ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት የተጋድሎ ውሎ

____፩
የ109ኛ ኮር 99 ክፍለጦር የጠላትን እቅድ በማዛባት ዋድ አዲስ ዓለምን ከተማ ማስለቀቅ ተችሏል።

መክረትረት የለመደው የአገዛዙ ሰራዊት በለሊት በመግባት እረፍት የነሳው የ109 ኮር 99ኛ ክፍለ ጦር ዋአድ ዓዲስ አለም ከተማን በለሊት ወጥቶ ወደ ደምበጫ ከተማ ገብቷል።

የብልፅግናን መንግስታዊ መዋቅሩን እዘረጋለሁ ብሎ ያሰበው የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እረፋት የነሳው የ109 ኮር 99ኛ ክፍለጦር ዋድ ዓዲስ አለም ከተማን ለቆ ወደ መጣበት ተመልሷል።

____
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር እና 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ሀይል በድሮን የታገዘዉን ተጋድሎ በመቋቋም ከተለያዬ አካባቢ ተሰባስቦ የመጣውን በርካታ አረመኔ ቡድን አጉት ላይ ደምስሶታል

በትላንትናው ዕለት ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 እስከ ምሽት 1:00 ድረስ በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሰከላ ወረዳ አጉት ቀበሌ ዙሪያ ከሚገኙ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ መሽጎ የሚገኘውን ዙፍን ጠባቂ ሰራዊት የያዘዉ የድንጋይ ካብ ሳያተርፈው ተደምስሷል።

ለተከታታይ 3 ሰሃት በተደረገዉ የእጅ በእጅ የቦምብ ትንቅንቅ ለማትቀረዋ የነገ ነፃነት፤ ጀግኖቹ 44ኛ እና 77ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች ዉድ ዋጋ በመክፈል ጡት ቆራጩን ቡድን፣ ጡትና ምላስ ብልት በቆረጠበት፤ አሰቃቂ ድርጊት በፈፀመበት ሰከላ ቀጠና አጉት ላይ ቀብረዉ አስቀርተዉታል።

አረመኔው ቡድን ለሳምንት ሲቆፍር ሲዘጋጅበትና አንገት ድረስ ሲሰራዉ የሰነበተዉ ምሽግ በነበልባሎቹ ሲደረማመስ መድረሻ ያጣዉ ወንበዴ ቡድን በእግር አልችል ብሎ በድሮን የታገዘ ዉጊያ በማድረግ ተከታታይ ሁለት የድሮን ቅንቡላ ቢጠቀምም ከመደምሰስ አላተረፈዉም።

ቤተክርስቲያንና ተራራ ላይ ጉድጓድ እንደ ቀበሮ በመቆፈር ለማምለጥ የሚሞክረዉ ዙፋን ጠባቂዉ ሰው በላው ቡድን በጀግኖች ከባድ ምት ተደቁሶ በቆፈረዉ ጉድጓድ አፈር ለብሶ ቀርቷል።

በ105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር እና በ109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ጥምር ሀይል የደረሰበትን ሽንፈት መቋቋም ያቃተው ጡት እና ምላስ ቆራጩ የጠላት ሀይል ከሽንዲና ከተለያዬ ቦታ በማሰባሰብ መቀበሪያው ወደ ሆነው ወደ ሰከላ ወረዳ አጉት ከተማ ተጨማሪ ሀይል አስገብቷል።

___፫

የገበሬው ጦር የብልፅግናን ሰራዊት አንገት አስደፍቶ መልሶታል።

በጎንቻ ሲሶ እነብሴ ወረዳ ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2018 ዓ/ም ከግንደወይን ከተማ የቡችር እና የቁራ አራስማ ቀበሌዎች ላይ ጭፍጨፋ ለመፈፀም በርካታ መከላከያ፣ ምኒሻና ፖሊስ በማሰለፍ በሌሊት ተንቀሳቅሶ በየቡችር ቀበሌ ሚካዔል ቤተክርስቲያን እና የቁራ አቦ ቤተክርስቲያን ህዝቡን በግድ ሰብስቦ በሬውን ሽጦ የገዛውን መሳሪያ ለማስውረድ ደፋ ቀና ሲል ቢያረፍድም የ74ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት የቡችር ሚካዔል የከተመውን የብልፅግና ሰራዊት እንዲሁም የአራስማ ቀጠና የገበሬው ጦር ደግሞ የቁራ አቦ ዙሪያ በመስፈር የተደረገውን ሙከራ ጀግኖች በክንድቻው ሲያዝረከርኩት ያረፈዱ ሲሆን በየጥሻው ሙትና ቁስለኞችን በመያዝ ወደምጣበት እግሬ አውጭኝ ብሎ እንዲመለስ አድርገውታል።

በዚህ አውደ ውጊያም የገበሬው ጦር ተጋድሎ መንግስት ህዝቡ ይደግፈኛል እያለ የሚሰራውን የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ገደል የከተተ ሆኗል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስአስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም
1👎1🙏1
የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ፋኖዎች ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፀሙ:: አንድ ተሽከርካሪ ሙሉ ጠላት ከጥቅም ውጭ ተደርጓል::

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ (ሸዋንግዛው ካሣ) ሻለቃ ፋኖዎች በምዕራብ ወሎ ግንባር ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ ከገነቴ ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ ቦታ ላይ ደፈጣ ጥለው ከደሴ ወደ አማራ ሣይንት በመጓዝ ላይ ያለ የጠላት ኃይልን ድባቅ መተዋል::

ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ የሻለቃይቱ ፋኖዎች በጠላት ላይ በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት ተሽከርካሪው ላይ ያለው ጠላት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል:: በተሽከርካሪው ተጭኖ ሲጓጓዝ ከነበረው የጠላት ኃይል መካከል አንድ አድማ ብተና በህይወት ተርፎ ሲማረክ ሌሎች ዶግ አመድ መሆናቸው ተረጋግጧል::

በአርበኛ አለልኝ ተሰማ የሚመራው የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ሰራዊት በቅርቡ ሪፎርም ሰርቶ ወደ ግዳጅ ከገባ ወዲህ በየዕለቱ በሚባል ደረጃ ታሪክ እየሰራ መሆኑን ልብ ይሏል:: ሰራዊቱ ባለፈው ወር ወታደራዊ እና የፓለቲካ ስልጠና ወስዶ እና ተበውዞ ሁሉም በሚባል ደረጃ ከሰፈሩ ወጥቶ የሚታገልበት ዕድል በመፈጠሩ የተነሳ አሁን ላይ የክፍለ ጦሩ ሰራዊት ተወርዋሪ ከመሆኑ ባሻገር የማድረግ አቅሙ በብዙ እጥፍ ጨምሯል ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ይመር ሁሴን ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ገልጿል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 12 ቀን 2018 ዓ.ም
2🙏1
#ዜና_ምሥራቅ_ወለጋ

ትናንት ቅዳሜ ማለትም ታኅሣስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አሊ ቀበሌ ከመቶ በላይ ንጹሓን ታፍነው ወደ ወረዳው ከተማ በ 10 ተሽከርካሪዎች ተጭነው ተወስደዋል።

ሕጻናት፣ አዛውንቶች፣ አቅመ ደካሞችና እመጫት እናቶች ጭምር ይገኙበታል። ይኽ የኾነው በክልሉ የፀጥታ ኃይል ነው የሚሉት ነዋሪዎች አካባቢው ከሣምንት በላይ ተከቧል፤ ሕዝቡን እየጫኑ ይወስዳሉ ተውና ለምን የሚለውን በድብደባና በተኩስ ይገድላሉ፤ ነገ ምን እንደሚገጥመን አናውቅም ብለዋል።

ፓርቲያችን በዚኽ ጉዳይ ከሣምንት በፊት የማስጠንቀቂያና የነዋሪውን የጭንቅ ድረሱልን ጥሪ ያወጣ ሲኾን አኹንም በመንግሥታዊ ወዋቅር ንጹሓንን ማንገላታት እንዲቆም፣ ታፍነው የተወሰዱትም ያለምንም ቅድመ ኹኔታ ወደቤታቸው እንዲመለሱ አበክረን እንጠይቃለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ታኅሣስ ፲፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
🙏1
ምኒልክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ወረዳ እና ኩታበር ወረዳ ባደረጉት ተጋድሎ አራት ቀበሌዎችን ተቆጣጠሩ::

በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ዛሬ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ በደቡብ ወሎ ደሴ ዙርያ ወረዳና ኩታበር ወረዳ ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል::

በተጋድሎዉም በጠላት ይዞታ የነበሩ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል። ነጻ የወጡት ከተሞች አያታ፣ፋላ ፣ጽድ ገበያ፣ አጥንት መስበርያ የተባሉ ከተሞች ሲሆኑ በተጋድሎዉም የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ መከላከያ፣አድማ ብተና እና ሚሊሻ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ኪሳራ አስተናግደው ሙትና ቁስለኛቸውን ይዘው ወደ ደሴ ፈርጥጠዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም
1🙏1
ለህዝብ ደህንነት ሲባል መንገድ ዝግ መሆኑን ስለማሳወቅ‼️

═════════❁✿ ❁══════============

አፋብሓ ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር  በሚያስተዳድራቸው ቀጨናዎች የህዝብን ደንነት ለመጠበቅ ሲባል መንገድ የተዘጋ ስለመሆኑ ማሳወቅ፣

በሆዱ ተገዝቶ የአብይ አህመድ አሊን ወንበር ለመጠበቅ የሚዝረከረከው የጠላት ሀይል  ፋኖን ዘራፊ ነው ለማስባል ፋኖ መሣይ ብልጽግናዎችን በማደራጀት ሹፌሮቻችንን እና ህዝባችንን እያገላታ መሆኑን ደርሰንበታል።

በመሆኑም  ህዝባችንን እና ሹፌሮቻችንን ከነዚህ ወንበዴዎች ዘረፋና ግድያ   መከላከል ያመች ዘንድ ከነገ 13/04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መንገዶች ማለትም፦
                       1.ከባህር ዳር ጭንባ ቁንዝላ ደለጎ
                       2.ከዱርቤቴ ዝህብስት ወገዳ
                        3.ከዱርቤቴ ሀሙሲት ማማላ
                        4.ከዱርቤቴ _ቀደምት ላሊበላ ልሁዲ መንገዶች 
ዝግ እንደሆኑ ማሳወቅ እንወዳለን ።ህዝባችንም በነዚህ  ዘራፊ አካላት ላይ እርምጃ ወስደን ፣በማስተካከል በፍጥነት ክፍት ስለምናደርግ፣ እንደወትሮው ሁሉ በትግስት እንድትጠብቁን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።

ማሳስቢያ፦ ይህንን መልክት ጥሶ እገዳ በተጣለባቸው መንገዶች ሲንቀሳቀስ ለሚደርስበት ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱን እራሱ ባለቤቱ የሚወስድ መሆኑን በድጋሜ እናሳውቃለን።

አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️

የፋብሀ ምዕ/አ/ቀ/ቴዎድሮስ-ዕዝ
የ105ኛ ኮር 55ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት
1👍1🙏1
የአገዛዙ ኃይሎች በጎንደር ሻሁራ ከተማና አፀደማርያም አከባቢ በፈፀሙት ጥቃት ሁለት ታዳጊዎች ተገደሉ!

በእረኝነት ላይ የነበሩ የ10 ዓመት እና የ15 ዓመት ታዳጊዎች ናቸው በጥቃቱ የተገደሉት።

ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማና አፀደማርያም ቀበሌ ሰፍረው የሚገኙት የፀረ አማራው ብልፅግና አገዛዝ ወታደሮች ታህሳስ 11/2018 ዓ/ም በከፈቱት የዘፈቀደ የሞርተር እና የድሽቃ ተኩስ፡ በከብት እረኝነት ላይ የነበሩ ሁለት ታዳጊዎች መገደላቸውን ከአከባቢው ነዋሪዎች ለማረጋገጥ ተችሏል።

ንፁኋንን በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ቆራርጦ መግደል፣ የዘፈቀደ ተኩስ በመክፈት ህፃናትና ነፍሰጡር እናቶችን ሳይቀር መረሸን፣ ታዳጊ ሴቶችን መድፈር፣ ሐይማኖታዊ ስፍራዎችን ማርከስ ልዩ መገለጫቸው የሆነው የአገዛዙ ወታደሮች፡ በፈፀሙት የሞርተርና የድሽቃ ጥቃት፡ ምስጋናው አቤ የተባለ በከብት እረኝነት ላይ የነበረ የ15 ዓመት ታዳጊ እና ሌላ አንድ የ10 ዓመት ታዳጊ ተገድለዋል ነው ያሉት መረጃውን ያደረሱን የአከባቢው ነዋሪዎች።

በተጨማሪም በዚኸው የከባድ መሣሪያ ጥቃት የንፁኋን መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ነው የተነገረው።

የአገዛዙ ኃይሎች በቀጠናው ከፋኖ ጋር ውጊያ አድርገው ሽንፈት በገጠማቸው ቁጥር ሲሸሹ በመንገድ ላይ የሚያገኟቸው ንፁኋኖች ላይ ከሚፈፅሙት ግድያ በተጨማሪ፡ የዘፈቀደ የከባድ መሣሪያ ድብደባ በማካሄድ በእረኝነት፣ ሰብል በመሰብሰብና በመኖሪያ ቤታቸው የነበሩ ንፁኋኖችን  ገድለዋል፡ በርካታ ሀብት ንብረትም አውድመዋል።

@መረብ ሚዲያ
2🙏1
በአርበኛ ሸጋ ጌታቸዉ የሚመራ የዕዝ አመራር ለክፍለ ጦር አመራሮች ለብርጌድ አመራሮች ለሻለቃ አመራሮች የማጥራት ስልጠና ሲሰጥ የቆየዉ በቀን12/4/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ
ሰበር የድል ዜና

64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ በደፈጣ ጥቃት ወረጎ እና አካባቢው ቀበሌ ታሪክ ሰርቷል።

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ማህበረሰቡን በመልሶ ማደራጀት የሰለጠነ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት እና በመገንባት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ እያደራጀ ባለው ግዙፍ ኃይል ስጋት ውስጥ የገባው የአገዛዙ ተቅበዝባዥ ኃይል በቀጠናው የሚገኘው የፋኖ አባላትን ለማጥቃት በየዕዱኃ ከተማ መሽጎ ከሚገኘውን የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ጨለማን ተገን በማድረግ በቁጥቋጥ ቀበሌ የፋኖ አባላትን ለማጥቃት ምክሮ ሳይሳካለት ቀርቷል።

በቁጥቋጥ ቀበሌ የገባውን የአገዛዙ አረመኔ ሰራዊትን ድጋፉ ለማድረግ ከየዕዱውኃ ከተማ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ተጨማሪ ኃይል በመያዝ በጉዞ ላይ የነበሩ በአንድ ፖትሮል እና በአንድ ላንድ ክሎዘር አመራር እና አባላት የጫነ ተሽከረካሪ በጉዞ ላይ እንዳሉ #በወረጓ እና አካባቢው ቀበሌ ልዩ ቦታው #ደረቅ_ወንዝ በተባለ ቦታ 64ኛ ክፍለጦር 5ኛ ሬጅመንት በወሰደው የደፈጣ ጥቃት በፖትሮል ላይ የነበሩ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አመራር እና አባላት ሙት እና ቁስለኛ አድርጓል።

በሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ ወደ ቁጥቋጥ ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ በተሰራው የደፈጣ ጥቃት ከተደመሰሱት የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላት ውስጥ:-

ሻምበል ሰለሞን የሻለቃ (ሬጅመንት )አዛዡ እና አንድ ጋንታ መሪ ፓትሮል ላይ እንዳሉ ተመተው የሞቱ : 1 ሚሊሻ እና 4 የመከላከያ አባላት ከባድ ቁስለኛ ሆነው ሆስፒታል የገቡ

ሆሲፒታል ከገቡት አምስቱ ቁስለኞች ውስጥ ሚሊሻውን ጨምሮ 2ቱ የመከላከያ አባላት መሞታቸውን አረጋግጠናል። የቀሩትም የመትረፍ እድል እንደሌላቸው ከውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ተሰምቷል።

አንድ ፖትሮል እና አንድ ላንድ ክሎዘር ተሽከረካሪ በደፈጣ ጥቃቱ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!

@ፋኖ ይበልጣል ጌቴ
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
👍2🙏1