ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ኢትዮጵያ በአሸባሪወች መዳፍ ውስጥ ነች። ትላንት የፀረ-ቅኝ አገዛዝ ተጋድሎ እቅድ የወጣበት፣ የፓን አፍሪካኒዝም ፕሮጀክት የተተለመበት፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጥንስስ የተወለደበት የምኒልክ ቤተ መንግስት ዛሬ የአፍሪካ ቀንድ የትርምስ እና የጥፋት እቅድ የሚታቀድበት ሆኗል። ይህንን ሐቅ በአይኑ እያዬ በጆሮው እየሰማ ራሱን የሚያታልለው ደግሞ ቁጥሩ ቀላል አይደለም። የአገዛዙ የጥፋት ጫማወች ግን የሁሉንም ጉበን መርገጣቸው አይቀርም።

ሒትለር ለ2ኛው የዓለም ጦርነት ሲያሟሙቅ አሜሪካኖች ገለልተኛ መሆን ቢፈልጉም የኋላ ኋላ ገብተውበታል። ራሽያወች የናዚ አገዛዝ ወዳጅ ሆነው ከጦርነቱ ውጭ ለመሆን ቢፈልጉም አልቻሉም። እንግሊዞች የተከተሉት የተለማማጭነት ስልትም የጦርነቱ አካል ከመሆን አላዳናቸውም። አጥፊወች የሚራሩለት ህዝብ የለም። ከአብይ አህመድ አገዛዝ በረከት የሚጠብቅ ሁሉ የሰላም አየር የሚተነፍሰው የመጥፋት ወረፋው እስኪደርስ ብቻ ነው።

ትውልዱ እያከናወነ ያለው ያለፉት ትውልዶችን የቤት ስራ ጭምር ነው። ከጥቂት መቶ ዓመታቶች በፊት ፤ ከዚያም ወዲህ ከአንድ ምዕተ ዓመት ትንሽ ቀደም ብሎ፤ በቅርቡም ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት ሊከወኑ ሲገባ ባልተፈፀሙ ታሪካዊ ክንውኖች ምክንያት የአማራ ህዝብ ራሱ በሚከፍለው ግብር በተገዛ ጦር መሳሪያ እና አረመኔ ሰራዊት የተጋረጠበትን የመጥፋት አደጋ እየመከተ ይገኛል።

ይህንን ጦርነት በስኬት ከማጠናቀቅ በመለስ ያሉት አማራጮች ሁሉ የአማራን ህዝብ የከፋ አደጋ ውስጥ የሚከቱ ናቸው። የዓለም የኃይል አሰላለፍ የዓለም ጦርነቶች ውጤት ነው። የእንግሊዞች ኃያልነት ሙሉ በሙሉ በአሜሪካኖች የተተካው 2ኛውን የዓለም ጦርነት በጀርመን ሽንፈት በመጠናቀቁ ነው። ራሽያ ማንነቱን እና ስልጣኔውን ያተረፈው በዚሁ ጦርነት 27 ሚሊዮን ህዝብ ገብሮ ነው። እስራኤል የመካከለኛው ምስራቅ አውራ የሆነችው የ6ቱን ቀን ጦርነት ድል ማድረጓን ተከትሎ ነው።

የፀና ብቻ የድሉን ዋንጫ በሚያነሳበት በዚህ የዘመናችን አስደናቂ ፀረ አገዛዝ ተጋድሎ እልፍ ዋጋ ተከፍሎበት ብዙ ጠመዝማዛ መንገዶችን መሻገር ተችሏል። ዓለም በቂ ጆሮ ባይሰጠውም እየተካሄደ ያለው ጦርነት ብዙወችን የበላ ጦርነት ነው።

በየትኛውም ዓለም የጥፋት እጁን የሚዘረጋ፣ የራሱ ህዝብ ላይ የእልቂት ጦርነት ያወጀ አገዛዝ አያሸንፍም። ግዜ በሰጠነው ቁጥር ግን የምንከፍለውን ዋጋ እንደሚጨምረው እሙን ነው። የሽብር ፕሮጀክቶችን በማመንጨት ብቻ ስኬታማ የሆነው የአገዛዙ አንጎል ሊያጭበረብር የሞከረበት ፖለቲካዊ ስልት ሁሉ እየሟሸሸ ነው።

የነገው ትውልድ እጣ ፋንታ የሚፃፈው ዛሬ በምንከፍለው የመስዋዕትነት ደም ነው። ራሳችንን ከጥፋት ለመታደግ የምናደርገውን ትግል በስፋት እና በጥልቀት አጠናክረን እንቀጥላለን።

@አስረስ ማረ ዳምጤ
🙏1
ሰበር  ዜና ቢዛሞ ‼️

አፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ በሊሙ ገሊላ ወረዳ የአገዛዙ መንገድ መሪዎች ላይ ዕርምጃ ወሰደ።

አፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ በምስራቅ ወለጋ ዞን  ሊሙ ገሊላ ወረዳ የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት መንገድ መሪ የነበሩ ሚሊሻዎች ላይ ጀግኖች የአበጀ ጥበብ ብርጌድ አናብስቶች ዛሬ ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም አነጋግ 11:00 ስዓት ላይ  በወሰዱት ዕርምጃ ስድስቱ ወደ ላይኛዉ ሲሸኙ  በርካቶችን ደግሞ ክራንች አንጋች ሁነዋል።

ዛሬ የተሸኙት ሚሊሺያዎች በተደጋጋሚ የአማራ ህዝብ ወደሚኖሩባቸዉ አካባቢዎች የጠላትን ሀይል እየመሩ ሲመጡ የነበሩ ናቸዉ።

ፋኖ ዲ/ን ክንዱ አሸናፊ
የአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ
ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም
🙏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት በቢዛሞ እዝ የፋኖ አባላት ተማርከው ስለፋኖ ስነስርአት : የውጊያ ጥበብና አቅም እንዲሁም የስራቱን ጨፍጫፊነት ምስክርነታቸውን ሲሰጡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ነው

ቢዛሞ እዝ በቀጠናው አስደማሚ ትንቅንቅ ላይ ነው
ጥብቅና የሚቆም በሌለበትና ገዳይ “በማይታወቅበት” የቀጠለው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን የማጽዳት ተልዕኮ አኹንም ቀጥሏል!

(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በኦርቶዶክስ እምነትና ንጹሓን ዜጎች ላይ የተጀመረው የማጽዳት ዘመቻ ከአርሲ ወደ ወለጋ ፊቱን በማቅናት የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ኡፋ እና ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ በዓል ለማክበር በወጡበት ከኅዳር 21 ጀምረው ሻምቡ መግቢያ አካባቢ ታግተው ቅዳሜ ታኅሣስ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በአጋቾች መገደላቸውንና በአባትነት በተመላለሱበት ምድር የቀብር አፈር ተነፍገው አስከሬናቸውም እንዳልተገኘ እንዳልተቀበሩ ከቦታው ለማረጋገጥ ችለናል። አኹንም ገዳዮቹ ለላፉት 7 ዓመታት በሚገድሉብት የዳቦ ስም "ታጣቂዎች" ናቸው በሚል መሸፈኑ ነገሩን አስገራሚም ግራ አጋቢም አድርጎታል።  ከቦታው በደረሰን መረጃ መሠረት ግድያውን የፈጸሙት አስከሬንም የከለከሉት በሻምቡ አካባቢ ይንቀሳቀሳል የሚባለው ኦነግ ሸኔ(ራሱን ኦነሰ ብሎ የሚጠራው) ኃይል መኾኑን ደርሰንበታል፤ በከተማ የሚኖሩ በተባባሪነትና በጥቆማም የተሳተፉ ሊኖሩ እንደሚችሉ ፍንጮች አሉ፡፡ 

የቤተ ክርስቲያን አባቶችንና ምዕመናን ግድያ ስልታዊ በኾነ የሚፈጸም የዘር ማጽዳት ዘመቻ አካል እንጂ ድንገቴ እንዳልኾነ በጽኑ እናምናለን። እንደ ቀደሙት ግድያዎች ኹሉ በዚኽም ላይ ገዳዮችን አድኖ ፍትሕ እንዲሰፍን የሚወሰድ እርምጃ አይደለም ለሞቱ እውቅና እንኳን ያለመስጠት ብሎም ለወትሮው እንደሚደረገው የማስተባበል አዝማሚያ ነገሩ ምን ያኽል የተቀናጀና በጥንቃቄ የሚፈጸም ስለመኾኑ ማሳያ አድርጎ መውሰድ ይቻላል። ቀሲስ ዱጉማ የ6 ልጆች አባት ሲኾኑ ቀሲስ ደሳለኝ የመንግሥት ሠራተኛና የኹለት ልጆች አባት ናቸው፡፡

በአንጻሩ ለእነዚህ በእምነታቸውና በሃይማኖታዊ ተልዕኮዋቸው ምክንያት ለተገደሉ ወገኖቻችን ጥብቅና የሚቆምና የሚከራከርላቸው አካል እንደሌለ ብናውቅም እናት ፓርቲ ይኽን ሃይ ባይ በሌለበት ኹኔታ የሚደረግን ዘር ማጽዳትና ዘር ማሳሳት በጽኑ ያወግዛል። የእምነቱ ተከታዮችም ቦታና ጊዜው ይለያይ ካልኾነ በስተቀር ይኽ ተግባር ለኹሉም የሚቀር እንዳልኾነ ተረድተው ነቅተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ ያሳስባል።

በመጨረሻም ፓርቲያችን ለሞቱት እረፍተ ነፍስን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የእምነቱ ተከታዮች ደግሞ መጽናናትን ይመኛል።

እናት ፓርቲ
💔1
የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ::

የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃድ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ካራኤላ የተባለ ቦታ ላይ መሽጎ ያለ ጠላት ጋር ትናትና ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም ጧት 3:00 ጀምሮ እስከ ምሽት 1:00 ድረስ በተደረገ ተጋድሎ ከ30 በላይ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በመደምሰስና በማቁሰል ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

ቆቦ ከተማ ዙሪያ ካራኤላ የተባለ ቦታ ላይ መሽጎ ያለ ጠላት ወደ በዋ ሚካኤል እስከ ተኩለሽ ለመቆጣጠር በማሰብ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ልዩ ዘመቻዎቹ ባግባቡ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ እስከ ቆቦ ከተማ ጫፍ ድረስ ተከትለው በመምታት ከባድ መሳሪያውን ጨምሮ ይዞ እንዲሸሽ አድርገውታል::

በልዩ ዘመቻ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ የደረሰበት ጠላት እንደለመደው የበቀል አፈ ሙዙን ወደ ንፁሃን በማዞር ሞርተርና መድፍ በማስወንጨፍ የንፁሃንን ህይወት ቀጥፏል:: ከሰው ህይወት በተጨማሪ ቤትና ንብረትም አውድሟል እንስሳቶችንም ጨፍጭፏል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም
🙏1
ተቋሙን እያፈራረስነው ነው!

ዲሽቃ ተኳሽ እና ምክትል ቲም መሪው ከእነሙሉ ትጥቃቸው : መውኬ መንገሻ የተባለው  የመከላከያ ሻምበል መሪ ሉባ ጊወርጊስ  የሚታጀብበትን ውሻ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅለዋል::

➦660 የክላሽ ተተኳሽ
➦ 6የእጅ ቦንብ
➦የወገብ ትጥቅ በመያዝ ከስርዓቱ በመውጣት ወደ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል

1ኛ) ፍቅሩ አበባው... ዲሽቃ ተኳሽ 602ኛ ኮር 1ኛ ሬጅመንት
2ኛ) ፉአድ ሚፍታሂ ...ምክትል ቲም መሪ 602ኮር 1ኛ ሬጅመንት
3ኛ) ሀሰን አብዲ... 602ኛኮር 1ኛሬጅመንት

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ

@ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር  ህዝብ ግንኙነት
🙏1
ጋምቤላ ዋና ከተማ ላይ
የአገዛዙ ሰራዊት ከህዝብ ጋር ጦርነት ገጥሟል!!
በፀጥታ አካላት መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ የንዌር ተወላጅ የፀጥታ አካላት እና የአኝዋክ ተወላጅ የፀጥታ አባላት በትላንትናው እለት ሒወት ማለፉ የሚታወቅ ቢሆንም በዛሬው ቀን ግን የኑዌር ተወላጅ የሆኑት መከላከያውን ገጥመውታል። ሁኔታውም የብሔር መልክ እንዳይዝ ስጋታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ ንዋሪወቹ የችግሩ መነሻ ግን የፖለቲካ መሆኑን በቀጠናው የሚኖሩ አመራሮች ችግሩ የቆየ እና በቀጠናው ሰፊ የጦርነት ቀጠና እንደሚሆን እየገለፁ ይገኛሉ።
ዝርዝሩን እንመለስበታል።
1🙏1
አጋልጥ!

ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን የፀረ ማጥቃት እርምጃን መቋቋም አቅቶት ከባድ ኪሣራ የተከናነበው በ11ኛ ዕዝ ራሱን አንበሳው ክ/ጦር ብሎ የሚጠራው የብልፅግና ፓርቲ ተላላኪ መከላከያ ሰራዊት፡ የባለ ሦስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎችን ከነ ተሽከርካሪያቸው እንዲሁም ሌሎች ንፁኋኖችን ከየስራ ገበታቸውና ከትምህርት ቤት ውለው እየተመለሱ የነበሩ ታዳጊ ተማሪዎችን ትናንት ታህሳስ 07/2018 ዓ/ም በማፈን በውጊያ የማረኳቸው የፋኖ ምርኮኞች በሚል ሐሰተኛ መረጃ እያሰራጨ ይገኛል።

ድርጊቱ የተፈፀመው በራያ ቆቦ ወረዳ በአዲስ ቅኝና በአከባቢው ነው።

ይህ ነውረኛና ፀረ አማራ ኃይል፡ በአከባቢው ባሉ ጫማ ቤቶች <ጎንጎ ጫማ> በመዝረፍ፡ ያፈናቸው ንፁኋኖችን ጫማውን እንዲለብሱና የፋኖን ገፅታ እንዲላበሱ ካስደረገ በኋላ ምን ምን መናገር እንዳለባቸው በወረቀት ፅፎ ሰጥቶ የተንቀሳቃሽ ምስል ቀረፃ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል።

አፈናው የተፈፀመባቸው ወጣቶቹ፡ ኢንተርቪው ሲደረጉ "ከሕወሓት ሰራዊት ጋር ተቀላቅለው በአንድ ካምፕ እንደሚኖሩና በውጊያ ወቅት የሚመሩን የሕወሓት ሰዎች ናቸው" በሚል የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ፅፈው የሰጧቸውን ብቻ እንዲናገሩ ተደርገዋል።

ወጣቶቹ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩበት ባለሦስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪን "የፅንፈኛ ንብረት" በሚል በእሳት ሊያቃጥል መሆኑንም ነው በዛው በጠላት ቡድን ውስጥ የሚገኙ የውስጥ አርበኞች የጠቆሙት።

ከታፈኑት መካከል የቀን ስራ ሰርተው ለልጆቻቸው የእለት ምግብ ገዝተው የሚገቡ ወጣቶችና ጎልማሶች፣ ከትምህርት ቤት ውለው ሲመለሱ የነበሩ ተማሪዎች፡ ባጃጅ አሽከርክረው በሚያገኙት ገቢ ለአቅመደካማ ቤተሰቦቻቸው የእለት ቀለብ ገዝተው የሚገቡ፡ እንዲሁም ለሕመምተኛ ወላጆቻቸው መድኃኒት መግዣ ለማገኘት በጉልበት ስራ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች እንደሚገኙበት ነው ለማረጋገጥ የተቻለው።

ሁኔታው ያሳዘናቸው አንዳንድ የሰራዊቱ አባላት "ፋኖን ባልማረክንበት ሁኔታ ንፁኋንን በዚህ መልኩ እያፈንን ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ስናውል ሕዝቡ እውነታውን ስለሚያውቅ ይጠላናል" የሚል ሃሳብ እንዳነሱ የገለፁት ወታደራዊ ምንጮች፡ ነገር ግን የክፍለጦሩ አዛዥ "ሁሉም አማራ ፋኖ ነው ያገኛችሁትን ወጣትና ጎልማሳን ሁሉ እየደበደባችሁ አምጡልኝ" የሚል ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል።

(ምስል፦በስራ ገበታቸው ላይ እንዳሉ በአገዛዙ ወታደሮች የታፈኑት ወጣቶችና ጎልማሶች እንዲሁም ተሽከርካሪዎች)

@መረብ ሚዲያ
👍1
ዙ-23ቱ ተመቷል : 3 የተጠኑ ቦታዎች ላይ ከባድ የደፈጣ ጥቃት ተፈፅሟል!

በላስታ ግምባር በሦስት የተጠኑ ቦታዎች ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት 32 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ታወቀ!

በደፈጣ ጥቃቱ አንድ የጠላት ዙ23 መሣሪያ በፋኖ ድሽቃ ተመቶ ከጥቅም ውጭ የተደረገ ሲሆን፡ የተመታው ዙ23 በፋኖ እጅ እንዳይገባ ሌላ ተጨማሪ ዙ23 ከወደ ላሊበላ ተልኮ ሽፋን በመስጠት ማውጣቱን መረብ ሚዲያ ከፋኖ አባላቱና ከአከባቢዎ ነዋሪዎች ለማረጋገጥ ችሏል።

ደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመው የላሊበላ ከተማ አስተዳደር፣የላስታ ወረዳና የቡግና ወረዳ የካቢኔ አባላትን ከጋሸና ወደ ላሊበላ ከተማ አጅቦ ለማሳለፍ ጥቁር አስፓልቱን ወጥሮ በዘረጋው የአገዛዙ ኃይል ላይ ነው።

ካድሬዎቹ ካሰቡበት ሳይደርሱ ወደ ኋላ የፈረጠጡ ሲሆን፡ ካድሬዎቹን አጅቦ ሊያሳልፍ የነበረ ከ30 በላይ መከላከያ የሚሉት ተላላኪ ወታደርም ሕይወቱ አልፏል።
👍2
ሰበር ዜና!

የብልፅግና ሰራዊት 37 አስከሬኑን ጥሎ በሸሸበት ፍልሚያ የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት በመቶ የሚቆጠር ጠላት በመደምሰስ እና በማቁሰል እንዲሁም የቡድን እና በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

የምስራቅ አማራ ኮር አንዱ ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር እና የምስራቅ አማራ ኮር ሁለቱ ታጠቅ ክፍለ ጦር ዛሬ ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ መርሳ ከተማ ዙሪያ በጥምረት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ በመቶ የሚቆጠር ጠላት በመደምሰስና በማቁሰል እንዲሁም የቡድን እና በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ጠላት ከመርሳ ከተማ በምዕራብ በኩል ያሉ የፋኖ ቀጠናዎችን ለማጥቃትና ከቻለም ለመቆጣጠር አቅዶ በብዙ ግንባሮች ማለዳ በጀመረው ውጊያ የዋርካው ልጆች ባደረጉት ከባድ መከላከልና መልሶ ማጥቃት በመቶ የሚቆጠር ጠላት በመደምሰስና በማቁሰል ብሎም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ወደ መርሳ ከተማ የሸኙት ሲሆን 37 አስከሬኑንም ሳያነሳም እግሬ አውጭኝ ብሎ ለመሽሽ ተገዷል::

በተጋድሎው በምርኮ የተገኙ ድሎች፦

ምስራቅ አማራ ኮር 2 ታጠቅ ክፍለ ጦር

•1 ብሬን
•23 ክላሽ
•1393 የክላሽ ተተኳሽ
•700 የብሬን ተተኳሽ
•17 የደረት እና 8 የወገብ ትጥቅ
•12 ምርኮኛ (አራቱ የቆሰሉ)

ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር

•11 ክላሽ
•1800 የብሬን ተተኳሽ
•1500 የክላሽ ተተኳሽ
•7 የደረት እና 4 የወገብ ትጥቅ
•7 F1 ቦምብ
• 950 ስቃጥላ የታሸገ ምግብ

በአጠቃላይ ምኒልክ ዕዝ በተጋድሎው በሁለቱ ክፍለጦሮች አማካኝነት አንድ ብሬን 34 ክላሽ እንዲሁም ከ5300 በላይ ተተኳሽና የእጅ ቦምቦችን ጨምሮ በርካታ ንብረቶችን ያገኘ ሲሆን ከ950 በላይ ስቃጥላ የታሸገ ምግብም አግኝቷል::

በቀጣይ በተጋድሎው በምርኮ የተገኙ ድሎችን የቪዲዮ እና የምስል ማስረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም
1🙏1
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት ዘገባ

__፩

የበረሃዉ የሰደድ እሳት 66ኛ ክፍለጦር ከይላላ እሰከ ጃሂማላ ድረስ ባለ ቀጠና ከባድ ጥቃት አደረሰ።

በዛሬዉ እለት በቀን 08/04/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ ከይላላ እስከ ጃሂማላ ሰፊ ቀጠና በሸፈነዉ አዉደ ዉጊያ በጠላት ላይ ድልን መቀዳጀት ተችሏል።

በዚህም መሰረት ከ20 በላይ የጠላት ሀይል የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ተላላኪዎችን መደምሰስ ሲቻል በርካቶችን ደግሞ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል ሲል የ105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ር ህዝብ ግንኙነት ገልጿል።

___፪

የአረመኔው ጡት ቆራጩ የአገዛዙ ዙፋን አሰጠባቂ ሰራዊት ጋንታን መሪ ጨምሮ በርካታ አባላት የፋኖ ኃይሎችን እየተቀላቀሉ ነው።

በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ጋንታ መሪውን ጨምሮ በየጊዜው በርካታ የአረመኔው የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት የነበሩ ተቋሙን በመተው የፋኖ ኃይሎችን እየተቀላቀሉ ነው።

በዛሬው ዕለት ማለትም ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም በምስ/ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ መሽጎ ከሚገኘው ከአረመኔው ጨካኙ የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ የመከላከያ ተቋም ከ6ኛ ዕዝ 601ኛ ኮር 52ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት ጋንታ 3 መሪ የሆነው አስር አለቃ ካሳው አደባባይ ነጋ እና ግርማቸው ደሴ ተፈራ የተቋሙን አስከፊነትና አረመኔነት በመረዳት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ኛ ከፍለጦር አባል የሆነችውን ደባይ ጮቄ ሻለቃን ከነሙሉ ትጥቃቸው በክብር ተቀላቅለዋል።

በዚህ ወር ጠላት መሽጎበት ከሚገኘው ከ52ኛ ክ/ጦር ብቻ16 አባላት ፋኖን መቀላቀላቸው ይታወሳል!!!

___

በዳንግላ ከተማ የሚሊሻ ፋይናንስ ክፍል ኃላፊውን በ*ገ*ጀ*ራ ክላሽ ማርከው ፋኖን በይፋ ተቀላቀሉ!!

አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍና መከራ የተረዱ ሁለት የዳንግላ ወጣቶች የሚሊሻ ፋይናንስ ክፍል ኃላፊውን በገ*ጀ*ራ ክላሽ በመማረክ የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦርን በይፋ ተቀላቅለዋል።

ወጣቶቹ ጀጃው ደሳለኝ እና ዳዊት ጌቱ ይባላሉ። ወጣት ጀጃው ደሳለኝ ከአሁን በፊት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሁለት ዓመታት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በግዳጅ መቆየቱን ገልጿል።

በመከላከያ ቆይታውም በአማራ ተወላጆች ላይ ይደርስ የነበረውን ግፍና እና መከራ እንዳንገበገበው የገለፀ ሲሆን አጋጣሚዎችን በመጠቀም የመከላከያን ተቋም ለቆ እንደወጣ ተናግሯል።

ሌላኛው ወጣት ዳዊት ጌጡ ይባላል። በዳንግላ ከተማ የመንግስት ገቢ ግብር ሰብሳቢ እንደነበር ተናግሯል። አገዛዙ የከተማዋን ነዋሪዎች ለሚሊሻ ብር አውጡ በማለት ማህቀረሰቡን ሲያማርር ስራውን ለመልቀቅ እንደተገደደ እና የከተማ ውስጥ ቀኜ በመሆን ሲሰራ መቆየቱን ተናግሯል።

ሁለቱ የዳንግላ ወጣቶች በደንብ ከተመካከሩ በኋላ ጠ*ላ*ትን በገ*ጀ*ራ በመምታት ክላሽ በመማረክ ፋኖን ለመቀላቀል በቅተዋል።

የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ሰብሳቢና የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል አርበኛ ዘመነ ካሴ ለጀግኖቹ ትጥቅ እና ክላሽኮብ ሽልማት አበርክቷል ።

አርበኛውም "በፈፀማችሁት ጀብድ በጣም ኮርተናል ይህ ልብ የሚጠይቅ ድርጊት ነው " በማለት ለጀግኖቹ የማበረታቻ መልክት አስተላልፏል ። ጀግኖቹም በዚህ ታላቅ አርበኛ እውቅና እና ሽልማት መቀበላቸው ደስታ እንደፈጠረባቸው ተናግረው ወጣቱ የነእርሱን አርያ እንዲከተል መልክት አስተላልፈዋል ።

የአርበኛውን ጥሪ ተከትሎ በዳንግላ ከተማ በዚህ ሳምንት ብቻ ከ10 በላይ የሚሆኑ የጠላት ካምፕን ከድተው ፋኖን ተቀላቅለዋል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስአስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም
🙏21