ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት ዘገባ

___፩

የአረመኔው ሰራዊት አባላት ፋኖን በቡድን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል።

የአረመኔው ስርዓት የሚነዛው ተራ ፕሮፓጋንዳ ኃይሉን ከመበተን አልታደገውም በስሁት ምኞት 4 ክላሾች ጋር የሰላም ስምምነት አድርጊያለሁ ብሎ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛው የአረመኔው ውሸት ከሞት የማያድናቸው መሆኑን የተገነዘቡ አባላቱ ቀን በቀን እየከዱ ትግሉን እየተቀላቀሉ ሲሆን

ቻሌ ቤዛው፣ እናውጋው ላቀ የአድማ ብተና አባልና ማስረሻ ሰው አገኝ ፣ ይበልጣል ወርቄ የሚባሉ የአረመኔው ሰራዊት የ32ኛ ክ/ጦር አባላት ከደብረ ኤልያስ ከተማ በመውጣት 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ቀስተ ደመና ሻለቃን ሲቀላቀሉ አበበ ይበልጣል የተባለ የአድማ ብተና አባል ከደብረ ማርቆስ ከተማ በመውጣት ጅበላ ሙተራ ሻለቃን መቀላቀሉ ታውቋል።

በተመሳሳይ የመከላከያ ኦፕሬተሩ በአፋብኃ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦርን መቀላቀሉ ታውቋል።

ከ59ኛ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ ወጦ ፋኖን የተቀላቀለው ፍትሀለው ዳኛው የተባለው የመከላከያ ኦፕሬተሩ እንደተናገረው በአሁኑ ሰዓት ራሱን መከላከያ ብሎ የሚጠራው
አሸባሪ ሠራዊት ፋኖን የመቋቋም አቅም እንደሌለው ገልፆ፤ ሁሉም የሠራዊቱ አባላት እየተበተነ ወደ ፋኖ መቀላቀል እንደሚፈልግ አስረድቷል።

____፪

አውዳሚው ዐማራ ጠል ሥርዓት የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን አቋረጠ።

አውዳሚው ዐማራ ጠል ሥርዓት በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ የተጀመሩ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶችን ማቋረጡ ተረጋገጠ።
በፌደራል መንገዶች ባለሥልጣን ይሁንታ የተጀመረው የጅጋ_ቋሪት_ዓርብ_ገበያ_ግሽ_ዓባይ_ቲሊሊ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት በቋሪት ወረዳ የብልጽግና ሹማምንት አደናቃፊነት ተቋርጧል።

የውስጥ መረጃዎቻችን እንዳሳወቁት ከኾነ መንገዱ የተቋረጠው የቋሪት ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ፕሮጀክቱን ሊከፍል ከሚገባው የግዢ እና የሠራተኛ 2% ግብር በላይ ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ግብር በመጠየቁ ምክንያት ነው።

የጤና፣ የትምህርት፣ የግብርና፣ የማኅበራት፣ ወዘተ. ተቋማትን ዘርፎ እና አውድሞ እየጨረሰ ያለው የብልጽግና ሥርዓት አሁን ደግሞ የሕዝቡን ዐይን ይከፍታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት አቋርጧል።

የዐማራን ሕይወት እና የመልማት ተስፋ እየነጠቀ ያለው አረመኔው መዝባሪ የብልጽግና ሥርዓት ነባር የሕዝብ ተቋማትን ሲያወድም መቆየቱ ይታወሳል።

አውዳሚው ዐማራ ጠል ሥርዓት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ላይመለስ እስካልተነቀለ ድረስ ሕዝባችን የሚፈልገውን ልማት እና ሰላም ማየት እንደማይችል ተገንዝቦ ትግሉን በነበረ ግለቱ ለማስቀጠል ይበልጥ መበርታት እንደሚያስፈልግ የቋሪት ወረዳ ጊዜያዊ መንግሥት አሳስቧል።

አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም
🙏1
በምዕራብ ወሎ ግንባር ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ 17 የአድማ ብተና አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሣ ሻለቃ የፋኖ ኃይል ትናትና ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ ቡሶ ጊዮርጊስ የተባለ አካባቢ ላይ በጣለው ደፈጣ በኮሎኔል መብሬ አስማማው ዋሴ በሚመራው የአድማ ብተና ኃይል ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በዚህም 5 አድማ ብተናዎች ሲደመሰሱ 15 የሚሆኑት ቁስለኛ ተደርገዋል::

በተጋድሎው በድምሩ 2 ቲም የሚሆን የጠላት ኃይል ከጥቅም ውጭ ተደርጓል ሲል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ገልጿል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏2
በወሎ ግንባር የተለያዩ ቀጠናዎች በተደረገ ትንቅንቅ አኩሪ ድል ተመዘገበ::

*ደላንታ ዙሪያ* የዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ ሻለቃ አመራር ጥቃት ሲፈፀምበት በርካታ የፋሽስቱ እግረኛ ሰራዊቶች ደግሞ ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል!

አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር የጥላትን ሻለቃ አመራር ከባድ ቁስለኛ በማድረግና ከሶስት ጓድ በላይ እግረኛ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

ዚሃ ላይ በልጅ እያሱ ኮር አናብስቶች ሲጠዘጠዝ የዋለው የፋሽስቱ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ደላንታ ወረዳ ሲፈረጥጥ ፅናት ክፍለ ጦር መክት ሻለቃ 3ኛ ሻምበል ባደረጉት የደፈጣ ኦፕሬሽን በርካታ የጥላት ሰራዊት ዶግ አመድ ተደርገዋል።

አምባሰል ወረዳ ውስጥ ባትሪ በተባለ ቦታ ላይ በተደረገ ደፈጣ ሻለቃ መሪው ከባድ ቁስለኛ ሲሆን፣7(ሰባት) የጥላት ሰራዊትች ሲደመሰሱ አስራ አራቱ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል ሲል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ መረጃ አጋርቷል::

*"ሳይና በር"*
*እሸት ክፍለ ጦር* አዳራቸዉን ታላቅ ጀብድ ፈፅመው እጅን በአፍ የሚያስጭን ታሪክ ሰርተዉ ድል አስመዝግበዋል::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር እሸት ክፍለ ጦር ቃኝዎች አዳራቸዉን በተለምዶ "ሳይና በር" ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ መሽጎ የሚገኘዉን የአገዛዙ 65 ክፍለ ጦር በመቶ አለቃ አረጋ የምትመራዉ 4ኛ ሻለቃ ሰራዊት ላይ በጨለማ የማያዳግም እረምጃ ወስደዉበታል።

ንስሮቹ የእሸት ክፍለ ጦር ቃኝወችም ሰኞ ለማክሰኞ አዳር ከምሽቱ 3:00 እስከ ሌሊቱ 7:00 ባደረጉት ማጥቃትም ቁጥሩ ያልታወቀ የአገዛዙ ሰራዊት በቦንብ አረር እንደ በቀሎ እሸት ሲጠበስ ቀሪዉ ነፍሰ አዉጭኙን በየገደሉ እየተንከባለለ ማደሩ የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል::

*ደሴ ዙሪያ*
ምኒልክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ተከታታይ በተደረገ ተጋድሎ በርካታ ድሎችን አስመዘገቡ::

በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ደሴ ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ተከታታይ መደበኛ ውጊያ በማድረግ ጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

የተወርዋሪ ሻለቃዋ አናብስቶች ደሴ ዙሪያ ወረዳ ላይ ብዙ ቀበሌዎችን በመቆጣጠር የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት የህዝቡን አስተዳደራዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ሰፊ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ::

ሳምንቱን ያለማቋረጥ በተደረገው መደበኛ ትንቅንቅና ተጋድሎ በርካታ ድሎች የተመዘገቡ ሲሆን በትናትናው ዕለት ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ተለያየን እና ዚሃ ላይ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ተወርዋሪ ሻለቃዋ ከልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለጦር ጋር በመጣመር በርካታ የፋሽስቱ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ቀጠናውን በማስከበር ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
@አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
🙏1
የድል ዜና

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ከመልሶ ማደራጀት በኋላ በታቀደ ኦፖሬሽን ደብረወርቅ ከተማ ላይ ድል ተቀዳጅቷል ።

የአፋብኃ ቴድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር የጠላትን ካምፕ በጥልቀት በማጥናት በሌሊቱ በ5 የተለያዩ ቦታወች ውጊያው በመክፈት የ74ኛ ክ/ጦር ከ5ቱ ሬጅመንቶች የተውጣጣ ሃይል እና የክ/ጦሩ ቃኝ እና መሃንዲስ በውጊያው ተሳትፈውበታል።

ዉጊያውንም በወርቁ ማደያ፣ በፖሊስ ጣቢያው ፣ በጠዛ ወንዝ፣ በአዲሱ ገበያ እና በቴክኒክ በኩል ሙሉ ከበባ በማድረግ የደ/ወርቅ ፖሊስ ጣቢያን ጨምሮ ሙሉ ከተማዋን ለ6:00 ተቆጣጥሮ ቆይቷል ለህዝባችን ነፃነት በማለት ከተማውን ለቀን መውጣት ችለናል።

በዛሬው አውደ ውጊያ የተማረኩ

1/ ከ100 በላይ የግፍ እስረኞች አስለቅቋል
2/ 27 ክላሽንኮቭ ተማርኳል
3/ 1650 የክላሽ ተተኳሽ ተማርኳል
4/ 29 ቦንብ እስካሁን ምርኮ ተደርጓል።

5/ ከ50በላይ ፖሊስ፣ አድማበትን፣ ምኒሻ ተደምስሷል።
6/ በርካታ ምርኮኛም በእጅ ተይዟል።

ጀግናው 74ኛ ክፍለጦር ከመልሶ ማደራጀት በኋላ በተጠና መንገድ ያደረሰው ከባድ ጥቃት :-
1/  የአረመኔውን አገዛዝ የውሸት ትርክት የናደ
2/  የጠላትን ሰራዊት ስነ ልቦና ያራደ
3/ ፋኖ በማንኛውም ሰዓት በየትኛውም ከተማ ሙሉ ቁጥጥር ማድረግ የሚችል አቅም ያለው መሆኑን በተግባር ያረጋገጠበት ነው ። በሌላ አውደ ውጊያ ስናን አባጅሜ ሻለቃ በደፈጣ ጥቃት ጠላትን ደምስሷል።

በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በም/ጎጃም ዞን ስናን ረቡዕ ገበያ ከተማ መሽጎ በሚገኘው የአረመኔው ምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ዙፋን አስጠባቂ ጦር ላይ የደፈጣ ጥቃት በማድረግቁሳዊ እና ሰዋዊ ጉዳት አድርሰናል።

የደፈጣ ጥቃቱን የፈፀሙት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር አባል የሆነችው ጀብድ መስራት የማይሰለቻት የስናን አባጅሜ ሻለቃ ስትሆን በዚህ የማጥቃት ስራም በጠላት ላይ በህይወትም በቁስም ከፍተኛ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።ከጠላትም የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ከነተተኳሹ መማረክ የቻሉ ሲሆን  በወገን በኩል ያለምንም ጉዳት በመውጣት በሰላም ወደካንፓቸው መልሰዋል።

አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ

ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴድሮስ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የመቄት ወረዳ ጊዚያዊ ሕዝብ አስተዳደር ለወረዳና ንዑስ ወረዳ አመራሮች ስለ አማራ ሕዝብ ሁለተናዊ የህልውና ትግል አጫጭር ስለጠናዎችን ሰጠ።

ሕዝባችን የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የገጠመዉን ሁለተናዊ የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በሚያደረገው ብርቱ ተጋድሎ ሕዝቡ ማድረግ ያለበትን አበርክቶ በእጅጉ ከፍ ለማድረግና አስተዳደራዊ ስራዎችን ፣ የፍትሕ አገልግሎትን ለማሳለጥ ያግዝ ዘንድ ለወረዳና ለአራቱም(4) የንዑስ ወረዳ አመራሮች አጫጭር ስለጠናዎች ስጥቷል።

ስልጠናውን የሰጡት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ኢንጅነር አራጋው ያለው እና የዕዙ ፖለቲካ መኮነን ፋኖ መምህር ጋሻው ሙሉጌታ በጋራ በመሆን ሲሆን ስለ አማራ ሕዝብ ሁለተናዊ የህልውና አደጋ መነሻ ምክንያት ፣ አሁን ላይ ትግሉ ስለደረሰበት ደረጃ ፣ ስለ አማራ ሕዝብ የትግል መዳረሻ እንዲሁም ሕዝብን እንዴት ማደራጀት ፣ መምራት እና ማስተዳደር እንዳለባቸው ለሰልጣኞች በዝርዝር ቀርቧል።

ሰልጣኞች በበኩላቸው ስለተሰጠው ስልጠና በእጅጉ አመስገነው ከዚህ በላይ የትግሉ ደረጃ በሁሉም ዘርፍ ማደግ እንዳለበት እና የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የድል መዳረሻው ቅርብ እንዲሆን ድርጆቱ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል እንደ ድርጅት እንዲሁም ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ እንደ ዕዝ አበክሮ እንዲሰራ ምክር አዘል ሃሳቦችን ሰንዝረዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም
2🙏1
ተቋሙን እያፈራረስነው ነው 
ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም

ዲሽቃ ተኳሽ እና ምክትል ቲም መሪው ከእነሙሉ ትጥቃቸው መውኬ መንገሻ የተባለው  የመከላከያ ሻምበል መሪ ሉባ ገወርጊስ  የሚታጀብበትን ውሻ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅለዋል ።‼️
➦660 የክላሽ ተተኳሽ
➦ 6የእጅ ቦንብ
➦የወገብ ትጥቅ በመያዝ ከስርዓቱ በመውጣት ወደ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል

1ኛ) ፍቅሩ አበባው... ዲሽቃ ተኳሽ ከ602ኛ ኮር 1ኛ ሬጅመንት
2ኛ) ፉአድ ሚፍታሂ ... ምክትል ቲም መሪ ከ602ኛ ኮር 1ኛ ሬጅመንት
3ኛ) ሀሰን አብዲ... 602ኛኮር 1ኛሬጅመንት

አዲስትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስተስፋ
@ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር  ህዝብ ግንኙነት
🙏1