ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.19K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በወገራ ወረዳ የጠላት ኃይል ተመታ!!

በወገራ ሚጦ ቀበሌ የአገዛዙን ሰራዊት ስቦ በመደምሰስ ወታደራዊ ስልት አጭር ሰዓታት በፈጀ ብርቱ አውደ ውጊያ የብርሃኑ ጁላ ቅጥረኛ ሰራዊት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሶበታል።

የአፋብኃ በላይ ዕዝ 5ኛ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አጥናፉ ብርጌድ ስኬታማ የድምሰሳ ማጥቃት ያደረገች ሲሆን የጎንደሬ በጋሻው ቴዎድሮስ ብርጌድ ደግሞ በወገራ ወገራ ጀጀህና ኖራ ፃድቃ አካባቢ ጠላትን ሙትና ቁስለኛ ሁኖ ሽንፈት ተከናንቦ እንዲፈረጥጥ ማድረግ የተቻለበት ውጊያ ተደርጓል።

በደረሰበት ሽንፈት ሞራሉ የላሸቀው የጠላት ግሪሳ በሚሸሽበት አካባቢ 3 ንፁሃን አርሶ አደሮችን በሰብል መሰብሰብ ተግበር በተሰማሩበት በግፍ የረሸነ ሲሆን የንፁሃን መኖሪያ ቤቶችንና የቁም እንሰሳትን አውድሟል ገሏል። በማሰቃያ ኮድ የፋኖ ቤተሰብና ጎረቤት ናችሁ ያላቸውን ንፁሃን በማገት ፈርጥጦ ወደ አምባጊዮርጊስ ከተማ ሊሸሽ ችሏል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለጦር ስር በሚተደደረው ማጀቴ ከተማንን እና ጨፋ ከተማን የሚያገንኘው መንገድ በድጋሚ በአገዛዙ ወታደሮች ተዘጋ ።

በየቦታው የፋኖን ብትር መቋቋም ይቃተው የአገዛዙ ወታደር በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የሚተዳደረው የጨፋ ከተማ ህዝብ እና የማጀቴ ከተማ ህዝብ በግጭት ጠማቂው ሽመልስ ብዲሳ ሴራ ከዚህ በፊት በነበረው የብሄር ግጭት ተዘግቶ የነበረውን ከማጀቴ ከተማ ወደ ዋናው አስፋልት መውጫ መንገድ በሀገር ወግ እና ባህል መሰረት ከሁለቱም ብሄር በተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ቁጭ ብለው በመነጋገር ችግራቸውን በትላንት ዕለት በቀን 30/03/18 ፈተው መንገዱ ለአገልግሎት እንዲውል አስከፍተው ነበር ። ሆኖም የአብይ አህመድ አገዛዝ ወንበር አስጠባቂ መከላከያ የሁለቱን ብሄሮች ግጭት እንደ አንድ የፖለቲካ መሸቀጫ ስለሚጠቀምበት ዛሬ በአብይ አህመድ ጀነራሎች ጥርቅም ተደርጎ እንዲዘጋ በሚል ቀጭን ትዕዛዝ መንገዱ በዚህ መልኩ ተዘግቶ መኪኖቹ ሽንኩርት እንደጫኑ ወደ ማጀቴ እንዲመለሱ አድርጓል።

አማራውን አመት አምርቶ ለገብያ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደ ጤፍና ሽንኩርት የመሳሰሉ ሰብሎችን የሚያቀርብበት ወቅት በመሆኑ የአማራን ህዝብ ከመጥላቱም በላይ በኤፍራታ ግድም ወርዳ ውስጥ ከሆነችው ከታሪካዊቷ ከተማ ማጀቴ ተነስተው ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚወጡ ሽንኩርት የጫኑ መኪናዎች ላይ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ጨፋ (ጭሪ) በምትባል ከተማ ላይ አስቁሞ ሹፊሮችን በማስፍራራት በዚህ መልኩ እንዳይሄዱ ከማጉላላት አልፎ ተመልስው ወደ ማጀቴ እንዲመለሱ እያደረገ ይገኛል።

በመሆኑም ይህን አረመኔያዊ ሰራዊት ኃይል የአሳምነው አናብሶቶችኝ በትር መቋቋም ሲያቅተው በተደጋጋሚ በህዝባችን ላይ የክህደት ስራውን እየሰራ አማራ ጠሉ አብይና የእሱን ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት እና ተላላኪ ብአዴን ዛሬም እንደትናንቱ የክህደት ስራውን እየሰራም ከመህኑም ባሽገር ህዝባችን አላስፈላጊ እንግልት እያደረገ ይገኛል። ይህ የብልፅግና ስራት ከውልደቱ እስከ እድገቱ በአማራ ህዝብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረገ ያለውን አረመኔያዊ ተግባር በአማራ ፋኖዎች ግብዓተ መሬቱን የምንፈፅምበት ቀን ቅርብ ይሆናል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

መረጃውን የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ነው

ታህሳስ 01/04/2018 ዓ.ም
👍3
ዙ23 ማራኪዎቹ ካላኮርማ ክፍለጦር የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል ተጎናፀፉ::

ጠላትን በደፈጣ ጥቃት እና በሽምቅ የመምታቱ ረፍት የመንሳቱና የማማረሩ ብሎም የማፍረሱ ተጋድሎ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለጦር 1ኛ ሻለቃ ቃኝ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ውድመን የተባለ ቦታ በሁለት ኦራል እና በአንድ ፓትሮል ይንቀሳቀስ የነበረ ጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል:: 

ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከዘመቻ አባ ናደው ማግስት በርካታ እግረኛ ሰራዊት ወደ ቤተ-አማራ ያስገባ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህ አራዊት ሰራዊቱን ምኒልክ ዕዝ በየ ቀጠናው እንዲገባ ካደረገው በኋላ በሁሉም ቀጠና ያለ ሰራዊቱ በደፈጣ ጥቃት ጠላትን እየመታ እረፍት እየነሳና ተረጋግቶ እንዳይቀመጥ ብሎም እየተመረረ እንዲኮበልል በማድረግ ማጥቃት ቀርቶ ተረጋግቶ እንዳይከላከል አድርጎታል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም ምኒልክ ዕዝ በቂ ሁለንተናዊ ዝግጅት ማድረጉንና ለአዲስ ትልቅ ድል መዘጋጀቱን ያወቀው ጠላት ከተለያዩ አካባቢዎች መካናይዝድ እና አንዳንድ ንብረቶችን በማሸሽ ላይ ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 1/2018 ዓ.ም
1
አፋብኃ ምዕራብ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የምሽት ዜና

_____፩

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 7ኛ ቀኑን ያስቆጠረው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ሰራዊት በበረሃ አናብስቶቹ የፋኖ ብርቱ ክንድ ተቀጥቅጦ እንደ ቅጠል ረግፏል።

በዛሬዉ እለት ማለትም በቀን 01/04/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት ድረስ ቀኑን ሙሉ በተደረገ አዉደ ዉጊያ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር የጦር ጠበብቶቹ (መሀንዲሶቹ) በሰሩት ድንቅ ጥበብ የተሞላበት ኦፕሬሽን:- ደረቅ ወንዝ፣ ፍል ዉሃ፣ ብሔራዊ ከተባሉ ቦታዎች ላይ ድንቅ ተዓምር የተባለለት ፍልሚያ ተካሂዷል።

በዚህም አዉደ ዉጊያ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። ጠላት በዙ-23 እና መካናይዝድ የታገዘ ዉጊያ ቢያደርግም የፋኖን ከባድ ምት ግን መቋቋም አልቻለም።

_____፪

ከመሽ 11 የአገዛዙ ሀይል 201ኛ ኮርን ተቀላቀሉ ።

ስቦ ማስከዳት በጀግንነት ታጅቦ እንደቀጠለ ሲሆን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ : 54ኛ እንዲሁም 64ክ/ጦር ስቦ ማስከዳትን በአግባቡ አየተጠቀምንበት ነው::

1. ሙጫየ ገዛሃኝ ኮርያ ክላሽ ከጎንቻ ምኒሻ
2. ደርሶ ተሜ አብራራው = ከጎንቻ ምኒሻ
3 አየለ ጌቴ ኤስኬስ= ከጎንቻ ምኒሻ
4. ሙሉ ድረስ ኮርያ= ከጎንቻ ምኒሻ
5 መሌ ካሴ ኮፍ ክላሽ
6. በለጠ አታለል= ከመርጦ ለማርያም ከተማ ምኒሻ የነበረ /አንድ ፖሊስ በመግደል እና ሁለት ፖሊስ በማቁሰል በጀግንነት
7. ሹመት ወለላው በፈለገብርሃን የሚገኘው የ14ኛ ክ/ጦር አባል የነበረ ኮርያ ክላሽ እና 30 ጥይት በመያዝ
8. እሻለሁ ሱሌራ 602ኛ ኮር 25ክ/ጦር
9. ይበልጣል አለኸኝ
10. ፀሀው አለባቸው ጅምስሪ በመያዝ
11. መስፍኔ መለሰ 602ኛ ኮር 75ክ/ጦር መከላከያ አባል የነበሩ ወደአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ተቀላቅለዋል።

__

በደብረ ማርቆስ ከተማ ለስብሰባ የተገኙ 5(አምስት) ሴት ካድሬዎች በአረመኔው ሰራዊት መደፈራቸው ታውቋል።

በከፍተኛ ወታደራዊ ሽፋን እጀባ ተደርጎላቸው ለስብሰባ ደብረ ማርቆስ የተገኙ ከተለያዩ ከተሞች ከተገኙት አመራሮች መካከል አምስት የብልፅግና ፓርቲ ካድሪዎችን ጨምሮ በአረመኔው ሰራዊት መደፈራቸው ተረጋግጧል።

በደብረ ማርቆስ ከተማ በጭንቀት ተወጥረው የተገኙት ካድሬዎች በተለየ እጀባ እንዲንቀሳቀሱ የተደረገ ሲሆን ይከዳሉ ተብለው የተገመቱ ካድሬዎች ቀበሌ 10 በሚገኘው 15ኛ ሻለቃ ወታደራዊ ካምፕ እንዲተኙ የተደረጉ 3 ሴት ካድሬዎች በሌሊት በአረመኔው ሰራዊት መደፈራቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በማርክላንድ ሆቴል ከነበሩት ቅምጥል ካድሬዎች መካከል በአረመኔው ሰራዊት የጦር አመራሮች ጭምር ሁለት ሴት ካድሬዎች የተደፈሩ ሲሆን በደረሰባቸው ጥቃት ተሸማቀው ወደ ስብሰባ ቦታው እንዳልገቡ ተረጋግጧል።

የአረመኔውን ስርዓት ተነጥፈው በሚያገለግሉ ባንዳዎች ላይ አገዛዙ የሚያደርሰው ክህደት የተለመደ ቢሆንም ስርዓቱን በአመራርነት በሚያገለግሉ ሴት ካድሬዎች ላይ በደብረ ማርቆስ ከተማ የተፈፀመው አስገድዶ መድፈር የአረመኔው ሰራዊት ለአማራ ህዝብ ያለውን ጭካኔ የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም
2👍1