ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በማህበረሰቡ ላይ አሰቃቂ ዝርፊያ እየተፈፀመ ነው።
ሕዝብ አላማ ያደረገ ጥቃት እና ዝርፊያ በጎጃም ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ነው።

_____፩ ሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ
የአገዛዙ ሥርዓት ጠባቂ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ዘረፈ።

በጦር ሜዳ ሽንፈት የተከናነበው የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ በትናንትናው ዕለት ኅዳር 26/2018 ዓ/ም ሜጫ ወረዳ አማሪት ፣አውጣ(አንድነት) ፣ ጠለታ ፣ እድገት ፣ ተክለድብ ፣ ቆለላና እንጉቲ ቀበሌዎች በጋራ በመሆን ለመስኖ ልማት የሚውል የማዳበሪያና ለተለያዩ ወጭዎች አርሶ አደሮቹ በማህበር ያሰባሰቡትን ብር 2 ሚሊዮን በላይ ደብድበውና አሰቃይተው በኃይል ገንዘቡን በመቀማት በልማት ስራ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጆችን በማገት ገንዘብ አምጡ በማለት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል።

በተጨማሪም ባችማ : አንድነት(ኢፊሳ ሀሙሲት)ና አብሮ መኖር ቀበሌ የሚገኙ አርሶ አደሩን ቤቱ ውስጥ ድንገት ከበባ በማድረግ ፋኖ የት ነው የሚገኘው መሳሪያም አላችሁ አምጡ በማለት በጥይት ደብድበውና አቁስለው ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት አድርሰው 5 ክላሽንኮቭ ጠመንጃና 13 የቃታ መሳሪያዎችን በመውሰድ 2 የግለሰብ ሱቆችንና መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።
ሱቅ የተቃጠለባቸው ግለሰቦች:-
1ኛ, አታላይ አለሙ
2ኛ, ዘመነ ታምሩ ሱቅ የተቃጠለበትና 25ሺህ ብር የተዘረፋ ናቸው።
መሳሳሪያ አምጡ ተብለው በጥይት የተደበደቡ ቁስለኞች በማህበረሰቡና በቀጠናው የሚገኝ የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር 2ኛ ሻለቃ ጦር ቀጠናውን ከጠላት በመታደግ ወደ ህክምና በማድረስ ክትትል እያደረጉ ይገኛል።

በመሆኑም ማህበረሰቡ ራሱንና የጦር መሳሪያውን ከወራሪው ኃይል በመጠበቅ በየቀጠናው ወደ ሚገኙ የፋኖ ካምፖች በመቅረብ የስርዓቱን ስልጣን ጠባቂ ኃይል በጋራ እንድንታገለው ክፍለ ጦራችን ጥሪ ያቀርባል።

_____፪ ሰሜን ጎጃም ጎንጅ ቆለላ ወረዳ

ራሱን "የሀገር መከላከያ" ብሎ የሚጠራው ተቅበዝባዡ የዐቢይ አሕመድ አረ መኔ አ ራ ጅ ሠራዊት ዛሬም የንፁሃንን የመኖሪያ ቤት አቃጥሏል።
አፋብኃ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር አንደኛ ሻለቃ ለተለያየ ግዳጅ አካባቢውን መልቀቋን የሰማው የዐቢይ አሕመድ አረ መኔ አ ራ ጅ ሠራዊት ዛሬም በጎንጂ ቆለላ ወረዳ ዜጋንሳ ቀበሌ አትርሴ በልስቲ የሚባል የአንድ ንፁሃን የመኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ አቋጥሏል።
በዛሬው ዕለት በአገ ዛ ዙ ሙሉ የቤት ዕቃ፣ ወደ ቤት የተሰበሰበ እኽል፣ የቤተሰቡ አልባሳት፣ ወ.ዘ.ተ. እንደያዘ የወደመው የአቶ አትርሴ በልስቲ ቤት በብር ሲገመት ወደ ሰባት መቶ ሺህ ብር ሊያወጣ እንደሚችል ይገመታል።
#የተወሰነውን_የወደመ_ንብረት_እና_የሀብት_ግምት_ለማሳየት ያክል፦
#72_ዚንጎ ቆርቆሮ ቤት ግድግዳውን ሳይጨምር 250,000 ብር
አንድ ትልቅ በሬ 85,000 ብር
አንድ አህያ 10,000 ብር
15 ኩንታል ጤፍ 150,000 ብር
5 ኩንታል በቆሎ 20 ሺ ብር
2.5 ኩንታል ስንዴ 15 ሺህ ብር
1.5 ኩንታል ባቄላ 14 ሺህ ብር
1.5 ኩንታል አተር 16 ሺህ ብር
የቤት እቃ እና የቤተሰብ አልባሳት 120,000 ብር
#ጠቅላላ_ድምር 680 ሺህ ብር ተገምቷል።

በተጨማሪም በአካባቢው በሻይ ቡና አገልግሎት በሚተዳደሩ የንፁሃን ቤት በመግባት የሥራ ቁሳቁሳቸውን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን ተጎጂዎቹ አሳውቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው ዐፋብኀ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ጊዜያዊ መንግሥት አስተዳደር የጎንጂ ቆለላ ዋና አስተዳዳሪ ፋኖ አረጋ አበረ በተፈጠረው ችግር አዝነው፤ የአካባቢው ማኅበረሰብ የመረዳዳትና የአብሮነት እሴቱን በማጎልበት ተጎጂዎችን እንዲያቋቁሙ አስተያየት ሰጥተዋል።
በመኾኑም በአቅራቢያው የነበሩ ውስን የ33ኛ ክ/ጦር አባላት በጎንጂ ቆለላ ከተማ በከፈቱት ድንገተኛ ጥቃት ለዝርፊያ ወደ ዜጋንሳ የወጣው አውዳሚ ሠራዊት ተመልሶ ወደ ጉድጓዱ ገብቷል።

____፫ ምስራቅ ጎጃም እነብሴ ሳርምድር ወረዳ


በምስራቅ ጎጃም እነብሴ ሳርምድር ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች የፋኖን ብትር መቋቋም ሲያቅተው የብልፅግናው ሰራዊት ዝርፊያወችን እየፈፀመ ይገኛል።

በሰኞ ገበያ እና ድቦ ቀጠና በንፁሃን ላይ ዝርፊያውን እና የድብደባ ወንጀሉን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ከኛ ጋር ሆናችሁ ፋኖን አልወጋችሁም በማለት፦
➦ከ51 በላይ የግል ባለመሳራያ በሬውን ሸጦ የገዛውን መሳሪያ ቀምቷል
➦ ተዘግተው የነበሩ 13 ባለሆቴሎችና መኖሪያ ቤቶች ቁልፍ በመስበር ውስጥ ያሉ ሃብቶችን ሙሉ በሙሉ ተዘርፏል።
➦5 ባለትዳር ሴቶች ባሎቻችሁን አምጡ ተብለው ታስረዋል፤ 4ሰወች አሰቃቂ ድብደባ ተፈፅሞባቸው ሜዳ ተጥለዋል
➦ 28 የአካባቢወ ንፁሃን ከባድ ድብደባ ተፈፅሞባቸው በእስር ላይ ሲሆኑ ሁሉንም እስረኞ ፋኖ ተኩስ ከከፈቱ ቀድመው እንዲመቱ ለማድረግ እና ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት በማድረስ አረመኔያዊ ድርጊት በመፈፀም ላይ ይገኛል

ወንጀል የተፈፀመባቸው ግለሰቦችም
ከሰኞ ገበያ ቀጠና
በሬ ሸጠው የገዙት መሳሪያ የተወረሰባቸው
1. ደርብ ጌታቸዉ ክላሽ፣
2. አብይ ዮሀንስ ክላሽ፣
3. ይርሴ ክላሽ እና
በስም ያልተጣሩ 31 እንዲሁም 5 ሴቶች ፤
ድቦ ቀጠና=
1. መርሻ አክሊሉ ክላሽ፣
2. ሀብቴ ክላሽ፣
3. ወጣ ገበየ ክላሽ፣
4. መልካ ዘለቀ ክላሽ፣
5. መሰሉ ይመኑ ክላሽ፣
6. ልየው በላቸው ክላሽ፣
7 ሽፈራው ሙንየ እና ሌሎች 10
በድምሩ 51 መሳሪያ በመዝረፍ

3, የወደመ እና የተዘረፈ ሆቴል እና መኖሪያ ቤት
1. ትርንጎስጦታው =ሆቴል
2. ነበረ መለሰ =ሆቴል
3. አዳሙ አለባቸው =ሆቴል
4. ደርብ አድማሴ =ሆቴል
5. አኔ ይበልጣል =መኖሪያ ቤት
6. ተሜ ይልማ =መኖሪያ ቤት
7. የሹ ፈንታ=መኖሪያ ቤት
8. ጌትነት ይሜ=መኖሪያ ቤት
9. ሻምበል ይሜ=መኖሪያ ቤት
10. ምኒሊክ ይሜ =መኖሪያ ቤት
11. ተስፋው ታደሰ =መኖሪያ ቤት
12. ሙንየ ምሬ =መኖሪያ ቤት
13. መልካሙ አብየ =መኖሪያ ቤት
የተሰበረ ስለጠፋባቸው = ውለታው ወሌ፣

ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመባቸው ሜዳ የተጣሉ
1. ጌታቸው ደርብ፣
2. ደርብ አድማሴ፣
3. በላይነህ ተረፈ
4. መርሻ መሰሉ

ድብደባ ተፈፀሞባቸው የታሰሩ ወጣቶች
1. ማማር መንጋው፣
2. ሙሉቀን ዳምጤ፣
3. ውቡ ተምትም፣ በስም ያልተጠቀሱ ከ25 በላይ ንፁሃን ወጣቶች ናቸው።


___፬ በሰሜን ጎጃም አዴት ወረዳ

የአማራን ህዝብ ያነጣጠረ ጥቃት በኦህዴድ መራሹ አገዛዝ ሰራዊት በህዝቡ ላይ የንብረት ጉዳት አደረሰ።
ሰሞኑን ከሌላ ተጨማሪ ኃይል በማምጣት በይልማና ዴንሳ ወረዳ ላይ ኀይሉን በብዛት በማሰማራት የተንቀሳቀሰ ሲሆን ከተንቀሳቀሰባቸው ቦታዎች መካከል ዴንሳ ባታ፣ድንጅ፣አግታ፣አንጋርና ተጨማሪ ቀበሌዎች ላይ በህዝቡ ላይ ከባድ ውንብድናና ዝርፊያ ፈፅሟል።
1👎1
1.የይግረመው ሽቴን 1 በሬ
2.የጋሻው ሞገስ 1ላምና 1በሬ
3.የአንተነህ ምስጋናው 1በሬና 1 ጊደር
4.ክንዴነህ አድማሱ 1ላምና 2 ጊደር
5.አወቀ በላይነህ 2በሬ
6.ቀኔ ጌቴ 1ላምና 1በሬ
7.መልካሙ አገኘሁ 1ላም
8.አዱኛ ይታይህ 1ላም
9.የ፲አለቃ ንብረት 5በግ
10.የጎላ ንግሩ 4በግ
11.የመልካሙ አገኘሁን 3በግ በአጠቃላይ 14ላምና በሬ እና 12 በግ እያረደ ሲበላ ሰንብቶ የተረፈውን ወደ ከተማ ጭኖ ሲወስድ
➯ በተጨማሪም
12.4ሞተርና 3ባጃጅ በማቃጠል፤በአቶ ጌታሲል ቢሻው የልብስ ስፌት ቤት ውስጥ ያለን ጣቃ ከልብስ መስፊያ መኪና ጋር ሙሉ ጣቃውን በመዝረፍ የውንብድና ተግባር ሲፈፅም፦
13.የአቶ ድረስ ሞላን የወፍጮና የባጃጅ ቅያር እቃዎችን ሙሉ ለሙሉ ዘርፎ ወስዷል።
14.የደረጀ አያሌውን ቤት ሙሉ በሙሉ ዘርፈው ቀሪውን አውድመዋል።
➯ አሁንም ከዚያው ዴንሳ ባታ ቀበሌ ላይ አርሶ አደር ቤት በመግባት እህልን በመመረዝ ቤተሰቡ በሙሉ እንዲያልቅ ለማድረግ ሚሊሻው መርዝ መጨመሩን የተመለከተ ግለሰብ ለባለቤቶች በሰጠው ጥቆማ የተመረዘውን እህል በማስወገድ ቤተሰቡን መታደግ ተችሏል።

አግታ ቀበሌ ላይ
በመግለጫችን የወረዳው የብል*ፅግና አመራር ሁሉንም አዋሳኝ የገጠር ከተሞች የትራንስፖርት እገዳ አድርጎ ወላድ እናቶችና ፅኑ ህሙማን ተጨማሪ ህክምና ሳያገኙ ለህልፈተ ህይዎት መዳረጋቸውን ገልፀናል። እናም ይህ አገዛዝ ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ ባለባጃጆችን
1. ወጣት አከለን በመግደል ባጃጁን አቃጥለዋል።
2.የወጣት ያየው ሰው አታላይን ፋራ ሞተር
3.የወጣት ጌታየ ሙሉን ፍራ ሞተር
4.የወጣት አበባው ጌትነት ባጃጅ
5.የወጣት አንሙት ገብሬ ባጃጅ
ሲወስዱ
6.የወጣት ወለላው ደሴን ሞተር በማቃጠል ሳምሰንግ ሞባይሉን እንዲሁም የየንጉሴ ዳኛውን ተች ስልክ ዘርፈው ወስደዋል
7.አየለ መኳንንት የተባለን ነጋዴ 97 ኩንታልና 2ኢታሊይ ሚዛን
8.ከአቶ ዘሩ ያየህ ቤት ሰብሮ በመግባት 15000ብር
9.የወይዘሮ የንጉሴን መቀነት በማስፈታት 1500ብር
10.የአቶ አውግቸው ዘሪሁንን ሙጢ ጓንዴና 3000ብር የተገዛ የሌሊት ብርድልብስ
11.የአቶ አታላይ ከበደን ሙጢ
12.የአቶ ሙላት መኮነን ሚኒሽር
13.የአቶ ሀብቴ ወርቁን ማይካ ክላሽና ቤተሰቡን በሬ ይልማ የተባለን ግለሰብ አፍኖ ወስዷል።
14.የተዋበ ክንዴን የግል ልብሱን በሙሉ
15.የቻሌ ጌቴን ፀረ አረም መድሃኒት ቤት በመስበር ዝርፊያና ውድመት አድርሰዋል።

በአጠቃላይ ንፁሃን ማህበረሰብን ያነጣጠረ ግድያና ዝርፊያ በሚሊሻና በጨፍጫፊው መከላከያ ተፈፅሟል።

በተመሳሳይ ምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ ፣ደብረኤልያስ ወረዳ እና ባሶሊበን ወረዳ ፣እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም ደንበጫ ወረዳ ከባድ ዝርፊያ ዝርፊያ የተፈፀመ በመሆኑ በዝረዝር ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የምናደርስ ይሆናል።

ሕዝባችን የገባበትን የህልውና ስጋት ለመቀልበስ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኝ አማራ የሆነ ሁሉ ይህን አስከፊ ድሪጊት በሚችለው ሁሉ ሊቃወመው ይገባል።

አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ህዳር 29/2018 ዓ.ም
"የሐሰት ድምፅ ቅጂው አገዛዙ ድል እንደራበው የሚያሳይ ነው"

የአገዛዙ ብልፅግና የሐሰት ዘገባዎች ሲገለጡ እርቃኑን እያስቀሩ መሳቂያ መሳለቂያ እያደረጉት ነው:: ከሰሞኑ በማስረሻ ሰጤ ክህደት ተጠቅሞ ድርጅቱን ጭምር ተደራደረኝ ያለው ብልፅግና ንፁሃን ታጋዮችን ጭምር ስም እያጠፋ የፋኖና ህዝብን አንድነት ለማላላት : የመሪዎችን ግንኙነት ለመሸርሸርና የአንድነት ውይይቶችን ለማበላሸት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት ቀርቶ የህዝቡ ምላሽ የፌዝ ሳቅ ሆኗል : የነአብይ አህመድ ድራማ ጠላቴ ብለው ለፈረጁት ሕዝብ ይቅርና ለራሳቸው ሎሌ አገልጋዮች እንኩአን የሚያሳምን አልሆነም::

የጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ዋና አዛዥ የሆነው አርበኛ ተሾመ አበባው እጁን ሊሰጥ ነው የሚለው የሐሰት የድምፅ ቅንብር መሰረታዊ ስህተት በራሱ በአርበኛው አንደበት ተነግሯል:: አርበኛው "በዚህ ትግል ብቻዬን እንኩአን ብቀር የምሰጠው እጅ የለም" ሲል ቁርጡን ነግሯቸዋል::

የልጅ አዋቂው : የጦር ፊታውራሪው : ደግ ቅን ታጋዩ አርበኛ ተሾመ አበባው "ጠላት ከፈለገ ያለንበትን ያውቀዋል ይሞክረን : እንደየአመጣጡ እናስተናግደዋለን ብሏል::

@አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ
የፋኖ ድምፅ
1🙏1
የድል ዜና

‎የከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር አራተኛ ቦጋለ ሬጅመንት ከአባት አርበኞች ጋር በመጣመር ታላቅ ጀብዱ ፈጸመ
‎===========
‎የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የከሰም 2ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር አራተኛ ቦጋለ ሬጅመንት ከአባት አርበኞች ጋር ተቀናጅቶ ሸኖ ከተማ በመግባት በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ አድርሷል::

‎የኃይለ ማርያም ክ/ጦር አራተኛ ቦጋለ ሬጅመንት ከአባት አርበኞች ጋር ከአዲስ አበባ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሸኖ ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት የብልጽግናን አራጅ ሰራዊት ረፍርፎታል::

‎የብልጽግና ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት የሸኖ ከተማን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ አስገድዶ ለስብሰባ እያስወጣ ባለበት ወቅት የኃይለ ማርያም ማሞ አራተኛ ቦጋለ ሬጅመንት ከአባት አርበኞች ጋር ሰርጎ በመግባት ሶስት የጠላት ኃይል እስከወዳኛው ሸኝተው አምስቱን ደግሞ አቁስለዋል::

‎የወገን ምት ያበሳጨው የብልጽግና ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ያለ የሌለ ግትልትል ኃይሉን ከሰንቦና ጫጫ አግተልትሎ በሶስት ግንባር አውደ ውጊያ ቢያካሄድም በሚገባው ቋንቋ በማናገር ልክ አስገብተውታል::

‎ይህ ግትልትል ሰራዊት በፊጦ አላ መሥኖ ቀበሌ ግንባር÷ በጫጫ መንደር በአራጌቻ ግንባር እና በሸኖ ከተማ ዳር ለማጥቃት ቢሞክርም አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ እና ተዋርዶ ወደመጣበት ጥሎ ፈርጥጧል።

‎ በመጨረሻም  የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር አራተኛ የቦጋለ ሬጂመንትና የአባት አርበኞች ጠላት ያቀደውን   የሥብሠባ አጀንዳ እንዲቋረጥ በማድረግ በሰላም ወደ ምድብ ቦታቸው ተመልሰዋል።

‎     መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ ይታገሱ  ጌታሁን  ነው።
‎                 " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።    
‎ህዳር 29/2018 ዓ.ም
🙏1
አሳዛኝ መረጃ ከ ወደ ጎንደር ተሰምትዋል....ከዚ በታች በምስሉ ላይ እምታዮት ግለሰብ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከጥቂት ቀናት በፊት እጁን ለ አገዛዙ በመስጠት እና አብሮ አንድ ክላሽ ይዞ መግባቱ ተገልፆ የነበረ ቢሆንም፤ ለመንግስት ይዞት የ ገባዉ መሳሪያ እና የ ሰዉ ሀይል ሁሉ በመርሳት በአሰቃቂ ሁኔታ በምስሉ እንደምታይቱ እጁን የ ፍጥኝ ታስሮ እና ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት እንዲደርስበት ከተደረገ በኃላ በመጨረሻም ሂወቱ ማለፉ ተሰምትዋል።አርፋቹ ተቀመጡ እያልን ስናስጠነቅቅ የነበርነዉም ዝም ብለን ሳይሆን በአራዊት ሰራዊቱ እጅ እንዳትገቡ እና መጫወቻ ሆናቹ እንዳትቀሩ ነበር ያሳዝናል በጣም ለሌሎች መማሪያ ሆና ያልፋል ብዬ አምናለዉ....Uno Amhara
👍7
ሰበር ዜና

በአፋብኃ በላይ ዘለቀ እዝ 3ኛ ኮር አያሌው ብሩ ክፍለጦር በአገዛዙ ሃይል ላይ በወሰደው ርምጃ ከፍተኛ ድል ተቀዳጀ::

አያሌው ብሩ ክፍለጦሩ ከሌሎች ክፍለጦሮች ጋር በመሆን ትልቅ ተጋድሎ በማድረግ ድል ሲቀናው ያገዛዙ ዘራፊ ሃይል በንፁሃን ላይ ዝርፊያ : ግድያና እገታ ፈፅሟል::

የኮሩ ፅህፈት ቤት መምሪያ ሃላፊ አርበኛ መምህር አብርሃም እያሱ በቀጠናው የተደረገውን አጠቃላይ አውደውግያና የተገኙ ድሎችን አስመልክቶ ላለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ መረጃውን አጋርቶናል::

ዝርዝሩን በማታ የዜና እወጃችን በዩቱዩብ ቻናላችን Global Fano Media ይከታተሉ
1👍1
የጠላትን ተልዕኮ ተቀብሎ ሲንቀሳቀስ በነበረው የሰራዊት አባል ላይ እርምጃ መውሰረዱን 206ኛ ኮር አስታወቀ።

ህዳር 29/2018 ዓ.ም

በመልሶ ማደራጀት ትግበራው ሰራዊቱን በተቀናጀ መልኩ እያደራጀ የሚገኘው 206ኛ ኮር በሰራዊቱ መካከል የተሰገሰጉ የጠላት እጆችን እየቆረጠ ሲሆን በ14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ አባል በነበረው አንተነህ ናዴ ላይ ክትትልና ምርመራ ከተደረገበት በኋላ ወንጀለኛ ሁኖ በመገኘቱ የድርጅቱን መመሪያና ደንብ መሰረት በማድረግ  ኮሩ እርምጃ ወስዶበታል።

ከጠላት ዋና አጀንዳዎች መካከል ሰራዊቱን እርስ በእርስ ማጋጨትና ማስከዳት ፣በፋኖ ስም ፀያፍ ተግባራትን መስራት በዋናነት የተቀበለው አንተነህ ናዴ ፦

1ኛ .የጅበላ ሙተራን ሻለቃ ሰራዊትን በማጋጨት
2ኛ .በአስገድዶ መድፈር
3ኛ . አባላትን በማስከዳት
4ኛ.ወታደራዊ ሚስጢሮችን ለጠላት አሳልፎ በመስጠት
5ኛ. ከማህበረሰቡ በማስገደድ ገንዘብ በመቀበልና በመዝረፍ
6ኛ. ከጠላት ኃይል አመራሮችና ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተልዕኮውን ጨርሶ በፋኖ አመራሮች ላይ ግድያ ፈፅሞ ወደ ጠላት ለመቀላቀል ሲነጋገር በተገኘ የስልክ ልውውጥ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ከላይ የተዘረዘሩ ወንጀሎችን ፈፅሞ በመገኘቱ ኮሩ አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

የሰራዊቱን የውስጥ አንድነትና የትግሉን ህልውና ለማስቀጠል በትኩረት እየሰራ የሚገኘው 206ኛ ኮር በጅበላ ሙተራ ሻለቃ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር በመፍታት ሰራዊቱ  አንድነቱን በማፅናት ማንኛውንም ግዳጅ መወጣት በሚያስችልበት ቁመና ላይ መገኘቱንም ኮሩ አክሎ ገልጿል።

በቀጠናው እረጅም እጆቹን አስገብቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው ጠላት መሰል እርምጃዎችን ለማደናቀፍ የተንቀሳቀሰ ሲሆን አንተነህ ናዴ ላይ እርምጃ ከተወሰደ በኋላ ወደ ቸርተከል ከተማ የተንቀሳቀሰውን ጠላት የጅበላ ሙተራ ሻለቃ ወደ ኋላ መመለሷም በመረጃው ተመላክቷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የትግሉን ህልውና ለማስቀጠል የሰራዊቱን አንድነትና ደህንነት ማስጠበቅን የቅድሚያ ቅድሚያ አድርጎ እየሰራ የሚገኘው 206ኛ ኮር አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ በወንጀለኞች ላይ ድርጅታዊ እርምጃ መወሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

የሰራዊታችን ደህንነት ለማይቋረጠው ትግላችን!

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
3👍2