ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 2ተኛ እንድሪስ ተሾመ ሻለቃ ሰራዊት ዛሬ ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ/ም በምዕራብ ወሎ ግንባር ከላላ ወረዳ ቆርኬ ቀበሌ ውስጥ ድል አስመዘገበ::

ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) 2ተኛ (እንድሪስ ተሾመ) ሻለቃ ሰራዊት ከጧቱ 2 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት ባካሄደው ውጊያ ከከላላ ከተማ ተነስቶ ለወረራ ወደ ቆርኬ የገባው ጠላት ላይ ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰ ሲሆን በድምሩ 7 የአድማ ብተና አባላት በእነ ሞት አይፈሬ ጥይት ተመትተው ሁለቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎችን ቁስለኞች ሸክሮ ጠላት ፈርጥጧል ሲል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ይማም ሁሴን ለዕዙ በላከው ሪፓርት አስታውቋል። 

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም
1🙏1
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ የተላለፈ መልዕክት

ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም መካነሰላም ከተማ ውስጥ የአንድ ካህን ሚስትን ጨምሮ በድምሩ 3 እመጫት እናቶች ታፍነው ወደ ካምፕ ተወስደው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ገረድ በሆነው የፀጥታ ኃይል አባል ተደፍረው የግፍ ግፍ እንደተፈፀመባቸው በሰማሁ ጊዜ እጅጉን ማዘኔን እየገለፅኩ ህዝባችን እንዲህ አይነት ዘግናኝ ድርጊት እየፈፀሙ ታሪኩን እና ሀይማኖቱን እንዲሁም እሴቱን የሚሸረሽሩትን ለመታገል ጥርሱን ነክሶ ዳር እስከ ዳር ይነሳ ዘንድ ይህን የትግል ጥሪ ለማቅረብ እወዳለሁ።

አማራ በእርስቱ፣ በሚስቱ እና በእምነቱ ማለትም በድኑ እና በማተቡ አይደራደርም። የተፈፀመው ዘግናኝ ድርጊት ደግሞ በእርስት እና በማንነት ብቻ ሳይሆን በሚስት እና በሀይማኖት የመጣ ጠላት ስለመኖሩ አስረጅ ነው። የካህን (ቄስ) ሚስትን አስገድዶ የሚደፍር ኃይል በአማራ ምድር እንኳን 3 ዓመት 3 ቀን ውሎ ማደር አልነበረበትም። ይህን ያክል ጠላት በነፍሳችን ጭምር ሊጫወት የቻለው አንድ ሆነን ዳር እስከ ዳር ባለመነሳታችንና ጠላታችንን አምርረን ባለመጥላታችን ነው።

የሰሞኑ የግፍ ግፍ ብቻ ሳይሆን ባለፉት ዓመታት ህዝባችን የተሸከመው የመከራ ቀንበርን ክብደት ሁላችንም የምናውቀው ነው።

ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመካነሰላም ከተማ ዙሪያ ገጠር ወረዳ መቅደላ ታዳጊ ከተማ አቅራቢያ ይሄው ኦሮሙማው ስርዓት ዘብ የሆነው ፀረ አማራ ቡድን 5 ንፁሓን ወጣቶችን መረሸኑም ይታወሳል። የልጆቻችንን የመከራ ድንኳን ሳይነቀል ድጋሜ ቀያችን ላይ የተፈፀመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፀረ አማራውን ቡድን አረመኔነት ገላጭ ነው።

ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም የተደፈሩት እናቶቻችን ለህፃናት ልጆቻቸው ፓምፕሌት እንድወስዱ በጤና ባለሙያዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ከገጠር ወደ መካነሰላም ከተማ የሄዱ መሆናቸው ታውቆ ከእንግዲህ መሰል ጥሪ ሲደረግ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መጓዝ እንደሚያስፈልግ ለማሳሰብም እወዳለሁ። እመጫት እናቶችን እና የካህናት ሚስቶችን በመድፈር የአማራ ህዝብን ክብር እና ታሪክ ለማበላሸት ቆርጦ የተነሳውን አረመኔ ቡድን ለማስወገድ የምናደርገውን የህልውና ትግል በመደገፍ ህዝባችን ለአይቀሬው ድል እንድዘጋጅ ከወዲሁ ለማሳሰብም እወዳለሁ።

የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ ምትኩ

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም
1🙏1
ለህዝባችን ለምንሰጠዉ አገልግሎት የተሳካ እንዲሆን ፋኖ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል ሲሉ የጤና ባለሙያዎች ተናገሩ።

በሰሜን ጎንደር ዞን በተለያዩ አካባቢዎች የህፃናት ክትባት በተገባው መንገድ እየተሰጠ መሆኑን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የራስ አሞራዉ ዉብነህ ሶስተኛ ኮር አስታዋቋል።

ለህፃናት ክትባት ለመስጠት ወደ ቀጠናው የገቡ የጤና ባለሙያዎችን በተገቢው መንገድ እንክብካቤ እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝ የራስ አሞራዉ ዉብነህ ሶስተኛ ኮር ጫና ክፍለጦር አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አርበኛ መለሰ ብርሀን ለግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተናግሯል።

የህክምና ባለሙያዎች የመንከባከብ ግዴታ አለብን ያለዉ አርበኛ መለሰ፣በዚህ መሸረትም ባለሙያዎቹ በነፃነት በመንቀሳቀስ ለህዝባችን የህክምና አገልግሎት እየሰጢ ይገኛሉ ብሏል።ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ህዝብ የጣለባቸዉን ሙያዊ ኃላፊነት በሚገባ እየተወጡ በመሆናቸዉ በአማራ ፋኖ ብሄራዊ በላይ ዘለቀ ዕዝ ላቅ ያለ ምስጋና ተችሯቸዋል።

ለህዝባችን የተሳካ የህክምና አገልግሎት እንድሰጥ አስቻይ ሁኔታ ለፈጠረልን ፋኖ ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ በቀጠናው የተሰማሩ የጤና ባለሙያዎች ገልፀዋል።ወደ ፊትም ለምናከናውነው ስራ የተሳካ እንዲሆን የፋኖ ድጋፍ እንዳይለየን ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት ለመንግሥት ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበን ያልተፈታልን ጥያቄ አሁን ላይ ጥያቄያቸን ለፋኖ በማቅረባችን አፋጣኝ ምላሽ ተሰቶናል ሲሉ የአካባቢው ማህበረሰብ ተናግረዋል ።አገልግሎቱ ቀጠይነት እንዲኖረዉ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተጠቁሟል።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
2🙏1
በከተሞቾ የሚደረገዉ የወጣቶች አፈሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የአገዛዙ ብልፅግና ጥምር ጦር ኃይል በአማራ ክልል በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ወጣቶችን አፍሶ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምሀርት ቤት መዉስዱ እየተነገረ ይገኛል።

በዚህ ሳምንት በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች የተጠናከረ አፈሳ ተካሂዷል።በአማራ ክልል በሚደረገዉ የወጣቶች አፈሳ የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት የቆሎ ተማሪዎች መታፈሳቸዉ የብልፅግናዉን መንግስት አረመኒያዊነት በግል ያሳየ ተግባር ተብሏል።

አገዛዙ ከዚህ በፊት በጎጃም ሜጫ 16 የቆሎ ተማሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸኑ ይታወሳል።ዛሬ ላይ ደግሞ በእየ አብያተክርስቲያናቱ የሚሊሺያ ኃይል በማሰማራት በርካታ የቆሎ ተማሪዎችን እንዲታፈሱ አድርጓል።ፀረ አማራው የአብይ አህመድ አሊ አገዛዝ ከአማራ ህዝብ ላይ እና አብያተክርስቲያናት ላይ የሚፈፅመዉ የተጠና ጥቃት አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በሰሜን ወሎ ዞን መናገሻዋ ወልድያ የፈፀመዉ ግፍ አሳዛኝ ክስተት ነዉ ሲሉ የወልድያ ከተማ ኗሪዎች ተናግረዋል።

ዛሬ ህዳር 20/2018 ዓ.ም ከጧቱ 2:00 የአገዛዙ ለብልፅግና ሚሊሺያ ኃይል የቆሎ ተማሪዎች አፍሰው ወደ አልታወቀ የወሰዱ ሲሆን ከአፈሰዉ ለማምለጥ የሞከሩ የቆሎ ተማሪዎች ደግሞ መገደላቸው ተረጋግጧል።

ይህ የአገዛዙ ድርጊት በጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች የተፈፀመ ሲሆን በሰሜን ጎንደር ጃናአሞራ፣አጅሬ እና ዳባት ቁጥራቸው በዉል የማይታወቅ የቆሎ ተማሪዎች ታፍሰዉ ተወስደዋል።በደቡብ ጎንደር ጉና በጌምድር ከወራት በፊት 20 የቆሎ ተማሪዎች ታፍሰዉ የተወሰዱ ሲሆን ሰሞኑን እየተደረገ ባለዉ አፈሳ ደግሞ ወለላባህር፣አጎና፣ስማዳ፣ደራ እና ፎገራ እንዲሁም ስማዳ የቆሎ ተማሪዎች መታፈሳቸዉ ተረጋግጧል።

አገዛዙ ከቆሎ ተማሪዎች አፈሳ በተጨማሪ የከተማ ወጣቶችን አፈሳም አጠናክሮ ቀጥሏል።ባለፈዉ ሳምንት ቅዳሜ በመዲናዋ አዲስአበባ ሁለት ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ወጣቶች መታፈሳቸዉን መዘገባችን ይታወሳል።

ዛሬም አፈሳው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የታፈሱ ወጣቶች በየክፍለከተመዉ በሚገኝ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ታጉረዉ እንደሚገኙ ተገልጿል።በባህርዳር፣ጎንደር፣ደብታቦር፣ማርቆስ እና ፍኖተ ሰላም የወጣቶች አፈሳ ከወትሮው በተለየ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተነገረ ሲሆን በደቡቡ የሀገሪቱ ክፍልም አፈሳዉ ተጧጡፎ ቀጥሏል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጅ፣ቦንጋ፣አሪ፣ጅንካ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ፣ጋሞ፣ጎፍ፣በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዉልቂጤ፣ቡታጅራ እና ሰልጤ በአስገዳጅ ሁኔታ የታፈሱ ወጣቶች ተጭነዉ ወደ አዲስአበባ እየተወሰዱ ነዉ ተብሏል።

በኦሮሚያ ክልል የሚታፈሱ ወጣቶች መኖራቸዉን እና አብዛኞቹ በቤተሰቦቻቸው በተከፈለላቸዉ ገንዘብ መለቀቃቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል።አንድ ቤተሰብ በሚሊሻ የተያዘዉን ልጁን ለማስለቀቅ እስከ 200 ሺህ ብር ድረስ እንደሚከፍል ተገልጿል።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
💔1
እስካሁን በጫካ የቆያችሁት ምን እስክታገኙ ነበር???!!!

👉አብረዋችሁ የወጡ ወንድሞቻችሁ በሞት እስኪለዩዋችሁ?
ወንድምን ጫካ ላይ ቀብሮ በናት መቀነት ሳንቲም የተገዛን መሳሪያ ተሸክሞ ለጠላት እጅ መስጠት የሚያስችል ሞራልስ ከየት አገኛችሁት?
👉 የቤተሰብ፣ዘመድ፣ጎረቤት፣ቤተ እምነት..ሀብት ንብረት በድሮን፣ጀትና መድፍ እስኪወድም?
👉 እውነተኛ ወንድሞቻችሁ ባስታጠቋችሁ መሳሪያ ወንድሞቻችሁን በማገት፣በስርቆትና ውንብድና ስጋዊ ፍላጎታችሁ እስኪሟላ?
👉 ባይን ጥቅሻ ይግባቡ የነበሩ ወንድሞቻችሁ በናንተ ሀሳዊ ነገር በማመላለስ እስኪጋጩ?
👉 በብዙ ውጣ ውረድ በመልካም ስብዕና የታነጹ መሪዎች በናንተ ምክኒያት እስኪዋረዱ?
👉 ምን ብላችሁ ወጥታችሁ ምን አሳክታችሁ ነው ለገዳዮቻችሁ እጅ የሰጣችሁ???!!!

ከትላንት እስከዛሬ እጅ ለመስጠት የሚያስችል በቂ ምከኒያት አለን በማለት እራሳችሁን ለምታረኩ ባንዳዎች ሁሉ ነው ጥያቄየ?!!!
አርበኛ እሸቱ ጌትነት አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ አደረጃጀት መምሪያ ሃላፊ።


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
👍31
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር  ውጤታማ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን አከናወነ።
    በጀነራል ተፈራ ማሞ የተሰየመችው ብርጌድ  ሻለቃ አንድን (መብረቁ እየተባለች የምትጠራውን  እንደስሟ መብረቅ የሆነችውን  ሻለቃ ) ለከተማ ኦፕሪሽን ሸማቂዎቹን በመላክ አስገራሚ ጀብድ ፈፀመች።
    ቀን 20/03/2018 ዓ ም  የብልፅግና የዕድሜ ማራዘሚያ እየተባሉ በህዝባቸው ላይ የመከራ ቀንበር እንዲሸከም የሚያረጉ ዙፋን ጠባቂ ሚሊሻዎች ውስጥ   አምስቱ (5)  የሚሆኑት በመብረቁ ሻለቃ ሸማቂዎች ወደ ፈጣሪያቸው የተሸኙ ሲሆን ሶስት የሚሆኑት ደሞ በህክምና ላይ ነፍስ ውጭ ነፍስ ጊቢ ላይ እንደሚገኙ በውስጥ መረጃችን ማረጋገጥ ችለናል።
መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።
   ይህ ኦፕሪሽን የፈፀመው በአረርቲ ከተማ በቀን 19/03/2018  ዓ ም ከምሽቱ 1:45 አካባቢ  ላይ መጠጥ ቤቶችን ለማዘጋት ሲንቀሳቀሱ  እንደሆነ ተገልፀጿል።
መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
1🙏1
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ንፁሃን አማራዎችን በግፍ እየጨፈጨፈ ቀጥሏል::

የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ አንድ አቶ ብርሃኑ ተሾመ የተባለ አባት ከባለቤቱና ከአራት ልጆቹ ፊት በግፍ የገደለ ሲሆን ሁለት ዲያቆኖችንም ባደባባይ ረሽኗል::

ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ንፁሃን አማራዎችን በግፍ ባደባባይ እየረሸነ ያለ ሲሆን ዛሬ ህዳር 21/2018 ዓ.ም ሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ መርጦ ከተማ ላይ አቶ ብርሃኑ ተሾመ የተባሉ የ48 አመት አባት ከባለቤቱ እና ከአራት ልጆቹ ፊት መኖሪያ ቤቱ ላይ በዱላ ደብድበው ባሰቃቂ ሁኔታ ገድለውታል::

በተመሳሳይ ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ስሙ አባርጎ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ሁለት ዲያቆኖች በፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት ባደባባይ በጥይት ተደብድበው በግፍ ተረሽነዋል::

እድሜያቸው 15 እና 18 አመት የሆኑት እነዚህ ታዳጊዎች ዲያቆንና የመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን አገልጋይ ሲሆኑ የቀብር ስነስርዓታቸውም እዚያው ሲያገለግሉት በነበረው ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል::

ፋሽስቱ አገዛዝ ወጣቶችን ዩንቨርስቲና ትምህርት ቤቶች ብሎም ሃይማኖታዊ ቦታዎች ላይ ሳይቀር እያፈሰ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እያስገባ ያለ ሲሆን ሰሞኑን ወልድያ ከተማ ከአፈሳው ለማምለጥ የሞከሩ ንፁሃን ወጣቶችን ባደባባይ በጥይት ደብድቦ መግደሉ ይታወቃል::

ይህ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ንፁሃን ላይ ነፃ እርምጃ የመውሰድና በግፍ የመጨፍጨፍ ተግባሩ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፋኖ ትላልቅ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎች ከተጎናፀፈበት ዘመቻ "አባ ናደው" በኋላ ፋኖውን መቋቋም ሲያቅታቸው ንፁሃኑን መጨፍጨፍ በሚል በርካታ የሰው ህይወት በተናጠልና በጅምላ እያለቀ ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ሕልውናችን በተባበሩ ክንዳችንዜ
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 21/2018 ዓ.ም
💔21
ወጣቱ ሁለት የአገዛዙ ወታደሮችን አንገት አንቆ ባህር ውስጥ በመስጠም የአጥፍቶ ጠፊ እርምጃ ወሰደ!

ዮናስ ክንፈ ይባላል። ገና የ24 አመት ወጣት ነበር። ተወልዶ ያደገው አንጎት ወረዳ 01 ቀበሌ ውስጥ ነው። በዚህ ወረዳ ከዚህ ቀደም የወረዳው የሚኒሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በፋኖ መገደሉ ይታወቃል።

ከሚኒሻው ግድያ ጋር ተያይዞ ዮናስ ክንፈን የአገዛዙ ወታደሮች ከቤቱ አፍነው በመውሰድ ያሰቃዩታል። ለአንድ ወር ሲያሰቃዩት ከርመው ምንም አይነት የወንጀል ፍንጭ ሲያጡበት ከአንድ ወር እገታ በኋላ ተለቆ ወደ ትውልድ ቀየው ተመለሰ።

ፀረ አማራው ኃይል፡ ዮናስን"መልክህ አላማረንም" በሚል ሰበብ እንደገና የክፋትና የስቃይ መረቡን ያጠምድበታል። ዮናስ የአረመኔዎችን እንቅስቃሴ ተመልክቶ አካባቢውን ለቆ ተሰወረ። ሌላ ቦታም የቀን ስራም ቢሆን እየሰራ ለመኖር የትውልድ ቀየውን ለቆ ተሰደደ።

ዮናስ ሀገር ለቆ መሰደዱን የሰማው የብልፅግና ኃይል፡ የዮናስን አባት ከመኖሪያ ቤታቸው ሂዶ በማፈን ለእስር ይዳርጓቸዋል።

ዮናስ የአባቱን በአረመኔዎች እጅ መውደቃቸውን ሲሰማ እራሱን በአባቱ የስቃይ ቦታ ላይ ለማድረግ ወስኖ ወደ አረመኔው የአገዛዙ ሰራዊት መጥቶ እጅ ሰጠ።

የፋሽስቱ ዐብይ አህመድ ገዳይ ወታደሮች ዮናስን እደተራበ ጅብ እያፋሸጉ ተቀበሉት።

ዮናስን ልብሱን አስወልቀው እርቃኑን አቁመው ለመስማት የሚሰቀጥጥ፡ ለማየት የሚዘገንን ግፍ ፈፀሙበት።

እጆቹን የፍጥኝ ወደኋላ አመሰቃቅለው 8 ቁጥር እስር ካሰሩት በኋላ በገላው ላይ በእሳት የሚነድ ላስቲክ  አንጠባጠቡበት።

በላስቲኩ የእሳት ጠብታ ተቃጥሎ ስጋው ቀልጦ አጥንቶቹ ጠቁረው እስኪታይ ድረስ እጅግ ከባድ ግፍ ፈፀሙበት።

በመጨረሻም ዮናስ፡ ከዚህ ስቃይ ይገላገል ዘንድ ጨፍጫፊዎቹን "የደበቅኩት መሣሪያ አለኝ እሱን ልስጣችሁ ወደ ደበቅኩበት ቦታ ውሰዱኝ" ይላቸዋል።

ደብዳቢዎቹም ለአለቃቸው ሂደው ይነግሩታል። "ጥሩ መሳሪያውን አምጡት ይሄማ ጥሩ ብር ነው። ሽጠን ወደ ኪሳችን እናደርጋለን። ከዚህ ጦርነትኮ ያለን ትርፍ ገንዘብ ነው።ሰለዚህ ከደበቀበት ቦታ ያሳያችሁና መሣሪያውን አምጡ" የሚል መልክት ሲሰጣቸው ዮናስን በላስቲክ የተቃጠለ አካላቱን ልብስ አልብሰውና ሸፍነው መሳሪያውን ከቀበረበት ቦታ እንዲወስዳቸው አደረጉት።

ዮናስ አንድ ውሳኔ በልቡ ወስኗል። በጋዞ ከሚገኝ እግድ ባህር ከሚባል ቦታ ላይ እንደደረሱ መንገዳቸው በባህሩ ዳርቻ ነበር።

ዮናስ፡ ከተከተሉት ሶስት የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የሁለቱን ወታደሮች አንገት አንቆ በመያዝ ወደ ጥልቁ ባህር ይዟቸው ሰጠመ።

ዮናስ ገዳዮቹን ገሎ ራሱን ከስቃይ ታድጎ የፀጋ፣ የክብር፣ የጀግና ሞትን ሞተ።

ሦስተኛው የመከላከያ ሰራዊት አባል፡ ዮናስ ሁለቱ ጓዶችህን ባህር ገፍትሯቸው እሱም ሲገባ አንተ ምን አየሰራህ ነበር በሚል ትጥቅ እንዲያወርድ ተደርጎ ተረሽኗል።

የሁለቱ መከላከያ ሰራዊት አባላት አስከሬን እና የዮናስ ክንፍ አስከሬን ከሰጠሙበት ባህር በስምንተኛው ቀን ተንሳፎ ታየ።

የአገዛዙ ወታደሮች የራሳቸውን አስከሬን ከባህሩ አውጥተው ከቀበሩ በኋላ የዮናስን አስከሬን አናስወጣም በሚል የከለከሉ ቢሆንም፡ የአከባቢው ማሕበረሰብ "ከዚህ በላይ ምን ልታደርጉት ነው?" በሚል ቁጣና እቢተኝነት የዮናስን አ*ስ*ከ*ሬን ከባህሩ አውጥተው  ተወልዶ ባደገባት መንደር የጀግና ስርዓተ ቀብር ፈፀሙለት።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም
🔥1🙏1
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የህዝብ አስተዳደር መምሪያ ንዑስ ወረዳዎችን እያዋቀረ ያለ ሲሆን በጉባላፍቶ ወረዳ ማሶ ንዑስ ወረዳን አዋቀረ::

ምኒልክ ዕዝ ነፃ በወጡ ቀጠናዎች የህዝብ አስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ ሲሆን ሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ማሶ ንዑስ ወረዳን አዋቅሮ የህዝብ አስተዳደርና ፍርድ ቤት ጭምር አደራጅቷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 21/2018 ዓ.ም
👍1🙏1