ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ባለሽርጡ ክፍለጦር ለተከታታይ ሁለት ቀናቶች ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገበ::

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ ቁጥር 8 ጠዶት በተባለው አካባቢ የመጣው የአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ጋር በተደረገው ተጋድሎ አይበገሬው የባለሽረጡ ክፍለ ጦር ኮማንዶ ፋኖዎች ከህዳር 19 እስከ ህዳር 21/2018 ዓ.ም ሲቀጠቅጡት ዉለዉ አድረው ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት እንዲመለስ በማድረግ ድል አስመዝግበዋል::

በመርሳ አቧሬ ገብርኤል ቤተ ክረስቲያን ከ16 በላይ አስከሬኑን በጅምላ ቀብርሲፈፅም በመርሳ ሆስፒታል ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ቁስለኛ በህክምና ላይ ይገኛል:: በዚህም የመርሳ ከተማና አካባቢው ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና ቦታው በመጨናነቁ የተነሳ በመጉላላት ላይ ይገኛሉ።

በዚህም የተበሳጨው የመከላከያ አዛዥ ሚሊሻዎችን እናንተ ናችሁ መረጃ ያወጣችሁብኝ በማለት ከአራት በላይ ሲረሽን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሚኒሻ እንደታሰረ የውስጥ መረጃችን አድርሶናል። የጠላት ሰራዊት ጠዶት ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ምሽግ ምሶ ውጊያ በማካሄድ ለሃይማኖቱ ክብር እንደለለው አሳይቷል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 21/2018 ዓ.ም
2🙏2
ሰበር የድል ዜና!!!!

ህዝባዊ ክብረበዓልን ለማደናቀፍ የሄደዉ የአገዛዙ ጥምር ጦር ሽንፈትን አስተናግዶ ተመልሷል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ  ሀይል ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር  በሸዋ ሀገረማሪያም መስኖ ማሪያም ለሁለት ቀን የዘለቀ አዉደዉጊያ በማድረግ ድል ተቀዳጅቷል።

በአያመቱ በድምቀት የሚከበረዉን የህዳር ፅዮን አመታዊ ክብረበዓል ለማደናቀፍ እና እኩይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመፈፀም ወደ መስኖ ማሪያም ያቀነዉ የአገዛዙ የመጨረሻ ምሽግ ሰባሪ ኃይል በጀግኖቹ የኃይለማርያም ማሞ አናብስቶች ተመቶ ወደ መጣበት ሾላ ከተማ ተመልሷል።

የአገዛዙ ብልፅግና ጥምር ጦር ከሀገረማሪያም ከሰም ሾላ ገበያ ያለ የሌለውን ሀይሉን በ አራቱም አቅጣጫ  ቢያሰማራም  የሃይለማርያም  ማሞ ክ/ጦር አናብስቶች  በአራቱም አቅጣጫ የመጣውን የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው መልሰውታል ።

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ቦጋለ ሻለቃ  በገበሬ ሸንጎ ግንባር የገበዉን የጠላት ኃይል ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰችበት ሲሆን በሌላ ግኖባር ደግሞ የነዳኛቸው ሻለቃ እና የክፍለ ጦሩ ቃኝዎች በጋራ በመሆን በመስኖ ግባር የገበዉን የጠላቶ ኃይል ከበባ ዉስጥ በማስገባት በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት  ማድረስ ችለዋል።

  በቅዱስኬ እና በጎርፎ እንዲሁም በመስቀለየሱስ ግንባር የገባዉን የጠላት ኃይል ደግሞ የቤዛ ሻለቃ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወደ መጣበት እንዲመለስ ማድረግ ችላለች።
           
ዛሬ በዋለዉ አዉደዉጊያ ከ9 በላይ የጠላት ኃይል  ሙት ሲደረግ  ከ13በላይ ደግሞ ቁስለኛ  አስተናግዶ ወደ ሾላ ከተማ ተመልሷል።

በአዉደዉጊያዉ  አንድ ከፍተኛ የጠላት  አዋጊ መቶ አለቃ እስከወዲያኛዉ መሸኘቱም ተረጋግጧል።

በአዉደዉጊያዉ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር  ቦጋለ ሻለቃ፣ቤዛ ሻለቃ እና ዳኛቸው ሻለቃ  የተሳተፉ ሲሆን  ሰላም ሰው ሻለቃ ደግሞ  ከአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት  ከሰም ኮረማሽ ንዑስ ወረዳ ላይ በሚገኘው  ኮረማሽ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅማለች።

በፖሊስ ጣቢያው ላይ በተሰነዘረ ጥቃት የደረሰዉ ጉዳት በዉል አልታወቀም።

በሸዋ ሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ መስኑ ቀበሌ በዋለዉ አዉደዉጊያ ከፍተኛ ሽንፍትን ያስተናገደዉ የአገዛዙ ሰራዊት የአርሶአደሩን ሰብል በማቃጠል የቂም ቁርሾዉን አወራርዷል።ዉጊያዉ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተደረገ ሲሆን የሃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በድል አጠናቋል።

የዛሬዉን አዉደዉጊያ አርበኛ መለሰ ከሳዬ የሃይለማርያም  ዋና ወታደራዊ አዛዥ እና አርበኛ አስር አለቃ ደፋሩ ተክለሚካኤል የክፍለጦሩ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ እንዲሁም የክፍለጦሩ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ዋሴ ማንጉዳይ እና ም/ዘመቻ  አስር አለቃ ሀይሌ ካሳ በተሳካ ሁኔታ መርተዉታል።

በተያያዘ መረጃ እራሱን ጥምር ጦር እያለ የሚጠራዉ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል በቀን 10/3/2018  የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ለምን ለማህበረሰቡ አገልግሎት ትሰጣላችሁ በማለት እገዳ በመጣል በእያንዳንዱ አሽከርካሪ 500 ብር ቅጣት በመጣል አሳፋሪ ተግባሩን በግልፅ አሳይቷል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በአንጎለላ እና ጠራ ጫጫ ወረዳ እንዲሁም በፊጦና አላ መስኖ ቀበሌ የአብይ አራዊት  ሰራዊት እና የብአዴን ቅጥረኛ ፖሊስና ሚሊሻ ወጣቱን በማፈስ ወደ አልታወቀ ቦታ መዉሰዱን የአይን እማኞች ለኃለማሪያም ማሞ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መረጃዉን አድረሰዋል።

ከታፈሱት መካከል አንድ ወጣት በሁለት ፖሊሶች  ተደብድቦ ከባድ ጉዳት ማስተናገዱ ተገልጿል።አፈሳውን እየመራ እና የአገዛዙን አጀንዳ እያስፈፀመ ያለው ደግሞ አረጋ ሞገስ የሚባል የጉልባና ቃፈሮ ቀበሌ ሊቀመንበር እንደሆነም ታዉቋል።


በሌላ መረጃ በኦሮሚያ ሸኖ ከተማ ከዘጠና( 90) በላይ  የአማራ ተወላጆች መታሰራቸዉ ተሰምቷል። ወጣቶቹ የታሰሩት በብሄራቸዉ ምክናየት መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

መድረሻው  ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ  ይቀጥላል።
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር
ህዳር 20/2018  ዓ.ም


መረጃዉ የሃይለማርያም ማሞ ክፍለጦ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሀቀኘዉ ይታፈር!!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
3🙏2
ከወራት በፊት በአገዛዙ ብልፅግና ተይዘዉ መኮድ ታስረዉ የነበሩት አባት ማረፈቸዉ ተነገረ።

ታላቁ ዋርካ አረፉ!!!!

እንዲህ ብለው ነበር!
ገዳሙን የሚመራ - በጉባኤ ቤቱ የሚያስተምር መምህር ፈልጉ!
{አራት ዐይና ይባቤ በላይ}

የታላቋ ናዳ ማርያም ገዳም ታሪክ በአጭሩ ይሄ ነው 👇

ፈለገ ብርሃን ናዳ ቅድስት ማርያም ገዳም በምዕራብ ጐጃም ሀገረ ስብከት ሜጫ ወረዳ ቤተ ክህነት በጉታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ናዳ በሚባል ቦታ ይገኛል፡፡ ገዳሙ በዐሥራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሠረተ ሲኾን፣ ታቦተ ሕጉም ከጣና ቂርቆስ ገዳም እንደ መጣ ይነገራል፡፡ ለብዙ ዓመታት ‹እንቍርቍሪት ጽዮን› እየተባለ ሲጠራ የቆየው ገዳሙ፣ ከዓመታት በኋላ ‹ናዳ ማርያም› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ናዳ የተባለበት ምክንያትም የሚከተለው ታሪክ ነው፤ በአካባቢው ዋናው ገዳም የሚባል ሌላ ጥንታዊ ገዳም ነበረ፡፡ በዚህ ገዳምም አባ ናዳ የሚባሉ አባት ይጸልዩበት ነበር፡፡ በዙርያውም በርካታ መነኮሳት ነበሩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አባ ናዳ በመሰላል ወጥተው የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ጣርያ ሲከድኑ መሰላሉ አንሸራቷቸው ወደቁ፡፡ በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻ በደኅና ካነሣቻቸው በኋላ ‹‹ወዳጄ አባ ናዳ ሆይ! ለዘለዓለም ስምህ በዚህ ቦታ ይጠራ›› በማለት ቃል ኪዳን ሰጠቻቸው፡፡ አባ ናዳም ገዳሙን አሁን ባለበት አኳኋን እንዲጸና አደረጉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‹እንቍርቍሪት› የሚለው ስያሜ ተለውጦ ‹ናዳ ማርያም› ወይም ‹ናዳ ጽዮን› ተብሎ መጠራት ጀመረ፡፡

ፈለገ ብርሃን ናዳ ማርያም ገዳም በየጊዜው የመጥፋት ፈተና ቢያጋጥመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደ ገና እየተመለሰ እስካሁን ድረስ ክብሩ እንደ ተጠበቀ፤ ወሰኑ እንደ ተከበረ፤ ልማቱም እንደ ቀጠለ ነው፡፡ ገዳሙ የአብነት ትምህርት ማእከል በመኾኑና ዙርያው በምንጭ በመከበቡ የተነሣ ከ፲፱፻፹፮ ዓ.ም ጀምሮ በጊዜው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበሩት ብፁዕ አቡነ በርናባስ ፈቃድ ‹ፈለገ ብርሃን› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ገዳሙ በዚህ መልኩ እየሰፋ መጥቶ በአሁኑ ሰዓት አገልግሎቱም ጉባኤ ቤቱም በአግባቡ እየተከናወነ ነው፡፡ ከፈለገ ብርሃን ናዳ ማርያም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በተጨማሪ የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላልይበላ እና የጋፈራ ደብር ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት ለመነኮሳቱ እና ለአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓትም የክብረ ደናግል ቅዱስ ላሊበላ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ ጥበብ በአዲስ መልክ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

(ምንጭ፡- ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ፤ ገዳሙ ያሳተመው ብሮሸር)

ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ

ምንኵስናን ከሊቅነት፣ አባትነትን ከሥራ ጋር አስተባብረው በያዙት በሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ አማካይነት ከ፲፱፻፸፱ ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ በገዳሙ የትርጓሜ መጻሕፍት እና የቅኔ ትምህርት በመሰጠት ላይ ነው፡፡ ከሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ ጉባኤ ቤት ተምረው በልዩ ልዩ የአገልግሎት ዘርፍ ተሰማርተው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉ ካህናትና መምህራንም እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ የገዳሙ ዋና አስተዳዳሪ፣ የትርጓሜ መጻሕፍትና የቅኔ መምህሩ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ እኒህን ታላቁን ሊቀ ነው ዛሬ ከዓለም ድካም ያረፉት!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
4💔2
ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በዛሬዉ ዕለት ከ8 በላይ የአገዛዙ ሰራዊትን በመደምሰስና ከ17 በላይ የሚሆኑ የአገዛዙ ሰራዊትን በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፏል ::

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነው ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ባደረገው አውደ ዉጊያ ከ8 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ17 በላይ ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል።

የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት 12ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት፣የ65ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት ኃይልና የ65ኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ በጥምረት አንድ ዙ-23 እና አራት ዲሽቃ በመያዝ መነሻውን ከላስታ ወረዳ ብልባላ ከተማ በማድረግ ህዳር 16/2018 ዓ/ም ዳቢያና አሞራ ደብር ድባቅ ተመትቶ መመለሱ ይታወቃል።

በዚህ ሽንፈቱ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ከህዳር 18 ጀምሮ ኃይሉን ጨምሮ በድሮን ታግዞ ውጊያ ያደረገ ቢሆንም ተወርዋሪዎቹ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ፋኖዎች ሦስት ቀን ሙሉ ምሽግ መከላከል በማድረግ በአራተኛው ቀን ዛሬ ህዳር 21/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በጠረዛና መዛርድ ግንባር በቆረጣ በመግባት በተደረገ አውደ ውጊያ የጠላት ኃይል ወደ ነበረበት ምሽግ ተቀጥቅጦ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ተመልሷል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 21 / 2018 ዓ.ም
🙏21👍1
አዛሳኝ መረጃ!

አገዛዙ በተደጋጋሚ እስርና እንግልት ሲፈፅምባቸው የነበሩት አራት አይናው አበምኔት አረፉ!

የትርጓሜ መጻሕፍት፣ የአቡሻኽር፣ የፍትሐ ነገሥት እና የቅኔ መምህር፤ በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት የክብረ ደናግል ናዳ ቅድስት ማርያም ገዳም አበምኔት የሆኑት አራት አይናው መምህር ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ ከዚህ አለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።

ታላቁ አባት መምህር ቆሞስ አባ ይባቤ፡ አገዛዙ ተደጋጋሚ  የሆነ እስርና እንግልት ሲፈፅምባቸው እንደነበር አይዘነጋም።

እየደረሰባቸው ካለው መንግስታዊ እስርና ማሳደድ አኳያ "ገዳሙን የሚመራ - በጉባኤ ቤቱ የሚያስተምር መምህር ፈልጉ" በሚል ለገዳሙ አበምኔቶች መልዕክት ሲያስተላልፉ መሰንበታቸውም ተነግሯል።

አራት አይናው አባት፡ ትናንት ህዳር 21/2018 ዓ/ም ለዛሬ አጥቢያ ሕይወታቸው ማለፉ ነው የታወቀው።
💔31