ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በቆቦ ከተማ ዙሪያ በተደረገ ውጊያ የጠላት ኮንክሪት ምሽግ በፋኖ ሲሰበር በርካታ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት መገደላቸው ተሰምቷል።

በቆቦው ዙሪያው ውጊያ፡ የፋኖ አባላቱ ጨለማው ሳይበግራቸው ከምሽግ ምሽግ እየተወረወሩ በጠላት ላይ ከባድ የጥቃት ዶፍ ማዝነባቸው ታውቋል።

ከቆቦ በቅርብ ርቀት ካራይላ እና አጣዋ ጋሪያ ላይ እስከ ትናንት አመሻሽ ድረስ የጠላት አ*ስ*ከ*ሬ*ን አለመነሳቱንና የሰማይ አሞራ እየተሻማበት ውሏል።

በተመሣሣይ ከሪፐብሊካን ኮማንዶ ክፍለጦሮች ጋር በተደረገ ውጊያ፡ ፋኖ ከ50 በላይ የሚሆኑት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል መቀዳጀቱን ለማረጋገጥ ተችሏል።

የሪፐብሊካን ጋርድ አባላቱ፡ የፋኖን ክንድ መቋቋም አቅቷቸው ሙትና ቁስለኛቸውን ማንሳት እስኪከብዳቸው ድረስ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራን ተከናንበዋል።

የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!
https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏1
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር እና የደጋው መብረቅ ኮር የጋራ የአውደ ውጊያ የድል ቱፊቶች።

ህዳር 26/2018 በዳውንት ወረዳና በደላንታ ወረዳ መካከል ልዩ ስሙ ሾጋ በሚባል ቦታ ላይ ለሁለት ቀን በቆየው አውደ ውጊያ የተገኙ ውጤቶች፦

ሚኒሊክ ዕዝ በሁለቱ ኮሮች መካከል ካሉ በተውጣጡ ሻለቃዎች ከፋሽስቱ ቅጥረኛ ሰራዊት ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ በጥላት ላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራን ከማድረስም በላቀ አካላዊ ጉዳትንም ማድረስ ተችሏል። በዚህ አውደ ውጊያ ከአምስት መኪና በላይ የጥላትን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ከሾጋ ወዴ ደላንታ ሲያመላልስ የነበረ ሲሆን፤በቁጥር የተረጋገጠ በደላንታ የፋሽስቱ ሰራዊት ካምፕ ውስጥ 93 ቁስለኞች ሲገኙ፤ሌሎች ሙት ሆነዋል።

ከ93ቱ መካከል 41ዱ ቦርድ የወጡና በደላንታ ሆስፒታል ውስጥ ለከፍተኛ ህክምና ከካምፕ ተነስተው የገቡ ናቸው። ለሁለት ቀን በፈጀው አውደ ውጊያ ፋሽስቱ ስርዓት ሞርተርና ዙ23ትን እንደ እጅ በእጅ የክላሽ መሳሪያ ያክል የተጠቀመ ሲሆን በዳውንት ወረዳ ውስጥ ሲብል ማህበረሰቦችን ጨፍጭፏል። አንድት መነኩሴና ሁለት አርሶ አደሮችን (የሶስት ንፁሃን) ህይወት ነጥቋል።በርካቶች ደግሞ ቁስለኛ ሆነዋል።

አገዛዙ ከ10 በላይ የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶች በዛው በዳውንት ወረዳ ሙሳፋፍ በሚባል ከባቢ በሞርተር አቃጥሏል። እንስሶች ሁሉ አማራ ምድር ላይ በመገኘታቸው አማራዊ የሁቱትሲ እርምጃ እደሚወሰድባቸው ሁሉ በቤቶችም ላይ ተፈፅሞባቸዋል።

የአለምን የጦርነት ህግን በጣሰ መልኩ ሰንደቃላማ ከወረደ በኋላ ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ እስከ ግማሽ ሌሊት ድረስ ንፁሃኖች ላይ የጅምላ ግድያን ፈፅሟል።

ሽፈትና ሞት አፍጫው ስር ደርሰው የሚጨፍሩበት የፋሽስቱ አገዛዝ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ይሉ ዘንድ ደመነፍሱን ከጫማ በታች ባለው መፈራገጥ ንፁሀኖችን ታርጌት አድርጓል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምኒልክ ዕዝ
የደጋው መብረቅ ኮር እና የምስራቅ አማራ ኮር 2
ህዳር 27/2018 ዓ.ም

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏1
በትግሉ ዉስጥ የተሰገሰጉ ሰርጎ ገቦች መፅዳታቸዉ ትግሉን አንድ እርምጃ ከፍ እያደረገዉ ይገኛል!!

በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) የተሰገሰጉ የብአዴን ተልዕኮ አስፈፃሚዎች ለህልውና ትግሉ መሰናከል ሁነዉ ቆይተዋል።

በተለይ በደቡብ ጎንደር በእነ ቀለመወርቅ ምህረቴ እና ይርጋ ሲሳይ ተመርጠዉ የገቡ የብአዴን ሰዎች በፋኖ ትግል ዉስጥ ጉልህ ድርሻ የነበራቸዉ የፋኖ አመራሮችን በማስገደል ግዳጃቸዉን ተወተዋል።

በጋይንት ሰርገዉ የገቡት እነ ማስረሻ ሰጤ አርበኛ ከፊያለዉ ደሴን በሴራ ከአስገደሉ እና ሰራዊቱን ከበተኑ በኋላ ወደ ቀድሞዉ ቤታቸዉ ተመልሰዋል።

የእነዚህ ሰዎች ከአፋህድ መዉጣት በቀጠናው ላለዉ ፋኖ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል።

ከቴዎድሮስ ቀኝ እጅ በገብርዬ ቀዬ የሚንቀሳቀሱት የአፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የ206ኛ ኮር በጠላት ላይ በወሰዱት የተጠና የደፈጣ እና የጨበጣ ዉጊያ ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
የፋኖ ድምፅ!!!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
1
በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ አሻሚት ቀበሌ ባንቧ ዉሃ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ፋኖ ባደረገዉ አዉደዉጊያ ድል ተቀዳጅቷል።

ከአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አራተኛ ደጃዝማች ኮር፣ከሁሉም ክፍለ ጦር የተዉጣጣ እና የኮሩ ልዩ ጥበቃ በጋራ በመሆን በዘራፊዉ የብልፅግና ሰራዊት ላይ እርምጃ ተወስዷል።


በመተማ ወረዳ አሻሚት ቀበሌ ቧንቧ ውኃ በተሰኘ ልዩ ቦታ አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ደጃዝማች 4ኛ ኮር የአርሶ አደር የጦር መሳሪያ ዝርፊያ ተሰማርቶ የነበረውን የዓብይ አህመድ ፋሽስታዊ ታጣቂ ጥቃት ሰንዝሮበታል ።

በጥቃቱ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታልደ

ዝርዝር መረጃውን በቀጣይ እናደርሳለን ሲል የዕዙ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አስታዉቋል።


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
🙏1
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ዉድ የተከበራቹህ አድማጭ ተመልካቾቻችን በነገዉ የህልዉናችን ፕሮግራም፣በወቅታዊ ጉዳይ ከአርበኛ ሰፈር መለሰ ጋር ቆይታ እናደርጋለን!!!

በሰሜን አማራ ቀጠያ በላይ ዕዝ ብቻዉን አንድ የጠላት ዕዝ እያንቀጠቀጠ የሚገኛዉ ጀግና ልበ ሙሉ አርበኛ ሰፈር መለሰ ከብልፅግናዉ ቀይ ባህር ሳይሆን ከአማራዉ ቀይ ባህር እንገናኝ ብሏል።

በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች የሚነሳበት እና ምላሽ የሚሰጥበት ህልዉናችን የተሰኘው ፕሮግራም በነገዉ ዕለት ከአርበኛ ሰፈር መለሰ ጋር ቆይታ እናደርጋለን በአክብሮት ትጠብቁን እና ትከታተሉ ዘንድ የአክብሮት ግብዥዣችን ነዉ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️🙏❤️❤️❤️

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏1
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ዉድ የተከበራቹህ አድማጭ ተመልካቾቻችን በነገዉ የህልዉናችን ፕሮግራም፣በወቅታዊ ጉዳይ ከአርበኛ ሰፈር መለሰ ጋር ቆይታ እናደርጋለን!!!

በሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ብቻዉን አንድ የጠላት ዕዝ እያንቀጠቀጠ የሚገኛዉ ጀግና ልበ ሙሉ አርበኛ ሰፈር መለሰ ከብልፅግናዉ ቀይ ባህር ሳይሆን ከአማራዉ ቀይ ባህር እንገናኝ ብሏል።

በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች የሚነሳበት እና ምላሽ የሚሰጥበት ህልዉናችን የተሰኘው ፕሮግራም በነገዉ ዕለት ከአርበኛ ሰፈር መለሰ ጋር ቆይታ እናደርጋለን በአክብሮት ትጠብቁን እና ትከታተሉ ዘንድ የአክብሮት ግብዥዣችን ነዉ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️🙏❤️❤️❤️

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏2
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ 109ኮር 99ክ/ጦር በደጋ ዳሞት ሻለቃ ከባድ በትር የተናደደው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በየሄደበት ቀጠና ያገኘውን ሀብት ንብረት እያወደመ እና እየዘረፈ ይገኛል ከነዚህም ውስጥ የሰቀላ እና የደልሙ ጤና ጣቢያወችን ሀብት እና ንብረት የዘረፈ ሲሆን በተጨማሪም ፈንቴ ታረቀኝ የተባለን ግለሰብን በአሰቃቂ ሁኔታ ገሏል።

እንስሳትን ገሏል፤ የገበሬውን እህል አቃጥሏል፤ የልብስ፥ የጫማ እና የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆችን ዘርፏል።
💔1
በእዉነቱ ድንቅ ጦማር ነዉ!!!
በጥሞና አንብቡት!!!

አለማዎቃችንን በአደባባይ እውቅና የምንሰጥ ጉደኛ ፍጡሮች ሆነናል...

አንብቡት!

ደድበን፣ ደንቁረን፤የኃፍረት የይሉኝታ ሸማችንን(ልብሳችንን) ጥለን፣እብደትን ብራንዳችን፤አለማዎቅን ደግሞ ጌጣችን አድርገን፣ በአደባባይ አላማዎቃችንን እውቅና የሰጠን፣ ምስኪን ራዕይ የሌለን መረን ያጣን ህዝቦች ሆነናል።

"ደንቆሮ ህዝብ ይጠፋል" እንዳለው ቅዱስ ዳዊት በስጋ ቆመን በነፍስ ጠፍተናል።ለግብናችን ጨርቅ ደርበን የህሊና፣የመንፈስ፣ የነፍስና የሞራል ሕግ ልቦናችን ልባሱ ተፍቆ መለመላችንን ቀርተናል።

"ራዕይ የሌለው ህዝብ መረን ያጣ ነው" እንዳለው ቅዱስ መጽሐፉ መነሻችንን የረሳን፣መዳረሻ የሌለን፣ከዕምነት የተፋታን፣ማኀበረሰባዊ እሴትን፣ልማድ፣ባህልና ወግን የተውን፤ መረን የሌለን ከንቱ ተቅበዝባዦች ሆነናል።
መቀመጫን በመግለብ፣ሕሊናን በድንቁርና አክስቶ፣ አካልን ኃፍረተ ስጋን በማይደብቅ በብልጭልጭ እራፊ ጨርቅ ገምዶ፣የድንቁርናን ጥንብ ጥሎ፣ለውሸት፣ለአዕምሮ ዝገት፣ለማኀይምነትና ለእርጣተ እውቀት "ሱፐር ገገማዎች" ሁኑ! "እጃችሁን ስጡ" ስንባል "እሺ" ብለን እጃችንን ከፍ አድርገን የምናጨበጭብ፣ዓለምን ጉድ ያስባልን ጉደኞች ሆነናል።

አገርንና ሕዝብን በእኛ ጉድጓድ ልክ የምንመለከት ዳፍንታም ሆነናል።ነውርን ፀጋ፣ሐፍረትን ድፍረት፣አላዋቂነትን ማዎቅ፣ውሸትን እውነት፣ከንቱነትን ግብረገብ፣ኀጥያትን ፅድቅ፣ከእሴት መፋታትን ስልጣኔ፣ከማንነት፣ከእምነትና ከባህል መፋታትን እንድ ቅዱስ ጌጥ የምንመለከት የዓለምን የጋራ ስምምነት እውነታ(The reality of the world consensus) በራሳችን ዓለም የለወጥን ዕድፋሞች ሆነናል። መንፈሳዊ አስተምህሮቱ የሚለንን የምንኖር ሳይሆን በእምነት ካባ ተጠቅልለን ሌሎችን ሳይሆን እራሳችንን ለራሳችን የምንዋሽ ግብዞች ሆነናል።

መኖር ማለት ሆድን መሙላት፣አዕምሮን ማገርጣት ሆኗል።ገንዘብ ለማግኘት የገንዘብ ባሮች ሆነናል። ማስመሰል፣አድርባይነት፣ከራስና ከእውነት መፋታት፣አዕምሮንና ስጋን ለከርስ ግርድና ማከራየት መለያችን ሆኗል። በአጠቃላይ አለማዎቃችንን በአደባባይ እውቅና የምንሰጥ፣ድንቁርናችንን የማናስነካ ያለማዎቅ አለቆች ሆነናል።

"የስግጥ(ድንቁር) ፍምስ ቱር" እና የማስረሻ አረጋ ከበደ "የሰላም ስምምነት" ደግሞ የዚህ ዋነኛ መልኮች ናቸው።

ወግደረስ ጤናው ህዳር /26/ 2018 ዓ.ም


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
1👍1
የአብይ አህመድ የ103ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ ጡት ቆራጥ ኃይል በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ  ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር በሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመታ!

የአብይ አህመድ አገዛዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር አናብስቶች አሉበት ወደ ተባለው ዘልቆ በመግባት ከበባ ለማድረግ ቢሞክርም በክንደ ነበልባሎች ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ (7/70) ክፍለ ጦር በዛሬ ዕለት በቀን 27/03/18 በኤፍራታ እና ግደም ካራለጎማ ቀበሌ አገዛዙ ከፋኖ ጋር ባደረገው ውጊያ በአሳምነው ክንደ ነበልባሎች አከርካሬውን የተመታው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ መከላከያ ሰራዊት የፋኖን በትር መቋቋም ሲያቅተው በመመለስ ላይ እያለ አቶ እምሻው ከፈለኝ የተባለውን  አርሶ አደር የግብርና ስራውን እያከናወነ ባለበት ሰዓት በግፍ ረሽኖ ሄዷል።

በመሆኑ አብይ አህመድና የብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ኃይል በአማራ ህዝብ ላይ እያሳየ ባለው ጥላቻ ዛሬም እንደትናንቱ የፖለቲካ ምንነት የማያውቁ የአማራን ህዝብ የአማራ ፋኖዎች ጋር ፊት ለፊት መግጠምና መፋለም ሲያቅተው ንፁሃንን በአገኘው አጋጣሜ እየረሸነ ይገኛል። አብይ አህመድ አማራን ለማጥፋት የቀን ተቀን ስራው ስለሆነ መላው የአማራ ህዝብ የህን አረመኔያዊ ስራት ነቅለን እስከምንጥለው መላው ህዝባችን በአለበት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ስንል በአክብሮት እንገልፃለን።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው

ህዳር 27/03/2018 ዓ.ም
🙏3
ትርክት — እጣ ፈንታን የሚቀርጽ የጋራ ምናብ

ዩቫል ኖህ ሃራሪ በሳፒየንስ ውስጥ እንደገለጸው፣ "ሰው ልጅ ዓለምን የሚገዛው በስፋትና በተለዋዋጭነት አብሮ ለመስራት የሚችል ብቸኛ እንስሳ ስለሆነ ነው—ይህም የሚቻለው በጋራ ትርክቶች ስለሚያምን ነው።" የሰው ልጆች በትርክት የሚነዱ ፍጥረቶች ነን፤ ከተማዎችን ከመገንባታችን በፊት ትርክቶችን እንገነባለን። ሕገ መንግሥት ከመፃፉ በፊት አፈ ታሪኮች ነበሩ፤ አገራት ከመፈጠራቸው በፊት የትርክት መዋቅሮች ነበሩ። ትርክት ንግርት ብቻ አይደለም፤ ምን እውነት እንደሆነ፣ ምን አስፈላጊ እንደሆነ እና ምን መደረግ እንዳለበት የሚገልጽ ትርጉም ሰጭ መዋቅር ነው።

የትርክት ኃይል በተግባር የተለያዩ ሚናዎችን ይጫወታል፦ አንድነትን ይገልጻል፣ ለምሳሌ "እኛ ሕዝቡ" የሚለው የአሜሪካ የነጻነት ትርክት፤ ለግለሰብ ሕይወትና ለጋራ ተግባር ዓላማን ይሰጣል፣ "አንድ ሕዝብ፣ አንድ እጣ ፈንታ" የሚለው የአፍሪካ ነጻነት ትግል መሪ ቃል፤ የተለያዩ ቡድኖችን በአንድ በማስተሳሰር ተግባርን አነሳስቷል፣ "እንችላለን" የሚለው የጦርነት ጊዜ መሪ ቃል፤ በሐዘንና በመከራ ውስጥ ጽናትን ያጎናጽፋል።

የትርክት ኃይልን የሚያጠናክሩ የተለያዩ ንድፈ ሐሳቦች አሉ፦ የትርክት ማንነት ንድፈ ሐሳብ (ፖል ሪኮር) ራሳችንን የምንረዳው ስለ ራሳችን በምንነግረው ትርክት ነው ይላል፤ የእውነታ ማህበራዊ ግንባታ ደግሞ እውነታ የሚገኝ ብቻ ሳይሆን በጋራ ትርጉሞችና ትርክቶች የሚገነባ መሆኑን ያብራራል። የዘይቤ ንድፈ ሐሳብ (ጆርጅ ላኮፍ) ትርክት ግጭትን እንዴት እንደምንረዳ እንደሚወስን ይገልጻል። የትርክት ሥርዓት (ዎልተር ፊሸር) ሰዎች የሚነዱት በሎጂክ ሳይሆን በትርክቶች ተመሳሳይነትና አስተማማኝነት እንደሆነ ይናገራል። ማህበራዊ ምናባዊነት (ቻርልስ ቴይለር) ታላላቅ ሥልጣኔዎች የሚነሱት ማን እንደሆኑ እና ለምን እንደተፈጠሩ በሚተነትኑ የጋራ ትርክቶች ላይ ተመስርተው እንደሆነ ይገልጻል።

የትርክት ኃይል የሚከተሉትን ውጤቶች ያስከትላል፦ የማነቃቃት ውጤት፣ ትርክቶች ሰዎችን ከሕግ እና መመሪያ በበለጠ ፍጥነት ወደ ተግባር ያነቃቃሉ—የማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር "ሕልም አለኝ" ንግግር የዚህ ምሳሌ ነው። የሕጋዊነት ውጤት፣ መሪዎችና ሥርዓቶች በአሳማኝ ትርክቶች ኃይል ያገኛሉ—የማንዴላ "የቀስተ ደመና አገር" ትርክት ከዘር መለያየት በኋላ ያለችውን ደቡብ አፍሪካ ሕጋዊ አደረገ። የማጥፋት ውጤት፣ የሐሰት ትርክቶች አገራትንና እውነትን ሊያጠፉ ይችላሉ—የናዚ ጀርመን ዘረኝነት አፈ ታሪክ ወደ ጅምላ ጭፍጨፋ መራ። የመፈወስ ውጤት፣ የጋራ ትርክት በመነጋገር መፍጠር የአደጋ ስሜትን ያድናል—የሩዋንዳ ጋቻቻ ፍርድ ቤቶች ፍትህን በትርክት አስገኝተዋል። በመጨረሻም የፈጠራ ውጤት፣ አዳዲስ ትርክቶች ለፈጠራና ለማሻሻል መንገድ ይከፍታሉ—የሲሊኮን ቫሊ "ሰባት ፈጣሪዎች" ትርክት የቴክኖሎጂ ፈጠራን አስገኝቷል።

የትርክት ኃይል በራሱ ተቃርኖዎች አሉት፦ ነጻ ሊያወጣ ወይንም ሊገዛ ይችላል። ሕዝብን የሚያንጽ ትርክት ለሌሎች ሰዎች ሥቃይ ዓይን ሊያሳውር ይችላል። እውነት ወይም ውሸት ሊያስተላልፍ ይችላል፤ እያንዳንዱ አምባገነን አገዛዝ በአንድ ትርክት ላይ ይኖራል—"የሀገር አባት"፣ "ውስጣዊ ጠላት"፣ "የክብር ዘመናዊ ታሪክ"። በመጨረሻም፣ ሊያጠነክር ወይም ሊያጠፋ ይችላል—ትርክቶች ሥልጣኔዎችን መገንባት ወይም ማጥፋት የሚችሉት ማን እንደአጻጻፋቸው፣ እንደንግርታቸውና እንደተቆጣጣሪአቸው ነው።

አሜሪካዊ ሕልም፣ መልእክቱ ነጻነት፣ በጥረት መበልጸግና ወደ ላይ መውጣት ሲሆን፣ በዓለም ላይ ተጽዕኖ ያለው የሃገር አፈ ታሪክ ፈጠረ። ኡቡንቱ፣ መልእክቱ "እኔ ያለሁት እኛ ስላለን ነው።" ሲሆን፣ ለደቡብ አፍሪካ እርቅ መሠረት ሆነ። የኮሙኒስት ማኔፌስቶ፣ መልእክቱ የመደብ ትግልና አብዮት ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ፖለቲካን ለአንድ መቶ ዓመት እንደገና ጻፈ። የኢትዮጵያ ሕዳሴ፣ መልእክቱ ዳግም መወለድ፣ ክብርና በራስ መተማመን ሲሆን፣ ትውልድን አገርን እንደገና ለመገንባትና ለማስነሳት ያበረታታል።

በደንብ የተነገረ ትርክት ከመረጃ በላይ የሆኑ የአንጎል ክፍሎችን—ስሜት፣ ርኅራኄ እና የእንቅስቃሴ ክፍሎችን ጨምሮ—ያነቃቃል። የነርቭ ኢኮኖሚስቱ ፖል ዛክ ትርክቶች ኦክሲቶሲን እንዲለቀቅ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ሰዎች ትርክቶችን ከደረቅ መረጃዎች 22 እጥፍ ያህል በቀላሉ ያስታውሳሉ። በመሪነት ውስጥ፣ ትርክቶች የመልእክትን የማሳመን አቅም እስከ 70% ያህል ሊያሳድጉ ይችላሉ።

የጋራ ትርክት ሲጠፋ፣ ማህበረሰቦች ይፈርሳሉ፣ መተማመን ይጠፋል እና ራዕይ ይዳክማል። በዚህ ጊዜ "የትርክት ባዶነት" ይፈጠራል—ይህም በፍጥነት በሌሎች (ሚዲያ፣ ሕዝባዊ መሪዎች፣ የውጭ ሃይሎች) ይሞላል። በተቃራኒው፣ ትርክት ሲታደስ፣ ሰዎች በጋራ ዓላማ ዙሪያ ይሰለፋሉ፣ መሪዎች ሞራላዊ ሥልጣንን እንደገና ያገኛሉ፣ እና አዲስ እጣ ፈንታ ሊታሰብ የሚችል ይሆናል።

ታላላቅ መሪዎች የትርክት መሃንዲሶች ናቸው። ትርክትን ይገነቡታል፣ ይኖሩበታል፣ እና ይጠብቁታል። ለምሳሌ ማንዴላ በበቀል ፋንታ ይቅርታን አቀረበ፣ ጋንዲ ድክመትን ወደ ሞራላዊ ኃይል ቀየረው፣ እና ቸርችል ተስፋ መቁረጥን ወደ መቋቋም ቀየረው።

"መሪዎች የተስፋ ነጋዴዎች ናቸው።" – ናፖሊዮን ቦናፓርት

በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI)፣ በውሸት ቪዲዮዎች (deepfakes) እና በድህረ እውነት ዓለም፣ ትርክት ጦርም ጋሻም እየሆነ ነው። ትርክቱን የሚቆጣጠረው ሁሉ አስተሳሰብን ይቆጣጠራል፤ ትርክቱን ተአማኒ አድርጎ የሚያቀርብ ሁሉ ሕጋዊነትን ይቆጣጠራል፤ የመጪውን ትርክት የሚጽፈው ሁሉ እጣ ፈንታን ይወስናል። የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትግል በዋናነት በሀብት ወይም በግዛት ላይ ሳይሆን፣ በራሱ በእውነታው ላይ ነው—ሰዎች ለመኖር በሚመርጡት ትርክት ላይ።

"በዓለም ላይ በጣም ኃይለኛ ሰው ታሪክ ተናጋሪው ነው። የታሪክ ተናጋሪው የአንድን ትውልድ ራዕይ፣ እሴቶች እና አቅጣጫ ያስቀምጣል።" – ስቲቭ ጆብስ



(የዛዲግ ቢሮ መጣጥፎችን ማየት አያጎድልም)
👍1