ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሻለቃዋ በጣለችው የደፈጣ ጥቃት የጠላት 104ተኛ አየር ወለድ ቃኝ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ‼️

ፀረ አማራው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ አየር ወለድ ኮማንዶ ከይፋትና ጥሙጋ አውራጃ ከደብረሲና ከተማ፣ ከደብረብርሃን እና ከጣርማበር በመነሳት ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ወደ መዘዞ ለዘረፋ የተንቀሳቀሰውን የጠላት 104ኛ አየርወለድ ኮማንዶ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደፅዮን ኮር ጀግናው የራንቦ ክፍለ ጦር መለያ (በልበላ) ላይ የክፍለጦሩ 2ተኛ ነበልባል ሻለቃ ደፈጣ በመያዝ በጠላት ላይ ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት የ104ኛ የአየር ወለድ ክፍለጦር ቃኝ አራዊት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።

በሌላኛው ግንባር ከመንዝና ግሼ አውራጃ ከሞላሌ ከተማ የተነሳው የአየር ወለድ ኮማንዶ በተመሳሳይ ወደ መለያና ወደ ባሽ ከተማ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ጀግኖቹ የራንቦ ክፍለጦር 3ኛ ማንበግር ሻለቃ ከጨፍጫፊው አራዊት ሰራዊት ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ እያደረገች ትገኛለች።

ወደ መዘዞ ለማቅናት በመጣው የወራሪው አየር ወለድ የጠላት ሀይልና ወደ ባሽ ለማቅናት በተንቀሳቀሰው የጠላት ሀይል ላይ በሁለቱም ግንባር የአርበኞች ፋኖ ጦር በውጊያው እየተሳተፈ ይገኛል። ውጊያው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እንደቀጠለ ነው።

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በየአውራጃው ጠንካራ ምት እያስተናገደ የሚገኘው አየር ወለድ፣ የስርዓቱ አሽከር አድማ ብተናና ሚሊሻ ስርዓቱን በመክዳት ፋኖን እየተቀላቀሉ ሲሆን ዛሬም መርሃቤቴ አውራጃ ከሚዳ አገዛዙን የከዱ የሚሊሻ አባላት ለአፄ አምደ ፅዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦር 3ኛ ቀስተ ንህብ ሻለቃ እጅ ተሰጥተዋል።

ክብር ለትግሉ ጀግኖች ሰማዕታት!!
ድል ለአማራ ፋኖ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
👍1
የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በጥምረት እያደረጉት ባለው ተጋድሎ ድል ማስመዝገባቸውን ቀጥለዋል::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ታህሳስ 6/2018 ዓ/ም በተለያዩ ወረዳዎች ላይ ፅናት ክፍለ ጦር እና ሰንጥቅ ክፍለ ጦሮች ከጥላት ጋር ባደረጉት አውደ ውጊያ የጥላትን ሰራዊት አከርካሪውን በመስበር ድላቸውን አጠናክረው አስቀጥለዋል::

ፅናት ክፍለ ጦር በተሪ ተራራዎች ላይ በደፈጣ የብርሀኑን ጁላ ሰራዊትን ዶግ አመድ ሲያደርጉት፤ በዳውንት ወረዳ ሰንጥቅ ክፍለ ጦር ጋግቢያ በረሀ ላይ ውሀ ውሀ ያሰኜ ጠንካራ ጥቃትን በጥላት ጥምር ሰራዊት ላይ ፈፅመዋል።

ሁለቱ ክፍለ ጦሮች በተለያዩ ቦታዎች በአንድ አስትንፋስ በጥላት ሰራዊት ላይ ባደረሱት የማጥቃት እርምጃ የአብይ አህመድን ድፋታን ከማተርቦሽ ባሻገር በርካታ ቁሳዊና አካላዊ ጉዳትን በማስተናገድ እፍረትንና ሽፈትን ተከናንቦ ወዴ መወሸቂያ ካፑ እንዲፈረጥጥ ማድረግ ተችሏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም
🙏1
ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር አምባሰል ዙሪያ ተጋድሎ በማድረግ ድል አደረገች::

ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 23 ክፍለ ጦር ታህሳስ 5/2018 ዓ/ም ማለትም በትናትናዉ እለት አምባሰል አባላ ተራራ ላይ ሰፍሮ ያለውን የጥላት ሃይል ድባቅ በመምታት ድል አደረገች።

ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለጦር ደቡብ ወሎ አምባሰል ጅጎዶ አባላ ተራራ ላይ ሰፍሮ የነበረዉ የብልፅግና አራዊት ሰራዊት ጋር ብርቱ ፍልሚያ እያደረጉአይቀጡ ቅጣት እየቀጡት ይገኛሉ።

አሁንም ዛሬ ታህሳስ 6/2018 ዓ/ም አድማሱን በማስፍት ዉጊያው እንደቀጠለ ሲሆን አባላ ተራራ እና ጊሸን ማርያም ገዳም መሽጎ የነበረዉ የአገዛዙ ሰራዊት ወደ ተለያየን እና ዚሀ ጥቁር አስፓልት ወርዶ እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ጊዜ 23ኛ ክፍለ ጦር መብረቃዊ ጥቃት በመክፈት ድባቅ እየመታችዉ ትገኛለች።

አናብስቶቹ 23 ክፍለ ጦሮች ከደሴ ደላንታ የሚወስደዉን ጥቁር አስፍልት በመዝጋት ዉጊያ እያደረገች ሲሆን አሁንም ከስከ ተሪ ያለዉን ቀጠና በመሸፈን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱን መዉጫ መግቢያ በማሳጣትና ሃይል እንዳይጨመረው በማድረግ ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሙት እና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተጎናፅፈዋል::

መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏1
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ  ከሰም 2ኛ ኮር አመራሮችና የኃይለ ማርያም ማሞ ክፍለ ጦር አመራሮች ፋኖ በሚያሥተዳድራቸው ቀበሌዎችና ግዛቶች ሰፊ የማህበረሰብ ውይይት ተካሄደ::

በይይቱ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኮር ምክትል አዛዥ ለአስተዳደር አርበኛ ፶ አለቃ ገረመው ታደሰ : የኃይለማርያም  ማሞ  ክ/ጦር ዋና ሰብሳቢ  አርበኛ ደመላሽ መንግስቴ : የሃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ሲቪል አስተዳደር ኃላፊ ኢንጂነር እደገው ሽፈራው እንዳሁም የሃይለማርያም  ማሞ አመራሮች ተገኝተው ከማህበረሰቡ  ጋር የተሳካ ውይይት  አካሒደዋል።

   በውይይቱም ከማህበረሰቡ ከይርማታገር ቀበሌ የተነሱ ጥያቄዎችና ከአመራሩ የተሰጠ የፖለቲካ ትጥቅ ትግል እንዲሁም የፋኖ የትግል መሥመር ለማህበረሰቡ በሰፊው የተገለፀ ሲሆን ከማህበረሰቡ የተነሱ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ግልጋሎት ጋር የማሟላት እንደ ጤና የግብርና አገልግሎት እና የአካባቢያዊ የፀጥታ ሁኔታ ፋኖ ከትግሉ ጎን ለጎን ለማህበረሰቡ ግልጋሎት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቀዋል::

በተመሳሳይ ጎጥ   ከጎርፎ ቀበሌ ሥር ባላች ጎጥ በአስቂኝ ጎጥ ማህበረሰቡን ማወያየት  የተቻለ ሲሆን የሃይለማርያም  ማሞ ክፍለ ጦር ግዥ አርበኛ ፋኖ ሰለሞን ታደሰ እና 
የኃይለማርያም  ማሞ ም/አዛዥ  ለአስተዳደር  ሞገስ ሸዋዬና ሌሎችም የኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት ተካሒዷል።

መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ ይታገሱ ጌታሁን ነው።
‎ " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
‎ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም
🙏1
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለጦር ለተከታታይ ሶስት ቀናት በወሰደ ውይይት የክፍለጦሩን አመራሮች የማተካካት ስራ ሰራ!!

የአማራን ሕዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ወደ አማራ ክልል የገባው የዐቢይ አሕመድ ዙፋን አስጠባቂ ሠራዊት አሁንም በአማራ ምድር እየተቀበረ ይገኛል። መውጣት እንደ መግባት ቀላል ያልሆነለት የኦሮሙማው ብልፅግና መራሽ የጥፋት ሠራዊት "ሰማዩም ምድሩም የእኔ ነው" በማለት ለአማራ ሕዝብ እልቂትን ደግሶ ከመጣ እነሆ 3 ዓመታትን አስቆጥሯል።

ሁኖም የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር በስሩ ያሉትን  ሻለቃዎች ከበፊቱ በጠነከረና በተሻለ መንገድ ትግሉን ከፋ በማድርግ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና  የአሳምነው ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሎጅስቲክ መምሪያ ኃላፊ ሻለቃ ሞገስ፣ የአሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩ፣ የአሳምን ዕዝ ምክትል የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ሀላፊ አርበኛ ተፈሪ ወንዶሰን እና የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የፖለቲካ እና የትጥቅ  ትግሉን በሚመጥን መልኩ የመዋቅር ሪፎርም  ለተከታታይ ሶስት ቀናት  ጥልቅ ግምገማ በማድርግ የተወሰኑ የክፍለጦሩ አመራሮችን በማንሳት እና የሚቀጥሉትን በነበሩበት እንዲቀጥሉ በማድረግ ሪፎርም ተሰርቷል።

በዚህም መሰርት
1. ዋና መሪ … አርበኛ አረጋ ሙሉነህ
2. ወታደራዊ አዛዥ… አርበኛ ጌታሁን ሻረው
3. ም/አዛዥ ለኦፕሬሽን… አርበኛ መላኩ ምኒል
4. ዘመቻ … አርበኛ ነጋ ንጉሴ
5. ም/አዛዥ ለሎጀስቲክ… አርበኛ ዘመድ ማንደፍሮ
6. ድርጅት ጉዳይ … አርበኛ እሸቱ በቀለ
7.ፕርሰኔል … አርበኛ ኤፍሬም እሸቴ እና
ሌሎች አመራሮች በነበሩበት እንዲቀጥሉ ተደርጓል።

በዚህ መሠረት የተመረጡ የክፍለ ጦር የሥራ ኃላፊዎችም በበላይ አመራሮችና በአባላት ፊት ቀርበው ቃለ መኃላ የፈፀሙ ሲሆን በአዲስ ወኔና መንፈስ ተሞልተው በታማኝነትና በቁርጠኝነት የኅልውና ትግሉን እንደሚያስቀጥሉ ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም አማራ ጠሉን የአብይ አህመድ አረመኔያዊ ስርዓትን በተባበረ ክንዳችን አብረን በአንድነት እንመክራለን፣ እንወያያለን፣ እንደራጃለን፣ እናቅዳለን፣ ጠላትን በገባበት ገብተን ድባቅ እንመታለን።

መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ ነው።

" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል"
‎  
   ታህሳስ 06/ዐ4/2018 ዓ.ም
1🙏1
ሰበረ ዜና!

የደጋው መብረቅ አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ አንድ ሙሉ ኦራል ሲደመሰስ በርካታ የብልፅግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተቀዳጁ::

አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለ ጦር እና ቀኝ አዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር ከትናንትናው የጋሸና ግሩም ኦፕሬሽን የቀጠለ ድል በጥላት ላይ ተቀዳጅተዋል::

ታህሳስ 6/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ እስከ አመሻሽ 11:00 ሰዓት እልክ አስጨራሽ ፍልሚያ የተደረገ ሲሆን፤ ሁለቱ ክፍለ ጦሮች በጥላት ሰራዊት ላይ በወሰዱት መራር እርምጃ አንድ ኦራል ሙሉ በሙለ ሲወድም፤በሰባት ፓትሮል ሙትና ቁስለኛ የብልፅግና ሰራዊትን ሲያመላልስ ውሏል።

በመቄት ወረዳና በዋድላ ወረዳ እስከ ጋሸና ከተማ እንደ ወጣት ነስር የሚምዘገዘጉት ሁለቱ ክፍለ ጦሮች ሰንሰለታዊ ትስስርን በመዘርጋት ወደ አርቢት ወቄጣ እና ዋድላ ኮን ወረዳዎች የብአዴን ሎሌ አመራሮችን ለማሳለፍ በዙ23 ታጅቦ የተንቀሳቀሰውን የጥላት ሰራዊት ከበባ በማድረግ በርካታ ሃይል በመደምሰስና በማቁሰል ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

ከሽመልስ አብደሳ ጉረና ተከፍቶ የተለቀቀው ስጋት ቀለቡ የግለሰቦች ተከፋይ ሰራዊት ለተከታታይ ቀናቶች በተወሰደባቸው እርምጃ ከስጋት ቀለብነት ወደ አሞራ ቀለብነት የመሸኘቱ ዘመቻ በኮሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ስለሆነም ብርቱ የፋኖዎችን ክንድ መቋቋም የተሳነው የብልፅግና ሰራዊት ወደየመጣበት ፈርጥጦ ሲሸሽ ሁለት የጋሸና ነዋሪ ንፁሀኖችን ጭምር በአሰቃቂ ሁኔታ እረሽኗል። የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ ሊያጠፋ የመጣው የአብይ ሰራዊት ይሄንን ተግባሩን በጋሸና አደባባይ ላይ በጠራራ ፀሀይ በንፁሃን አማራዎችን በመረሸን ዛሬም ፋሽስትነቱን አስመስክሯል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር
ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ታህሳስ /2018 ዓ.ም
👍1
የበላይ እዝ የተጠቃለሉ ግንባር የድል መረጃዎች

🔸በመተማ ወረዳ መሸሃ ቀበሌ የቁም ምሽግ ሰርቶ ህዝብ ሲያንገላታና ሲዘርፍ የሰነበተው የጠላት 78ኛ ክ/ጦር አካል ሬጅመንቶች ተደምስሰዋል።

ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም በልዩ ወታደራዊ ዕቅድ የማጥቃት ውጊያ የከፈተው ልማደኛው በላይ ዕዝ ደጃዝማች ፬ኛ ኮር ጎቤ ክ/ጦር ፣ አርበኞች ክ/ጦርና ረመጡ ደጀን ክ/ጦሮች የተወጣጣ ደምሳሽ ፈጣን ተወርዋሪ ኃይል ጠላት የመሸገባቸውን ከፍተኛ ቦታዎች በመዝለቅ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት ከባድ የጨበጣ ውጊያ በማድረግ ጠላትን የደመሰሰ ሲሆን ከመተማ ተነስቶ በነጋ ውኃ አድርጎ መሸሃ በመድረስ የውጊያ ድጋፍ ለማድረግ ከምዕራብ ወደ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የተንበሳቀሰው ጠላት በደጃዝማች 4ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦር ምት ደርሶበት ተልዕኮው እንዲከሽፍበት ተደርጓል።

ከምዕ/አርማጭሆ አብርሃ ጅራ በመነሳት መሸሃ ደርሶ ከድምሰሳ ሊታደግ የተንቀሳቀሰው የዓብይ ፋሽስት ሰራዊት ቀድሞ ስምሪት በተሰጣቸው በደጃዝማች 4ኛ ኮር ዘራይ ክ/ጦርና ተከዜ ክ/ጦሮቻችን መተላለፊያ መንገዱ በእሳት መታጠሩን በማረጋገጥ መሸሃ ለተከበበው ጠላት ሊደርስለት አልቻለም ሁሉም መንገዶች የገሞራ ባህር ተደርገዋል።

በቀበሮ ጉድጓድ ተወሽቆ የሰው ሀይሉንና የመሳሪያ ክምችቱን ተጠቅሞ እጅግ ከፍተኛ ቋሚ መከላከል ሲሞክር ቢውልም ልማደኞቹ በክላሽና በስናይፐር ግንባር እየነደሉ በጨበጣ በቦምብ እያቃጠሉ በሳንጃ እየተረተሩ የተማመነበትን ምሽግ በመስበር በወርቅ ቀለም የሚከተብ እጅግ አኩሪ የጀብዱ ታሪክ ፅፈዋል።

የጠላት 78ኛ ክ/ጦር ሁለት ሻለቀ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።

*253 የተደመሰሰ ጠላት
*58 የቆሰለ
*55 እጅ የሰጠ የተማረከ
*83 የተማረከ ክላሽ
* 02 የተማረከ ብሬን
* 1 ድሽቃ
*15 ሽህ ልዩ ልዩ ተተኳሽ ጥይት ተማርኳል።
በማጥራትና ማብቃት ተሞርዶ የተሰናዳው ደጃዝማች 4ኛ ኮር በመተማና አርማጭሆ የነበረውን ጠላት እያፈረሰው ይገኛል።

🔸 የሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
*መካነ እየሱስ
*አርብ ገቢያ
*ጉማራ እና
*አምበሳሜ ከተሞች
የጁላ ሰራዊት የአማራ መሬት ወደ መጣበት ላይመለስ መቀበሪያው እንዲሆን አይበገሬዎቹ በቀጠናው የመሸገውን ጠላት ሲፋለሙት ውለዋል።

🔸ጉና ክ/ጦር : ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር መካነ እየሱስ እና ጉማራ አምበሳሜ ከተማ የመሸገው ጠላት የተለያዩ ብርጌዶችን በማሰለፍ አጥቅተዋል።

አርብ ገቢያን ከተማ የመሸገውን አረመኔ ደግሞ ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ...
102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር የተወጣጡ ሻለቆች (አርብ ገቢያ) ሁለቱ ዕዞች በመጣመር ግራና ቀኝ ተጠምደው ጠላትን እንደ ቅጠል ያረገፉበት ግንባር ነበር።

ራስ አሞራው 3ኛ ኮር
🔸 ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም ዳባት ወረዳ ላይ አራቡር ሀሙሲት ሲንቀሳቀስ የነበረ የአረመኔው ዓብይ ሰራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ የ3ኛ ራስ አሞራው ኮር አያሌው ብሩ ክ/ጦር ሲሆን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ በነበረው ውጊያ በደረሰበት ምት ሙትና ቁስለኛ የሆነው የአገዛዙ ጦር ወደመጣበት ሸሽቷል።

🔸3ኛ ኮር ራስ ደጀንና ጭና ቁጥር ሁለት ክ/ጦሮች እንቃሽ አኖራ ጠላትን የተፋለሙት ሲሆን ቁጥሩ በውል ያልተረጋገጠ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።

በከባድ መሳሪያ በመተኮስ የንፁሃን አርሶ አደሮችን ሰብል በማውደም ጫና አድርጎ ሰርጎ ለመግባት ያደረገው ሙከራ በበላይ ዕዝ ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ራስ ደጀንና ጭና ቁጥር 2 ክ/ጦሮች ሳይሳካለት እግሬ አውጭኝ ብሎ ሸሽቶ እንዲመለስ ተገዷል።

ማጥራትና ማብቃት እንዲሁም ማጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም
5🙏1
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት ዘገባ

___፩

የአረመኔው ሰራዊት አባላት ፋኖን በቡድን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል።

የአረመኔው ስርዓት የሚነዛው ተራ ፕሮፓጋንዳ ኃይሉን ከመበተን አልታደገውም በስሁት ምኞት 4 ክላሾች ጋር የሰላም ስምምነት አድርጊያለሁ ብሎ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛው የአረመኔው ውሸት ከሞት የማያድናቸው መሆኑን የተገነዘቡ አባላቱ ቀን በቀን እየከዱ ትግሉን እየተቀላቀሉ ሲሆን

ቻሌ ቤዛው፣ እናውጋው ላቀ የአድማ ብተና አባልና ማስረሻ ሰው አገኝ ፣ ይበልጣል ወርቄ የሚባሉ የአረመኔው ሰራዊት የ32ኛ ክ/ጦር አባላት ከደብረ ኤልያስ ከተማ በመውጣት 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ቀስተ ደመና ሻለቃን ሲቀላቀሉ አበበ ይበልጣል የተባለ የአድማ ብተና አባል ከደብረ ማርቆስ ከተማ በመውጣት ጅበላ ሙተራ ሻለቃን መቀላቀሉ ታውቋል።

በተመሳሳይ የመከላከያ ኦፕሬተሩ በአፋብኃ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦርን መቀላቀሉ ታውቋል።

ከ59ኛ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ ወጦ ፋኖን የተቀላቀለው ፍትሀለው ዳኛው የተባለው የመከላከያ ኦፕሬተሩ እንደተናገረው በአሁኑ ሰዓት ራሱን መከላከያ ብሎ የሚጠራው
አሸባሪ ሠራዊት ፋኖን የመቋቋም አቅም እንደሌለው ገልፆ፤ ሁሉም የሠራዊቱ አባላት እየተበተነ ወደ ፋኖ መቀላቀል እንደሚፈልግ አስረድቷል።

____፪

አውዳሚው ዐማራ ጠል ሥርዓት የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን አቋረጠ።

አውዳሚው ዐማራ ጠል ሥርዓት በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ የተጀመሩ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶችን ማቋረጡ ተረጋገጠ።
በፌደራል መንገዶች ባለሥልጣን ይሁንታ የተጀመረው የጅጋ_ቋሪት_ዓርብ_ገበያ_ግሽ_ዓባይ_ቲሊሊ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት በቋሪት ወረዳ የብልጽግና ሹማምንት አደናቃፊነት ተቋርጧል።

የውስጥ መረጃዎቻችን እንዳሳወቁት ከኾነ መንገዱ የተቋረጠው የቋሪት ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ፕሮጀክቱን ሊከፍል ከሚገባው የግዢ እና የሠራተኛ 2% ግብር በላይ ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ግብር በመጠየቁ ምክንያት ነው።

የጤና፣ የትምህርት፣ የግብርና፣ የማኅበራት፣ ወዘተ. ተቋማትን ዘርፎ እና አውድሞ እየጨረሰ ያለው የብልጽግና ሥርዓት አሁን ደግሞ የሕዝቡን ዐይን ይከፍታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት አቋርጧል።

የዐማራን ሕይወት እና የመልማት ተስፋ እየነጠቀ ያለው አረመኔው መዝባሪ የብልጽግና ሥርዓት ነባር የሕዝብ ተቋማትን ሲያወድም መቆየቱ ይታወሳል።

አውዳሚው ዐማራ ጠል ሥርዓት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ላይመለስ እስካልተነቀለ ድረስ ሕዝባችን የሚፈልገውን ልማት እና ሰላም ማየት እንደማይችል ተገንዝቦ ትግሉን በነበረ ግለቱ ለማስቀጠል ይበልጥ መበርታት እንደሚያስፈልግ የቋሪት ወረዳ ጊዜያዊ መንግሥት አሳስቧል።

አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም
🙏1
በምዕራብ ወሎ ግንባር ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ 17 የአድማ ብተና አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሣ ሻለቃ የፋኖ ኃይል ትናትና ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ ቡሶ ጊዮርጊስ የተባለ አካባቢ ላይ በጣለው ደፈጣ በኮሎኔል መብሬ አስማማው ዋሴ በሚመራው የአድማ ብተና ኃይል ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በዚህም 5 አድማ ብተናዎች ሲደመሰሱ 15 የሚሆኑት ቁስለኛ ተደርገዋል::

በተጋድሎው በድምሩ 2 ቲም የሚሆን የጠላት ኃይል ከጥቅም ውጭ ተደርጓል ሲል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ገልጿል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏2