ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ዉድ የተከበራቹህ አድማጭ ተመልካቾቻችን በነገዉ የህልዉናችን ፕሮግራም፣በወቅታዊ ጉዳይ ከአርበኛ ሰፈር መለሰ ጋር ቆይታ እናደርጋለን!!!

በሰሜን አማራ ቀጠያ በላይ ዕዝ ብቻዉን አንድ የጠላት ዕዝ እያንቀጠቀጠ የሚገኛዉ ጀግና ልበ ሙሉ አርበኛ ሰፈር መለሰ ከብልፅግናዉ ቀይ ባህር ሳይሆን ከአማራዉ ቀይ ባህር እንገናኝ ብሏል።

በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች የሚነሳበት እና ምላሽ የሚሰጥበት ህልዉናችን የተሰኘው ፕሮግራም በነገዉ ዕለት ከአርበኛ ሰፈር መለሰ ጋር ቆይታ እናደርጋለን በአክብሮት ትጠብቁን እና ትከታተሉ ዘንድ የአክብሮት ግብዥዣችን ነዉ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️🙏❤️❤️❤️

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏1
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ዉድ የተከበራቹህ አድማጭ ተመልካቾቻችን በነገዉ የህልዉናችን ፕሮግራም፣በወቅታዊ ጉዳይ ከአርበኛ ሰፈር መለሰ ጋር ቆይታ እናደርጋለን!!!

በሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ብቻዉን አንድ የጠላት ዕዝ እያንቀጠቀጠ የሚገኛዉ ጀግና ልበ ሙሉ አርበኛ ሰፈር መለሰ ከብልፅግናዉ ቀይ ባህር ሳይሆን ከአማራዉ ቀይ ባህር እንገናኝ ብሏል።

በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች የሚነሳበት እና ምላሽ የሚሰጥበት ህልዉናችን የተሰኘው ፕሮግራም በነገዉ ዕለት ከአርበኛ ሰፈር መለሰ ጋር ቆይታ እናደርጋለን በአክብሮት ትጠብቁን እና ትከታተሉ ዘንድ የአክብሮት ግብዥዣችን ነዉ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️🙏❤️❤️❤️

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏2
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ 109ኮር 99ክ/ጦር በደጋ ዳሞት ሻለቃ ከባድ በትር የተናደደው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በየሄደበት ቀጠና ያገኘውን ሀብት ንብረት እያወደመ እና እየዘረፈ ይገኛል ከነዚህም ውስጥ የሰቀላ እና የደልሙ ጤና ጣቢያወችን ሀብት እና ንብረት የዘረፈ ሲሆን በተጨማሪም ፈንቴ ታረቀኝ የተባለን ግለሰብን በአሰቃቂ ሁኔታ ገሏል።

እንስሳትን ገሏል፤ የገበሬውን እህል አቃጥሏል፤ የልብስ፥ የጫማ እና የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆችን ዘርፏል።
💔1
በእዉነቱ ድንቅ ጦማር ነዉ!!!
በጥሞና አንብቡት!!!

አለማዎቃችንን በአደባባይ እውቅና የምንሰጥ ጉደኛ ፍጡሮች ሆነናል...

አንብቡት!

ደድበን፣ ደንቁረን፤የኃፍረት የይሉኝታ ሸማችንን(ልብሳችንን) ጥለን፣እብደትን ብራንዳችን፤አለማዎቅን ደግሞ ጌጣችን አድርገን፣ በአደባባይ አላማዎቃችንን እውቅና የሰጠን፣ ምስኪን ራዕይ የሌለን መረን ያጣን ህዝቦች ሆነናል።

"ደንቆሮ ህዝብ ይጠፋል" እንዳለው ቅዱስ ዳዊት በስጋ ቆመን በነፍስ ጠፍተናል።ለግብናችን ጨርቅ ደርበን የህሊና፣የመንፈስ፣ የነፍስና የሞራል ሕግ ልቦናችን ልባሱ ተፍቆ መለመላችንን ቀርተናል።

"ራዕይ የሌለው ህዝብ መረን ያጣ ነው" እንዳለው ቅዱስ መጽሐፉ መነሻችንን የረሳን፣መዳረሻ የሌለን፣ከዕምነት የተፋታን፣ማኀበረሰባዊ እሴትን፣ልማድ፣ባህልና ወግን የተውን፤ መረን የሌለን ከንቱ ተቅበዝባዦች ሆነናል።
መቀመጫን በመግለብ፣ሕሊናን በድንቁርና አክስቶ፣ አካልን ኃፍረተ ስጋን በማይደብቅ በብልጭልጭ እራፊ ጨርቅ ገምዶ፣የድንቁርናን ጥንብ ጥሎ፣ለውሸት፣ለአዕምሮ ዝገት፣ለማኀይምነትና ለእርጣተ እውቀት "ሱፐር ገገማዎች" ሁኑ! "እጃችሁን ስጡ" ስንባል "እሺ" ብለን እጃችንን ከፍ አድርገን የምናጨበጭብ፣ዓለምን ጉድ ያስባልን ጉደኞች ሆነናል።

አገርንና ሕዝብን በእኛ ጉድጓድ ልክ የምንመለከት ዳፍንታም ሆነናል።ነውርን ፀጋ፣ሐፍረትን ድፍረት፣አላዋቂነትን ማዎቅ፣ውሸትን እውነት፣ከንቱነትን ግብረገብ፣ኀጥያትን ፅድቅ፣ከእሴት መፋታትን ስልጣኔ፣ከማንነት፣ከእምነትና ከባህል መፋታትን እንድ ቅዱስ ጌጥ የምንመለከት የዓለምን የጋራ ስምምነት እውነታ(The reality of the world consensus) በራሳችን ዓለም የለወጥን ዕድፋሞች ሆነናል። መንፈሳዊ አስተምህሮቱ የሚለንን የምንኖር ሳይሆን በእምነት ካባ ተጠቅልለን ሌሎችን ሳይሆን እራሳችንን ለራሳችን የምንዋሽ ግብዞች ሆነናል።

መኖር ማለት ሆድን መሙላት፣አዕምሮን ማገርጣት ሆኗል።ገንዘብ ለማግኘት የገንዘብ ባሮች ሆነናል። ማስመሰል፣አድርባይነት፣ከራስና ከእውነት መፋታት፣አዕምሮንና ስጋን ለከርስ ግርድና ማከራየት መለያችን ሆኗል። በአጠቃላይ አለማዎቃችንን በአደባባይ እውቅና የምንሰጥ፣ድንቁርናችንን የማናስነካ ያለማዎቅ አለቆች ሆነናል።

"የስግጥ(ድንቁር) ፍምስ ቱር" እና የማስረሻ አረጋ ከበደ "የሰላም ስምምነት" ደግሞ የዚህ ዋነኛ መልኮች ናቸው።

ወግደረስ ጤናው ህዳር /26/ 2018 ዓ.ም


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
1👍1
የአብይ አህመድ የ103ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ ጡት ቆራጥ ኃይል በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ  ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር በሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመታ!

የአብይ አህመድ አገዛዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር አናብስቶች አሉበት ወደ ተባለው ዘልቆ በመግባት ከበባ ለማድረግ ቢሞክርም በክንደ ነበልባሎች ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ (7/70) ክፍለ ጦር በዛሬ ዕለት በቀን 27/03/18 በኤፍራታ እና ግደም ካራለጎማ ቀበሌ አገዛዙ ከፋኖ ጋር ባደረገው ውጊያ በአሳምነው ክንደ ነበልባሎች አከርካሬውን የተመታው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ መከላከያ ሰራዊት የፋኖን በትር መቋቋም ሲያቅተው በመመለስ ላይ እያለ አቶ እምሻው ከፈለኝ የተባለውን  አርሶ አደር የግብርና ስራውን እያከናወነ ባለበት ሰዓት በግፍ ረሽኖ ሄዷል።

በመሆኑ አብይ አህመድና የብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ኃይል በአማራ ህዝብ ላይ እያሳየ ባለው ጥላቻ ዛሬም እንደትናንቱ የፖለቲካ ምንነት የማያውቁ የአማራን ህዝብ የአማራ ፋኖዎች ጋር ፊት ለፊት መግጠምና መፋለም ሲያቅተው ንፁሃንን በአገኘው አጋጣሜ እየረሸነ ይገኛል። አብይ አህመድ አማራን ለማጥፋት የቀን ተቀን ስራው ስለሆነ መላው የአማራ ህዝብ የህን አረመኔያዊ ስራት ነቅለን እስከምንጥለው መላው ህዝባችን በአለበት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ስንል በአክብሮት እንገልፃለን።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው

ህዳር 27/03/2018 ዓ.ም
🙏3
ትርክት — እጣ ፈንታን የሚቀርጽ የጋራ ምናብ

ዩቫል ኖህ ሃራሪ በሳፒየንስ ውስጥ እንደገለጸው፣ "ሰው ልጅ ዓለምን የሚገዛው በስፋትና በተለዋዋጭነት አብሮ ለመስራት የሚችል ብቸኛ እንስሳ ስለሆነ ነው—ይህም የሚቻለው በጋራ ትርክቶች ስለሚያምን ነው።" የሰው ልጆች በትርክት የሚነዱ ፍጥረቶች ነን፤ ከተማዎችን ከመገንባታችን በፊት ትርክቶችን እንገነባለን። ሕገ መንግሥት ከመፃፉ በፊት አፈ ታሪኮች ነበሩ፤ አገራት ከመፈጠራቸው በፊት የትርክት መዋቅሮች ነበሩ። ትርክት ንግርት ብቻ አይደለም፤ ምን እውነት እንደሆነ፣ ምን አስፈላጊ እንደሆነ እና ምን መደረግ እንዳለበት የሚገልጽ ትርጉም ሰጭ መዋቅር ነው።

የትርክት ኃይል በተግባር የተለያዩ ሚናዎችን ይጫወታል፦ አንድነትን ይገልጻል፣ ለምሳሌ "እኛ ሕዝቡ" የሚለው የአሜሪካ የነጻነት ትርክት፤ ለግለሰብ ሕይወትና ለጋራ ተግባር ዓላማን ይሰጣል፣ "አንድ ሕዝብ፣ አንድ እጣ ፈንታ" የሚለው የአፍሪካ ነጻነት ትግል መሪ ቃል፤ የተለያዩ ቡድኖችን በአንድ በማስተሳሰር ተግባርን አነሳስቷል፣ "እንችላለን" የሚለው የጦርነት ጊዜ መሪ ቃል፤ በሐዘንና በመከራ ውስጥ ጽናትን ያጎናጽፋል።

የትርክት ኃይልን የሚያጠናክሩ የተለያዩ ንድፈ ሐሳቦች አሉ፦ የትርክት ማንነት ንድፈ ሐሳብ (ፖል ሪኮር) ራሳችንን የምንረዳው ስለ ራሳችን በምንነግረው ትርክት ነው ይላል፤ የእውነታ ማህበራዊ ግንባታ ደግሞ እውነታ የሚገኝ ብቻ ሳይሆን በጋራ ትርጉሞችና ትርክቶች የሚገነባ መሆኑን ያብራራል። የዘይቤ ንድፈ ሐሳብ (ጆርጅ ላኮፍ) ትርክት ግጭትን እንዴት እንደምንረዳ እንደሚወስን ይገልጻል። የትርክት ሥርዓት (ዎልተር ፊሸር) ሰዎች የሚነዱት በሎጂክ ሳይሆን በትርክቶች ተመሳሳይነትና አስተማማኝነት እንደሆነ ይናገራል። ማህበራዊ ምናባዊነት (ቻርልስ ቴይለር) ታላላቅ ሥልጣኔዎች የሚነሱት ማን እንደሆኑ እና ለምን እንደተፈጠሩ በሚተነትኑ የጋራ ትርክቶች ላይ ተመስርተው እንደሆነ ይገልጻል።

የትርክት ኃይል የሚከተሉትን ውጤቶች ያስከትላል፦ የማነቃቃት ውጤት፣ ትርክቶች ሰዎችን ከሕግ እና መመሪያ በበለጠ ፍጥነት ወደ ተግባር ያነቃቃሉ—የማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር "ሕልም አለኝ" ንግግር የዚህ ምሳሌ ነው። የሕጋዊነት ውጤት፣ መሪዎችና ሥርዓቶች በአሳማኝ ትርክቶች ኃይል ያገኛሉ—የማንዴላ "የቀስተ ደመና አገር" ትርክት ከዘር መለያየት በኋላ ያለችውን ደቡብ አፍሪካ ሕጋዊ አደረገ። የማጥፋት ውጤት፣ የሐሰት ትርክቶች አገራትንና እውነትን ሊያጠፉ ይችላሉ—የናዚ ጀርመን ዘረኝነት አፈ ታሪክ ወደ ጅምላ ጭፍጨፋ መራ። የመፈወስ ውጤት፣ የጋራ ትርክት በመነጋገር መፍጠር የአደጋ ስሜትን ያድናል—የሩዋንዳ ጋቻቻ ፍርድ ቤቶች ፍትህን በትርክት አስገኝተዋል። በመጨረሻም የፈጠራ ውጤት፣ አዳዲስ ትርክቶች ለፈጠራና ለማሻሻል መንገድ ይከፍታሉ—የሲሊኮን ቫሊ "ሰባት ፈጣሪዎች" ትርክት የቴክኖሎጂ ፈጠራን አስገኝቷል።

የትርክት ኃይል በራሱ ተቃርኖዎች አሉት፦ ነጻ ሊያወጣ ወይንም ሊገዛ ይችላል። ሕዝብን የሚያንጽ ትርክት ለሌሎች ሰዎች ሥቃይ ዓይን ሊያሳውር ይችላል። እውነት ወይም ውሸት ሊያስተላልፍ ይችላል፤ እያንዳንዱ አምባገነን አገዛዝ በአንድ ትርክት ላይ ይኖራል—"የሀገር አባት"፣ "ውስጣዊ ጠላት"፣ "የክብር ዘመናዊ ታሪክ"። በመጨረሻም፣ ሊያጠነክር ወይም ሊያጠፋ ይችላል—ትርክቶች ሥልጣኔዎችን መገንባት ወይም ማጥፋት የሚችሉት ማን እንደአጻጻፋቸው፣ እንደንግርታቸውና እንደተቆጣጣሪአቸው ነው።

አሜሪካዊ ሕልም፣ መልእክቱ ነጻነት፣ በጥረት መበልጸግና ወደ ላይ መውጣት ሲሆን፣ በዓለም ላይ ተጽዕኖ ያለው የሃገር አፈ ታሪክ ፈጠረ። ኡቡንቱ፣ መልእክቱ "እኔ ያለሁት እኛ ስላለን ነው።" ሲሆን፣ ለደቡብ አፍሪካ እርቅ መሠረት ሆነ። የኮሙኒስት ማኔፌስቶ፣ መልእክቱ የመደብ ትግልና አብዮት ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ፖለቲካን ለአንድ መቶ ዓመት እንደገና ጻፈ። የኢትዮጵያ ሕዳሴ፣ መልእክቱ ዳግም መወለድ፣ ክብርና በራስ መተማመን ሲሆን፣ ትውልድን አገርን እንደገና ለመገንባትና ለማስነሳት ያበረታታል።

በደንብ የተነገረ ትርክት ከመረጃ በላይ የሆኑ የአንጎል ክፍሎችን—ስሜት፣ ርኅራኄ እና የእንቅስቃሴ ክፍሎችን ጨምሮ—ያነቃቃል። የነርቭ ኢኮኖሚስቱ ፖል ዛክ ትርክቶች ኦክሲቶሲን እንዲለቀቅ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ሰዎች ትርክቶችን ከደረቅ መረጃዎች 22 እጥፍ ያህል በቀላሉ ያስታውሳሉ። በመሪነት ውስጥ፣ ትርክቶች የመልእክትን የማሳመን አቅም እስከ 70% ያህል ሊያሳድጉ ይችላሉ።

የጋራ ትርክት ሲጠፋ፣ ማህበረሰቦች ይፈርሳሉ፣ መተማመን ይጠፋል እና ራዕይ ይዳክማል። በዚህ ጊዜ "የትርክት ባዶነት" ይፈጠራል—ይህም በፍጥነት በሌሎች (ሚዲያ፣ ሕዝባዊ መሪዎች፣ የውጭ ሃይሎች) ይሞላል። በተቃራኒው፣ ትርክት ሲታደስ፣ ሰዎች በጋራ ዓላማ ዙሪያ ይሰለፋሉ፣ መሪዎች ሞራላዊ ሥልጣንን እንደገና ያገኛሉ፣ እና አዲስ እጣ ፈንታ ሊታሰብ የሚችል ይሆናል።

ታላላቅ መሪዎች የትርክት መሃንዲሶች ናቸው። ትርክትን ይገነቡታል፣ ይኖሩበታል፣ እና ይጠብቁታል። ለምሳሌ ማንዴላ በበቀል ፋንታ ይቅርታን አቀረበ፣ ጋንዲ ድክመትን ወደ ሞራላዊ ኃይል ቀየረው፣ እና ቸርችል ተስፋ መቁረጥን ወደ መቋቋም ቀየረው።

"መሪዎች የተስፋ ነጋዴዎች ናቸው።" – ናፖሊዮን ቦናፓርት

በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI)፣ በውሸት ቪዲዮዎች (deepfakes) እና በድህረ እውነት ዓለም፣ ትርክት ጦርም ጋሻም እየሆነ ነው። ትርክቱን የሚቆጣጠረው ሁሉ አስተሳሰብን ይቆጣጠራል፤ ትርክቱን ተአማኒ አድርጎ የሚያቀርብ ሁሉ ሕጋዊነትን ይቆጣጠራል፤ የመጪውን ትርክት የሚጽፈው ሁሉ እጣ ፈንታን ይወስናል። የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትግል በዋናነት በሀብት ወይም በግዛት ላይ ሳይሆን፣ በራሱ በእውነታው ላይ ነው—ሰዎች ለመኖር በሚመርጡት ትርክት ላይ።

"በዓለም ላይ በጣም ኃይለኛ ሰው ታሪክ ተናጋሪው ነው። የታሪክ ተናጋሪው የአንድን ትውልድ ራዕይ፣ እሴቶች እና አቅጣጫ ያስቀምጣል።" – ስቲቭ ጆብስ



(የዛዲግ ቢሮ መጣጥፎችን ማየት አያጎድልም)
👍1
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ::

በምኒልክ ዕዝ አብራክ ውስጥ ያሉት የደጋው መብረቅ ኮር እና ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር በደላንታ ወረዳ በጥላት ላይ በጋራ ጥቃት ፈፅመው ድል ተቀዳጅተዋል::

የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር እና ኮር 2 ዞብልአምባ ክፍለ ጦር 3ኛ (ራያ ሻለቃ) እና 7ኛ ሻለቃ የጥላትን አከርካሪ በመስበር ታሪክን በአሮጌው ጃኖስና ቦረና ኪዳነምህረት ሰርተዋል።

ህዳር 27/2018 ዓ/ም ደላንታ ወረዳ ፀሀይ መውጫ አሮጌው ጃኖስ ላይ ከጠዋቱ 12:00 እስከ 2:00 በዘለቀ አውደ ውጊያ የአቶ አብይ አህመድን ቅጥረኛ ሰራዊት ስቦ በማስገባት የበርካቶች ሰራዊት ነፍስ ወደ አምላካቸው ሲላኩ ገሚሶቹ ቁስለኛ ተደርገዋል። የአማራ ህዝብ ጥላት ሆኖ የተነሳው የመራዡ ብልፅግና ቡድን በዛሬው እለት በተሽከርካሪ አስከሬንና ቁስለኛዎቹን እያነባበረ ወደ ቁስጢንጢና ካምፕ ሲያመላልስ ውሏል።

በዳውንት ወረዳ በሁለቱ ውህድ የኮር ሃይሎች አይቀጡ ቅጣት የተገረፈው የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ካፈርኩ አይመልሰኝ ባለበት መንገድ የሞትን ፅዋ እየተጋታት ይገኛል። በአራቱም የአማራ አቅጣጫ ለአሞራ ቀለብ እየተደረገ ያለው የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ሰራዊት በጀነራል አሳምነው ፅጌ ስም እየማሉ ጥላትን አፈር ከደቼ የሚቀላቅሉት ፋኖዎች ከድሮን እስከ ታንክና መድፍ የታጠቀውን የፋሽስቱን ሰራዊት አስከሬን በአስከሬን አቆላልፈውታል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 27/2018 ዓ.ም

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
2🙏2
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አዛዥ አርበኛ አብነው ታደሰ የተላለፈ የትግል ጥሪ!!

በመጀመሪያ ደረጃ ለሁሉም አማራ እና የህልውና ትግላችን ደጋፊዎች ለሆናችሁ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት የምሻው የአማራ ፋኖ የጄኔራል አሳምነው ፅጌን የኑዛዜ ቃል አክብሮ በቅንጅት እና በአንድነት እየታገለ መሆኑን በማብሰር ነው:: ቀሪው ስራችን አንድ እናት ድርጅት መመስረት ነው ይህም በቅርቡ እንደሚሳካ ጥርጥር የለኝም::

እንደምታውቁት እኛ አማሮች በፋሽስቱ አብይ አህመድ መንግስት የተከዳን እና ጥርስ የተነከሰብን ነን:: "አማራን ላጠፋ ነው" በማለት አብይ አህመድ ቃል በቃል ለኦሮሞ ተወላጅ የፌደራል እና ኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት መናገሩን የተከበሩ አቶ ታዬ ደንደአ ማጋለጣቸው ይታወሳል:: የማጥፋት ፕሮጀክቱ ትግበራ ከተጀመረ እነሆ ዓመታት ተቆጠሩ:: አብይ አህመድ እነ ጄኔራል አሳምነው ጽጌን ገድሎ ክልላችንንም አስወርሮ በክተት መክት ስትራቴጅ ህዝባችንን አስጭውፍጭፎ ሲያበቃ በድህረ ሰሜኑ ጦርነት ወቅት ፋኖን ትጥቅ አስፈትቶ አማራ ክልልን አባውራ የሌለው ቤት በማስመሰል ህዝባችንን ለማጥፋት እና የአማራን ጥንተ እርስት ለመቀማት አስቦ ብዙ እርቀት ሄዷል:: በዚህም መሰረት በህግ ማስከበር ስም አማራን ለመጨፍጨፍና ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት ዘመቻ መጀመሩና በርካታ ንፁሀንን መግደሉ ይታወቃል:: ይህን መንግስታዊ ክህደት በመቃወም አማራ አይጠፋም ትጥቁንም አይፈታም ብለን ወደ ጫካ በመግባት አፈሙዝ ወደ ህዝባችን ጠላት አዙረናል::

አማራ ሲፈናቀል፣ ሲገደል፣ ሲታሰር እና ሀብት ንብረቱ ሲዘረፍ ቆመን አናይም ይልቁንስ ባለጋራችንን እየገደልን እንሞታለን ብለን ፈንነናል::

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አማሮችን ፀረ ህዝቦች በጅምላ ሲያቃጥሏቸው እና የአንድት ነፍሰ ጡር እናትን ሆድ በስለት ሰንጥቀው ሽሉን ሲያፈነዱት አማራ የሆነ ፅንስ ጭምር መኖር የለበትም ብለው ማወጃቸው መሆኑን ልብ ይሏል::

አዲስ አበባ አማራ እንዳይገባ ሸኖ እና ሰንዳፋ ላይ በኦሮሞ መንገድ ሲዘጋበት እና በየጊዜው ሀገር አቋራጭ አውቶቢስ እየታገተ መንገደኞች ታፍነው ተወስደው በሸኔ ሲገደሉ፣ መስጅድ እና ቤተክርስቲያን ሲቃጠል አማኞችም ሲረሸኑ እንድሁም አማራ በመሆናቸው ብቻ ወገኖቻችን በኦሮሚያ ክልል በየጊዜው በኦነግ ሸኔ ሲገደሉ እና ሲፈናቀሉ ይህም አልበቃ ብሎ እዚሁ ክልላችን ውስጥ የአብይ መንግስት ተላላኪው ካድሬ ለአርሶ አደራችን በቂ ማዳበሪያ ላለማረቅብ ወስኖ አማራን በርሀብ እንቀጣለን ብሎ ቆርጦ ሲነሳ አስተውለናል:: ገበሬው "የገመድ መሬቴ ጦም አደረ" ብሎ ሰልፍ ሲወጣ "የጅራፍ ፓለቲካ" የሚል ስላቅ ነበር የብልጽግና መልስ::

ክልላችን ውስጥ የማዳበሪያ እጥረት የገጠመን ተረኞች ሆን ብለው ማዳበሪያውን ኦሮሚያ ክልል ከዝነውት ነበር:: ለአማራ ያላቸው ጥላቻ ከልክ ያለፈ ነው:: ስለሚፈሩን እንደምንም ብለው ለርሀብ እና ስደት እንድሁም ሞት እንድንጋለጥ ይሰራሉ:: ይህ ሴራቸው የገባውና ቀድሞ የነቃው ፋኖ በአራቱም የአማራ ግዛት አገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀውን አኩሪ ገድል ፈጽሟል::

ወገኖቻችንን አትግደሉብን ብለን ሰልፍ ስንወጣ "ልቅሶ አይሰለቻቸውም ወይ?" በማለት ሰላማዊ ትግልን ብልጽግናዎች አጣጥለዋል:: ችግር አለ ችግሩ ይፈታ ስንልም ችግር ፍቱልን ያለውን አካል በማሰር ነው መልስ የሰጡን::

ሰላማዊ አማራጭ እንደማያዋጣ አውቀን እጅጉን ተገፍተን እና ግፍ ተፈጽሞብን ዘራችንም እየሳሳ ስለሆነ ነው የትጥቅ ትግል የጀመርነው:: ይህን የህልውና ትግል ለማደናቀፍ የሚጥር ባንዳ ወዮለት::


ባንዳ የሆንክ ሁሉ ዋ! ለራሴ በል:: እንግዲህ ባንዳን አንምርም:: አንድት ብርጭቆ ውሀ ውስጥ ጠብታ አንድ መርዝ ከተጨመረ ውሀው ይመረዛል::

ንፁህ ህዝብ ውስጥ አንድ ባንዳ ካለ ህዝቡ በየጊዜው ዋጋ ይከፍላል:: በአንዳንድ ባንዳ ምክንያት ህዝባችን ዋጋ መክፈል ስለሌለበት ተባብረን ባንዳን እናፀዳለን:: ለዚህ ተልእኮ ደግሞ ህዝባችን ሊተባበረን ይገባል::

የአማራን ህዝብ ክብር እና ጥቅም የሚያስከብር እንዲሁም አማራ የሚለውን ስም በበጎ የሚያስጠራ የአባቶቻችንን አትንኩኝ ባይነት የሚዘክር ድንቅ ስራ እየሰራ ያለው የአማራ ፋኖን ከድሉ አደባባይ ሳይደርስ ለመመለስ የሚታትር ባንዳ መጨረሻው ሞት ነው::

ከእንግዲህ በራሳችን ባንዳዎች ላይ የምንወስደው እርምጃ ከባድ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም::

ፋኖ የበረሃው ሙቀት እና የደጋው ብርድ፤ የስንቅ እጥረት ብሎም የጥቁር አማሮች እንቅፋትነት ሳይበግረው የክረምቱ ዶፍ ዝናብ ሳይገታው ለአማራ ህዝብ ዘብ ሆኖ ሌት ከቀን ትንቅንቅ ላይ ነው።

መከላከያ ሰራዊት የኦሮሞ ወንበር አስጠባቂ ዝና የአብይ አህመድ ገረድ ነው:: ይህን ሰራዊት አጥፍቶ አብይን ለፍርድ ማቅረብና የአማራን ህዝብ እንባ ማበስ የፋኖ ግደታ ነው::

አማራውያን ሆይ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና እና ፓሊስ እንድሁም መከላከያ ውስጥ ዘመድ ወዳጅ ያላችሁ መክራችሁ ወደ ቤቱ አስገቡ። በተለይ ሚሊሻ በአስቸኳይ ቢቻል አዳሩን ወደ ቤቱ እንድገባ ይነገረው:: ይህ ሳይሆን ቢቀር እኛ እንግዲህ ባንዳን ስለማንምር በገቡበት ገብተን እንደመስሳለን::

ይህ አዋጅ ታውጆ የሚተርፍ ባንዳ ላይኖር ይችላል:: አንዳንዶች ተደብቀው ውለው ቢያድሩም መጨረሻቸው አያምርም!

መንግስትን አሽመድምደነዋል:: ክልላችንን ከ80 ፕርሰንት በላይ ተቆጣጥረናል:: ይህን ሀቅ ቢቢሲም ለዓለም አውጆታል:: በቅርቡ የማዕከላዊ መንግስት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባ ከተማን እንደምንቆጣጠር ተገማች ነው:: አዎ፤ ፋኖ በጎጃም እና ሸዋ እንድሁም በሸዋ እና ጎንደር ብሎም ወሎ ሰፊ ግዛት ተቆጣጥሮ እያስተዳደረ ሲሆን ወደፊት የሚያደርገው ግስጋሴም እንደቀጠለ ነው::

በምዕራብ ወሎ ግንባርም ከፋሽስቱ አብይ አህመድ መንግስት በርካታ ቀጠናዎችን ነፃ አውጥተን የጊዜያዊ መንግስት መዋቅር ዘርግተን ህዝባችንን እያስተዳደርን ነው::

የድል ባለቤት መሆናችን አይቀርም፤ እውነትን ስለያዝንና ግፍ አንገሽግሾን ስለተነሳን እናሸንፋለን ስለዚህ ባንዳ ሆይ ቶሎ ወደ ቤትህ ተመለስ::

በየእለቱ የወገኖቻችን ደም እየፈሰሰ ነው:: ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍም በአማራ ምድር እየተፈፀመ ነው::

በያዝነው ወርም የካህን ሚስትን ጨምሮ በድምሩ 3 እመጫት እናቶች መካነሰላም ከተማ የሚገኘው አድማ ብተና ካምፕ ውስጥ በአንድ የፋሽስቱ መንግስት የፀጥታ ኃይል አባል መደፈራቸው ይታወቃል:: ከለላ ወረዳ ዉስጥም ቲርቲራ ታዳጊ ከተማ አጠገብ የቀነሶ መንደር ነዋሪ የሆነው አቶ ሁሴን ከማል የተባለው አርሶ አደር አጨዳ ላይ ሳለ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአድማ ብተናዎች እንደተረሸነ ለማረጋገጥ ችለናል::

ሰኞ ማለትም ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጃማ ወረዳ ደጎሎ ከተማ ውስጥ አንድት ከአረብ ሀገር ተመላሽ እህታችንን መከላከያ ሰራዊት ተኩሶ ገድሏታል:: ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስበት በምዕራብ ወሎ ግንባር ብቻ ሳይሆን በመላው አማራ ዘግናኝ ግፍ በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ነው:: ይህ የግፍ ግፍ አንገፍግፍ ሊቆም የሚችለው አንድ ሆነን መታገል ስንጀምር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል::
2
ስለዚህ ከጠላት ጎን ተሰልፋችሁ ወገናችሁን እየወጋችሁ ያላችሁ የሚሊሻ፣ አድማ ብተና እና ፓሊስ እንድሁም መከላከያ ሰራዊት አባላት ከዛሬ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ የምህረት አዋጅ ይፋ ስላደረግን ይህን ወርቃማ እና ታሪካዊ እድል እንድትጠቀሙበት ስንል ከወዲሁ እያሳሰብን ጠላትን ከድታችሁ ስትመጡ እኛ በበኩላችን ለምታስረክቡን ትጥቅ ተገቢውን ካሳ በመስጠት ወደምትፈልጉበት ቦታ ለመላክ ዝግጁዎች መሆናችንን እንገልፃለን:: አብሮን ለመታገል ፈቃደኛ ለሚሆነውም ሁኔታዎችን የምናመቻችለት ይሆናል::



መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏2
የአማራ ሰቆቃ በወልድያ ዩንቨርስቲ !

በአማራ ምድር በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የግቢ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊሶች እየተደፈሩ ነው ሁለት ሴት ተማሪዎች ከጠፉ ከ3 ቀን በኃላ አንዷ ትላንት በፌደራል ፖሊስ ተደፍራ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ አንገቷ ታጥፋ ተጥላ ተገኝታለች አንዷ እስከ አሁን አልተገኘችም መረጃው እንዳይወጣ ሁሉም የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ተነግሯቸዋል።

ነገሩን አጠፋፍተው ሊያልፉ አስበው ግን ይሄ ነገርን ተደጋጋሚ እየተፈፀመ በመሆኑ መረጃው ለመውጣት ችሏል።

በተጨማሪ ደግሞ ቀን በቀን የቆሎ ተማሪዎችን ያተኮረ አፈና እየተደረገ ነው ሊያመልጡ የሚሞክሩትንም ተኩሰው እየገደሉ ነው ሚሊሻ እና ፖሊስ የየጁ ገነት 04 ቀበሌ እና ቲንፋዝ 02 ቀበሌ በታፈኑ ሰዎች ሞልቶ አገልግሎት አንሰጥም ከአሉ ሰነባብተዋል ።

27/ዐ3/2018 ዓ.ም
💔3