ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ወልዲያ ከተማ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የዓብነት ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ታፍሰው መወሰዳቸው ታወቀ


በቅርብ ወራት በበርካታ ከተሞች ውስጥ ወጣቶች ከየመንገዱ እና ከስራ ቦታ እየታፈሱ ለስልጠና ወደ ካምፖች እየገቡ እንደሆነ በተደጋጋሚ ያወጣናቸው መረጃዎች ጠቁመዋል።

አሁን ከወደ ወልዲያ የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው በርካታ የዓብነት ተማሪዎች ባሳለፍነው ሳምንት ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ታፍሰው ተወስደዋል።

ስልካቸውን ከተቀሙ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት በሚሊሻዎች የተወሰዱት የዓብነት (የቤተክርስቲያን) ተማሪዎቹ በወልዲያ ከተማ የሚገኘው የቲንፋዝ ደብረ በረከት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርሰቲያን እና የሌሎች ቤተክርስቲያኖች ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል።


ቲንፋዝ ደብረ በረከት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርሰቲያን

"ቤተ ክርስቲያኒቱ ተማሪዎቹ እንዲለቀቁ በደብዳቤ ብትጠይቅም እስካሁን ምላሽ አልተገኝም። አፍነው የወሰዱት የሚሊሻ አባላቱ በወሰዱት በእያንዳንዱ ተማሪ 7 ሺህ ብር እየጠየቁ ይገኛሉ" በማለት አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ እና ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ምንጫችን ጠቁመዋል።

ሚድያችን የደረሰው ተጨማሪ መረጃ እንደሚያሳየው ታግተው የተወሰዱት ተማሪዎች ከቲንፋዝ ደብረ በረከት ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር ሶስት፣ ከፒያሳ መንበረ ንግስት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ደብር አምስት፣ ከተማው ውስጥ በሚገኙ ሌሎች ደብር የሚማሩ አስራ አምስት ናቸው።

"በአጠቃላይ ከሃያ ሶስት በላይ ተማሪዎች ተወስደዋል። አሁን ላይ በከተማው ውስጥ በሚገኝ አንድ ቀበሌ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ከቤተክርስቲያን አካባቢ ሰምተናል" በማለት ሌላኛ የከተማው ነዋሪ ተናግረዋል።

ባሳለፍነው ሀሙስ ከተያዙት ተማሪዎች መካከል አንደኛው አርብ ለማምለጥ ሲሞክር ከሚሊሻ በተተኮሰበት ጥይት ተመትቶ ከፒያሳ ወደ ቲንፋዝ በሚወስደው መንገድ ላይ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል።

"ተማሪዎቹ ወደየት ይሂዱ? ገጠር ቤተሰብ ጋር ሲሄዱ ፋኖ ይወስዳቸዋል፣ ከተማ ሲሆኑ ሚሊሻ ይወስዳቸዋል። ፖሊሶች ሲጠየቁ እኛ የለንበትም፣ የምናውቀው ነገር የለም ይላሉ" በማለት ምንጫችን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ታፍሰው ከተወሰዱ በኋላ ነፃ ለመሆን እስከ 1 ሺህ ዶላር እየተጠየቁ መሆኑ ሚድያችን ከተያዥ ቤተሰቦች ሰምቷል።

"ከአሁን ቀደም ወጣቶቹን የደህነነት ስጋት ነው፣ አጣርተው እንለቃለን ብለው ይለቋቸው ነበር። አሁን ግን እስከ አንድ ሺሕ ዶላር እየተጠየቅን ነው። ገቢው ለማነው? ምክንያቱስ ምንድነው? ፖሊስ ጣቢያዎች በገንዘብ ሊቀጡ ይችላሉ ወይ? የሚቀጡትስ በዜግነታቸው ነው ወይ?" በማለት ጥያቄ ያቁርባሉ።

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ በአዲሱ ሸገር ሲቲ ፉሪና ኬንቴሪ አካባቢ ወጣቶች እየተያዙ የቀድሞ ፍፁም በላይ ሆቴል እና ወጣቶች ማዕከል ውስጥ እየታሰሩ መሆኑም ታውቋል። ብዙዎች ከክፍለ ሀገር ስራ ፍለጋ የመጡ መሆናቸው የታወቁ ሲሆን ቤተሰብ ለማስለቅ ከ30 ሺህ ብር እስከ 50 ሺህ ብር እየተጠየቁ መሆኑን ሰምተናል።

-መሠረት ሚድያ-

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ሕዳር 24/2018)

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
💔21
በአገዛዙ ሰራዊት ላይ በተጠና የደፈጣ ውጊያ ሙት እና ቁስለኛ ተደርጓል።

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ሊዲና ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢው እና ገዳያሱ ቀበሌ ከባድ ተጋሃድሎ ሲያካሂድ አድሯል።

በሸበል በረንታ ወረዳ በሊዲና አካባቢው ወፍትማ ጎጥ ህዳር 24/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በነበረው የጨለማ የጨበጣ ውጊያ በረካታ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላት ደፈጣ ውስጥ በማስገባት ሙት እና ቁስለኛ ሲሆኑ በረከት ታደሰ የሚባል 1(አንድ) የአገዛዙ ሰራዊት አባል በንስሮች የበላይ ዘለቀ ልጆች እና የሽፈራው ገርባው ልጅች ተማረኳል።

ከቢቸና ከተማ የዕዱኃ ከተማ መረገጭ ከተማ የተሰባሰበው  የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ፋኖን እንደመስሳለን በሚል ቅዥት  ወደ ሊዲና አካባቢው ቀበሌ መሪ ጎጥ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም በፋኖ ሀይሎች በተወሰደው የጨለማ ጨበጣ ደፈጣ ውጊያ ተደምስሶ ወደ መረገጭ ከተማ እየፈረጠጡ ሄደዋል።

በሌዲና አካባቢው ወፍትማ ጎጥ በተካሄደው የጨለማ የጨበጣ ውጊያ የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር፣በክፍለ ጦር ስር የምትገኘው 1ኛ እሪጅመንት እና የሸበል በረንታ ደጀኑ ህዝባችን ተሳትፏል ሲል አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ይበልጣል ጌቴ መረጀዉን አድርሶናል።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
👍1
የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ የመረጃና ደህንነት እንዲሁም የመከላከያ መንገድ መሪ የሆኑ ባንዳዎች ራያ ቆቦ አራዱም ወታደራዊ ካምፕ ላይ እርምጃ ተወሰደባቸው::

የራያ ቆቦ ወረዳ መረጃ እና ደህንነት፣ የመከላከያ መንገድ መሪ፣ እንዲሁም ንፁሃን አማራዎችን በማሳፈንና በማስረሸን ብሎም ወጣቱን በሃይል በማስገደድ ወደ መከላከያ በማስገባት የባንዳነት ተግባር ሲፈፅሙ የኖሩት የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ ሰዎችና ሆድ አደር የራያ ቆቦ ወረዳ ካድሬና ሚሊሻዎች በሰማዕቶቹ ጀግኖች በነ አርበኛ አለሙ ገብሩ በነ አርበኛ ዋሴ ከበደ በነ አርበኛ ፍሬው አለና እና ሌሎች አርበኞች ልጆች በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል::

ከአማራ ህዝብ ተፈጥረው ከፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ጋር በመተባበር የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙ የኖሩት ሆድ አደሮች አቶ ጉሽሽ ደረስን ጨምሮ አራት ባንዳዎች ህዳር 24/2018 ዓ.ም ራያ ቆቦ አራዱም ወታደራዊ ካምፕ ላይ በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች እርምጃ ተውስዶበታል:: በቀጣይም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኘነት መምሪያ ኃላፊ!!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏1
አገዛዙ በጎንደር ከተማ የሰላም ጥሪ በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በአስገዳጅ ሁኔታ እንዲካሄድ አድርጓል።

በአገዛዙ የተጠራዉ የከተማዋ ህዝብ ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ አላዳመጠዉም ነበር።ነገር ግን አገዛዙ ብልፅግና በሴፍትኔት የታቀፉ እና ከመስጅድ እንዲሁም ከቤተክርስቲያን የከተማዋን ኗሪዎች አፍሶ ወደ አደባባይ ወተዉ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል።

የአገዛዙ ምስለኔ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከለሊቱ 10:00 ጀምሮ በሁሉም የከተማዋ በቤተክርስቲያን ተገኝቶ ወደ ቤተክርስቲያን የመጣዉን ምዕመን አስገድዶ ሰልፍ አስወጥቷል።

የከተማዋን የሙስሊም ማህበረሰብ ደግሞ ለዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም በጧቱ በመስጂድ እንዲገኙ ካደረገ በኋላ በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ አደባባይ እንዲወጡ አድርጓቸዋል።

በዚህ ሰልፍ በማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ብዙ ተከታይ ያላቸዉ ግለሰቦች እንዲጋበዙ ተደርገዋል።"ከተማዋ ሰላም ናት" የሚል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሊጀመር እንደሆነ እና ብዙ ተከታይ ላላቸዉ የማህበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች ደግሞ ረብጣ ገንዘብ እንደማከፈላቸዉ ቃል ተገብቶላቸዋል።

ነገር ግን አሁንሞ በከተማዋ ዉስጥ የወጣቶች አፈሳ፣አስገድዶ መድፈር፣ዘረፋ፣እገታ እና ሌሎችም ወንጀሎች በአገዛዙ ጥምር ጦር የሰራዊት አባላት እየተፈፀሙ ቀጥለዋል።

በጎንደር ከተማ የብልፅግና ተወካዮች ግን በማህበረሰቡ የማፈፀሙ ወንጀሎችን ለመደበቅ አስገድዶ ሰላማዊ ሰልፍ እና በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ተከታዮች ባለቸዉ ግለሰቦች ለማስተባበል ሞክሯል።

@ግሎባል ፋኖ ማዲያ
የፋኖ ድምፅ!!!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
የደፈጣ ጥቃት ተፈፀሞ ሁለት ፓሊሶች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ እና74ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ገዳያሱ ቀበሌ እና መርጦ ለማራይም ከባድ ተጋሃድሎ ሲያካሂድ አድሯል።

በሸበል በረንታ ወረዳ ወፍትማ ጎጥ ህዳር 24/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በነበረው የጨለማ የጨበጣ ውጊያ በረካታ የአረመኔዊ ሰራዊት አባላት ሲደመሰስ በረከት ታደሰ የሚባል1 የአገዛዙ ሰራዊት አባል በንስሮች የበላይ ዘለቀ ልጆች እና የሽፈራው ገርባው ልጅች የተማረከ ሲሆን መርጦለማርያም ላይ ሁለት ፓሊሶችላይ እርምጃ በመውሰድ ጀብድ ሰርቶ መውጣት ተችሏል። በውጊያ የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮችእና ጥምር ጦሩ እና1ኛ እሪጅመንት እና የሸበል በረንታ ደጀኑ ህዝባችን ተሳትፈዋል።

ህዳር 25/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ ፣ዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏2
ሩሲያ ግብረ ሰዶምን በሸብር ዝርዝር ውስጥ አስገባች

#ቢዝነስሚዲያ l ሩሲያ የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴን በአክራሪነት እና ሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ ማከተቷ ተሰምቷል፡፡

የተመሳሳይ ጾታ እንቅስቃሴ አራማጆች በአክራሪነትና በአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሩሲያ ሚዲያዎች ዘገባ ያመላክታል፡፡

ውሳኔው የግብረ ሰዶማዊያን እና ትራንስጀንደር ተወካዮችን ለእስር እና ለሽብርተኝነት ቅጣት የሚዳርግ ነው ተብሏል፡፡

የሩሲያ ውሳኔ ዓለም አቀፍ የግብረ ሰዶም ማኅበራት እንቅስቃሴ እና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን ጭምር ይመለከታል ተብሏል፡፡ በሩሲያ ምድር የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴ ማድረግ ከዚህ በኋላ በሸባሪነት አስከስሶ ዘብጥያ የሚያስወርድ ከባደ ወንጀል ሆኗል፡፡

በአገሪቱ የግብረሰዶማዊ እንቅስቃሴን የሚደግፉና የሚያስፋፉ አካላት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ይነገራል፡፡

የእንቅስቃሴው አራማጆች መሰረት ሩሲያ ባላንጣ ካደረገቻ ቸው ከእነ አሜሪካና አውሮፓ ምድር የሚነሳ መሆኑ ደግሞ የቭላድሚር ፑቲንን አስተዳደር አስቆጥቷል፡፡

እንደ አሜሪካ ያሉ አገራት የግብረ ሶዶማዊያን እንቅስቃሴን እንደ መብት ቆጥረው እያስፋፋት ነው፡፡ ግብረ ሶዶማዊያነት ከምዕራቡ አለም አልፎ እስከ አፍሪካ የዘለቀ ሲሆን፣ አንዳንድ አገራት እንስቅቃሴውን በሕግ እያገዱ ነው፡፡


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
👍5👏1
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል አፋብኃ እና የአማራ ህዝባዊ ድርጅት አፋህድ በጋራ ባደረጉት አዉደዉጊያ ታላቅ ድል ፈፅመዋል።

ከቅርብ ጊዜህ ወዲህ አንድነት ላይ መሰረት ያደረገ አዉደዉጊያ እያደረጉ ሲሆን በምስራቅ አማራ ቀጠና እና በደቡብ አማራ ቀጠና በተደጋጋሚ ጊዜ በጋራ አዉደዉጊያ አድርገዉ ድል አስመዝገበዋል።

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር እና የአፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዓፄ ዐምደፂዮን ኮር የተውጣጣ የፋኖ ኃይል በምዕራብ ወሎ ግንባር ከላላ ወረዳ ውስጥ ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፅመዋል።

በቅንጅት በተሰራው ኦፕሬሽን ከ20 በላይ ጠላት የተማረከ ሲሆን ጠላት 3 መኪና የሚሆን ሙት እና ቁስለኛ ጭኖ ፈርጥጧል:: በትናንትናው እለት በደገር ግንባር የተጀመረው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በስተመጨረሻ ፋኖ ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏታል::

ከዚህ በተጨማሪ ከደገር ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኙት ቲርቲራ እና ቆርኬ ታዳጊ ከተሞችም በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል::

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ትንቅንቅ በቲርቲራ በኩል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሳ ተሾመ ሻለቃ ጠላትን ሲያስፈረጥጠው ቆርኬ ላይ ደግሞ የዚሁ ክፍለ ጦር አካል የሆነችው 2ተኛ እንድሪስ ተሾመ ሻለቃ ታሪክ ሰርታለች:: የፋኖዎችን ምት መቋቋም ያቃተው ጠላት ከቲርቲራ ጎራ ወርዶ እየፈረጠጠ ተጉዞ ቀነሶ መንደር ሲደርስ አቶ ሁሴን ከማል የተባለ ገበሬን በአጨዳ ላይ ሳለ እረሽኖታል::

በቆርኬ ግንባር 17 የጠላት ኃይል የተመታ ሲሆን 5ቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ 12ቱ ቁስለኛ ሆነዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር በጃማ ግንባር በተለይም በአቦልድ፣ ዘርቃሚ እና ደጎሎ በኩል የጠላትን አከርካሪ መስበሩ ተረጋግጧል:: የወረዳው መቀመጫ የሆነችው ደጎሎ ከተማ እስከ ዛሬ ጧት ድረስ በተኩስ ስትናጥ እንደነበረ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል:: ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ የዋሲል ክፍለ ጦር 2ተኛ መብረቅ ሻለቃ አባላት ጠላትን እረፍት ነስተውት ሰንብተዋል:: በዚህ የተበሳጨው ጠላት ከአረብ ሀገር ከመጣች 1 ወር በትክክል ያልሞላትን እህታችንን መረሸኑም ታውቋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
2🙏2
የአደረጃጀት ዜና

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር የአመራር ሪፎርም አደረገ::

ቀናትን የፈጀ ውይይት እና ግምገማ ከተደረገ በኋላ አዳዲስ አመራሮች የተሰየሙ ሲሆን ከነባሮች የኃላፊነት ርክክብ አድርገዋል::

የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ በተገኘበት የተካሄደው የውውይት እና ግምገማ መድረክ በስኬት መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን ጉባኤተኞች ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን አርበኞች የክፍለ ጦሩ አመራሮች አድርገው መምረጣቸውን ነው ከስፍራው የደረሰን መረጃ የሚያመላክተው:: በዚህም፦

1ኛ. አርበኛ ስንደው ገዜ - የክፍለ ጦሩ አዛዥ
2ኛ. አርበኛ ዱቤ አሻግሬ - የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ
3ኛ. አርበኛ ንጉሥ ጌታቸው - ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
3.1. አርበኛ መብሬ ጫብሲ - ዘመቻ መምሪያ ምክትል ኃላፊ
4ኛ. አርበኛ መብሬ ምስጌ - ወታደራዊ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ
5ኛ. አርበኛ ደምሰው ጎቼ - ሎጀስቲክ ሃላፊ
6ኛ. አርበኛ ደመቀ አረጋ - የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ
7ኛ. አርበኛ አስማማው ፈንታው - የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
8ኛ. አርበኛ ጀንበሩ ጌታቸው - ስልጠና መምሪያ ኃላፊ

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም
🙏2
የአውደ ውጊያ መረጃ

ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ባጃ ከተማን ተቆጣጠረ።

ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካሎች ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ፣ ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ፣ የመብረቅ ክ/ጦር 2 ብርጌዶች አንድ ላይ በመቀናጀት ከጓህላ መጥቶ ባጃ ከተማ ላይ የሰፈረውን የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት በፊት ለፊት ውጊያ እያሯሯጡ ሲያደባዩት አርፍደዋል።

በዚህ ፈጣን ውጊያ ከምሽግ ምሽግ እየዘለሉ በመግባት የጠላትን ኃይል ሰፍሮበት የነበረውን ካምኘ ወዲያውኑ መቆጣጠር የቻሉ ሲሆን ጠላትም የወገንን ከፍተኛ ምት መቋቋም ባለመቻሉ ከተማዋን ለአናቭስቶቹ ፋኖዎች አስረክቦ እግሩ ወዳመራው አቅጣጫ ፈርጥጧል።

🔸 ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ሸማቂው ብርጌድና መብረቅ ክ/ጦር ብርጌዶች ከሊቦ ባጃና ከሚካኤል ደብር ባጃ የሚወስዱ ቁልፍ ቦታዎችን በመዝጋት የጠላትን ኃይል እንዳይቀሳቀስ ማድረግ መቻላቸው ታውቋል።

ውጊያው ለ8 ሰዓታት ያህል የቆየ ሲሆን በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛም ተደርጓል።

🔸 በዚህ እልህ አስጨራሽ ውጊያ 15 እስከ ወዲያኛው የተሸኙ 19 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ቁስለኛ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን አርባያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በቁስለኞች ለቅሶና ዋይታ ተጨናንቆ እንደሚገኝም የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል።

🔸 አምቦ ሜዳ ከተማ ላይ በአርበኛ በላያ ጌቴ የምትመራውን ንጉሱ መልዛ ብርጌድና የአፄ እያሱ ክ/ጦር የተወሰኑ አባላትን ለማጥቃት ወደ ከተማዋ የመጣው የጠላት ኃይል መመታቱም ተገልጿል።

ድምሰሳ ለመፈጸም አቅዶ የመጣው ጠላት ከ5 በላይ አባላቱ ክፉኛ ቆስሎበት ወደመጣበት እንዲመለስ አድርገውታል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ

ህዳር 25 /2018 ዓ.ም
🙏31
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የአገዛዙ ጥምር ሀይል መነሻውን ከአለፋ ወረዳ ሻሁራና አፀደማርያም ከተማ ፣ ከሰሜን አቸፈር ሊበን ከተማ እና ከቋራ ወረዳ ደለጎ በማድረግ ወደ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የተንቀሳቀሰው ሃይል ላይ ከፍተኛ ርምጃ ወሰደ::

ሰሞንኛ አጀንዳው ፋኖን በየቀጠናው አፅድቻለሁ በህዝቡ ላይም የተሻለ ቅቡልነት አግንቻለሁ እያለ ቅዠት ላይ ያለ ቢሆንም አሁን ላይ በጨለማ በመንቀሳቀስ የአርሶ አደሩን ትጥቅ ለማስፈታት እና ዘረፋ ለመፈፀም አቅዶ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ፣ ማህበረሰቡ ከፋኖ ሀይል ጋር መረጃ ቀድሞ በመለዋወጥ ከፋኖ ጎን በመሆን በሁሉም ቀጠና ማለትም በአለፋ ወረዳ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የፋሽስት ሰራዊት አድዋ ክ/ጦ ከማህበረሰቡ ጋር በመጣመር የጠላትን እቅድ ከማክሸፍ ባሻገር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ተችሏል::

ከደለጎ ከተማ ተነስቶ ወደ ኮሩ ቀጠና የገባው በቋራ ኦሜድላ ነብሮ ብርጌድ አማካኝነት በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ በትር ማሳረፍም ተችሏል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የፋኖ ሀይል አሰላለፉን በመቀያየር የአገዛዙን ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት መግቢያ መውጫ እያሳጣው ይገኛል።አውደ ውጊያው አሁንም እንደ ቀጠለ ይገኛል አህዛዊ የድል ዜናዎችን በቀጣይ የዜና ጥንቅራችን የምናቀርብ ይሆናል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ህዳር 25/2018
🙏3