ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አገዛዙ በጎንደር ከተማ የሰላም ጥሪ በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በአስገዳጅ ሁኔታ እንዲካሄድ አድርጓል።

በአገዛዙ የተጠራዉ የከተማዋ ህዝብ ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ አላዳመጠዉም ነበር።ነገር ግን አገዛዙ ብልፅግና በሴፍትኔት የታቀፉ እና ከመስጅድ እንዲሁም ከቤተክርስቲያን የከተማዋን ኗሪዎች አፍሶ ወደ አደባባይ ወተዉ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል።

የአገዛዙ ምስለኔ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከለሊቱ 10:00 ጀምሮ በሁሉም የከተማዋ በቤተክርስቲያን ተገኝቶ ወደ ቤተክርስቲያን የመጣዉን ምዕመን አስገድዶ ሰልፍ አስወጥቷል።

የከተማዋን የሙስሊም ማህበረሰብ ደግሞ ለዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም በጧቱ በመስጂድ እንዲገኙ ካደረገ በኋላ በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ አደባባይ እንዲወጡ አድርጓቸዋል።

በዚህ ሰልፍ በማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ብዙ ተከታይ ያላቸዉ ግለሰቦች እንዲጋበዙ ተደርገዋል።"ከተማዋ ሰላም ናት" የሚል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሊጀመር እንደሆነ እና ብዙ ተከታይ ላላቸዉ የማህበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች ደግሞ ረብጣ ገንዘብ እንደማከፈላቸዉ ቃል ተገብቶላቸዋል።

ነገር ግን አሁንሞ በከተማዋ ዉስጥ የወጣቶች አፈሳ፣አስገድዶ መድፈር፣ዘረፋ፣እገታ እና ሌሎችም ወንጀሎች በአገዛዙ ጥምር ጦር የሰራዊት አባላት እየተፈፀሙ ቀጥለዋል።

በጎንደር ከተማ የብልፅግና ተወካዮች ግን በማህበረሰቡ የማፈፀሙ ወንጀሎችን ለመደበቅ አስገድዶ ሰላማዊ ሰልፍ እና በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ተከታዮች ባለቸዉ ግለሰቦች ለማስተባበል ሞክሯል።

@ግሎባል ፋኖ ማዲያ
የፋኖ ድምፅ!!!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
የደፈጣ ጥቃት ተፈፀሞ ሁለት ፓሊሶች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ እና74ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ገዳያሱ ቀበሌ እና መርጦ ለማራይም ከባድ ተጋሃድሎ ሲያካሂድ አድሯል።

በሸበል በረንታ ወረዳ ወፍትማ ጎጥ ህዳር 24/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በነበረው የጨለማ የጨበጣ ውጊያ በረካታ የአረመኔዊ ሰራዊት አባላት ሲደመሰስ በረከት ታደሰ የሚባል1 የአገዛዙ ሰራዊት አባል በንስሮች የበላይ ዘለቀ ልጆች እና የሽፈራው ገርባው ልጅች የተማረከ ሲሆን መርጦለማርያም ላይ ሁለት ፓሊሶችላይ እርምጃ በመውሰድ ጀብድ ሰርቶ መውጣት ተችሏል። በውጊያ የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮችእና ጥምር ጦሩ እና1ኛ እሪጅመንት እና የሸበል በረንታ ደጀኑ ህዝባችን ተሳትፈዋል።

ህዳር 25/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ ፣ዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏2
ሩሲያ ግብረ ሰዶምን በሸብር ዝርዝር ውስጥ አስገባች

#ቢዝነስሚዲያ l ሩሲያ የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴን በአክራሪነት እና ሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ ማከተቷ ተሰምቷል፡፡

የተመሳሳይ ጾታ እንቅስቃሴ አራማጆች በአክራሪነትና በአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሩሲያ ሚዲያዎች ዘገባ ያመላክታል፡፡

ውሳኔው የግብረ ሰዶማዊያን እና ትራንስጀንደር ተወካዮችን ለእስር እና ለሽብርተኝነት ቅጣት የሚዳርግ ነው ተብሏል፡፡

የሩሲያ ውሳኔ ዓለም አቀፍ የግብረ ሰዶም ማኅበራት እንቅስቃሴ እና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን ጭምር ይመለከታል ተብሏል፡፡ በሩሲያ ምድር የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴ ማድረግ ከዚህ በኋላ በሸባሪነት አስከስሶ ዘብጥያ የሚያስወርድ ከባደ ወንጀል ሆኗል፡፡

በአገሪቱ የግብረሰዶማዊ እንቅስቃሴን የሚደግፉና የሚያስፋፉ አካላት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ይነገራል፡፡

የእንቅስቃሴው አራማጆች መሰረት ሩሲያ ባላንጣ ካደረገቻ ቸው ከእነ አሜሪካና አውሮፓ ምድር የሚነሳ መሆኑ ደግሞ የቭላድሚር ፑቲንን አስተዳደር አስቆጥቷል፡፡

እንደ አሜሪካ ያሉ አገራት የግብረ ሶዶማዊያን እንቅስቃሴን እንደ መብት ቆጥረው እያስፋፋት ነው፡፡ ግብረ ሶዶማዊያነት ከምዕራቡ አለም አልፎ እስከ አፍሪካ የዘለቀ ሲሆን፣ አንዳንድ አገራት እንስቅቃሴውን በሕግ እያገዱ ነው፡፡


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
👍5👏1
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል አፋብኃ እና የአማራ ህዝባዊ ድርጅት አፋህድ በጋራ ባደረጉት አዉደዉጊያ ታላቅ ድል ፈፅመዋል።

ከቅርብ ጊዜህ ወዲህ አንድነት ላይ መሰረት ያደረገ አዉደዉጊያ እያደረጉ ሲሆን በምስራቅ አማራ ቀጠና እና በደቡብ አማራ ቀጠና በተደጋጋሚ ጊዜ በጋራ አዉደዉጊያ አድርገዉ ድል አስመዝገበዋል።

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር እና የአፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዓፄ ዐምደፂዮን ኮር የተውጣጣ የፋኖ ኃይል በምዕራብ ወሎ ግንባር ከላላ ወረዳ ውስጥ ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፅመዋል።

በቅንጅት በተሰራው ኦፕሬሽን ከ20 በላይ ጠላት የተማረከ ሲሆን ጠላት 3 መኪና የሚሆን ሙት እና ቁስለኛ ጭኖ ፈርጥጧል:: በትናንትናው እለት በደገር ግንባር የተጀመረው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በስተመጨረሻ ፋኖ ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏታል::

ከዚህ በተጨማሪ ከደገር ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኙት ቲርቲራ እና ቆርኬ ታዳጊ ከተሞችም በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል::

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ትንቅንቅ በቲርቲራ በኩል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሳ ተሾመ ሻለቃ ጠላትን ሲያስፈረጥጠው ቆርኬ ላይ ደግሞ የዚሁ ክፍለ ጦር አካል የሆነችው 2ተኛ እንድሪስ ተሾመ ሻለቃ ታሪክ ሰርታለች:: የፋኖዎችን ምት መቋቋም ያቃተው ጠላት ከቲርቲራ ጎራ ወርዶ እየፈረጠጠ ተጉዞ ቀነሶ መንደር ሲደርስ አቶ ሁሴን ከማል የተባለ ገበሬን በአጨዳ ላይ ሳለ እረሽኖታል::

በቆርኬ ግንባር 17 የጠላት ኃይል የተመታ ሲሆን 5ቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ 12ቱ ቁስለኛ ሆነዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር በጃማ ግንባር በተለይም በአቦልድ፣ ዘርቃሚ እና ደጎሎ በኩል የጠላትን አከርካሪ መስበሩ ተረጋግጧል:: የወረዳው መቀመጫ የሆነችው ደጎሎ ከተማ እስከ ዛሬ ጧት ድረስ በተኩስ ስትናጥ እንደነበረ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል:: ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ የዋሲል ክፍለ ጦር 2ተኛ መብረቅ ሻለቃ አባላት ጠላትን እረፍት ነስተውት ሰንብተዋል:: በዚህ የተበሳጨው ጠላት ከአረብ ሀገር ከመጣች 1 ወር በትክክል ያልሞላትን እህታችንን መረሸኑም ታውቋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
2🙏2
የአደረጃጀት ዜና

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር የአመራር ሪፎርም አደረገ::

ቀናትን የፈጀ ውይይት እና ግምገማ ከተደረገ በኋላ አዳዲስ አመራሮች የተሰየሙ ሲሆን ከነባሮች የኃላፊነት ርክክብ አድርገዋል::

የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ በተገኘበት የተካሄደው የውውይት እና ግምገማ መድረክ በስኬት መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን ጉባኤተኞች ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን አርበኞች የክፍለ ጦሩ አመራሮች አድርገው መምረጣቸውን ነው ከስፍራው የደረሰን መረጃ የሚያመላክተው:: በዚህም፦

1ኛ. አርበኛ ስንደው ገዜ - የክፍለ ጦሩ አዛዥ
2ኛ. አርበኛ ዱቤ አሻግሬ - የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ
3ኛ. አርበኛ ንጉሥ ጌታቸው - ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
3.1. አርበኛ መብሬ ጫብሲ - ዘመቻ መምሪያ ምክትል ኃላፊ
4ኛ. አርበኛ መብሬ ምስጌ - ወታደራዊ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ
5ኛ. አርበኛ ደምሰው ጎቼ - ሎጀስቲክ ሃላፊ
6ኛ. አርበኛ ደመቀ አረጋ - የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ
7ኛ. አርበኛ አስማማው ፈንታው - የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
8ኛ. አርበኛ ጀንበሩ ጌታቸው - ስልጠና መምሪያ ኃላፊ

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏2
የአውደ ውጊያ መረጃ

ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ባጃ ከተማን ተቆጣጠረ።

ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካሎች ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ፣ ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ፣ የመብረቅ ክ/ጦር 2 ብርጌዶች አንድ ላይ በመቀናጀት ከጓህላ መጥቶ ባጃ ከተማ ላይ የሰፈረውን የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት በፊት ለፊት ውጊያ እያሯሯጡ ሲያደባዩት አርፍደዋል።

በዚህ ፈጣን ውጊያ ከምሽግ ምሽግ እየዘለሉ በመግባት የጠላትን ኃይል ሰፍሮበት የነበረውን ካምኘ ወዲያውኑ መቆጣጠር የቻሉ ሲሆን ጠላትም የወገንን ከፍተኛ ምት መቋቋም ባለመቻሉ ከተማዋን ለአናቭስቶቹ ፋኖዎች አስረክቦ እግሩ ወዳመራው አቅጣጫ ፈርጥጧል።

🔸 ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ሸማቂው ብርጌድና መብረቅ ክ/ጦር ብርጌዶች ከሊቦ ባጃና ከሚካኤል ደብር ባጃ የሚወስዱ ቁልፍ ቦታዎችን በመዝጋት የጠላትን ኃይል እንዳይቀሳቀስ ማድረግ መቻላቸው ታውቋል።

ውጊያው ለ8 ሰዓታት ያህል የቆየ ሲሆን በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛም ተደርጓል።

🔸 በዚህ እልህ አስጨራሽ ውጊያ 15 እስከ ወዲያኛው የተሸኙ 19 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ቁስለኛ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን አርባያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በቁስለኞች ለቅሶና ዋይታ ተጨናንቆ እንደሚገኝም የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል።

🔸 አምቦ ሜዳ ከተማ ላይ በአርበኛ በላያ ጌቴ የምትመራውን ንጉሱ መልዛ ብርጌድና የአፄ እያሱ ክ/ጦር የተወሰኑ አባላትን ለማጥቃት ወደ ከተማዋ የመጣው የጠላት ኃይል መመታቱም ተገልጿል።

ድምሰሳ ለመፈጸም አቅዶ የመጣው ጠላት ከ5 በላይ አባላቱ ክፉኛ ቆስሎበት ወደመጣበት እንዲመለስ አድርገውታል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ

ህዳር 25 /2018 ዓ.ም
🙏31
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የአገዛዙ ጥምር ሀይል መነሻውን ከአለፋ ወረዳ ሻሁራና አፀደማርያም ከተማ ፣ ከሰሜን አቸፈር ሊበን ከተማ እና ከቋራ ወረዳ ደለጎ በማድረግ ወደ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የተንቀሳቀሰው ሃይል ላይ ከፍተኛ ርምጃ ወሰደ::

ሰሞንኛ አጀንዳው ፋኖን በየቀጠናው አፅድቻለሁ በህዝቡ ላይም የተሻለ ቅቡልነት አግንቻለሁ እያለ ቅዠት ላይ ያለ ቢሆንም አሁን ላይ በጨለማ በመንቀሳቀስ የአርሶ አደሩን ትጥቅ ለማስፈታት እና ዘረፋ ለመፈፀም አቅዶ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ፣ ማህበረሰቡ ከፋኖ ሀይል ጋር መረጃ ቀድሞ በመለዋወጥ ከፋኖ ጎን በመሆን በሁሉም ቀጠና ማለትም በአለፋ ወረዳ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የፋሽስት ሰራዊት አድዋ ክ/ጦ ከማህበረሰቡ ጋር በመጣመር የጠላትን እቅድ ከማክሸፍ ባሻገር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ተችሏል::

ከደለጎ ከተማ ተነስቶ ወደ ኮሩ ቀጠና የገባው በቋራ ኦሜድላ ነብሮ ብርጌድ አማካኝነት በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ በትር ማሳረፍም ተችሏል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የፋኖ ሀይል አሰላለፉን በመቀያየር የአገዛዙን ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት መግቢያ መውጫ እያሳጣው ይገኛል።አውደ ውጊያው አሁንም እንደ ቀጠለ ይገኛል አህዛዊ የድል ዜናዎችን በቀጣይ የዜና ጥንቅራችን የምናቀርብ ይሆናል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ህዳር 25/2018
🙏3
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ24 ስዓት የውሎ ዘገባ

__፩
የአማራን ሕዝብ ከምድረገፅ ለማጥፋት በሰማይም በምድርም የሚንቀሳቀሰው የብልፅግና ሰራዊት ባላሰበው መልኩ በየቀጠናው ከባድ ኪሳራን አስተናግዷል።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ሰከላ ላይ በወሰደዉ እርምጃ የሰከላ ወረዳ አስተዳድር ዋና ባንዳ #ይልማ_ጥላሁን ጨምሮ ከሁለት ደርዘን በላይ የሚነሻና የመከላከያ አባላት ተወግዷል።

የስቦ መምታት ጥበበኞች 44ኛ ክፍለ ጦር  ጠላትን #ከሰከላ #ከማንኩሳና #ከቡሬ በመተንኮስ ወደ ቀጠናቸዉ  ድረስ ሰተት አድርገዉ በማስገባት #ሰከላ ላይ የቀረዉን ሰፈር ጠባቂ፣ ዘራፊ ሚኒሻና ሆድ አደሩን የብልፅግና አመራር መሃል ሰከላ ላይ አራምጠዉታል።

"ፋኖን ባለበት አሳድጄ አጠፋዋልሁ" እያለ ሲፎክር የነበረዉ ዋና አስተዳድር እና አምስት ሚኒሻ ሲማረክ ብዛት ያለዉ ሰራዊት ደግሞ እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል።

አረመኔው ቡድን በአጉትና ባሽፋ ከማንኩሳ ፔንፔ፣ዘ_23 ከሰከላ ግትልትል ሰራዊቱን በማስከተል #ምላስና #ብልት በመቁረጥ የስድስት ንፁሃንን ህይወት በቀጠፈበት ቀጠና እየተልከሰከሰ የባህር ኩበት በሆነበት ሰሃት ጀግኖቹ የ44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች ሰከላ ከተማ የሚገኘውን የብልፅግና ጦር በመቀጥቀጥ #12 ክላሽንኮፍና በሺዎች የሚቆጠር ተተኳሽ ማርኳል።

ከዚህ በተጨማሪ መንግስታዊ ስርዓት አስቀጥላለሁ በሚል ሃሳዊ ህልም ሲገለገልባቸዉ የነበሩ ኮምፒወተሮችና ላብቶቦች ማተሚያ ማሽኖች ሲማረኩ፤ የወረዳዉ መገልገያ ተቋም በሙሉ ፓትሮሎችን ጨምሮ ከጥቅም ውጭ ሁኗል።

ከተማዋ ላይ የተሰገሰጉ በመረጃነት የሚያገለግሉ እንቁላል ቀቃይ ባንዳዎች መዉጫ መግቢያ ጠፍቷቸዉ ብዙዎቹ ተሸኝተዋል።

ቁሞ መግጠም ያልቻለዉ አረመኔ ቡድን ከተለያ የቦታ እያፈነ እስረኛ ያደረጋቸዉን የሰከላ ወረዳ 25 ንፁሃን እስረኞችን ጭምር ከአረመኔዉ መንጋጋ ማስለለቅ ተችሏል።



_____፪
በ109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋ ዳሞት ወረዳ ልዮ ስሙ ደልሙ በሚባል ቦታ ላይ የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በርካታ ኪሳራን አስተናግዷል።

የግለሰብ የግል ፍላጎት ላይ የተመሰረተው እና የአማራን ማጥፍት ተልኮ በመያዝ ወደ ደጋ ዳሞት ደልሙ ሲደርስ በአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ያላሰበው ወረጅብኝ ገጥሞታል ።
በዚህ ምት የተደናገጠው የብርሃኑ ጁላ ወታደር ሞርተር እና ዲሽቃ ቢጠቀምም 99ኛ ክፍለጦር በርካቶችን በመደምሰስ ታሪክ ሰርቷል።


__

በ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ሊዲና አካባቢው ቀበሌ እንዲሁም ገዳያሱ ቀበሌ ከባድ ተጋሃድሎ ሲያካሂድ አድሯል።

በሸበል በረንታ ወረዳ በሊዲና አካባቢው ወፍትማ ጎጥ ህዳር 24/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በነበረው የጨለማ የጨበጣ ውጊያ በረካታ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላት ደፈጣ ውስጥ በማስገባት ሙት እና ቁስለኛ ሲሆኑ በረከት ታደሰ የሚባል 1(አንድ) የአገዛዙ ሰራዊት አባል በንስሮች የበላይ ዘለቀ ልጆች እና የሽፈራው ገርባው ልጅች ተማረኳል።

በሌዲና አካባቢው ወፍትማ ጎጥ በተካሄደው የጨለማ የጨበጣ ውጊያ የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር፣በክፍለ ጦር ስር የምትገኘው 1ኛ እሪጅመንት እና የሸበል በረንታ ደጀኑ ህዝባችን በመሳተፍ የጠላትን ሀይል መበታተን ችለዋል።



___፬
በ201ኛ ኮር የ74ኛ ክፍለጦር በእነብሴ ሳርምድር ባደረገው ተጋድሎ በርካታ የጠላት ሰራዊት ሲደመሰስ አስክሬናቸውን መርጡለማርያም ኮሌጅ ውስጥ በጅምላ ቀብሯቸዋል።

ከሰሞኑ በበርካታ አካባቢዎች የንፁሃን አርሶአደሮችን ሰብል በማቃጠል እና በመዝረፍ ፣ መንገደኞችን በማገት ከ100 - 200 ሺህ ብር ድረስ እየጠየቀ እየቀማ እና እየዘረፈ ሲሆን የመክፈል አቅም የሌላቸውን ደግሞ በአደባባይ እየገደላቸው ይገኛል ።

ከወትሮው አማራን ለመጨፍጨፍ እና ለመዝረፍ ወደክልሉ የገባው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ለተከታታይ 28 እና ከዛ በላይ ወራት ሲያደርግ የነበረውን የአስገድዶ መድፈር ፣ የንፁሃን ጭፍጨፋ ፣ የሐብት ንብረት ዘረፋና ውድመት ከሰሞኑ በእጅጉ አጠናክሮ ቀጥሏል።

በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የነበረውን ተጠባባቂ ሀይሉን በብዛት በማስገባት ወደገጠራማ አካባቢዎች ለማስፋት እያደረገ ያለው ሙከራ በጀግናው ፋኖ ብርቱ ክንድ እየከሸፈበት ያለው የአገዛዙ ሰራዊት የአርሶአደር ሰብል መዝረፍን እና ማቃጠልን የከተማውን ማህበረሰብ በእገታ እና በኢሰብዓዊ ድርጊቶች መመዝበሩን ቀጥሎበታል ።

አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ

አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ህዳር 25/2018 ዓ.ም
🙏1
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር

በዛሬው እለት የአገዛዙ ጥምር ሀይል መነሻውን ከአለፋ ወረዳ ሻሁራና አፀደማርያም ከተማ ፣ ከሰሜን አቸፈር ሊበን ከተማ እና ከቋራ ወረዳ ደለጎ በማድረግ ወደ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የተንቀሳቀሰ ሲሆን ሰሞንኛ አጀንዳው ፋኖን በየቀጠናው አፅድቻለሁ በህዝቡ ላይም የተሻለ ቅቡልነት አግንቻለሁ እያለ ቅዠት ላይ ያለ ቢሆንም አሁን ላይ በጨለማ በመንቀሳቀስ የአርሶ አደሩን ትጥቅ ለማስፈታት እና ዘረፋ ለመፈፀም አቅዶ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ፣ ማህበረሰቡ ከፋኖ ሀይል ጋር መረጃ ቀድሞ በመለዋወጥ ከፋኖ ጎን በመሆን በሁሉም ቀጠና ማለትም በአለፋ ወረዳ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የፋሽስት ሰራዊት አድዋ ክ/ጦ ከማህበረሰቡ ጋር በመጣመር የጠላትን እቅድ ከማክሸፍ ባሻገር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ሲቻል ከደለጎ ከተማ ተነስቶ ወደ ኮሩ ቀጠና የገባው በቋራ ኦሜድላ ነብሮ ብርጌድ አማካኝነት በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ በትር ማሳረፍ ተችሏል። ይህ በንዲህ እንዳለ የፋኖ ሀይል አሰላለፉን በመቀያየር የአገዛዙን ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት መግቢያ መውጫ እያሳጣው ይገኛል።አውደ ውጊያው አሁንም እንደ ቀጠለ ይገኛል አህዛዊ የድል ዜናዎችን በቀጣይ የዜና ጥንቅራችን የምናቀርብ ይሆናል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ህዳር 25/2018
3🙏1
አፋህድ በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ ካላወጣ ነገሩን ዉስብስብ ያደርገዋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡ ስምምነቱን የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር አረጋ ከበደ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን በመወከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተፈራርመዋል።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
የአፋህድ አስቸኳይ መግለጫ

"አፋህድ በጦርነት እያሸነፈው ካለው አገዛዝ ጋር የፈረመው ስምምነት የለም!!!"

በፋኖ ብርቱ ትግል እየተመታ ለመውደቅ እየተንገዳገደ መያዣውና መጨበጫው የጠፋው የኦህዴድ/ብልፅግና አገዛዝ፣ ከፈረሰ ሁለት ዓመታትን ካስቆጠረው የአማራ ክልል መንግሥት የሙት መንፈስ ጋር የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የ"ሰላም ስምምነት" አደረገ ብሎ ዛሬ ረፋዱን ያወጣው መግለጫ ፍፁም ሐሰት ነው።

አፋህድ ከኦህዴድ/ብልፅግናም ሆነ ከአማራ ክልል መንግሥት ተብዬው የሙት መንፈስ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተገናኝተን ድርድር አድርጎ አያውቅም። ከአገዛዙ ጋር የምንገናኘው በጦር ሜዳ ላይ ብቻ ነው።

በምናባዊ ዓለም ተደረገ በተባለው ድርድር ተገኝተዋል የተባሉት የአፍሪቃ ህብረት እና ኢጋድ በቀጣይ ቀናት ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናቀርባለን።

በአፋህድ በኩል ስምምነት ፈረመ የተባለው ማስረሻ ሰጤ፣ ከአገዛዙ ጋር ተልዕኮ ተቀብሎ ሲንቀሳቀስ ተደርሶበት ከአመራርነት እና አባልነት የታገደ እና የተባረረ መሆኑን በዚህ ሳምንት ባወጣነው መግለጫ መግለፃችን ይታወሳል። ከአገዛዙ ጋር ሲቀላቀልም፣ ለስራ ተብሎ የተላከለት በርካታ ያልተወራረደ የህዝብ ገንዘብ በእጁ እንደሚገኝ እና "የሰላም ስምምነቱን" ለዘረፋ ሽፋን ለማድረግ ከአገዛዙ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

አገዛዙ ሰሞኑን በተለያዩ በበሬ ወለድ ዜናዎች የሚፈራገጠው የፋኖ አንድነት ለማደናቀፍ ብሎ መሆኑን ህዝብ ተገንዝቦ፣ በቀጣይነት የምናወጣቸውን መግለጫዎች እንዲጠባበቅ እናሳስባለን።

ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት!!!

ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
/
ህዳር 25፣ 2018 ዓ.ም።
2