ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.35K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአፋህድ አስቸኳይ መግለጫ

"አፋህድ በጦርነት እያሸነፈው ካለው አገዛዝ ጋር የፈረመው ስምምነት የለም!!!"

በፋኖ ብርቱ ትግል እየተመታ ለመውደቅ እየተንገዳገደ መያዣውና መጨበጫው የጠፋው የኦህዴድ/ብልፅግና አገዛዝ፣ ከፈረሰ ሁለት ዓመታትን ካስቆጠረው የአማራ ክልል መንግሥት የሙት መንፈስ ጋር የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የ"ሰላም ስምምነት" አደረገ ብሎ ዛሬ ረፋዱን ያወጣው መግለጫ ፍፁም ሐሰት ነው።

አፋህድ ከኦህዴድ/ብልፅግናም ሆነ ከአማራ ክልል መንግሥት ተብዬው የሙት መንፈስ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተገናኝተን ድርድር አድርጎ አያውቅም። ከአገዛዙ ጋር የምንገናኘው በጦር ሜዳ ላይ ብቻ ነው።

በምናባዊ ዓለም ተደረገ በተባለው ድርድር ተገኝተዋል የተባሉት የአፍሪቃ ህብረት እና ኢጋድ በቀጣይ ቀናት ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናቀርባለን።

በአፋህድ በኩል ስምምነት ፈረመ የተባለው ማስረሻ ሰጤ፣ ከአገዛዙ ጋር ተልዕኮ ተቀብሎ ሲንቀሳቀስ ተደርሶበት ከአመራርነት እና አባልነት የታገደ እና የተባረረ መሆኑን በዚህ ሳምንት ባወጣነው መግለጫ መግለፃችን ይታወሳል። ከአገዛዙ ጋር ሲቀላቀልም፣ ለስራ ተብሎ የተላከለት በርካታ ያልተወራረደ የህዝብ ገንዘብ በእጁ እንደሚገኝ እና "የሰላም ስምምነቱን" ለዘረፋ ሽፋን ለማድረግ ከአገዛዙ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

አገዛዙ ሰሞኑን በተለያዩ በበሬ ወለድ ዜናዎች የሚፈራገጠው የፋኖ አንድነት ለማደናቀፍ ብሎ መሆኑን ህዝብ ተገንዝቦ፣ በቀጣይነት የምናወጣቸውን መግለጫዎች እንዲጠባበቅ እናሳስባለን።

ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት!!!

ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
/
ህዳር 25፣ 2018 ዓ.ም።
2
ሐውጃኖ ክፍለጦር የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሪፐብሊካን ጋርድ ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጁ::

ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ከሪፐብሊካን ጋርድ ጋር በመፋለም ከ50 በላይ ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

በተጋድሎው ጠላት ከራያ አላማጣ ጥሙጋ ከተማ ተነስቶ በዙ23 እና ሞርተሮች ታግዞ ወደ ሐውጃኖ ክፍለጦር ቀጠና ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ክፍለጦሯ ሁለት ሻለዎችን ተጠቅማ መልሶ ማጥቃት በማድረግ ከ50 በላይ ሪፐብሊካን ጋርድ ሙትና ቁስለኛ በማድረግና ቀጠናቸውን በማስከበር ጭምር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

በርካታ ሃይሉ የተመታበት የፋሽስቱ አብይ አህመድ የመጨረሻ ምሽግ ሪፐብሊካን ጋርድ ከግራም ከቀኝም ተጨማሪ ሃይል በማያገኝበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ራያ አላማጣ ጥሙጋ ከተማ ት/ቤት ውስጥ በከፍተኛ ድንጋጤና ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ይገኛል::

በሌላ በኩል ለሪፐብሊካን ጋርዱ ተጨማሪ ሃይል ማስገባት ያልቻለው አገዛዙ ሰራዊት ከራያ ቆቦ ጮቢ በር ሆኖ ኦራል ላይ የተጠመዱ ሁለት ቻይና ሰራሽ 155 Mm መድፍ ወደ ራያ ቆቦ ባይባወ እና ኩቢ ቀረንሳ እያስወነጨፈ ንፁሃን ላይ ጉዳት እያደረሰ አምሽቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 25/2018 ዓ.ም
2
#በቢቸና_ከተማ_የአገዛዙ_ሀይል_ንፁሀን_መረሸኑ_ተሰማ!!

የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ በቢቸና ከተማ ፍራሽ ሰፍቶ ይተዳደር የነበረን #ዘውዱ_ዳኘ የተባለ የእነቆራ ቀበሌ ንፁሃን ግለሰብን በግፍ እረሽኗል።

ራሱን በራሱ ጥምር ጦር ብሎ በጭንቀት የሚንቀሳቀሰው የአገዛዙ አረመኔዊ ኃይል በየዱኃ ገዳእያሱ እና አራጤ ዙሪያ ተንቀሳቅሶ የነበረ ቢሆንም በጀግኖቻችን የበላይ ዘለቀ እና የሽፈራው ገርባው
ልጆች 64ኛ ክ/ጦር አመራር እና አባላት እንዲሁም ደጀኑ ህዝባችን በደፈጣ ጥቃት ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ኃይል በመደመሰስ ሁለት ፖሊስ እና ከአራት በላይ ቁስለኛ በማድረግ አንድ የአገዛዙ መከላከያ አባል ከነሙሉ ትጥቁ በመማረክ ጠላትን ወደመጣበት መርገጭ ከተማ እያሯሯጡ መልሰውታል።
                                                                                                        #ማሳሰብያ:-
በአሁኑ ሰዓት 1:40 በቢቸና አባሮ ዙሪያ፣በቢቸና ገብርኤል ዙሪያ፣ በቢቸና ወይናም ጽዱ ጊዮርጊስ ዙሪያ በተጠንቀቅ ሆኖ ሰፍሮ የተቀመጠ ሀይል መኖሩን ማረጋገጥ ችለናል፡፡

የአገዛዙ አረመኔው ሰራዊት በሸበል በረንታ ወረዳ ሊዲና አካባቢው እንዲሁም ገዳያሱ ቀበሌ የደረሰበትን ሽንፈት አምኖ ከመቀበሉ ጎን ለጎን የፋኖ ሀይሎችን እደመስሳለሁ የሚል ቅዥት በደንሳ እነቆራ፣ ስረ ኢየሱስ፣ ቅድስጌ፣ ዲማ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት እስከ ጥዋቱ 12:00 ሰዓት በየትኛውም ቀጠና ያላችሁ የፋኖ ኃይሎች በተጠንቀቅ ልትጠባበቁ ይገባል፡፡

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
            ህዳር 25/2018 ዓ.ም

ፋኖ ይበልጣል ጌቴ
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
በአማራ ክልል የገበዉ የአገዛዙ የጠላት ኃይል በሴቶች ላይ የሚፈፅመው ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ።

BBC በአማራ ክልል በ43 ጤና ጣቢያዎች 2697 ተማሪዎች መደፈራቸዉን መዘገቡ ይታወሳል።

ይህ ፀረ አማረረዉ ቡድን በጎንደር አጅሬ ጃኖራ፣ዳባት፣ገደብየ፣ደንቢያ፣ጯሂት፣አርማጭሆ፣በለሳ እና እብናት ብቻ ከ121 በላይ ሴት ልጅ አገረዶችን አስገድዶ ደፍሯል።

ከተደፈሩት መካከል እድሚያቸዉ 50 አመት የሆኑ እናት እና የ12 አመት ታዳጊ ህፃናት ይገኙበታል።በአርማጭሆ ከሶስት ቀን በፊት እድሜያቸው 50 አመት የሆናቸዉ እናት በአገዛዙ ወታደር ተደፍረዉ ወዲያውኑ ህይወታቸዉ ማለፉን ግሎባል ፋኖ ሚዲያ ከስፍራዉ ለማረጋገጥ ችሏል።

በእብናት ወረዳ እብናት ከተማ የ5ኛ ክፍል ተማሪ ታዳጊ ህፃናት በአገዛዙ አረመኔ ሰራዊት ተደፍራ ህክምና እንደገባች የተረጋገጠ ሲሆን የደፈሯት የአገዛዙ ወታደሮች ሚስጥሩ እንዳይወጣ በሚል ልጅቷ ቤተሰቦች እና ለታከመችበት ጤና ጣቢያ ሰራተኞች ማስጠንቀቂያ መስጠታቸዉን ከ
ነጤና ጣቢያው ባለሙያዎች መረጃዉን አጋርተዉናል።

ታዳጊዋ አድሜ 12 አመት እንደሆነችም የህክምና ባለሙያዎቹ ተናግረዋል።በደረሳባት የአስገድዶ መደፈር ጥቃት አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እንደደረሰባት ጭምር አክለዉ ገልፀዋል።

በአጅሬ እና ጃናሞራ 10 ሴት ልጅ አገረዶች ከገቢያ ሲመለሱ የተደፈሩ መሆናቸዉ ተሰምቷል።ከተደፈሩት ዉስጥ 7 የሚሆኑት ባለትዳር ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ ትዳር የሌላቸው መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁ አጅሬ፣ ጃናሞራ እና አካባቢ 35 ተማሪዎች በአገዛዙ ሰራዊት በጭካኔ የተደፈሩ ሲሆን ሁሉም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ናቸዉ።

በገድብየ እና በለሳ እንዲሁም እብናት እና ሊቦከምከም 70 ሴት ልጅ አገረዶች ተደፍረዋል።ከእነዚህ ዉስጥ 47 የሚሆኑት በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ገብተዉ ህክምና የተደረገላቸዉ መሆኑ ተረጋግጧል።17 የሚሆኑት ደግሞ ደብረታቦር አጠቃላይ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ጎንደር ሆስፒታል የታከሙ ናቸዉ።

በደንቢያ እና ጯሂት 5 ተማሪዎች በአድማ ብተና አባላት ብቻ ተደፍረዋል።ጥቃቱ ከደረሳባቸዉ ሶስቱ ወደ ህክምና አልሄዱም ተብሏል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!
የፋኖ ድምፅ!!!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ሕዳር 25/2018ዓ.ም

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ለወራት ያሰለጠነውን የ፩ኛ ኮር ''ቃኝና መሐንዲሥ'' ሰራዊት በደማቅ ሁኔታ አሥመርቋል። የምርቃት መርሐ ግብሩ ሲከወን የበላይ ዕዝ መሪዎች፣ የ፩ኛ ኮር ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የክፍለ ጦር እና ብርጌድ መሪዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።

በመረቃ ስነ ስርዓቱ የአፋብኃ በላይ ዕዝ ከፍተኛ አመራርና የ፩ኛ ኮር አስተባባሪ ግብረ ኃይል አርበኛ አንተነህ ድረስ እና ሌሎች ከፍተኛ የኮርና የክ/ጦር አመራሮች ተገኝተው አስመርቀዋል።

ለተመረራቂዎች እና ለመላ ሰራዊቱ መልዕክት ያስተላለፈው አርበኛ አንተነህ ድረስ አማራዊ አንድነት የድል መሳሪያችን ነው ሲል አፅንኦት በመስጠት ንግግር አድርጓል።

ጋፋት ባንድ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች በማቅረብ የመርሃ ግብሩ ድመቀት የነበረ ሲሆን ተመራቂዎች በስልጠና ያገኙትን አቅም ተጠቅመው ለተሻለ ግዳጅ አፈፃፀም በአካላዊ፣አአዕምሯዊና ስነ ልቦናዊ ክህሎት ብቁ ሁነዋል ሲሉ የስልጠናው አስተባባሪዎች አረጋግጠዋል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
🙏2
ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ድል ተጎናፀፉ::

ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ካራኤላ እና አጣዋ ጋሪያ ላይ ጠላት ኮንክሪት ምሽግ ሰርቶ ከመሸገበት ድረስ ትናትና ህዳር 25/2018 ዓ.ም ምሽት በመግባት በርካታ ሃይሉን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

ጠላት ወደሚመታበትና በጅምላ ወደሚማረክበት ቦታ ተስቦ የገባ ሲሆን በተደጋጋሚ የደፈጣ ጥቃት እየተመታ ሲሆን መካናይዝዱንም ማሸሽ ጀምሯል:: በቀጣይም በደፈጣ እና በሽምቅ ውጊያ የማሰላቸት የማሸማቀቅና የማፍረስ ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥልና ባመች ጊዜ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ወደሚደመሰስበትና ወደሚማረክበት መደበኛ ተጋድሎ በማስገባት ድል እናደርገዋለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 26/2018 ዓ.ም
🙏3
ፋኖ የብልፅግናው ቡድን ቁልፍ የመረጃና ደህንነት አባላት የነበሩ አራት ሰላዮች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

የምድር ኃይል እና የአየር ኃይል በሙሉ አቅሙ ካሰለፈው የብልፅግና አገዛዝ ጋር ገጥሞ ድል እየተቀዳጀ የሚገኘው የፋኖ ኃይል፡ አሁን ደግሞ  የዚኸው ፀረ አማራ አገዛዝ ቁልፍ የመረጃና ደህንነት ሰዎች ናቸው ባላቸው ላይ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ጥብቅ እርምጃ እየወሰደባቸው ይገኛል።

ከቀናት በፊት የራያ ቆቦ ወረዳና የሰሜን ወሎ ዞን መረጃና ደህንነት ቡድን ቁልፍ ሰው የነበረው አቶ ጥጋቡ ደርቤ የተባለ ደህንነት ከነ አጃቢዎቹ መገደሉን መዘገቡ አይዘነጋም።

በራያ ቆቦ ወረዳና በሌሎች የዞኑ አከባቢዎች እየተንቀሳቀሱ "የፋኖ ደጋፊ ናቸው፣ ፋኖን የተቀላቀለ ቤተሰብ አላቸው፣ ብልፅግና ፓርቲን አይደግፉም፣ በየስብሰባው ከመንግስት የሚወርዱ መመሪያዎችን ይተቻሉ" በሚል ንፁኋንን በገፍ ሲያስረሽኑ፣ በጅምላ ሲያሳስሩ የነበሩ አራት ሰላዮች በፋኖ ስናይፐር ጥይት ተመተው ግብአተ መሬታየው ተፈፅሟል።

እነዚህ የመረጃና ደህንነት ቡድን አባላት ንፀኋንን በገፍ ከማስረሸንና ከማሳሰር በተጨማሪ በውጊያ ወቅት የድሮን፣ የመድፍና የሞርተር እንዲሁም የሌሎች ከባባድ መሣሪያዎች አስተኳሽ በመሆን ንፁኋንን ለእልቂት የዳረጉ፡ ታሪክ በጥቁር መዝገቡ በደማቁ ያሰፈራቸው የዘመናችን ባንዳዎች ነበሩ።

በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስር የምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኞች ህዳር 24/2018 ዓ/ም አመሻሹን በራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ቦታው አራዱም ወታደራዊ ካምፕ ዙሪያ ላይ በፈፀሙት የተጠና ጥቃት፡ ጉሽሽ ደረስ የተባለ ሕዝብ ያስለቀሰ ደህንነትን ጨምሮ አራት የመረጃና ደህንነት አባላትን መግደላቸውን ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ ያሳወቀው ዕዙ፡ እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል ገልጿል።

ቆቦ ከተማን ጨምሮ የራያ ቆቦ ወረዳ እና የሰሜን ወሎ ዞን የመረጃ እና ደህንነት አባል በመሆን ንፁኋንን "የፋኖ ደጋፊ ናቸ፡ ፋኖን የተቀላቀለ ቤተሰብ አላቸው" በሚል እያሳፈነ እንዲሁም የድሮን አስተኳሽ በማሰማራት ለአገዛዙ ሲላላክ የነበረው አቶ ጥጋቡ ደርቤ ህዳር 17/2018 ዓ/ም ማለዳ ከነ አጃቢዎቹ በተወሰደበት ጥቃት ሕይወቱ ማለፉን በወቅቱ ጣቢያችን የአይን እማኞችንና ምኒልክ ዕዝን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ አይዘነጋም።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏3
ሐውጃኖ ክፍለጦር የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሪፐብሊካን ጋርድ ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጁ::

ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ከሪፐብሊካን ጋርድ ጋር በመፋለም ከ50 በላይ ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

በተጋድሎው ጠላት ከራያ አላማጣ ጥሙጋ ከተማ ተነስቶ በዙ23 እና ሞርተሮች ታግዞ ወደ ሐውጃኖ ክፍለጦር ቀጠና ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ክፍለጦሯ ሁለት ሻለዎችን ተጠቅማ መልሶ ማጥቃት በማድረግ ከ50 በላይ ሪፐብሊካን ጋርድ ሙትና ቁስለኛ በማድረግና ቀጠናቸውን በማስከበር ጭምር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

በርካታ ሃይሉ የተመታበት የፋሽስቱ አብይ አህመድ የመጨረሻ ምሽግ ሪፐብሊካን ጋርድ ከግራም ከቀኝም ተጨማሪ ሃይል በማያገኝበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ራያ አላማጣ ጥሙጋ ከተማ ት/ቤት ውስጥ በከፍተኛ ድንጋጤና ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ይገኛል::

በሌላ በኩል ለሪፐብሊካን ጋርዱ ተጨማሪ ሃይል ማስገባት ያልቻለው አገዛዙ ሰራዊት ከራያ ቆቦ ጮቢ በር ሆኖ ኦራል ላይ የተጠመዱ ሁለት ቻይና ሰራሽ 155 Mm መድፍ ወደ ራያ ቆቦ ባይባወ እና ኩቢ ቀረንሳ እያስወነጨፈ ንፁሃን ላይ ጉዳት እያደረሰ አምሽቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 25/2018 ዓ.ም
2🙏2
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ የነበረው አቶ ማስረሻ ሰጤ ከቀናት በፊት እጁን ለፀረ አማራው አገዛዝ ሰጥቶ ነበረ።

ትናንት ህዳር 25/2018 ዓ/ም ደግሞ የኢጋድና የአፍሪካ ሕብረት ተወካዮች ተሳትፈውበታል የተባለ የሰላም ስምምነት መፈረሙን የአገዛዙ ልሳናት በሰበር ዜና መልክ ሲዘግቡት ተስተውለዋል።

ማስረሻ ሰጤ ከቀናት በፊት በደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ ለአገዛዙ እጁን ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፡ ከከላላ ወደ ደሴ ከደሴ ወደ ባህርዳር ተወስዶ የስጋ ዘመዱ ከሆነው ከአቶ አረጋ ከበደ ጋር የሰላም ስምምነት በሚል ሲጨባበጥ ታይቷል።

አቶ ማስረሻ ሰጤ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን ወክሎ ነው ከበአዴን ጋር የተደራደረው የተባለ ቢሆንም፡ ነገር ግን ድርጅቱ ከቀናት በፊት ማስረሻ ሰጤን ከየትኛውም ድርጅታዊ ስራዎችና ከአባልነትም ማገዱን አሳውቆ ነበረ።

"የበአዴን የእቃቃ ጨዋታ" በተባለው በዚህ የአንድ ሰውና የበአዴን ድርድር ላይ የኢጋድና የአፍሪካ ሕብረት ተወካዮች መገኘታቸው ብዙዎችን አነጋግሯል።ድርጅቱ አፋህድ አባርሬዋለሁ ካለዉ ግለሰብ ጋር በአፍሪካ ህብረት እና በኢጋድ አደራዳሪነት ከአማራ ክልል መንግስት ጋር ተደራደረ የሚል ዜና መሰማቱ የብአዴንን የቀነጨረ የፖለቲካ አካሄድ በግልፅ ያሳየ ነዉ ተብሏል።

17 ሰዎችን ብቻ ይዞ እጁን በሰጠው ማስረሻ ሰጤ እና በክልሉ መንግስት መካከል ተፈረመ በተባለው ስምምነት ላይ የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ ተወካዮች መገኘታቸውን አስመልክቶ፡ አንዳንዶች "ይህንን የልጆች የእቃቃ ጨዋታ" የሚመስል ጉዳይን እነዚህ ሁለት ተቋማት እንዴት እውቅና ሊሰጡ ቻሉ?" በሚል ግርምታቸውንና ትዕዝብታቸውን ሲገልፁ ተስተውለዋል።

አንዳንዶች ደግሞ ሁለቱ ተቋማት ስለጉዳዩ ጥልቅ መረጃ ሳይኖራቸው ነው በእነ አረጋ ከበደ "እቃ እቃ ጨዋታ" ላይ የተገኙት ሲሉ ትችት ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል።

ሌሎቹ ደግሞ በተለይ በነ ወርቅነህ ገበየሁ የሚመራው ኢጋድ በኦህደድ ብልፅግና የተጠለፈ ስለሆነ፡ በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኘውን ብልፅግናን ለመታደግ የማይፈነቅለው ድንጋይ አለመኖሩን በግልፅ ያሳየ ነው ሲሉ ወቀሳ ሰንዝረዋል።

የአቶ ማስረሻ ሰጤን ድርድር በሚመለከት የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት "አፋህድ በጦርነት እያሸነፈው ካለው አገዛዝ ጋር የፈረመው ስምምነት የለም" በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፡ የማውቀው ነገር የለኝም፡ ባልዋልኩበት ስሜን አታንሱ አይነት ይዘት ያለው መልዕክት አስተላልፏል።

በፋኖ ብርቱ ትግል እየተመታ ለመውደቅ እየተንገዳገደ መያዣውና መጨበጫው የጠፋው የኦህዴድ/ብልፅግና አገዛዝ፣ ከፈረሰ ሁለት ዓመታትን ካስቆጠረው የአማራ ክልል መንግሥት የሙት መንፈስ ጋር የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የ"ሰላም ስምምነት" አደረገ ተብሎ የወጣው መግለጫ ፍፁም ሐሰት ነው ሲል አፋህድ በመግለጫ አሳውቋል።

አፋህድ ከኦህዴድ/ብልፅግናም ሆነ ከአማራ ክልል መንግሥት ተብዬው የሙት መንፈስ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተገናኝቶ ድርድር አድርጎ አያውቅም ያለው ድርጅቱ፡ ከአገዛዙ ጋር የምንገናኘው በጦር ሜዳ ላይ ብቻ ነው ሲል ገልጿል።

ድርጅቱ በመግለጫው፡ በአፋህድ በኩል ስምምነት ፈረመ የተባለው ማስረሻ ሰጤ፣ ከአገዛዙ ጋር ተልዕኮ ተቀብሎ ሲንቀሳቀስ ተደርሶበት ከአመራርነት እና አባልነት የታገደ መሆኑን በዚህ ሳምንት ባወጣው  መግለጫ መግለፁን ያስታወሰ ሲሆን፡ ከአገዛዙ ጋር ሲቀላቀልም፣ ለስራ ተብሎ የተላከለት በርካታ ያልተወራረደ የህዝብ ገንዘብ በእጁ እንደሚገኝ እና "የሰላም ስምምነቱን" ለዘረፋ ሽፋን ለማድረግ ከአገዛዙ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲል አሳስቧል።

በምናባዊ ዓለም ተደረገ በተባለው ድርድር ተገኝተዋል የተባሉት የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ በቀጣይ ቀናት ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጡ ጥሪ እናቀርባለን ነው ያለው አፋህድ በመግለጫው።

አፋህድ በመግለጫው፡ አገዛዙ ሰሞኑን በተለያዩ በበሬ ወለድ ዜናዎች የሚፈራገጠው የፋኖ አንድነት ለማደናቀፍ ብሎ መሆኑን ህዝብ ተገንዝቦ፣ በቀጣይነት የምናወጣቸውን መግለጫዎች እንዲጠባበቅ እናሳስባለን ሲልም መልዕክት አስተላልፏል።

በተያያዘ ዜና!

የአፋብኃ እና የአፋሕድ የአንድነት ጉዞ እየሰመረ መሆኑ ተሰምቷል።

ሁለቱም ድርጅቶች "ለአንድ ዓላማ እየታገልን በተናጠል የምናደርገው ጉዞ ከጥቅሙ ጉዳቱ እያመዘነ በመሆኑ፡ አንድነታችን ለአማራ ህዝብ ነፃ መውጣት አማራጭ የሌለው ብቸኛ መንገዳችን ነው" በሚል በቅርቡ አንድነታቸውን እንደሚያበስሩ ነው የተሰማው።

የሁለቱ ድርጅቶች ወደ አንድ መምጣት ያስጨነቀው አገዛዝ ስርዓቱ፡ ከወዲሁ ሊያሰናክሉልኝ ይችላሉ ያላቸው እኩይ ተግባራት ላይ ተጠምዷል።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
💔1
ከመቶ በላይ ጠላት ተደመሰሰ!!

ልማደኛው ደጃዝማች 4ኛ ኮር በመተማ ወረዳ ሽመለ ጋራ ቀበሌ በቀን 25/32018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ቀበሌ ሆርጃሙስ ክሬቸሩ እና ቁጥር 1መዉጫ አዲስ አለም አካባቢ በ3 አቅጣጫ የመጣዉን ፋሽሽቱ አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጠንካራ ጥቃት በመክፈት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል።
ከ6 ክፍለ ጦር የተዉጣጣ የበላይ ዕዝ 4ኛ ኮር ሰራዊት በወሰደዉ የተሳካ ማጥቃት ከ100 በላይ ሲደመሰስ ከ55 በላይ ቁስለኛ ሁኗል።
በተጨማሪም ሲጓጓዙበት የነበረው ተሽኸርካሪ በተሰነዘረበት ጥቃት ከጥቅም ውጭ ሁኗል።

በላይ ዕዝ በጀመረው ጥልቅ የማጥራትና የማረም ስራ ተሞርዶ ስሉ እየሆነ የሚገኘው ደጃዝማች ኮር ይህን ውጤታማ የድምሰሳ ውጊያ ግዳጅ ሲፈፅም ያለ መስዕዋትነት ነው።

ፈህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
ህዳር 26/2018 ዓ.ም
1🙏1