ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የይርጋ ሲሳይ ሌቦች በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

አገዛዙ ብልፅግና ያሰማራቸው የአድማ ብተና ሌቦች በዘረፋ ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

በደቡብ ጎንደር ቀጠና የተሰማሩ የአገዛዙ ተልዕኮ ፈፃሚ ሌቦች በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ፩ኛ ኮር ቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተነግሯል።

ሰው በማገት፣አስገድዶ በመድፈር፣አሽከርካሪዎች
ን በማገት እና በመግደል ወንጀል ላይ የተሰማሩ የብአዴን አጀንዳ ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተደረገባቸዉ ይገኛሉ።

በአገዛዙ ብልፅግና የተሰማሩ የአድማ ብተና እና የሚኒሻ አባላት የፋኖን ልብስ አልብሶ ወደ ቀጠናው እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ በማህበረሰቡ ላይ ዘረፋ እንዲፈፅሙ ግዳጅ ስለመሰጠታቸዉ መናገራቸዉን ኮሩ አስታዉቋል።

ትናንት ህዳር 19/2018 ዓ.ም በደራ ወረዳ የአገዛዙ ጥምር ጦር ሰራዊት እየተተራመሰ ባለበት ቀጠና አገዛዙ ያሰማራቸው #ሁለት_የአድማ_ብተና አባላት አስፓልት ላይ የህዝብ መኪና በማስቆም ስልክን ፣ገንዘብ፣የእጅ ቀለበት ሳይቀር እየቀሙ በነበረበት ሰአት የሚጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር የጣና ገላውዲዎስ ክፍለጦር በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

አናብስቶች በልዩ ኦፕሬሽን ወሮበላዎችን ያለምንም ተኩስ እስከ ዘረፉት ንብረት ስልክ እና ሙሉ ትጥቃቸው በመማረክ በቁጥጥር ስር አውለዋል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አስታዉቋል።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
💔1
የ206ኛ ኮር አደረጃጀት ዘርፍ መምሪያ የመልሶ ማደራጀት ተግባሩን በተቀላጠፈ ሁኔታ እየፈፀመ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ህዳር 20/2018 ዓ.ም

የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ መዋቅርን በማሻሻል ሰራዊቱን ለተሻለ ግዳጅ እያበቃ ሲሆን በመልሶ ማደራጀት ተግባሩ ትኩረት ሰጦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው 206ኛ ኮር በስሩ ያሉ ክ/ጦሮችን በማደራጀት ሰራዊቱን በጠንካራ ሻለቆች እያዋቀረ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን አጠቃሎ በአዲስ የተደራጀው ጊዜያዊ መንግስት በኮሩ ቀጠናዎች ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ቢሮ በመክፈት አገልግሎት መጀመሩን ያረጋገጠው የ206ኛ ኮር አደረጃጀት መምሪያ የተሰጠውን ድርጅታዊ ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግሯል።

ኮሩ የስራ ስምሪት ወስዶ ከተንቀሳቀሰ ጀምሮ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ያወሳው መምሪያው 24ኛ ክ/ጦርን በመልሶ ማደራጀት ተግባሩ ሙሉለሙሉ ያዋቀረ ሲሆን የክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስን ጨምሮ ቀጠናውን ሸፍነው የሚንቀሳቀሱ ጠንካራ ሻለቆችን በማደራጀት ክ/ጦሩ የሚሰጠውን ግዳጅ በብቃት ለመወጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ አክሎ ገልጿል።

ከመልሶ ማደራጀት ትግበራው ጎን ለጎን ከአካባቢው ማህበረሰብ ፣ከሀገር ሽማግሌዎች፣ሴቶችና ነጋዴዎች እንዲሁም ከመላው ሰራዊቱ ጋር አስቀድሞ ውይይት ያደረገው 206ኛ ኮር ግዳጆችን በብቃት ለመወጣት የማህበረሰቡ ተሳትፎ አይነተኛ ሚና እንደነበረው የ206ኛ ኮር አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ ፲አለቃ ደርሳችሁ አትንኩት ከ206ኛ ኮር የሚዲያ ክፍል ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
👍21
በሸዋ የተሰማረዉ የአገዛዙ አየር ወለድ ኮማንዶ እርምጃ ተወስዶበታል!!!

በሸዋ አልዩ አምባ ላይ በተደረገ ተጋድሎ አንድ አይሱዝ ሙሉ የአየር ወለድ ኮማንዶ አባላት ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸው ተሰምቷል።

በቀጠናው በተደረገ ትንቅንቅ እርምጃ ከተወሰደባቸው የአየር ወለድ ኮማንዶ አባላት በተጨማሪ፡ አንድ የአድማ ብተና አዛዥ ሲገደል ሌላኛው አዛዥ ደግሞ አንገቱ ላይ በስናይፐር ጥይት ተመትቶ በሕይወትና በሞት መካከል እንደሚገኝ ከስፍረዉ የደረሰን መረጃ ያመላክታል!!

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏2
እሸት ክፍለ ጦር ለወራት ያሰለጠናቸዉን የፋኖ ሰራዊቶች በዛሬዉ ዕለት በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር እሸት ክፍለ ጦር ለተከታታይ ወራት ያሰለጠናቸዉን ፋኖወች በዛሬዉ ዕለት ማለትም ህዳር 20/2018 ዓ.ም አስመርቋል።

ተመራቂ ፋኖወችም ለወራቶች በአካል ብቃት፣ በተኩስ ፣ በሰልፍ እና ወታደራዊ ሳይንሱ የሚጠይቀውን እውቀት እና ጥበብ ቀስመዉ ተመርቀዋል።

በዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይም የነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ አዛዥ ሻለቃ ደምሌ ጣፋጭ (ጥንቅሹ) ጨምሮ የላስታ አሳመነዉ ኮር ከፍተኛ አመራሮች እና የእሸት ክፍለ ጦር አመራሮች ተገኝተዉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተመራቂዎቹ የፋኖ አባላቶችም እኛ የህልውና ትግሉን በድል ለማጠናቀቅ ብቻ ሳይሆን ስለ ነገይቱ ኢትዮጵያ አስበን ጭምር ነዉ የሰለጠነዉ ብለዋል።

ሰልጣኞቹ አክለዉም እኛ ሰልጥነን ለዚች እለት ስንበቃ እኔ ጎጃም፣ እኔ ጎንደሬ፣ እኔ ሸዋዬ፣ እኔ ወሎዬ እንድንል ሳይሆን አንድ ሁኑ የሚለውን የጄኔራል አሳመነው ፅጌ የኑዛዜ ቃል አክብረን በአማራነታችን ፀንተን እንቆማለን ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ተመራቂዎቹ የተሰጣቸዉን አደራ በአግባቡ እንደሚወጡ ቃለ መሃላ በመፈፀም ቃል ገብተዋል።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ  ፋኖ ደረበ መኮንን!

"ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!"

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ
ህዳር 20/2018 ዓ.ም


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
2🙏1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 2ተኛ እንድሪስ ተሾመ ሻለቃ ሰራዊት ዛሬ ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ/ም በምዕራብ ወሎ ግንባር ከላላ ወረዳ ቆርኬ ቀበሌ ውስጥ ድል አስመዘገበ::

ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) 2ተኛ (እንድሪስ ተሾመ) ሻለቃ ሰራዊት ከጧቱ 2 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት ባካሄደው ውጊያ ከከላላ ከተማ ተነስቶ ለወረራ ወደ ቆርኬ የገባው ጠላት ላይ ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰ ሲሆን በድምሩ 7 የአድማ ብተና አባላት በእነ ሞት አይፈሬ ጥይት ተመትተው ሁለቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎችን ቁስለኞች ሸክሮ ጠላት ፈርጥጧል ሲል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ይማም ሁሴን ለዕዙ በላከው ሪፓርት አስታውቋል። 

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም
1🙏1
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ የተላለፈ መልዕክት

ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም መካነሰላም ከተማ ውስጥ የአንድ ካህን ሚስትን ጨምሮ በድምሩ 3 እመጫት እናቶች ታፍነው ወደ ካምፕ ተወስደው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ገረድ በሆነው የፀጥታ ኃይል አባል ተደፍረው የግፍ ግፍ እንደተፈፀመባቸው በሰማሁ ጊዜ እጅጉን ማዘኔን እየገለፅኩ ህዝባችን እንዲህ አይነት ዘግናኝ ድርጊት እየፈፀሙ ታሪኩን እና ሀይማኖቱን እንዲሁም እሴቱን የሚሸረሽሩትን ለመታገል ጥርሱን ነክሶ ዳር እስከ ዳር ይነሳ ዘንድ ይህን የትግል ጥሪ ለማቅረብ እወዳለሁ።

አማራ በእርስቱ፣ በሚስቱ እና በእምነቱ ማለትም በድኑ እና በማተቡ አይደራደርም። የተፈፀመው ዘግናኝ ድርጊት ደግሞ በእርስት እና በማንነት ብቻ ሳይሆን በሚስት እና በሀይማኖት የመጣ ጠላት ስለመኖሩ አስረጅ ነው። የካህን (ቄስ) ሚስትን አስገድዶ የሚደፍር ኃይል በአማራ ምድር እንኳን 3 ዓመት 3 ቀን ውሎ ማደር አልነበረበትም። ይህን ያክል ጠላት በነፍሳችን ጭምር ሊጫወት የቻለው አንድ ሆነን ዳር እስከ ዳር ባለመነሳታችንና ጠላታችንን አምርረን ባለመጥላታችን ነው።

የሰሞኑ የግፍ ግፍ ብቻ ሳይሆን ባለፉት ዓመታት ህዝባችን የተሸከመው የመከራ ቀንበርን ክብደት ሁላችንም የምናውቀው ነው።

ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመካነሰላም ከተማ ዙሪያ ገጠር ወረዳ መቅደላ ታዳጊ ከተማ አቅራቢያ ይሄው ኦሮሙማው ስርዓት ዘብ የሆነው ፀረ አማራ ቡድን 5 ንፁሓን ወጣቶችን መረሸኑም ይታወሳል። የልጆቻችንን የመከራ ድንኳን ሳይነቀል ድጋሜ ቀያችን ላይ የተፈፀመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፀረ አማራውን ቡድን አረመኔነት ገላጭ ነው።

ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም የተደፈሩት እናቶቻችን ለህፃናት ልጆቻቸው ፓምፕሌት እንድወስዱ በጤና ባለሙያዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ከገጠር ወደ መካነሰላም ከተማ የሄዱ መሆናቸው ታውቆ ከእንግዲህ መሰል ጥሪ ሲደረግ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መጓዝ እንደሚያስፈልግ ለማሳሰብም እወዳለሁ። እመጫት እናቶችን እና የካህናት ሚስቶችን በመድፈር የአማራ ህዝብን ክብር እና ታሪክ ለማበላሸት ቆርጦ የተነሳውን አረመኔ ቡድን ለማስወገድ የምናደርገውን የህልውና ትግል በመደገፍ ህዝባችን ለአይቀሬው ድል እንድዘጋጅ ከወዲሁ ለማሳሰብም እወዳለሁ።

የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ ምትኩ

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም
1🙏1
ለህዝባችን ለምንሰጠዉ አገልግሎት የተሳካ እንዲሆን ፋኖ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል ሲሉ የጤና ባለሙያዎች ተናገሩ።

በሰሜን ጎንደር ዞን በተለያዩ አካባቢዎች የህፃናት ክትባት በተገባው መንገድ እየተሰጠ መሆኑን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የራስ አሞራዉ ዉብነህ ሶስተኛ ኮር አስታዋቋል።

ለህፃናት ክትባት ለመስጠት ወደ ቀጠናው የገቡ የጤና ባለሙያዎችን በተገቢው መንገድ እንክብካቤ እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝ የራስ አሞራዉ ዉብነህ ሶስተኛ ኮር ጫና ክፍለጦር አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አርበኛ መለሰ ብርሀን ለግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተናግሯል።

የህክምና ባለሙያዎች የመንከባከብ ግዴታ አለብን ያለዉ አርበኛ መለሰ፣በዚህ መሸረትም ባለሙያዎቹ በነፃነት በመንቀሳቀስ ለህዝባችን የህክምና አገልግሎት እየሰጢ ይገኛሉ ብሏል።ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ህዝብ የጣለባቸዉን ሙያዊ ኃላፊነት በሚገባ እየተወጡ በመሆናቸዉ በአማራ ፋኖ ብሄራዊ በላይ ዘለቀ ዕዝ ላቅ ያለ ምስጋና ተችሯቸዋል።

ለህዝባችን የተሳካ የህክምና አገልግሎት እንድሰጥ አስቻይ ሁኔታ ለፈጠረልን ፋኖ ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ በቀጠናው የተሰማሩ የጤና ባለሙያዎች ገልፀዋል።ወደ ፊትም ለምናከናውነው ስራ የተሳካ እንዲሆን የፋኖ ድጋፍ እንዳይለየን ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት ለመንግሥት ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበን ያልተፈታልን ጥያቄ አሁን ላይ ጥያቄያቸን ለፋኖ በማቅረባችን አፋጣኝ ምላሽ ተሰቶናል ሲሉ የአካባቢው ማህበረሰብ ተናግረዋል ።አገልግሎቱ ቀጠይነት እንዲኖረዉ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተጠቁሟል።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
2🙏1