ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከወራት በፊት በአገዛዙ ብልፅግና ተይዘዉ መኮድ ታስረዉ የነበሩት አባት ማረፈቸዉ ተነገረ።

ታላቁ ዋርካ አረፉ!!!!

እንዲህ ብለው ነበር!
ገዳሙን የሚመራ - በጉባኤ ቤቱ የሚያስተምር መምህር ፈልጉ!
{አራት ዐይና ይባቤ በላይ}

የታላቋ ናዳ ማርያም ገዳም ታሪክ በአጭሩ ይሄ ነው 👇

ፈለገ ብርሃን ናዳ ቅድስት ማርያም ገዳም በምዕራብ ጐጃም ሀገረ ስብከት ሜጫ ወረዳ ቤተ ክህነት በጉታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ናዳ በሚባል ቦታ ይገኛል፡፡ ገዳሙ በዐሥራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሠረተ ሲኾን፣ ታቦተ ሕጉም ከጣና ቂርቆስ ገዳም እንደ መጣ ይነገራል፡፡ ለብዙ ዓመታት ‹እንቍርቍሪት ጽዮን› እየተባለ ሲጠራ የቆየው ገዳሙ፣ ከዓመታት በኋላ ‹ናዳ ማርያም› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ናዳ የተባለበት ምክንያትም የሚከተለው ታሪክ ነው፤ በአካባቢው ዋናው ገዳም የሚባል ሌላ ጥንታዊ ገዳም ነበረ፡፡ በዚህ ገዳምም አባ ናዳ የሚባሉ አባት ይጸልዩበት ነበር፡፡ በዙርያውም በርካታ መነኮሳት ነበሩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አባ ናዳ በመሰላል ወጥተው የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ጣርያ ሲከድኑ መሰላሉ አንሸራቷቸው ወደቁ፡፡ በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻ በደኅና ካነሣቻቸው በኋላ ‹‹ወዳጄ አባ ናዳ ሆይ! ለዘለዓለም ስምህ በዚህ ቦታ ይጠራ›› በማለት ቃል ኪዳን ሰጠቻቸው፡፡ አባ ናዳም ገዳሙን አሁን ባለበት አኳኋን እንዲጸና አደረጉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‹እንቍርቍሪት› የሚለው ስያሜ ተለውጦ ‹ናዳ ማርያም› ወይም ‹ናዳ ጽዮን› ተብሎ መጠራት ጀመረ፡፡

ፈለገ ብርሃን ናዳ ማርያም ገዳም በየጊዜው የመጥፋት ፈተና ቢያጋጥመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደ ገና እየተመለሰ እስካሁን ድረስ ክብሩ እንደ ተጠበቀ፤ ወሰኑ እንደ ተከበረ፤ ልማቱም እንደ ቀጠለ ነው፡፡ ገዳሙ የአብነት ትምህርት ማእከል በመኾኑና ዙርያው በምንጭ በመከበቡ የተነሣ ከ፲፱፻፹፮ ዓ.ም ጀምሮ በጊዜው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበሩት ብፁዕ አቡነ በርናባስ ፈቃድ ‹ፈለገ ብርሃን› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ገዳሙ በዚህ መልኩ እየሰፋ መጥቶ በአሁኑ ሰዓት አገልግሎቱም ጉባኤ ቤቱም በአግባቡ እየተከናወነ ነው፡፡ ከፈለገ ብርሃን ናዳ ማርያም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በተጨማሪ የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላልይበላ እና የጋፈራ ደብር ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት ለመነኮሳቱ እና ለአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓትም የክብረ ደናግል ቅዱስ ላሊበላ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ ጥበብ በአዲስ መልክ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

(ምንጭ፡- ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ፤ ገዳሙ ያሳተመው ብሮሸር)

ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ

ምንኵስናን ከሊቅነት፣ አባትነትን ከሥራ ጋር አስተባብረው በያዙት በሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ አማካይነት ከ፲፱፻፸፱ ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ በገዳሙ የትርጓሜ መጻሕፍት እና የቅኔ ትምህርት በመሰጠት ላይ ነው፡፡ ከሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ ጉባኤ ቤት ተምረው በልዩ ልዩ የአገልግሎት ዘርፍ ተሰማርተው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉ ካህናትና መምህራንም እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ የገዳሙ ዋና አስተዳዳሪ፣ የትርጓሜ መጻሕፍትና የቅኔ መምህሩ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ እኒህን ታላቁን ሊቀ ነው ዛሬ ከዓለም ድካም ያረፉት!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
4💔2
ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በዛሬዉ ዕለት ከ8 በላይ የአገዛዙ ሰራዊትን በመደምሰስና ከ17 በላይ የሚሆኑ የአገዛዙ ሰራዊትን በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፏል ::

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነው ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ባደረገው አውደ ዉጊያ ከ8 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ17 በላይ ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል።

የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት 12ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት፣የ65ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት ኃይልና የ65ኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ በጥምረት አንድ ዙ-23 እና አራት ዲሽቃ በመያዝ መነሻውን ከላስታ ወረዳ ብልባላ ከተማ በማድረግ ህዳር 16/2018 ዓ/ም ዳቢያና አሞራ ደብር ድባቅ ተመትቶ መመለሱ ይታወቃል።

በዚህ ሽንፈቱ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ከህዳር 18 ጀምሮ ኃይሉን ጨምሮ በድሮን ታግዞ ውጊያ ያደረገ ቢሆንም ተወርዋሪዎቹ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ፋኖዎች ሦስት ቀን ሙሉ ምሽግ መከላከል በማድረግ በአራተኛው ቀን ዛሬ ህዳር 21/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በጠረዛና መዛርድ ግንባር በቆረጣ በመግባት በተደረገ አውደ ውጊያ የጠላት ኃይል ወደ ነበረበት ምሽግ ተቀጥቅጦ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ተመልሷል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 21 / 2018 ዓ.ም
🙏21👍1
አዛሳኝ መረጃ!

አገዛዙ በተደጋጋሚ እስርና እንግልት ሲፈፅምባቸው የነበሩት አራት አይናው አበምኔት አረፉ!

የትርጓሜ መጻሕፍት፣ የአቡሻኽር፣ የፍትሐ ነገሥት እና የቅኔ መምህር፤ በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት የክብረ ደናግል ናዳ ቅድስት ማርያም ገዳም አበምኔት የሆኑት አራት አይናው መምህር ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ ከዚህ አለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።

ታላቁ አባት መምህር ቆሞስ አባ ይባቤ፡ አገዛዙ ተደጋጋሚ  የሆነ እስርና እንግልት ሲፈፅምባቸው እንደነበር አይዘነጋም።

እየደረሰባቸው ካለው መንግስታዊ እስርና ማሳደድ አኳያ "ገዳሙን የሚመራ - በጉባኤ ቤቱ የሚያስተምር መምህር ፈልጉ" በሚል ለገዳሙ አበምኔቶች መልዕክት ሲያስተላልፉ መሰንበታቸውም ተነግሯል።

አራት አይናው አባት፡ ትናንት ህዳር 21/2018 ዓ/ም ለዛሬ አጥቢያ ሕይወታቸው ማለፉ ነው የታወቀው።
💔31
መብረቅ ክፍለጦር ወግዲ ወረዳ ላይ ከፋሽስቱ አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ጋር በመፋለም ድል አስመዘገበ::

ንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክፍለጦር ወግዲ ወረዳ ልዩ ቦታው ወደ ጎረንጅ አቅጣጫ ማጥቃት ካደረገው ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት 105ኛ ክፍለጦር እንዲሁም አድማ ብተናና ሚሊሻ በአገዛዙ አጠራር ጥምር ጦር ጋር ህዳር 21/2018 ዓ.ም ጧት 1:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 1:00 ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዝግበዋል::

ሙሉ ቀን በዋለው ፍልሚያ መብረቆቹ የፋሽስቱ አገዛዝ መመኪያ የሆነውን ቅልብ ኮማንዶ ማጥቃቱን በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ በርካታ ቁጥር ያለው ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ቀጠናቸውን በማስከበር ድል አስመዝግበዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 22/2018 ዓ.ም
1
🎯 ዐፄ እያሱ ክ/ጦር ላይ ጥቃት ለመፈጸም የመጣው የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ክፉኛ መመታቱ ታወቀ።
ህዳር 21/2018 ዓ.ም ከአዲስ ዘመን በመነሳት ወደ አንቦ ሜዳ ታዳጊ ከተማ በትላንትናው እለት በመግባት ከንጋቱ 10:30 ሰዓት ጀምሮ የዐፄ እያሱ ክ/ጦር አባላት ወደሚገኙበት ካምፕ ልዩ ስሙ ሻሞ መድሀኒ አለም ተብሎ ወደ ሚጠራዉ ቀጠና በመጠጋት ከበባ ለማድረግ የሞከረ ሲሆን ያሰበውን እቅድ ግን ሊያሳካ አልቻለም።
ጥቃት ለመፈጸም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኃይሉን የተጠቀመ ቢሆንም ለመደምሰስ አቅደውበት የመጡበትን የወገን ኃይልን ግን አንዳችም ጉዳት ሊያደርሱበት አልቻሉም። ይልቁንም የዘወትር ግብሩ የሆነውን ሞትና ቁስል እንዲጎነጭ ሆኗል።
ከሌሊቱ 10:30 እስከ ረፋዱ 4:00 ድረስ በአናብስቶቹ ታፍኖ ወደ መጣበት ለመመለስ እንኳን መንገዱ እሾህ ሁኖበት እስከ ቀኑ 7:30 ድረስ ሲገረፍና ሲወቃ ዉሎ ወደ መጣበት ተመልሷል።
በጠላት ላይ የደረሰዉ ሰብአዊ ኪሳራም
የሞተ=>3
የቆሰለ=>5 ሲሆን ከፋተኛ የሆነ ቁሳዊ እና ሞራላዊ ኪሳራ አስተናግዶ ወደ መጣበት የራበዉ ቀበሮ ሁኖ ተመልሷል።
ሁሌም የነበልባሎቹን ምት መቋቋም ሲያቅተዉ ስሜቱን ንፁሀንን በማሰር፣በማገት፣በመዝረፍ እና በመግደል የሚረካዉ ደካመዉ የአብይ ወታደር በቀጠናዉ ላይ ሲሰበሰብ የነበረን የገበሬ አዝመራ የፋኖ ነዉ በማለት ሲዘርፍና ሲያወድም ዉሏል።
በተጨማሪ የፋኖ ምግብ አብሳይ ነሽ በማለት አንዲት ወጣት ሴትን እና የፋኖ መረጃ ናችሁ ብሎ ሁለት ታዳጊ ወጣት ወንዶችን አፍኖ ወስዶ የት እንዳደረሳቸዉ እስከ አሁን አልታወቀም ሲል የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የዳግማዊ ቴወድሮስ 5ኛ ኮር የዐፄ እያሱ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ ተናግሯል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ

ህዳር 22 /2018 ዓ.ም
2🙏1
መብረቅ ክፍለጦር ወግዲ ወረዳ ላይ ከፋሽስቱ አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ጋር በመፋለም ድል አስመዘገበ::

ንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክፍለጦር ወግዲ ወረዳ ልዩ ቦታው ወደ ጎረንጅ አቅጣጫ ማጥቃት ካደረገው ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት 105ኛ ክፍለጦር እንዲሁም አድማ ብተናና ሚሊሻ በአገዛዙ አጠራር ጥምር ጦር ጋር ህዳር 21/2018 ዓ.ም ጧት 1:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 1:00 ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዝግበዋል::

ሙሉ ቀን በዋለው ፍልሚያ መብረቆቹ የፋሽስቱ አገዛዝ መመኪያ የሆነውን ቅልብ ኮማንዶ ማጥቃቱን በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ በርካታ ቁጥር ያለው ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ቀጠናቸውን በማስከበር ድል አስመዝግበዋል::
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አገዛዙ በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ሰብሳቢ ላይ ያሰራጨዉ መረጃ በAI, በአርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ አማካኝነት የተቀናበረ መሆኑን እራሱ የክፍለጦሩ ሰብሳቢ አርበኛ ደመላሽ መንግስቴ በቪዲዮ የታገዘ መግለጫ አዉጥቷል እንከታተለዉ።
🙏5
የአገዛዙ ወታደር አንድ ስናይፐር ከነ ሙል ተተኳሹና አንድ መገናኛ ራዲዮ እንደያዘ ፋኖን ተቀላቀለ::

የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ሆኖ ሲያገለግል የነበረው አስር አለቃ ደጉ ከ48ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሻለቃ የአገዛዙን ግፍና መከራ በመፀየፍ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነውን ተከዜ ክፍለ ጦርን ህዳር 22/2018 ዓ.ም ተቀላቅሏል::

@ምንሊክ እዝ
🙏2