ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.19K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ኢንጅነር ደሳለኝ ክፍለ ጦር ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል ተጎናፀፉ::

በመካነሰላም ግንባር የ45ተኛ ክፍለ ጦር ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ መቻሉን የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር እንጂነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጌታሰው አስረስ ብርጌድ ቃል አቀባይ ገልጿል::

ትናንት ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት 6:00 ሰዓት በቀጠለው ተጋድሎ ሞት አይፈሬዎቹ የጌታሰው አስረስ ብርጌድ ፋኖዎች ድል ቀንቷቸዋል::


የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ተኛ ክፍለ ጦር ወታደሮች በ6 ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ጌታሰው አስረስ ብርጌድ ፋኖዎች የጦር ሰፈር ገብተው ከበባ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ደፈጣ ተጥሎባቸው ስለነበር የሞት ሸለቆ ውስጥ ገብተው በርካታ አባል ተነጥቀዋል::

ጠላት በ2 አቅጣጫ ተቆርጦ መግቢያ መውጫው ጠፍቶት የነፍስ አውጭኝ እሩጫ ላይ ባለበት ቅጽበት ጥቃት ተሰንዝሮበት አንድ ሲኖትራክ ሙሉ ወታደር ገደል መግባቱ ተረጋግጧል:: ሲኖትራኩ ከጥቃት ለማምለጥ ሲሮጥ ሰኞ ገበያ አቅራቢያ ሲደርስ በብሬን ጎማው ተመቶ በርካታ ወታደሮች አልቀዋል::

ቁስለኞችም ወደ መካነሰላም ጄኔራል ሆስፒታል ተወስደው ስለነበር ሆስፒታሉ ለተከታታይ 3 ቀናት ለሲቪል ታካሚዎች አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል ሲሉ የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል::

በኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ም/አዛዥ አርበኛ ዱቤ የተመራው ኦፕሬሽን የጠላት አከርካሪ የተሰበረበት ልዩ ኦፕሬሽን መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች የ45ተኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ ክፍል ሞርተር ጭምር በውጊያው ቢጠቀምም ከሽንፈት አለመዳኑን ነው የገለፁት::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም
3👍1
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት ዘገባ
_____፩

ከደጀን ከተማ አቅራቢያ 34 ክፍለጦር ድል ተቀዳጀ።

ከሌሊቱ 10:00 ስዓት ከደጀን ከተማ በመውጣት የአርሶ አደሮችን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ሲንቀሳቀስ በነበረ አንድ ፓትሮል ላይ የዛምበረሃ ሻለቃ በአደረገችው የደፈጣ ጥቃት ከ5 በላይ የጠላት ሰራዊት ሲገደሉ ከ15 በላይ የሚደርሱ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።

ያልተገመተውን የደፈጣ ጥቃት በፍጥነት ለማምለጥ በሚጣደፈው ፓትሮል ላይ ኢላማውን የጠበቀ ተኩስ የከፈተችው 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ዛምበረሃ ሻለቃ ሰራዊቱን ከነፓትሮሎ በመፈጥፈጥ ተሽከርካሪውን ከጥቅም ውጭ አድርገዋለች።

ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነስቶ ወደ ሊባኖስ ደምባ የተንቀሳሰው ጠላት በ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በተደረገ ታላቅ ትንቅንቅ የአረመኔውን ሰራዊት ድባቅ ተመቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአረመኔውን ስርዓት በታማኝነት ሲያገለግል የነበረው ዋና ሳጅን አስናቀ ማናየ በመጨረሻም በአረመኔው ሰራዊት ተገድሎ አስክሬኑ ደጀን ከተማ መንገድ ላይ ተጥሎ ተገኝቷል ። ከህዝብ ነፃነት ይልቅ ለአረመኔው ስርዓት በመታመን የራሱን ህዝብ ሲገድል የነበረው የደጀን ከተማ ፖሊስ ማንነቱን መለየት እስከሚከብድ ድረስ በጭካኔ አካሉ ተቆራርጦ መገደሉ ተረጋግጧል።
______፪

በትናንትናው ዕለት ከአነጋጉ 12:00 ጀምሮ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ የጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጥልቀት በፈፀመችው የማጥቃት ውጊያ የጠላትን ተደራራቢ 3 ምሽጎች በመስበር ጠላትን ለ7 ሰዓታት በመፋለም በየ ምሽጉ አጋድማዋለች።

ከደንባ ደብረ ማርቆስ ከተማ ማረሚያ ቤት ድረስ እያጣደፉ ጠላትን ያራገበችው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ 37 የጠላት ሰራዊት ጨምሮ ከዘራ ይዞ ሲያዋጋ የነበረውን ፻ አለቃ በስናይፐር ጭንቅላቱን በስተው ጥለውታል።

እንደ ንስር ታድሳ በቁጭት ጠላትን የተናነቀችው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ያለምንም መስዋትነት በጠላት ላይ ድል የተቀናጀች ሲሆን እስከ ምሽት 1:00 ስዓት በወሰደው አውደ ውጊያ አስክሬን ማንሳት ያልቻለው የአረመኔው ስርዓት ከደብረ ማርቆስ ከተማ መድፍ እየተኮሰ ይገኛል ።

በመልሶ ማደራጀት ትግበራው በ206ኛ ኮር እጁ የተቆረጠበት ጠላት ጅበላ ሙተራ ሻለቃን ሶስት ጊዜ ለማጥቃት የሞከረ ሲሆን በዛሬው ትንቅንቅ ጥቃቱን መቋቋም አቅቶት 4 ኪ.ሜ ወደ ኋላ ሲፈረጥጥ በርካታ አስክሬኖችን ማንሳት አልቻለም ።

______፫

የዳንግላ ቀኘ የከተማ አርበኞች ታአምር መስራታቸውን ቀጥለዋል።
ፈንታሁን ዮሐንስ የሚባል በከተማ የተደራጀ የቀኜ አባል ዛሬ በ03/04/2018ዓ.ም ዳንግላ ከተማ 02 ቀበሌ ላይ ደሴ አቤ የተባለን ቀንደኛ ባንዳ በቀን በጩቤ በመው,ጋት መሳሪያውን ቀምቶ አፋብሓ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር55ተኛ ክ/ጦር ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ሻለቃን ተቀላቅሏል ።
ጀግናው ወደ ጦሩ ሲደርስ በ105ተኛኮር ከፍተኛ አመራሮች እናበ55ተኛክ/ጦር አመራሮች እና በሻለቃው አባላት እና አመራሮች የጀግና አቀባበል ተደርጎለታል ።
ባንዳን የማፅዳት እንቅስቃሴያችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

__
ጠላት ከነሙሉ ትጥቁ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላትግን ወረዳ ቁይ ከተማ ላይ መሽጎ ከሚገኝበት ካንፕ በመክዳት 2 ሆነው ከነሙሉ ትጥቃቸው 24ኛ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል።

በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የአገዛዙ ክ/ጦር የአገዛዙ የጉጅሌው የዝርክርኩ ብርሀኑ ጁላ ና የአብይ አህመድ ዙፋን አሰጠባቂ ጦር እየፈረሰ የጀግኖች የፋኖ ኃይሎችን እየተቀላቀሉ ይገኛል።

ከደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ እንደ ቀንድ አውጣ ጭንቅላቱን በአንድ ኪ.ሜ ራዲየስ ቀብሮ መሽጎ ከሚገኝበት ቁይ ከተማ
1.ይስማው ማስሬ
2.ሙባረክ ሙህዬ
ከ6ኛ ዕዝ 601ኛ ኮር 52ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት ውስጥ ጡት ቆራጩን የአገዛዙን ሰራዊት በቃን በማለት 24ኛ ክ/ጦር የደባይ ጮቄን ሻለቃ በክብር ተቀላቅለዋል!!በ24ኛ ክፍለ ጦር ውስጥ ስቦ ማስከዳትን እንደ አንድ የትግል መርህ በመውድ ስናይፐር የቡድን መሳሪያን ጨምሮ በዚህ ወር ብቻ ከ14 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ወደ 24ኛ ክ/ጦር የፋኖ ኃይሎች መቀላቀላቸው የሚታወስ ነው!!!

አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም
🙏1
አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ታቦር ተራራ ብርጌድ ከ30 በላይ ጥምር የብልፅግና ጦር ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

ታቦር ተራራ ብርጌድ ሳይንት አጅባር ወረዳ አጅባር ከተማ ዙሪያ ህዳር 1/2018 ዓ,ም ንጋት ጀምሮ በክፍለጦሩ አዛዥ አርበኛ መኳንንት ንብረት (SKS) እየተመሩ ከባድ የሚባል ተጋድሎ በማድረግ በእዋ ግንባር አንድ ጓድ አድማ ብተና ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተጎናፅፈዋል::

በሌላ ግንባር አጅባር ከተማ ዙሪያ መንታ ዴፈር ማርያም አና አስላ በተባሉ ቦታዎች ከጧቱ 1:00 እስከ ምሽት 12:00 በተደረገ ተጋድሎ ከ22 በላይ ጠላት ሙትና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን አንድ ጠላት ይጠቀምበት የነበረ ተሽከርካሪ ወድሟል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም
1🙏1
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር አረርቲ ከተማ ዘልቆ በመግባት የተሳካ ኦፕሬሽ ፈፀሙ።

      ታህሳስ 03/04/2018 ዓ ም የነበልባል ክፍለ ጦር ተወርዋሪ ሻለቃ አረርቲ ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት ህዝብን ሲያሰቃይና ለአገዛዙ አራዊት ሰራዊት የመረጃ ምንጭ በመሆን ማህበረሰቡን የፋኖ ደጋፊ ነው በማለት ግፍ ሲያስፈፅም የነበረ ባንዳ ሚሊሻ ላይ በተጠና መንገድ እርምጃ ተወስዷል።

   ስሙም አለማየሁ የተባው ይህ ባንዳ በዛሬው ዕለት በአረርቲ ከተማ ኮንቦልሻ በር አካባቢ የለመደውን የባንዳነት ድርጊት ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የነብሮ ሻለቃ ሸማቂዎች ዘልቀው በመግባት ወደ ማይመለስበት አለም በመሸኘት የታጠቀውን ሙሉ ትጥቅ በመረከብ ለነበልባል ክፍለ ጦር ገቢ አድርገዋል።

   ወንበሬን ይጠብቁልኛል በማለት በብዙ ጥቅማጥቅም እና መደለያ የሰበሰባቸው ሆድ እንጂ ማሰቢያ ጭንቅላት የሌላቸው የሰፈር ወሮ በላ ስብስብ እንኳን ጌቶቻቸውን እራሳቸውንም መጠበቅ የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የሚያሳይ ነው።

@መረጃውን ያደረሰን የነበልባል ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።

" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም
2🙏1
ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ቆቦ ከተማ ባለ የብልፅግና ካድሬዎች ካምፕ ላይ ኢላማውን የጠበቀ እና የተሳካ የአር ፒ ጂ (ላውንቸር) ጥቃት በመፈፀም ድል ተጎናፀፈ::

ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ከአንድ ክፍለ ጦር አሃድ ላይ የተውጣጡ ቃኝዎችን በመጠቀም ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም ሌሊት 6:30 አካባቢ ቆቦ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እና አካባቢው ባለ ሁለት የብልፅግና ካድሬዎች ካምፕ ላይ በፈፀሙት የአር ፒ ጂ (ላውንቸር) ጥቃት የብልፅግና ካድሬዎች እና አጃቢዎቻቸው ላይ የሞት እንዲሁም ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ በማድረስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ባለፉት ሁለት አመታትና ከዛ በላይ ጊዜያቶች ወገናቸው የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት መፈፀማቸውን እንዲያቆሙ በተደጋጋሚ ተነግሯቸው አልሰማ ያሉ የብልፅግና ካድሬዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደ ያለ ሲሆን ይሄው ባንዳን የማፅዳት እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሎ የነ አርበኛ አለሙ ገብሩ አርበኛ ዋሴ ከበደ አርበኛ ፍሬው አለና እና ሌሎች ጀግኖች ልጆች ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም ሌሊት 6:30 አካባቢ የቆቦ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች የወረዳ ካቢኔዎችና አጃቢዎቻቸው ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስደዋል::

በዚህም ከንቲባውን ጨምሮ ለጊዜው በስም ያልተለዩ ባንዳዎች ቀላልና ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ ሌሎች በስም ያልተለዩ አራት ሞተዋል:: እስከ ስድስት የሚደርሱም ቀላልና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል:: የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰዎችም ሽንፈታቸውንና ውርደታቸውን ህዝብ እንዳያይባቸው በሚል የሞቱትን ባንዳዎች ደብቀው በሌሊት ወደ ጉባላፍቶ ወረዳ ሐራ ከተማ ወስደው እንደቀበሯቸው ለማወቅ ችለናል::

ይህ ድንቅ የሌሊት የከተማ ቀዶ ጥገና በታሰበው ልክ እንዲሳካና ግቡን እንዲመታ ከዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ቃኞች የሃውጃኖ ክፍለጦር ቃኞች እንዲሁም የዲቢና ወርቄ ቃኞች ቆቦ ከተማ ወሳኝ የሚባሉ ቦታዎች ላይ በመዝጋት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል::

ይህ ባንዳን የማፅዳት ተግባር በቀጣይም ለድል በቅተን የህዝባችንን ነፃነትና ህልውና እስከምናረጋግጥ ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ መምሪያ አሳውቋል::

በሌላ የምንሊክ እዝ መረጃ
ስድስት የብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ዙ23 ማራኪዎቹ ካላኮርማ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል::

የሚታገልበት አላማ የሌለውን የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት የማስኮብለሉ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጦር ስድስት አባላቶቹን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተረክበዋል::

በዚህም የኮበለሉት ሰራዊቶች 6 ክላሽ እና የወገብ ትጥቅ፣ ሰባት F1 ቦምብ፣ 1160 የክላሽ ተተኳሽ በመያዝ ካላኮርማ ክፍለ ጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን የክፈለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
🙏1
በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የተማረኩ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት በከፊል ያሉበት ነባራዊ ሁኔታ!

ፋኖ የማረካቸውን የጠላት ሰራዊት አለም አቀፍ ህግን ጠብቆ በዚህ መንገድ ቤት ባፈራው ተንከባክቦ አብሮ እያኖራቸው ይገኛል::

በአንፃሩ ግን የአብይ አህመዱ ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና አራዊት ሰራዊት አሰማርቶ በአማራ ህዝብ ላይ ምድር አንቀጥቅጥ ግፍ እየሰራ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ይገኛል!

ማስታወሻ፦ ለአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ምርኮኞችን እንዲረከበን ተደጋጋሚ ጥሪ ማድረጋችን የሚታወቅ ሲሆን ይህ ጥሪያችን ዛሬም እንደተጠበቀ መሆኑ እንዲታወቅልን እንፈልጋለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 4/ 2018 ዓ.ም
🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ከ16 በላይ የአገዛዙ ሰራዊትን ሲደመስስ 18 ያህሉን ማቁሰላቸው ታወቀ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦርና አሳምነው ኮር ሁለት ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ቃኝዎች በጥምረት በወሰዱት አፀፋዊ ምላሽ የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ተደርጓል።

ታህሳስ 03/2018 ዓ/ም መነሻውን ጋዝጊብላ ወረዳ አስከተማ ያደረገው የአገዛዙ ጥምር ጦር በሦስት አቅጣጫ ማለትም ከአዲ በር በምቆጎ አቅጣጫ፣ከአንሳይ ዋሻ በምዮ አቅጣጫ እንዲሁም በላይ በደጋው አድርጎ ወደ ቁልቋል አርባተንሳ አቅጣጫ አድርጎ በመምጣት የጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦር ፋኖዎችን አፍናለሁ ብሎ የመጣውን ጦር ሆን ተብሎ ወደ ውስጥ ሰርጎ እንዲገባ በማድረግና ስትራቴጂክ ቦታዎችን ይዞ ሰፊ ሰዓት በመስጠትና ቦታ በመያዝ እንደ እብድ ውሻ እየተክለፈለፈ የመጣውን የብልፅግና ጥምር ጦር የሚሉት ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ተመልሷል።

ከታህሳስ 02 እስከ 03/2018 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በመድፍ፣በሞርተርና በዲሽቃ የታገዘ ጥቃት የከፈተ ቢሆንም ተወርዋሪዎቹ የጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ልጆችና የወንድሞቹ ጋሻዎች ምስራቆቹ የሐውጃኖ ክፍለ ጦር ቃኝዎች በቅንጅት ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:30 ሰዓት ድረስ ጠላትን በሚገባው ቋንቋ አነጋግረው ከ16 በላይ ሙትና 18 ያህል ቁስለኛውን ይዞ ወደ ነበረበት ጉድጓድ መሸሸጊያው አስከተማ አስፈርጥጠው አስመልሰውታል።

በመጨረሻም የአማራና የአገው ህዝብ ህልው ማንነቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ በቁርጥ ቀን ልጆቹ በጋራና በቅንጅት በመመከትና በመደምሰስ ተከባብረንና ተቻችለን የምንኖርባትን የአባቶቻችን ኢትዮጵያን እንመሠርታለን ሲሉ የሐውጃኖ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራር አርበኛ ፋኖ ካሳ አበበ እና የጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ፋኖ ጣሰው አለልኝ በጋራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 04 / 2018 ዓ.ም
1🙏1
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኦነግ ታጣቂዎች ተገደሉ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ እና ሌሎች የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችና ወጣት የማህበራት የህዳር ፅዮን ማርያም ንግሰ በዓልን ለማክበር በሀገረ ስብከቱ ስር በምትገኘው
ከሻምቡ ከተማ በቅርብ ርቀት ወደ ሐረቶ ማርያም በመሄድ በዓሉን አክብረው ሲመለሱ እራሱን እነግ ሸኔ እያለ በሚጠራው ታጣቂ ኃይል ታግተው ነበር።

እገታው የተፈፀመባቸው ህዳር 21/2018 ዓ/ም አመሻሽ፡ ንግስ በዓሉን አክብረው የዞኑ መቀመጫ ወደ ሆነችው ሻምቡ ከተማ ሲመለሱ ነው።

ከታገቱት መካከል የወጣት ማህበራት አባላቱና ሌሎች የወረዳው ቤተክህነት ሰራተኞች ሲለቀቁ ነገ ግን የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ እና ሌላኛው የሀገረ ስብከቱ አመራር የሆኑት ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ ተገድለው አስከሬናቸው ለቤተሰቦቻቸው መላኩን የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።
👍1💔1
ሀሰተኛ መረጃ ነው!!

ሀጎስ የሚባል የፋኖ መሪ በጎንደር አይታወቅም!!

ባለፉት ዓመታት ልዩ ኃዬልን በማፍረስ ፋኖንና መላ አማራን ትጥቁን አይደለም ቀበቶውን እናስወልቀዋለን በሚል እብሪት አማራ ላይ ጦርነት የከፈተው ዓብይ አህመድ መራሹ ፋሽስት ቡድን ያልገመተውና ያልተነተነው አፀፋዊ ርምጃ ተወስዶበት እየፈራረሰ ይገኛል።

ነገሩ ወዲህ ነው በጠለምት፣ወልቃይት ጠገዴና አካባቢው በተለይም የተከዜ ተፋሰስ እና ዘሪማ ተፋሰስ የዓብይ ባለስልጣናትና የጦር መሪዎች ከነ ጌታቸው ረዳ ጋር የማዕድን ቁፋሮ ህገ ወጥ ኔትወርክ አላቸው።

ታድያ የማዕድን ብዝበዛው ዝም ብሎ የሚሰራ ሳይሆን የጥቅም ኔትወርኩ አካል የሆነ የታጠቀ ቅጥረኛ ጥበቃ ቡድን ያስፈልጋቸዋል።በጥንቃቄም ተመልምሎ ተዘጋጀ።

ከዚህ በፊት በማይጋባ፣በጠለምትና አካባቢው ንፁሃን የጨፈጨፈ፣ከተከዜ ወደ ሰሜን ከተከዜ ወደ ደቡብ እየተዛወረ ከአማራ ግዛት አለ ስትለው ከትግራይ ግዛት የሚሻገር በወንጀል ተጨማልቆ ተስፋ የቆረጠውን ሀጎስ የተባለ ግለሰብ ከግብራበሮቹ ጋር መልምለው ለወርቅ ማውጣት ተግባር የታጠቀ የጥበቃ የኃይል አማራጭ አድርገው በቅጥረኝነት በደሞዝና በጥቅማ ጥቅም ተሰማራ።(የማዕድን መንግስታዊ ዝርፊያ እስከ ኔትወርኩ በቀጣይ በሰፊው ይፋ የምናደርግ ሁኖ)...

ይህ ቡድን ከዚህ ቀደም በፈፀመው ወንጀል በፋኖ ሲታደን ትግራይ ሽሬ መሽጎ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በኦህዴድ ጀኔራሎች የዝርፊያ ኔትወርክ ከለላ እየተሰጠው ከወርቅ ማዕድን በዝርፊያና በቅጥረኝነት ተሰማርቶ ቆይቷል።

ጦርነትን በድል የመቋጨት ስንፈተ አቅም ያጠቃው ዓብይና ቡድኑ በቅርቡ በሀሰተኛ የሚዲያ ጫጫታ ብዥታ ለመፍጠር በማለም የወርቅ ዝርፊያ ተባባሪ የሆነውን ቡድን የፋኖ መዋቅር አካል የነበረ በማስመሰል ፕሮፖጋንዳ ለመስራት ተጋግጠዋል።
በየትኛው ድርጅት ?በየትኛው ክ/ጦር?በየትኛው ብርጌድ ተጠርንፈው እንደነበረ ያልተረጋገጠ መሆኑን መገንዘቡ ነገሩ የተለመደ የሴራ ቅጥፈት መሆኑን የሚያጋልጥ ሲሆን ባለፉት ዓመታት በፋኖ ትግል አሰላለፍ ምንም አበርክቶ እንዳልነበራቸው ትጥቃቸውና ጠቅላላ ቁመናቸው ልብ ብሎ ለተመለከተ አስቂኝና አሳቃቂ የከሸፈ ትወና ነበር።ተመሳስለው የሚሰራጩ የጠላት መረጃዎች ራሳችን እንጠብቅ እያልን ሀጎስ ምህረት የሚባል በፋኖ የሚፈለግ ወንጀለኛ እንጅ የፋኖ አመራር አልነበረም ኖሮም አያውቅም ።

እየለየን ዱባና ቅል ለየቅል!!

ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
👍3
ሰበር ዜና
የአርሶ አደር መሳሪያ እና ሀብት ለመዝረፍ የመጣው የአገዛዙ ቅልብ ሀይል በወገራ ወረዳ በጀጀህ ሀሙሲት ዙሪያ ተደመሰሰ።

  የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር  አሀድ የሆኑት የጎንደሬ በጋሻው እና ታድሎ ብርሃን ክፍለ ጦር የተወጣጡ አባላት  ከአካባቢው የአርሶ አደር አደረጃጀት  ጋር በጥምረት ተህሳስ 4/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት ድረስ ለመግደልና ለመዝረፍ ከመጣው የአገዛዙ ተላላኪ  ሀይል  ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ በማድረግ   ተደምሷል ።
ሰሞኑን ተስፋ የቆረጠው አገዛዙ  ሰራዊት  በወገራ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች  የአርሶ አደሩን ሀብትና ንብረት በመዝረፍና በማቃጠል ለማስፈራራት  በጀጀህ ሀሙሲት  ቀበሌ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ሞት ወይም ነፃነት ያሉት አርሶ አደሮች ከዳግማዊ ቴውድሮስ (5ተኛ)ኮር  አካል ከሆኑት ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር   ቴውድሮስ ብርጌድ እና ከታድሎ ብርሃን ክፍለ ጦር  ጣሰው ብርጌድ  አባላት ጋር በመቀናጀት ለዝርፊያ የመጣውን የአገዛዙን ሀይል  አስከሬን ሰብሶቦ በለቅሶ እንዲመለስ  አድርገውታል ።

በአውደ ውጊያው ከ17 በላይ የአገዛዙ ሀይል ሲደመሰስ ከ11 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ።
አርሶ አደሮቹ ከእንግዲህ በህልውናችንና በሀብታችን ለመጣብን ዘራፊ ስርዓት የምንበረከክበት ሞራል የለነም በማለት ነፃነት ትግሉ ቆርጠው ተነስተዋል።

        ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!!
የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )።
🙏21
#መረጃ

የተሳካ የደፈጣ ጥቃት ተፈፀመ።

ከጫሒትና ከደልጊ በሁለት  አቅጣጫ  የወጣ ጨፍጫፊ ቡድን አምስት ቁጥር ላይ በደፈጣ ቀምሶ ተመልሷል።
በምስራቅ ደንቢያ በሳንኪሳና ጅብጅባ መካከል በሚገኝ አምስት ቁጥር የሚባል ቦታ ላይ ሰፍሮ የነበረን የበጌ ምድር ክፍለጦርን ሐይል ለማፈን የተንቀሳቀሰ የጠላት ሐይል ባልጠበቀው ቦታና ጊዜ ተመቶ አስክሬን ታቅፎ ተመልሷል።

በክፍለጦሩ መረጃ ክፍል በኩል ቀድሞ በደረሰ መረጃ መሰረት እራሱን አመቻችቶ የቆየው የበጌምድር ክፍለጦር ናደው ብርጌድ ፋኖ ሐይል ካሰበበት ቦታ ሳይደር ከመኪናው እንዳለ በአየር ላይ ጨፍጭፎ መልሶታል።

በሁኔታው የተበሳጨው ጨፍጫፊ ቡድን መንገድ ላይ ያገኘውን ገበሬ ሁሉ እየደበደበ ተመልሷል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በትናትና ዕለት ጣቁሳ ወረዳ ድኩል አርባ አካባቢ በተመሳሳይ ደፈጣ ከፍተኛ ምት አስተናግዷል።

የበጌምድር ክፍለጦር አካል የሆነችው ጣና ብርጌድ በሰራችው ደፈጣ ከደልጊ ወደ ሻውራ የሚያቀናን ሐይል መንገድ ላይ በመደፈጥ መኪና ላይ እንዳለ በከፈቱበት ተኩስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ አስታቅፈው ልከውታል።

ድል ለአማራ   ህዝብ !
      ድል ለአማራ   ፋኖ!
 @ ጎ/ጠ/ግ/ዕዝ ግንኙነት መምሪያ!
🙏2