ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በቀጠለው የደጃዝማች ፬ኛ ኮር ማጥቃት ጠላት ተጨማሪ ጉዳት ደረሰበት!!


🔸 በደረሰበት ምት ሞራሉ የላሸቀው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ሞራሉን ለማነሳሳት በማለም ቁጥሩ የበዛ ኃይል ከጋብላ አቅጣጫ ወደ ሐዋሳ አርማጭሆ በሁለት ተከፍሎ የተጓዘ ሲሆን ግመል ዲንጋይ የተባለ ቦታ ሲደርስ ንፁሃን አርሶ አደሮች ላይ ጥቃት የከፈተ ቢሆንም ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦር ሲሳይ ብርጌድና ጎቤ ክ/ጦር ሰሜን ብርጌዶች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመጣመር ፈጣን የአፀፋ ምላሽ ውጊያ ከፍተው ጠላትን መተውታል።12 ጠላት ሲደመሰስ 4 ደግሞ ቁስለኛ ሁኗል።ውጊያውን መቋቋም የተሳነው የፋሽስቱ ሰራዊት ሬሳውን አንጠባጥቦ ወደ ጋብላ አቅጣጫ ሸሽቷል።

🔸 ወደ አርማጭሆ ሐዋሳ የተጓዘው 2ኛው የጠላት ሰራዊት ደግሞ የአካባቢው ነዋሪ በሁለት ሻለቃ ተደራጅቶ በመጠበቅ ሰብዓዊ ጉዳት ስላደረሰበት ወደ ጋብላ አቅጣጫ ሸሽቷል።

🔸 ከሐዋሳ ተመቶ የተመለሰውን ጠላት ጋብላ ከተማ አቅራቢያ ሲደርስ ከባድ የደፈጣ የጨበጣ ውጊያ ተከፍቶበት ተጨማሪ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሶበት ሌሊቱን ተሰውሮ ወደ ማሰሮደንብ ሸሽቶ ሀመሰወር እየሞከረ ነው።
በተከታታይ ሸመለጋራ ፣አሻሚት እና መሸሃ ከባድ ምት የደረሰበት ጠላት መሸሃን ፣ደለሎ ቁጥር አንድ እና አካባቢውን ለቆ የሸሸ ሲሆን ጋብላ ከተማን በተጨማሪ ለቆ ሸሽቷል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
🙏3
ታፍነው ወደ ማሰልጠኛ ቦታ ሲሄዱ የነበሩ የአማራ ህጻናት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ ሻለቃ ከመንገድ ላይ ተማረኩ።

ሕፃናትን ለጦርነት ማዋል አለማቀፋዊ ወንጀል ነው። ይህን በመተላለፍ የብልፅግና አረመኔ አመራር በተደጋጋሚ ህፃናትን ከትምህርት ቤት እየመለመለ ወደ ስልጠና እየላከ በጦርነት እያስጨፍጭፍቸው ይገኛል። በውጊያ የማረክናቸው ሕፃናትም የስነልቦና ጫና ውስጥ በመግባታቸው የጤና መታወክና የአዕምሮ ሰላም እንዳጡ በተለያዩ ጊዜ ያረጋግጠው ጉዳይ ነው።

ይህን የመከላከል ሀላፊነት የወደቀበት የአማራ ፍኖ በተለያዩ ጊዜ ስልጠና እንዳይገቡ በደፈጣ ከነመኪና በመማረክ የስነልቦና ስልጠና እና የተሀድሶ ስልጠና እየሰጠ ወደ ቤተሰቦቻቸው መላኩን ተያይዞታል። ከዚህ በፊትም ደብረማርቆስ ዙሪያ በበረኸኛው ጅበላ ብርጌድ በርካታ ህፃናትን በ2016ዓ.ም ማስለቀቁ የሚታወስ ነው።

ዛሬም ታፍነው ወደ ማሰልጠኛ ቦታ ሲሄዱ የነበሩ የአማራ ህጻናት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ ሻለቃ ከመንገድ ላይ በመማረክ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስአስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም
🙏1
ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር ውጫሌ ከተማ ዙሪያ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ::

ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ውጫሌ ከተማ ዙሪያ ዛሬ ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም ንጋት 12:00 ጀምሮ ወደ ጠላት ምሽግ ዘልቀው በመግባት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ እስከ ቦምብ ጭምር በመጫበጥ በርካታ የጠላት ሃይል ደምስሰውና አቁስለው ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዝግበዋል::

24ኛ ክፍለጦር በተጋድሎው ውጫሌ ከተማ ቁንጥሮ ላይ የጠላትን ምሽግ ሁሉ ደምስሰው በመግባት ትልቅ ጀብድ የፈፀሙ ሲሆን ከ40 በላይ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው ለጊዜው ቁጥሩ ያልታወቀ የነፍስ ወከፍ ክላሽና የተለያዩ ተተኳሾችንም ማርከዋል::

የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢ እና ከኦሮሞ ብልፅግና ልዩ ሃይል ጭምር ታፍሶ ሲመጣ በምድር በመካናይዝድና በአየር ሃይል ጄትና ድሮን ከፍተኛ ድጋፍ ሊደረግለት ቃል ተገብቶለት መጥቶ ውጊያ እያደረገ ያለ ሲሆን አየር ንብረቱ ለድሮን በማይመችበት በዳመና ጊዜ ወኔው ተሰልቦና ውጊያ ከብዶት በጅምላ እየተደመሰሰ እና እየተማረከ ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም
🙏1
የሻለቃ አዛዡ ከ12 ወታደሮች ጋር ተደመሰሰ!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጥላሁን ፈንታው ብርጌድ የፋኖ ኃይል መካነሰላም ዙሪያ ወረዳ ቢሊ ታዳጊ ከተማ ውስጥ ከማለዳው 11:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 5:00 ሰዓት በተደረገ ውጊያ የጥላሁን ፈንታው ብርጌድ ፋኖዎች ከፍተኛ የጦር ሜዳ ጀብዱ በመፈፀም 15 ወታደሮችን እና የ45ተኛ ክፍለ ጦር ሻለቃ አዛዥን ደምስሰዋል:: በዛሬው ተጋድሎ ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም በርካታ ወታደሮች ቆስለዋል:: ቁስለኞች በአምቡላንስ ተጭነው ወደ መካነሰላም ጄኔራል ሆስፒታል ተወስደዋል::

የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ ሻለቃ አብነው ታደሰ እና የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ ስንደው ገዜ በመሩት ውጊያ ቢሊ ላይ ዛሬ ታህሳስ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ታላቅ ድል ተመዝግቧል:: የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ተኛ ክፍለ ጦር የመካነሰላም ቀጠናን መሸፈን አልቻለም ተብሎ ሰሞኑን የ47ተኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት በድጋፍ ሰጭነት ወደ መካነሰላም መግባቱን ተከትሎ የፋሽስቱ አብይ መንግስት መጠነ ሰፊ ወረራ ለመፈፀም አስቦ የመጀመሪያ ሙከራውን ዛሬ ቢያደርግም ድል ሳይቀናው ቀርቶ አባላቱን አጥቷል::


መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 9 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏21
ነጻ በወጡ ቀጠናዎች የጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር መዋቅር የመዘርጋቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!

የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር ነጻ ባወጣቸው ቀጠናዎች የጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር መዋቅር ዝርጋታ ስራን እንድያስተባብሩ ምኒልክ ዕዝ የላካቸው ባለሙያዎች ተልዕኳቸውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን ለዕዙ በላኩት ሪፓርት ገልፀዋል::

የዕዙ ፓለቲካ መምሪያ ከትምህርትና ስልጠና መምሪያ ጋር በመተባበር በጃማ ግንባር የጊዜያዊ መንግሥት መዋቅር ዝርጋታ ስራውን ለማጠናቀቅ ችሏል::

ከህዝብ ጋር የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ተከታታይ የምክክር መድረኮች የተዘጋጁ ሲሆን በትግሉ ሂደት የተፈጠሩ ችግሮችን በተመለከተም ሰፊ ውይይት ተደርጎ ለመፍትሄዎቻቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል::

ለአካባቢያዊ ችግር አካባቢያዊ መፍትሄ የሚሰጥ የአስተዳደር፣ የፀጥታ እና የፍትህ መዋቅር የተዘረጋ ሲሆን ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ይችል ዘንድ ምቹ የሆነ እድል ተፈጥሯል:: ከቀበሌ መዋቅር ባሻገር የንዑስ ወረዳ አደረጃጀት ተፈጥሮ ከቀበሌ አቅም በላይ የሆኑ ችግሮች እልባት የሚያገኙበት አማራጭ እንድኖር ተደርጓል ሲል የዋሲል ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አቡሽ ተፈራ ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ገልጿል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 9 ቀን 2018 ዓ.ም
1🙏1
የደጋው መብረቅ ኮር ለበርካታ ወራቶች ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ፋኖዎችን በደማቅ ትርኢት ታጅቦ አስመረቀ!

አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ለአራተኛ ዙርና ለበርካታ ወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ የእግረኛ ሰልጣኝ ፋኖዎች በዛሬው እለት በድምቀት ተመርቀዋል።

በአንሻ ክፍለ ጦር ለአራተኛ ዙርና ለበርካታ ወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ እግረኛ ሰልጣኞች በደማቅ ትሪዕታዊ ሰልፍ ታጅበው ታህሳስ 9/2018 ዓ/ም ተመርቀዋል።

በምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የኮሩና ክፍለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኮሩ ም/ዘመቻ መምሪያ አርበኛ ጨለፍ ተስፋው "እናተ የአማራ ህዝብ ሰራዊት ናችሁ በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን ዘር ተኮር ስርዓታዊ አዳጋ አከርካሪውን ሰብራችሁ የህዝባችሁን ህልውና እውን ማድረግ ይጠበቅባችኋል ሲል መልክቱን አስተላልፏል::

አርበኛው ንግግሩን በመቀጠልም የአማራ ህዝብ ከፈጣሪው በታች ከናንተ መዳፍ ሰላሙን እድትሰጡትና ህልውናውን እንድታረጋግጡለት ተስፋ አድርጓል። ተወደደም ተጠላም እኛ አማራዎች መዳኛ መንገዳችን ክንዳችን ላይ ያለው ነፍጣችን ነው። ተገደን በራፋችን ድረስ ገዳዮቻችን መጥተው ነፍጣችንን እናነሳ ዘንድ አድርገውናል። ለዚህ ደግሞ መሰልጠን፣ መታጠቅና ዘመኑ የሚዋጀውን ሆኖ መገኘት ይጠበቅብናል። ያለን አማራጭ አንድና አንድ ማሸነፍና ማሸነፍ ብቻ ነው" ሲሉ መልክቱን አስተላልፏል!

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የቃል ኪዳን መርሃ ግብርም የነበረ ሲሆን ተመራቂ ፋኖዎች ከስልጠና ባገኙት ሙያዊና ወታደራዊ እውቀት ህዝባቸውን በታማኝነት ለማገልገልና የህዝባቸው መዳኛ ዘብ ሆነው መቆም እዳለባቸው ቃል ኪዳን ፈፅመዋል::

እየተዋጋን እንሰለጥናለን እየሰለጠን እንዋጋለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ታህሳስ 9 /2018 ዓ.ም
🙏31🔥1