ20
በላይ ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
አንድ #ኦራል መኪና እስከ ጫነዉ ሬሽንና ተተኳሽ በዲሽቃ ተመትቶ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ዉጭ ማድረግ ተችሏል።
ሌላዉ ከጥቅም ዉጭ የሆነዉን ኦራል ለመዉሰድ ከጃዊ ወደ ጦርነት ወደ ተካሄደበት ቀጠና የመጣዉ ክሬን መኪና በነበልባሎቹ 1ኛ ሻለቃ ተቃጥሎ ከጥቅም ዉጭ ሆኗል።
የክሬኑ ሾፌርም ተማርኳል!!!
በክ/ጦሩ ወታደራዊ አስተዳደር አርበኛ ዳዊት አይችሌ እና የሻለቃ 1 ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ በላይ ይታየዉ የተመራዉ ኦፕሬሽን በድንቅ ድል ታጅቦ ዉሏል።
________፪
64ኛ ክፍለጦር በሸበል በረንታ ወረዳ በደፈጣ በርካታ
የጠላት ሀይልን ደመሰሰ።
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ማህበረሰቡን በመልሶ ማደራጀት የሰለጠነ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት እና በመገንባት በረካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ እያደራጀ ባለው ግዙፍ ኃይል ስጋት ውስጥ የገባው የአገዛዙ ተቅበዝባዥ ኃይል በቀጠናው የሚገኘው የፋኖ አባላትን ለማጥቃት በየዕዱኃ ከተማ መሽጎ ከሚገኘውን የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ጨለማን ተገን በማድረግ በቁጥቋጥ ቀበሌ የፋኖ አባላትን ለማጥቃት ምክሮ ሳይሳካለት ቀረቷል።
በቁጥቋጥ ቀበሌ የገባውን የአገዛዙ አረመኔ ሰራዊትን ድጋፉ ለማድረግ ከየዕዱውኃ ከተማ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ተጨማሪ ኃይል በመያዝ በጉዞ ላይ የነበሩ በአንድ ፖትሮል እና በአንድ ላንድ ክሎዘር አመራር እና አባላት የጫነ ተሽከረካሪ በጉዞ ላይ እንዳሉ በወረጓ እና አካባቢው ቀበሌ ልዩ ቦታው ደረቅ_ወንዝ በተባለ ቦታ 64ኛ_ክፍለ_ጦር_5ኛ_ሬጅመንት በወሰደው የደፈጣ ጥቃት በፖትሮል ላይ የነበሩ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አመራር እና አባላት ሙት እና ቁስለኛ አድርጓል።
በሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ ወደ ቁጥቋጥ ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ በተሰራው የደፈጣ ጥቃት ከተደመሰሱት የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላት ውስጥ:-
➤ሻምበል ሰለሞን የሻለቃ (ሬጅመንት )አዛዡ እና አንድ ጋንታ መሪ ፓትሮል ላይ እንዳሉ ተመተው የሞቱ
➤1ሚሊሻ እና 4 የመከላከያ አባላት ከባድ ቁስለኛ ሆነው ሆስፒታል ገብተዋል።
➤ሆሲፒታል ከገቡት አምስቱ ቁስለኞች ውስጥ ሚሊሻውን ጨምሮ 2ቱ መሞታቸውን አረጋግጠናል። የቀሩትም የመትረፍ እድል እንደሌላቸው ከውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ተሰምቷል።
➤አንድ ፖትሮል እና አንድ ላንድ ክሎዘር ተሽከረካሪ በደፈጣ ጥቃቱ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።
_____፫
ከንጋቱ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 የተደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ:-
============
በትናንትናው ዕለትም ታህሳስ 12/ 2018 ዓ/ም የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለጦር እና የማቻከል ወረዳ አባት አርበኞች ጥምር ሀይል ከአማኑኤል ከተማ በሁለት አቅጣጫ ወደ ደብረቀለሞ /ደጋ ቀጠና/ የተንቀሳቀሰውን ጡት ቆራጭና #ወራሪ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ የሆነ የማጥቃት ውጊያ በማድረግ አስከሬኑን ሳያነሳ ወደ መጣበት አማኑኤል ከተማ እንዲፈረጥጥ አድርገውታል።
በሌላ አውደ ውጊያ 99ኛ ክ/ጦር በላይ ዘለቀ ሻለቃ አማኑኤል ከተማ በመግባት በጠላት ላይ የስነልቦና ፣አካላዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ማድረስ የተቻለ ሲሆን በርካታ የአረመኔው ሰራዊት ተደም*ስሷል።
የተረፈው አታንበሳ/ወተበት ሚካኤል ቤተክርስቲያን ገብቶ ለማምለጥ ቢሞክርም የበላይ ዘለቀ ልጆች ተስበው በመጠጋት በቆፈረው ጉድጓድ ቀብረውታል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

❤2👍1🙏1
ታላቁ እና ታሪካዊው ድብር ጨጨሆ መድኃኔዓለም በመከላከያ ሰራዊት ተዘረፈ!
በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በላይ ጋይንት ወረዳ የፈለገ ፀሐይ በቅሎ አግት ጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዝግ ሙዳየ ምፅዋት በመከላከያ ሰራዊት ዘረፋ እንደተፈፀመባቸው ተሰምቷል።
ነፍሰጡር እናቶችንና ህፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል፣ የስምንትና የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ ልጆችን ሳይቀር ሴቶችን በደቦ መድፈር፣ አዝመራ ማውደም ልዩ መገለጫው የሆነው መከላከያ ሰራዊቱ ከደቡብ ጎንደር ዞን ካቢኔዎች ጋር በጋራ በመሆን በታላቁ እና በታሪካዊው ድብር ጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ፍተሻ በሚል ሰበብ፡ ተጓዥ መንገደኞች ለደብሩ የሚሰጡትን ምፅዋትን ጨምሮ በዝግ ሙዳይ ምፅዋት የተቀመጠን ገንዘብና ሌሎች የቤተክርስቲያኗን ሀብት መዝረፉን የአይን እማኞች ገልፀዋል።
ወታደሮቹ ከሙዳየ ምፅዋቱ በተጨማሪ የቤተክርስቲያኗ ታሪካዊ ቅርሶችንም ዘርፈው መውሰዳቸው ነው የታወቀው።
በ5ኛው ክፍለዘመን እንደተመሠረተች የሚነገርላት ቤተክርስቲያኗ ከሁለት ዓመታት በፊት አገዛዙ ከሕወሓት ጋር ባደረገው ጦርነት የመድፍ ጥቃት ተፈፅሞባት የነበረ ሲሆን፡ አሁን ደግሞ በመከላከያ ሰራዊቱ እና በዞኑ ካድሬዎች የተቀናጀ የዘረፋ ጥቃት ተፈፅሞባታል።
የቀድሞ ነገስታቶች በስጦታና በእጅ መንሻነት ለቤተክርስቲያናት የሰጡትን የወርቅና ሌሎች ውድ ስጦታዎችን ቤተክርስቲያኗ እስከ ዛሬ ጠብቃ ያቆየች ሲሆን፡ እነዚህ ውድ ስጦታዎች በአገዛዙ ወታደራዊ አዛዦች እየተመዘበሩ በአለም አቀፍ ገበያዎች ላይ መቅረባቸው ሲዘገብ መቆየቱ ይታወቃል።

💔1
ቆቦ ከተማ መሬት ወረራ ላይ የተሰማሩት የብልፅግና ካድሬዎች ዘረፋቸው በተጨባጭ ማስረጃ ተጋለጠ!
ምኒልክ ዕዝ ባለፉት ጊዜያቶች በመመሪያ የተደገፈ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥበት የኖረውና አገዛዙ በሰፊው ተሰማርቶበት ያለው የመሬት ወረራና ዘረፋ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ የህዝብ ሃብት የሆነው ሁለገብ አዳራሽ የፋኖን መመሪያ በመጣስ አቶ ደጀኔ መንገሻ የተባለ ግለሰብ አረብ አገር ለሚኖር ወንድሙ 100000000 (አንድ መቶ ሚሊየን) ብር እንደገዛው ለማወቅና ለማረጋገጥ ችለናል::
አዳራሹ የተሸጠበት የገንዘብ መጠን ከፍ ያለ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች የገለፁ ቢሆንም ይፋ ከሆነው ከዚህ 100000000 (አንድ መቶ ሚሊየን) ብር ገንዘብ ውስጥ 80000000 (ሰማኒያ ሚሊየን) ብሩን ገቢዎችና ሌሎች ቢሮዎች የሚያውቁት ሲሆን 20000000 (ሃያ ሚሊየን) ብሩ በየደረጃው ላሉ የብልፅግና ካድሬዎችና ለደላላ የተሰጠ ገንዘብ ነው:: መጠኑ ያልተገለፀ ገንዘብም በየደረጃው ላሉ የመከላከያ አመራሮች እንደተሰጠ ለማወቅ ችለናል::
ቆቦ ከተማን ጨምሮ በራያ ቆቦ ህዝብ ሃብት እንደተገነባና በደርግ ዘመን ውድቀት ተጀምሮ በኢህአዴግ ዘመን መባቻ 1984 ዓ.ም እንደተጠናቀቀና አገልግሎት እንደጀመረ የሚነገረው ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ ዛሬ ላይ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ "የአማራን ህዝብ በአማራ ህዝብ ሃብት" በሚል መርህ መሰረት መሬት ሽጦ በሚገዛው ጦር መሳሪያና ተተኳሽ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ላለው ፋሽስታዊ አገዛዝ መጠቀሚያ ሆኗል::
በዚህም ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በፋኖ ትግል ተንኮታኩቶ የገንዘብ አቅሙም ሊጠገን በማይችል ሁኔታ የወደቀ ሲሆን ይህንን የገንዘብ ችግሩን ለመፍታት በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች ላይ የመሬት ወረራና ዘረፋ እየፈፀመ በህገወጥ ጨረታና ሌሎች መንገዶች እየሸጠ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም የህዝብ ሃብት የሆነውን ቆቦ ሁለገብ አዳራሽን ሸጠው ገንዘብ የተከፋፈሉና በሰውና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠባቸው የቆቦ ከተማ እና የሰሜን ወሎ ዞን አመራሮች የሚከተሉት ናቸው፦
1.አቶ ከድር ሙስጠፋ ---- የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ሃላፊ 1000000 (አንድ ሚሊየን) ብር
-ሻምበል እንዳየነው በተባለ ግለሰብ 1 ሚሊየን ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
2.አቶ ሃይለአብ ወንድሙ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ 6000000 (ስድስት ሚሊየን) ብር
-ንጉስ አያሌው ጌታሁን በተባለ ግለሰብ 2.5 ሚሊየን እና እስጢፋኖስ እምሩ ዘለቀ በተባለ ግለሰብ 2.5 ሚሊየን እና 1 ሚሊየን በድምሩ 3.5 ሚሊየን ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
3.አቶ ይርጋ ወዳጆ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ፅ/ቤት ሃላፊ 6200000 (ስድስት ሚሊየን ሁለት መቶ ሽ) ብር
-ሙሉ ታከለ ገ/ስላሴ በተባለች ግለሰብ 5.3 ሚሊየን ብር እና መቅደስ መለሰ ይመር በተባች ግለሰብ 9 መቶ ሽ ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኞች ከስር በማስረጃነት ተያይዘዋል::
4.ዶ/ር አዲሱ ወዳጆ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር መሬት አስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ 1000000 (አንድ ሚሊየን) ብር
-መሳይነሽ ደጀን ተገኘ በተባለች ግለሰብ 1 ሚሊየን ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
5.አቶ አበበ ይመር ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፅ/ቤት ሃላፊ 200000 (ሁለት መቶ ሽ) ብር
-ሁለት መቶ ሽ ብር በግል አካውንቱ በስሙ የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
6.አቶ ሙለታ መሃመድ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የመሬት ልማት ባንክ ቡድን መሪ 150000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሽ) ብር
-አንድ መቶ ሃምሳ ሽ ብር በግል አካውንቱ በስሙ የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
7.አቶ ሃይለማርያም አትክልት ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ፅ/ቤት ም/ሃላፊ 100000 (አንድ መቶ ሽ) ብር
-ደሳለ ፈንታው መንገሻ በተባለ ግለሰብ መቶ ሽ ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
8.ቦታውን ያሻሻጠው ደላላ ወይም ግለሰብ 5350000 (አምስት ሚሊየን ሶስት መቶ ሃምሳ ሽ) ብር
በአጠቃላይ ለፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ካድሬዎች 14650000 (አስራ አራት ሚሊየን ስድስት መቶ ሃምሳ ሽ) ብር የተሰጠ ሲሆን 5350000 (አምስት ሚሊየን ሶስት መቶ ሃምሳ ሽ) ብር የህዝብን ሃብት ደላላ ሆኖ ላሻሻጠው ግለሰብ የተሰጠ ገንዘብ ነው::
በመጨረሻም የአማራ ህዝብ ሆይ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ነውና ብሂሉ ግፈኞች ተመቸን ብለው በጉልበት ሃብትህን ተቀራምተው ታንክና መድፍ ጄትና ድሮን ታጥቀውበት ብሎም ለአራዊት ሰራዊታቸው ደመወዝ እየከፈሉበት መልሰው አንተው ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙበት እንደሆነ አለም ያወቀው ሐቅ ነውና በትግልህ ነፃነትህን በነፃነትህ ፍትህና ርትዕን ትጎናፀፍ ዘንድ ዛሬም መልክታችንን እናስተላልፋለን!
በመጨረሻም ግፈኞች መሬቱን ተሸክመውት የትም አይሄዱምና "የህዝብ ሃብት ጊዜውን ጠብቆ የህዝብ ነው!" የሚለው መመሪያችን እንደተጠበቀ መሆኑን እየገለፅን ህዝባችን ከግፈኞችና ይሄ ጊዜ የማያልፍና የማይነጋ ከመሰላቸው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰዎች ህገወጥ መሬት ባለመግዛት ራሳችሁን ከክስረት ብሎም ከጥፋትና ተጠያቂነት እንድትታደጉ ስንል ለማሳሰብ እንወዳለን!
ማስታወሻ፦ በሌሎች የቤተ-አማራ አካባቢዎችም ላይ ያሉ የመሬት ወረራና ዘረፋዎች በጥብቅ ክትትላችን ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ ሲሆን ማስረጃዎች እንደደረሱን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ይሆናል!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም

💔2