የዐራት ዐይናው ቆሞስ የኔታ ይባቤ በላይ ሥርዓተ ቀብር በክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈጸመ።
አጭር የሕይወት ታሪክ
ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ ከአባታቸው ከአቶ በላይ ፈንታ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ይታይሽ ወርቄ በቀድሞው አጠራር በጎጃም ክፍለ ሀገር በዳንግላ አውራጃ አብሽካን ቅዱስ ጊዮርጊስ በተባለ ቦታ መጋቢት 27 ቀን 1951 ዓ.ም ተወለዱ።
በ1956 ዓ.ም በአያታቸው (የእናታቸው እናት) ሞት ምክንያት እናታቸው አባታቸውን ሊቀ ካህናት ወርቄ ጀምበሬን ለመጦር ወደ ናዳ ሲሄዱ ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ በወቅቱ የ5 ዓመት ሕፃን ነበሩ።
ወዲያው ናዳ እንደደረሱ የወላጆቻቸውን ፍቅር አጣጥመው ሳይጨርሱ ገና በ5 ዓመታቸው ወደ አብነት ት/ቤት በመግባት ትምህርታቸውን በዝክረ አቦ ከፊደል ገበታ እስከ ጸዋትዎ ዜማ ከመምህር የኔታ ተአምር አስኪደዋል።
በመቀጠል ቻቫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደተባለ ቦታ በመሄድ የቅኔ እና የፍትሐ ነገሥት መምህር ከሆኑት ከየኔታ ወሀቤ ጸጋ ቅኔን ከእነአገባቡ፤ ግስን እስከ አመሉ እንዲሁም የአቡሻኽር ትምህርትን ተምረው በመምህራቸው ተመርቀዋል።
በተጨማሪም በመምህራቸው የኔታ ወሀቤ ጸጋ መልካም ፈቃድ ለግ ማርያም ወደተባለው ቦታ ወደሚገኙት መምህር የኔታ መንክር ጉባኤ ቤት ገብተው ለሁለተኛ ጊዜ የቅኔን ትምህርት ተምረው ተመርቀዋል። በሁለቱም ጉባኤ ቤት እየተመላለሱ የቅኔ ዘረፋን አስኪደዋል።
የቅኔ ትምህርታቸውንም ካስመሰከሩ በኋላ ምክትል መምህር በመሆን አስተምረዋል።
ዐራት ዐይና የኔታ ይባቤ በላይ ለትምህርት ባላቸው ፍላጎት የሊቃውንት መፍለቂያ ወደ ሆነው ደብረ ዲማኅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም በመሄድ ከመምህር አለቃ ወ/ማርቆስ የሐዲሳት ትርጓሜንና የፍትሐ-ነገሥትን ትምህርት ተምረዋል።
በዚህም ቦታ በመምህራቸው መልካም ፈቃድ በ1974 ዓ.ም ከትምህርታቸው ጎን ለጎን የቅኔ እና የአቡሻኽር ትምህርትን ወንበር ዘርግተው አስተምረዋል።
ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ መጻሕፍተ ብሉያትን ከመምህር ገብረ አምላክ እና ከመምህር ገብረ ኢየሱስ ተምረው ተመርቀዋል።
መዓርገ ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ቀዳማዊ በ1964ዓ.ም የተቀበሉ ሲሆን በፈቃደ እግዚአብሔር በ1985 ዓ.ም ግንቦት 12 ቀን በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሐይማኖት ገዳም ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጽመዋል።
በ1986ዓ.ም ደግሞ መዓርገ ቅስናን እና ቁምስናን በወቅቱ የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ በርናባስ ተቀብለዋል።
ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሱባኤ ገብተው ፈለገ ብርሃን ናዳ ማርያም ላይ ታላቅ ጉባኤና ገዳም እንደሚተከል በሱባኤ ተገልጦላቸው ጥቅምት 20 ቀን 1979ዓ.ም በመምህራቸው አለቃ ወ/ማርቆስ ሽኝት ተደርጎላቸው ወደ ናዳ መጥተዋል።
እንደመጡም ቀድሞ በሱባኤ የተረዱትን ሀሳበ እግዚአብሔር በቦታው የነበሩ አንዲት ባሕታዊት እናት በዚህ ቦታ ታላቅ ገዳም እና ጉባኤ ቤት እንደሚመሰረት ደግመው ነግረዋቸዋል።
ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ ከ1974-1978 ዓ.ም ለዐራት ዓመታት ከአለቃ ወ/ማርቆስ እየተማሩ ቅኔ እና አቡሻኽርን፤ ከ1979-2018ዓ.ም ለ39ዓመታት በድምሩ ከ44ዓመታት በላይ ከ25,000-30,000 ደቀ መዛሙርትን በማስተማር በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን አፍርተዋል።
ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ በተወለዱ በ67 ዓመታቸው ኅዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ሥርዓተ ቀብራቸውም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሩቅም ከቅርብም የተገኙ ዘመድ ወዳጆቻቸው፣ ያስተማሯቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ቦታዎች የሄዱ የመንፈስ ልጆቻቸው በተገኙበት ለ40ዓመታት በጸለዩበት፣ ብዙ ተጋድሎ በፈጸሙበት እና ወንበር ዘርግተው ባስተማሩበት በክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2018ዓ.ም ተፈጽሟል።
መረጃው በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው

❤2
አሳዛኝ መረጃ!!
በታች አርማጭሆ ወረዳ በምትገኝ ገጠራማ ስፍራ ልጅሽ የፋኖ አባል ነዉ በሚል በአገዛዙ ሰራዊት ታፍና ወደ ካምፕ የተወሰደችዉ የ65 ዓመት እናት በቡድን ተደፍራ ህይወቷ ማለፉ ተሰምቷል።
https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk

😭1
ሰበር ዜና!
ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያ ያለውን የፋሽስቱ ሰራዊት አንዱን ምሽግ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ላይ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያ ካሉት የፋሽስቱ ሰራዊት ምሽጎች አንዱ ላይ በሬ አርዶ ከሚበላበት ተስበው በመግባት ምሽጉን ሙሉ ለሙሉ በመስበርና በርካታ ሃይሉን በመደምሰስ ብሎም በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
የጠላት ሃይል ምንም አይነት ዋርድያ ባላስቀመጠበትና በሌለበት ሁኔታ ምሽጉ ላይ በሬ አርዶ በሚበላበት ቀን 10:00 ላይ ተስበው በመግባት እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ሲረመርሙት አምሽተው ታላቅ ጀብድ በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
ከዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ማግስት ፋሽስቱ አገዛዝ ቤተ-አማራ ከነበሩት ዕዞች በተጨማሪ ሁለት ዕዝ በማስገባት ወረራ ቢያደርግም ምኒልክ ዕዝ ጠላትን ወደሚመታበት ወረዳ በማስገባት ወደ ደፈጣ ውጊያ በመግባት ሲያመች ደግሞ መደበኛ ውጊያ በማድረግ በርካታ ሃይሉን ሙት ቁስለኛ እና ምርኮኛ እያደረገ በተጨማሪም እያስኮበለለ እያፈረሰው ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 23/2018 ዓ.ም

ቴዎድሮስ ዕዝ ዛሬ!
_፩
88ኛ ክ/ጦር በጠላት ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን አካሄደ!
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር አካል የሆነችው 88ኛ ክ/ጦር በአዲስ በተዋቀረ ማግስት በጠላት እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ የተሳካ የማጥቃት ኦፕሬሽን አካሄዷል።
ህዳር 22/2018 ዓ.ም ጠላት የለመደ የጥፋት በትሩን ህዝባችን ላይ ለመፈፀም ከሌሊቱ 9 ሠዓት ከወምበርማ ርዕሰ ከተማ ሽንዲ መነሻውን አድርጎ ወደ ኮኪ ቀበሌ የተንቀሳቀሰ ሲሆን በ109ኛ ኮር 88ኛ ክፍለ ጦር በተደረገ የማጥቃት ኦፕሬሽን በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። የአናብስቶቹን ምት መቋቋም ያቃተው ጠላት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደ መጣበት ፈርጥጧል።
__፪
ሶስት(03) የአድማ ብተና አመራሮች ተረሸኑ።
ብልፅግና የራሱን ጦሩን መረሸን ጀምሯል።
የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ
201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ህዳር 21 ቀን በመርጡለ ማርያም ዙሪያ በተካሄደ አውደ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የብልፅግና ቅጥረኛ ሰራዊት በወቅቱ ውጊያውን ከትእዛዝ ውጭ መርታችኋል በሚል 3 የአድማ ብተና አመራሮችን ረሽኗቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ ዉጊያ ላይ ከተደመሰሱት አንድ ቲም አድማ ብተና እና ምኒሻ በተጨማሪ በጠና ቆስሎ የነበረው 50 አለቃ ይርሳው የአድማ ብተና አዛዥ ተጨርሶ የቀብር ስነስርዓቱ በ22/03/20/8 ዓ/ም በመርጦለማርያም ከተማ በምትገኘው ማርያም ቤተክርስቲያን በወታደራዊ ስርዓት ከቀኑ በ6:00 ተፈፅሟል።
አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ!
አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት
ህዳር 23/2018

ለተከታታይ 6(ስድስት) ወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ የ64ኛ ክፍለ ጦር እግረኛ ሰራዊት በሸበል በረንታ በደማቅ ሁኔታ ተመረቁ።
ህዳር 23/2018 ዓ.ም
የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ለተከታታይ 6(ስድስት) ወራት ያሰለጠናቸውን የእግረኛ ሰራዊት ህዳር 23/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ወረዳ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ የሽፈራው ገርባው ልጆች ለ5ኛ ዙር በደማቅ ሁኔታ አስመረቀዋል።
በቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ስር የሚገኘው 64ኛ ክፍለ ጦር የእግረኛ ሰራዊት ለማስመረቅ በክብር የተገኙት የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበርሰብ በተገኙበት በሸበል በረንታ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል።
የተከበራቹህ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች የተከበራቹህ የሸበል በረንታ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች የተከበራቹህ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት የተከበራቹህ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በዚህ ፕሮግራም የተገኛቹህ የከተመዋ ኖሪዎች እንዲሁም የክብር እንግዶች የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ዙር የእግረኛ ሰራዊት የምረቃ ፕሮግራም እንኳን በሰላም አደረሳቹህ አደርሰን።
በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኛቹህ የክብር እንግዶች ክብራት እና ክብሯን እንዲሁም ተመራቄ የፋኖ አባላት እኛ እናተ እንዲህ የምንሰባሰበው፣ የምንደራጀው፣ የምንሰለጥነው ለሁላችንም የጋራ የሆነ ጉዳይ በየቤታችን ስላለን ነው? ሁላችንም እንድንደራጅ እና እንድንሰባሰብ ካደረጉን አንኳር ጉዳዩች ውስጥ ሰርቶ መብላትን ያስተማረው፣ ኢትዮጵያ ከውጭ ወራሪ እና ከውስጥ ሰላቶ እና ባንዳን በማፅዳት ሀገር የገነባው የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በራሱ ሀገር፣ በእራሱ እርስት ሲያሻቸው በሀይማኖቱ፣ ሲያሻቸው በዕርስቱ፣ በማንነነቱ ጣልቃ እየገቡ የአማራን ህዝብ ከ50 ዓመት እና ከዛ በላይ እረፍት በመንሳት በገዛ ሀገሩ እንዳይኖር ተደርጓል።
ሀገር መስራቹ፣ፊደል የቀረፀው፣የእራሱ እምነት፣ የእራሱ ባህል እና እሴት፣የእራሱ ወግ ያለው ለበርካታ ዘመናት የኢትዮጰያን ዳር ድንበር አስከብሮ የቆየው፣ በአራቱም መዓዘን ደሙን አፍሶ አጥንቶ የከሰከሰው ታላቁ የአማራ ህዝብ ዛሬ ላይ በገዛ ሀገሩ፣ በገዛ እርስቱ ባይተዋር ሆኖ በጅምላ ይገደላል፣ በጅምላ ይሰደዳል፣ በጅምላ ይፈናቀላል፣ ሀብት ንብርቱ በወራሪዎች እየተወረሰ ይገኛል። ኢትዩጰያን ያሻግራሉ፣ሀገር ይመራሉ በህዝብ ተወዳጅ የነበሩ የአማራ ሙህራን በጅምላ በጨለማ እስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። እንደ ምሳሌ ብንጠቅስ የመንጋው መድሀኒት የፖርላመው ንጉስ አቶ ክርስትያን ታደለ፣ አቶ ዩሀንስ ቦያለው እና መ/ር መስከረም አበራ እና ሌሎች ሙህራን በጅምላ በጨላማ እስር ቤት ታስረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ።
የአብይ አህመድ አረመኔዊ ስርዓት የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የአጭር እና የረጅም ግዜ ዕቅድ በማውጣት በአለም ላይ ተደርጎ የማይታወቅ ለማየት የሚሰቀጥጡ ዘግናኝ እና አስነዋሪ ተግባር እየፈፀሙብን እና እያስፈፀሙብን ይገኛሉ። ይህ ሁሉ ድርጊት የሚፈፅሙት ከአማራነታቸው ይልቅ ሆዳቸው የግል ጥቅማቸው በልጦባቸው ባንዳ በሆኑ አመራሮች እና ሚሊሻዎች ጭምር ነው። ክቡራን እና ክቡራት እንዲሁም ተመራቂዎች ይህ ድርጊት የሚፈፀመው አማራ በመሆናችን ብቻ ነው።
የአማራ ህዝብ በአማራነቱ ብቻ እንዲጠፋ የተፈረደበት ህዝብ ከሆነ ውሎ አድሯል። በመሆኑም የአማራ ህዝብ ህዝብ መዳኛ መንገድ አንድም በክንዱ አንድም በእግዚአብሄር ሀይል ብቻ ነው። የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የመኖር መብቱን ማስከበር የሚችለው አማራ አንድ ሆኖ በጋራ መታጋል ስንችል ብቻ ነው።
በመሆኑም ይህንን የአረመኔዊ አገዛዝን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ነቅሎ ለመጣል የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች እና የሽፈራው ገርባው ልጆች በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር አደረጃጀት ስር ታቅፈው በተለያዩ ቦታዎች የውጊያ እቅዶችን በማቀድ እርሀቡ፣ የውሀ ጥሙ፣ ብርዱ፣ ሙቀቱ ሳይበግራቸው በረካታ ውጊያዎችን በማድርግ በርካታ ገድል ሲፈፅሙ ቆይተዋል።
በዚህ ሰዓት 64ኛ ክፍለ ጦር በድርጅቱ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የሚሰጣቸውን የትኛውም አይነት ወታደራዊ ግዳጅ/ሚሽን በብቃት ከመፈፀም ጎን ለጎን በዚህ ፈታኝ ወቅት ህዝባችንን በመልሶ ማደራጄት፣ወታደሩን በመልሶ ማሰልጠን፣ ወጣቱን በልዩ ልዩ ስልጠና እና የውትድርና ሳይንስ በመስጠት ግዙፍ ሀይል እየገነባ ይገኛል። በዚህም ለጠላት ሀይል ቅስም መስበሪያ ለወዳጅ ደስታን ይዞ መጥቷል።
በሸበል በረንታ እና በእነማይ ምድር ጀግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ሀገራችንን ከቀኝ ግዛትና ከባርነት ነፃ አድረገው ለትውልድ ያስረከቡበት የአረበኞች መሰባሰቢያ ከሆኑት ውስጥ ይህ አካባቢውን አንዱ ነው።
በዛሬው እለት ህዳር 23/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ለመሰባሰባችን ምክንያት የሆናቹህ የ5ኛ ዙር እግረኛ ተመራቂ አባላት እናተ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ፣ የሽፈራው ገርባው፣ የእጅጉ ዘለቀ ልጆች ናቹህ። በዚህ ቅዱስ በሆነው የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል በስም ዘርዝረን የማንጨረሳቸው ጀግኖች የትግል ጓዶች ከጠላት ጋር ተናንቀው ብዙ ዋጋ ከፈለው ተለይተውናል። በመሆኑም ድርጅታችንን እና መሪያችንን ከጥግል ጠላፊዎች እንድትጠብቁ አደራ እያልኩ እኛ ለእናተ አደራ የምንሰጣቹህ መሪዎቻችን በብዙ ስቃይ እና መከራ ውጣ ውርድ፣ ጀግኖች ውድ ህይወታቸውን የገበሩበት ትግል ተቀብላቹህ የድል ባለቤት እንድታደርጉት አደራ እንላለን።
በመጨረሻም በመላው አማራ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን የአማራን ህዝብ የአረመኔዊ ድርጊት በመስራት በረካታ ግፎች እና ወንጀሎችን እየሰራ የሚገኜው የአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አረመኔዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ስለሚጠበቅብን ሁላችንም በዚህ የምረቃ ፕሮግሬም የምትገኝ በሙሉ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልኩ ለተመራቂ ፋኖዎች መልካም የምረቃ ጊዜ እንመኛለሁ።
እንደራጃለን፣ እንሰለጥናለን፣ እንታጠቃለን፣ የአማራን ህዝብ ከአረመኔው ጡት ቆራጭ አራጅ ሰራዊት ነፃ እናወጣዋለን።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህዳር 23/2018 ዓ.ም
ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64 ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

👎1🙏1