ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.19K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጉና ክ/ጦር
ገ/መሥቀል ብርጌድ
ጣይቱ ሻለቃ

ገና መጫወቻ ከተማ 02 ቦታዎች ላይ በወሰደው የታቀደ የደፈጣ ጥቃት ጠላት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደረሰበት።
🙏3
‎የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የከሰም 2ኛ ኮር አመራሮችን ይፋ አደረገ
‎=============
‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የከሰም ኮር 2ኛ ኮር ተሀድሶ በማካሄድ የኮሩ አመራሮችን ይፋ አድርጓል::

‎የከሰም 2ኛ ኮር ከተመሰረተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሀድሶ ያካሄደው ይህ ኮር የኮር አመራሮችን የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል ረዳት እና የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ ረ/ፕሮፌሰር ማርከው መንግስቴ በተገኙበት ይፋ አድርጓል::

‎በዚሁ መሰረት የከሰም 2ኛው ኮር አመራሮች

‎1ኛ. አርበኛ መቶ አለቃ ይላቅ ብርሃኔ ዋና መሪ
‎2ኛ .አርበኛ ደጉ ተሥፋዬ ድርጂት ጉዳዮች ኃላፊ
‎3ኛ. አርበኛ እንዳልካቸው ግርማ የአሥተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ
‎4ኛ.አርበኛ ሃምሳ አለቃ ጎሽመው ኃይሌ ወታደራዊ አዛዥ
‎5ኛ.አርበኛ እሸቱ ተ/ሚካኤል ም/አዛዥ ለኦፖሬሽናል።
‎6ኛ. አርበኛ ገረመው ታደሰ ም/አዛዥ ለአሥተዳደር
‎7ኛ.አርበኛ ፍቃደ ወርቁ ም/አዛዥ ለሎጀሥቲክ
‎8ኛ.አርበኛ ወርቁ ደርቤ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
‎9ኛ . አርበኛ ምክሩ ብዙነህ የፋይናንሥ ኃላፊ
‎10.አርበኛ አሥር አለቃ ሙልጌታ ፍቅሬ ዘመቻ መምሪያ
‎11ኛ.አርበኛ ወርቁ ሽመልሥ ምክትል ዘመቻ መምሪያ
‎12ኛ.አርበኛ   ይታገሥ ጌታሁን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
‎13ኛ.ትምህርትና ሥልጠና ኃላፊ----------
‎14ኛ. አርበኛ ሳሙኤል ፀጋዬ አደረጃጄት ዘርፍ ኃላፊ
‎15ኛ.አርበኛ ኃይሌ መሥፍን ኦዲት እና ቁጥጥር ኃላፊ
‎16ኛ.አርበኛ ይታገሥ ተሾመ ህግ ክፍል
‎17ኛ.አርበኛ ኮማንደር ነጋሽ አሠፋ ህግ ክፍል
‎18ኛ.አርበኛ ብርሃነ ቀፀላ ህግ ክፍል ኃላፊ
‎19ኛ.አርበኛ ሃምሳ አለቃ ሰለሞን አድነው ሥልጠናና ክህሎት ኃላፊ
‎20ኛ. አርበኛ እንግዳ በላይነህ ሃብት አሰባሳቢ ኃላፊ
‎21ኛ.አርበኛ አሸናፊ ብርሃኑ ፐረሶኔል
‎22ኛ አርበኛ ደመቀ ሥለሺ የኮር ፀኃፊ
‎23ኛ.አርበኛ ዘላለም ወርቅነህ ኦርዲናንሥ
‎24ኛ አርበኛ ክትነህ ሽፈራ ኦዲትና ቁጥጥር
‎25ኛ .አርበኛ አባይ ተሾመ ግዥ ክፍል
‎26ኛ.መረጃና ደህንነት ---------------
‎27ኛ አርበኛተፈሪ ሀይሉ የህዝብ ደህንነትና ፀጥታ ኃላፊ
‎28ኛ.አርበኛ አይናለም ዘረጋው ሴቶችና ማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ
‎29ኛ.አርበኛ ተመሥገን ባረጋ ህክምና ክፍል
‎30ኛ.አርበኛ አለማዬሁ ጌታነህ ኦዲትና ቁጥጥር
‎31ኛ.አርበኛ የሺጌታ ተገኝ ም/ ፋይናንሥ ኃላፊ
‎32ኛ. አርበኛ ሃምሳ አለቃ ሰይፈ ም/ሥለጠናና ክህሎት
‎33ኛ.አርበኛ ጋዜጠኛ አበባዬሁ ሰይፊ ሪፖርተር
‎34ኛ .አርበኛ ሰለሞን ገብሩ ባዶ አምሥት መሆናቸው ይፋ ተደርጓል።
‎እነዚህ አመራሮች የተሰጣቸውን ሀላፊነት ተቀብለው ወደ ስራ የገቡ መሆናቸውንም የአማራ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና 2ኛ  ከሰም ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሶናል::
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
2🙏2
በማጥራትና ማብቃት ህልውናችን እናረጋግጣለን!!

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በላይ ዘለቀ ዕዝ
የተሰጠ መግለጫ

ህልቆ መሳፍርት የሌለው የአማራ ህዝብ መከራና ስቃይ ያስቀጠለው ፋሽስታዊ የዓብይ አህመድ ቡድን በአማራ እና አማራነት ማንነት ላይ ያነጣጠረ ህልውናውን ፈፅሞ የማክሰም መዋቅር መር ሁለንተናዊ ጥቃት ለመከላከልና አደጋውን ለመቀልበስ ባለፉት ጥቂት ዓመታት አማራ ራሱን ለማትረፍ በነቂስ በፋኖ አደረጃጀ ተደራጅቶ ኢ ተገማች በሆነ ሁኔታ አስከፊውን አገዛዙ እያፈራረሰው ይገኛል።የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በላይ ዘለቀ ዕዝ በሁሉም የሰሜን አማራ ቀጠና (ጎንደር) ዞኖች በመንቀሳቀስ አያሌ ስኬታማ ወታደራዊ፣ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ተግባራትን በመከወን ሰፊ ህዝብ እያስተዳደረና በርካታ ጠንካራ ሰራዊት እየመራም ይገኛል።ቢሆንም ትግሉን ከመታገል በላይ ትግሉን መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ ውስጠ አደረጃጀት የማጥራትና የማብቃት ተቋማዊ ንቅናቄ በማድረግ በአጭር ጊዜ ለ ድል የሚያበቃ የአመለካከት፣የተግባር እና የአሰራር ጥልቅ መግራት ተግባር መከወን አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል።ትግላችን በአንድ ወጥ ድርጅት እየተመራ አስከፊውን አገዛዝ በመገርሰስ ለተሟላ አማራው የተሟላ ድል እንዲጎናፀፍ የምናደርገውን በጎ ሚና ከማስቀጠል መሳለመሳ ከድህረ ዓብይ አህመድ መገርሰስ በኃላ የምትፀናውን ሀገር የሚበይንና የሚረከብ ሁለንተናዊ ዝግጅት አስፈላጊ መሆኑን በማመን ብርቱ ስራዎችን በአፋጣኝ መከወን እንዳለብን እንረዳለን።

በእሳት ተፈትነው ያልተበገሩ ነባር አርበኞችና ወጣት አብዮተኛ ሙህራን መሪዎችን እንዲሁም ጀግና ሰራዊታችን ለተሻለ ድል ለአመርቂ ተቋማዊ አስተሳሰብና አሰራር ማብቃት የነገ ሳይሆን የዛሬ የግብር ግዴታችን መሆኑን የዕዙ ስራ አስፈፃሚ አመራር በመገምገም ግልፅ ስምሪት ተሰቷል።
በደም ዋጋ የጠራውን ዓላማና ግባችን ለመበረዝ ፣ለመጥለፍና ለማዳከም ከተቻለም በራሳቸው ፍላጎት ስር ለማስገበር የሚታትሩ የትግሉ ቁማርተኞችን እየመከትን መቆየታችን ታውቆና ታምኖ ያደረ ሀቅ ነው።

ላለፉት 20 ቀናት በተመረጡ ኮሮችና ክ/ጦሮች እንዲሁም ወረዳዎች የማጥራትና ማብቃት የሙከራ ስራዎቻችን ጀምረን የቆየን ቢሆንም በሁሉም ቀጠና በተሟላ ሁኔታ ንቅናቄውን ማስጀመር ታምኖበታል።

ስለሆነም ከዛሬ ህዳር 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ በማጥራትና በማብቃት ህልውናችን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል ለሚቀጥሉት 45 ቀናት ውስጠ አደረጃጀታዊ ንቅናቄ በይፋ መጀመራችንን እያበሰርን በማጥራትና ማብቃት ተልዕኳችን የሚከተሉት አንኳር ተግባሮች የሚከወኑ መሆኑን በመረዳት ህዝባችንና ሰራዊታችን ያለሰለሰ ድጋፍ እንዲያደርግልን ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን።

፩ኛ...በተዘጋጁ ሰነዶች ስልጠና መስጠት ማለትም ህዝብ አስተዳደርን ፣ ፋይናንስ አሰባሰብና አስተዳደርን፣የሰራዊት ማደራጃ የተሻሻለ መመሪያ ፣ሀገር ዓቀፍና ዓ/ዓቀፍ የተመረጡ ጉዳዮች ዙሪያ ፣ እና ሌሎች መሰል የተሰናዱ ሰነዶችን መነሻ በማድረግ ለመዋቅራችን አመራርና ዓባላት ስልጠና ይሰጣል፣
የአስተሳሰብና የተግባር እንዲሁም የአሰራር ወጥነት በማንበር ለተሻለ ግዳጅ ብቁና ንቁ ቁመና እንፈጥራለን፣

፪ኛ...በውስጥ መረጃ እና ማስረጃ ተመርኩዘን የጀመርነውን ሰርጎ ገብ ጥገኞች የማጥራትና የመግራት ተግባሮች በሁሉም ኮሮቻችን እስከ ታችኛው ሰራዊት ይፈፀማሉ።እንደ ህዝብ ህልው ሁኖ ለመትረፍ በምናደርገው መራር ትግል ተጠልለው መስዕዋትነታችን ለግል ማንኛውም ጉዳያቸው በማዋል ተመሳስለው የተሰማሩ ወንበዴዎችን ፣ ከአረመኔው ጠላት ትስስር ያላቸው የዘመናችን የዲናር ተመንዛሪዎች መርምረን እንለያለን መንጥረን እናጠራለን።

፫ኛ... ከውስጥም ሆነ ከውጭ ትግሉን ለማዳከም የተዘረጉ ኔትወርኮች ይበጣጠሳሉ።አፍራሽ ደላሎችና ቅጥረኛ ሳይበረኞች የካብ ውስጥ እባቦች የትግሉ ዕዳና ፍዳ ሁነው እንዳይቀጥሉ በጥልቅ ማጥራትና ማብቃት ንቅናቄያችን ቅድሚያ ትኩረት ከተሰጡት ተግባሮቻችን መካከል ይጠቀሳሉ።

፬ኛ...በቅርቡ ማስረሻ ሰጤ የተባለ ከሌላ ድርጅት የተባረረ ግለሰብ ከአገዛዙ ጋር ሁኖ በበርካታ ሚዲያ ፋኖን ወክሎ ተደራድሮ የሰላም ስምምነት እንደተፈራረመ የፋኖ ሰራዊት በየ አካባቢው ትግሉን ትቶ እንዲገባ እየተሰራጨ ያለው ወሬ ድርጅታችን እና ሰራዊታችን እንዲሁም እዛችን የማይመለከት የግለሰቡና የአጭበርባሪው አረመኒያዊ አገዛዝ የመጨረሻ የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ መሆኑን ተገንዝበን ተልዕኳችን ላይ ብቻ ትኩረት እንድናደርግ መልዕክት እናስተላልፋለን።

፭ኛ...ጨፍጫፊው ስርዓት በንፁሃን ወገናችን ላይ የህይወት እና የአካል ጉዳት ከማድረስ በተጨማሪ የፋኖ ዘመድ ወይም ወዳጅ አላችሁ በማለት ንፁሃን ወገናችን ያለ ጥፋት በማሰርና በማፈን እያንገላታና ሰብዓዊ መደራደሪያ እያደረገ ወንጀል እየፈፀመ ይገኛል።ንብረት ማውደም፣መዝረፍ እንዲሁም ከቀዬ የማፈናቀል የሰብዓዊ ወንጀሎችን እየፈፀመ የሚገኝ መሆኑ ታውቆ የሚመለከታችሁ ሀገር በቀልም ሆነ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችና ማህበራት ግለሰቦችና ሚዲያዎች ጉዳዩን በአንክሮ ትከታተሉ ዘንድ እያስጨበጥን ለሚፈፀሙ ኢ ሰብዓዊ ወንጀሎች ተመጣጣኝ አፀፋዊ ርምጃ እየወሰድን እንደቆየንና አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እናሳውቃለን።

ውድ ወገናችን የሰራዊታችን ዓባላትና አመራሮች እንዲሁም የትግሉ አጋሮች በሙሉ "ጥልቅ ማጥራትና ማብቃት ንቅናቄ "በሚል መሪ ቃል የጀመርነው ንቅናቄ
ከማብቃት በላይ ፤ከማታገልም በላይ፤ ከመታገልም በላይ፤ትግላችን የምንጠብቅበት የእርምት ክዋኔዎችን ገቢራዊ የምናደርግበት በመሆኑ ከወዲሁ ተረድታችሁና አስረድታችሁ ከጎናችን እንድትቆሙ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ዘመቻ ጥልቅ ማጥራትና ማብቃት ተጠናክሮ ይቀጥላል!!


ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

ህዳር 30/2018 ዓ.ም

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጎንደር /አማራ/ኢትዮጵያ
4👍1
የአርበኛው ዘመነ ካሴ ወቅታዊ መልዕክት

    ህዳር 30/2018 ዓ.ም

ዛሬም ለዐላማው የተሶረፈ ልብ፥ ዛሬም የፀና መንፈስ፥ ዛሬም የጋለ ወኔ፥ ዛሬም የእርስበርስ መከባበርና አንድነት ያስፈልገናል።ድልና "ተአምር" የሚመነጩት እነዚህ ውብ "ተራሮች" ስር ነውና።

ተወረናል፥ የዘር ፍጅት እየተፈፀመብን ነው። ነገር ግን መንፈሳችንና ልባችን አሁንም በእጃችን ነው። መንፈሳችንና ልባችን በእጃችን እስካለ ድረስ በአብይ አረመኔ የጉብል ሰራዊት የተወረረው መሬታችንና ህዝባችን ነፃ ወጦ ህልውናው ይረጋገጣል።ይህም በመሆኑ በጦር ሜዳ፥ በፖለቲካውና በዲፕሎማሲው ግንባር በየቀኑ ጠላታችንን እያሼነፍን ነው።
ልቡና መንፈሱን ራሱ ጋር አቅፎ የያዘ ህዝብ የጊዜ ጉዳይ እንጅ  ድሉ ከታዛው ነው፥ የሚፈልገው ነገር ሁሉ በአጠገቡ ነው።

ከራእያችን የሚቀዳው ለሰው ልጆች ሁሉ የሚበጅ በጎው ምኞታችን በጥረታችን ይሳካል። በጎ ምኞቶች ዳር ይደርሱ ዘንድ የሚንከባከብ አንዳች አይነት የራሳቼው እግዜር አላቼው።
አለም ጠንካሮች፥ ደፋሮች፥ ፅኑዎችና ለአላማቼው የመነኑ ብቻ ዋኝተው የሚሻገሩት ውቅያኖስ ነውና በእያለንበት እንበርታ።ሁልጊዜም የሚከተሉት የአቢዮታችንና የህልውናችን አራት ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርገን እንስራ!!

1)ጉልበት-ክላሽ(የማያቋርጥ የሃይል ግንባታ፥ እስከምፃት ማንቃት ፥ማደራጄት፥ ማሰልጠንና ማስታጠቅ!)

2)እውቀት(በየደቂቃው እውቀትን መሻት፥ አዲስ ነገር ለመገንዘብ መጓጓት፥ የማያቋርጥና የማይረካ የእውቀት ረሃብ!አለምን በልኩ መረዳት!ተፈጥሮን መረዳት!
ትሁት ስልጣኔ መገንባት!በሰዎች ለሰዎች የሆነ ጨዋና ትሁት ስልጣኔ መገንባት።
ሃፍረትና ይሉኝታ የሚያውቅ ማህበረሰብ መፍጠር።ሃፍረትና ይሉኝታ የለሽ ሃገር የዞምቢ ምድር ነው የሚሆነው።ሃፍረትና ይሉኝታ የአንድ ማህበረሰብ የክብር ልብሶችና ጌጦች ናቸው።ብቻም ሳይሆን ድፍን ህዝብን ለቁሙ ከመጥፋት የሚታደጉ የአለም መድሃኒቶች ናቼው።)

3)ጠንካራ ኢኮኖሚ(ጠንካራ የኢኮኖሚ ፓወር ሳንገነባ ጠንካራ የፖለቲካ ፓወር ልንገነባ አንችልም። ገንዘባችን ስለት /ዊያፓናዝ/ ማድረግ አለብን።)

4)ፈሪሀ-እግዚአብሄር(ሞራል፣ሰው መሆን፣ሰውን ማክበር፥ ሰውን መውደድ፥ ለሰው ልጆች ሃሴት መኖር-መንፈሳዊ ልእልና)

[ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም]
እስከ ምፃት አማራ!
ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
        ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

         አርበኛ ዘመነ ካሴ
      ህዳር 30/2018 ዓ.ም
🙏5
ምኒልክ ዕዝ ድርጅታዊ አመታዊ ስብሰባ አካሄደ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የኮርና የድርጅት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ለአንድ ሳምንት ተከታታይ ቀናቶችን የወሰደ አመታዊ ድርጅታዊ ከፍተኛ ስብሰባ አካሄደ::

ምኒልክ ዕዝ በስብሰባው የህልውና ትግሉ ለድልና ነፃነት ይበቃ ዘንድ የአመራር ሽግሽግ ያደረገ እና አዳዲስ ሹመቶችንም የሰጠ ሲሆን አስተዳደራዊ እርምጃዎችንም በመውሰድ ስብሰባውን ቋጭቷል::

ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ምኒልክ አመታዊ ድርጅታዊ ስብሰባውን እንዳያካሂድ በከፍተኛ የእግረኛ ጦርና መካናይዝድ እንዲሁም በአየር ሃይል በጄትና በድሮን ታግዞ ብርቱ ጥረት ያደረገ ቢሆንም ንስሮቹ በታላቅ ፅናትና ቁርጠኝነት ስብሰባውን አካሂደዋል::

በስብሰባው ምኒልክ ዕዝ አመቱን በጥልቀት በመገምገም ያሉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን በመለየት ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)ን ጨምሮ የተገኙ በርካታ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን በጥንካሬ እንዲሁም ከድሎቹ ባሻገር ያሉ ክፍተቶችን በደካማ ጎን በመገምገም ለቀጣይ ዝለቂ ድል በቂ ሁለንተናዊ ዝግጅት በማድረግ ስብሰባውን ባመርቂ ሁኔታ ደምድሟል::

ምኒልክ ዕዝ በአመታዊ ድርጅታዊ ስብሰባው የአመራር ሽግሽግ ማድረግ እና አዳዲስ ሹመቶችን የሰጠ ሲሆን ጠቅላላ የአመራር መዋቅሩም የሚከተለውን ይመስላል፦

1. ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን - ፀጋዬ ብርሃኑ
1.1. አምስት አባላት
2. ወታደራዊ ፍርድ ቤት - አርበኛ ተመስገን አማረ 
2.1. ሦስት አባላት
3. የህግና ሥነ ሥርዓት ጉባኤ -
3.1. ሦስት አባላት
4. ሰብሳቢ - ዋርካው ምሬ ወዳጆ
5. ወታደራዊ አማካሪ - ኮሎኔል ሞገስ
ዘገዬ
5.1 አርበኛ አለሙ ገላው- ምክትል ወታደራዊ አማካሪ
 
 
ወታደራዊ መዋቅር
1. ምክ/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ - አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ
1.1. ጸሐፊና ወታደራዊ ቃል አቀባይ - አርበኛ ትዝታ በዛብህ
2. ምክ/ወታደራዊ አዛዥ - አርበኛ ወንድሙ ማሩ
3. ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጅ - ኮሎኔል ዓባይ ባየው
4. ዘመቻ - አርበኛ በለጠ ሸጋው
4.1. ምክ/ዘመቻ ኃላፊ (ዘመቻ ስምሪት) - ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ
4.2. መረጃ፣ ካርታና ምህንድስና -
5. ወታደራዊ አስተዳደር - ሻለቃ ያረጋል አሰፋ
5.1. ምክ/ወታደራዊ አስተዳደር - 10 አለቃ ሙላቱ ሰጠ
5.2. ምክ/ለሰው ሃብት አስተዳደር - 50 ዓለቃ ሲሳይ ገላነው
5.2.1. ምክ/የሰው ሃብት አስተዳደር -
5.3. ምክ/ለጤና ጉዳይ - ዶ/ር አቡበክር ሰይድ
6. ሎጂስቲክስ መምሪያ - ሻለቃ ኢሳያስ መለሰ (ውክልና)
6.1. ምክትል ለስንቅና ትጥቅ ስርጭት - ሞላ ሰማው
6.2. ምክትል ለኦርዲናንስ ክፍል - ሻለቃ ኢሳያስ መለሰ
6.3. ምክትል ለትራንስፖርት ስምሪት -
7. ወታደራዊ ሥልጠና መምሪያ - መቶ ዓለቃ ዮሴፍ አስማረ
7.1. ምክትል የሥልጠና መምሪያ - አርበኛ ጌታቸው ሲሳይ
7.2. የሥልጠና ማዕከላት ኃላፊ -
8. ወታደራዊ መረጃና መገናኛ መምሪያ -
8.1. ምክ/ወታደራዊ መረጃ መምሪያ -
8.2. ምክ/ወታደራዊ መገናኛ መምሪያ -
9. ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን (ስርጸት) መምሪያ- ሻለቃ ደምሌ ጣፋጭ
9.1. ምክ/ኢንዶክትሪኔሽን - ሻለቃ ወንድሙ
9.2. የኪነትና መዝናኛ ክፍል - መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌ
9.3 ምክ/ኪነትና መዝናኛ ክፍል አርቲስት ፋኖ ኪሮስ ደርቤ
10. ልዩ ዘመቻ መምሪያ - አርበኛ ተሾመ ፈንታዬ
10.1. የልዩ ዘመቻ ወታደራዊ አዛዥ - አርበኛ ሐብታሙ ደምሴ
10.2. የልዩ ዘመቻ ፖለቲካ መምሪያ - አርበኛ አባተ ካሳነው
 
 
ፖለቲካዊ መዋቅር
1. ምክ/ሰብሳቢና የፖለቲካ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ - አርበኛ ሔኖክ አዲሴ
2. የፖለቲካ ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ - አርበኛ ሞገስ አብራራው
3. የጥናትና ስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ - አርበኛ አራጋው ያለው
3.1. ምክ/የስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ - አርበኛ ገ/መስቀል
4. የውጭ ጉዳይ መምሪያ - አርበኛ አብዮት ይመር
4.1. ምክ/የውጭ ጉዳይ መምሪያ - አርበኛ አብደላ አያሌው
5. የአደረጃጀት መምሪያ - አርበኛ አበበ ቀዬ
5.1. ምክ/የአደረጃጀት መምሪያ - አርበኛ አሰፋ መሰለ
6. የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ - አርበኛ አበበ ፈንታው
6.1. ምክ/የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ - አርበኛ ኑረዲን አበበ
6.2. ሚዲያና ኮሚኒኬሸን ኃላፊ -
7. የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ - ፋኒት ዚነት አደም
7.1. ምክ/የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ - ፋኒት አበበች ሲሳይ
8. ትምህርትና ስልጠና መምሪያ - አርበኛ ፍቅሩ ፈንታው
8.1. ምክ/ትምህርትና ስልጠና መምሪያ - አርበኛ ደርብ ተፈራ
9. አጋርነትና ትብብር መምሪያ - አርበኛ ብርሃን አራጌ
9.1. ምክ/አጋርነትና ትብብር መምሪያ -
10. ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ - አርበኛ አለምነው መብራቱ
10.1. ምክ/ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ - አርበኛ መኩሪያ ፈንታው
 
 
የድርጅት ጽ/ቤት መዋቅር
1. የጽ/ቤት ኃላፊ - አርበኛ ደስታው
1.1. ምክ/የጽ/ቤት ኃላፊ - አርበኛ አለባቸው ቀስቅሴ
2. የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ - አርበኛ ንጉስ አዳነ
2.1. ምክ/የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ - አርበኛ አማረ አያሌው
2.2. አካውንታንት - አርበኛ ልዑልሰገድ
2.3. ግዥ ክፍል - አርበኛ ዮሐንስ መኮንን
2.4. ገንዘብ ያዥ - አርበኛ አዲሴ ጌታሁን
3. የሐብት አፈላላጊ መምሪያ - አርበኛ ምንሊክ ፋንታሁን
3.1. ምክ/የሐብት አፈላላጊ መምሪያ - አርበኛ ዘሪሁን ደምሴ
4. የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ - አርበኛ እስራኤል እሸቴ
4.1. ምክ/የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ - አርበኛ ስንታየሁ ተስፋው
5. የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ መምሪያ - አርበኛ አክሎግ ቢራራ
5.1. ምክ/የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ መምሪያ -

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
5🙏1
ትኩረት የሚሻዉ የሀይማኖት አባቶች ጉዳይ!!!