ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር ዜና

በአልዩ አምባ ከተማ በተደረገው ፍልሚያ የአድማ ብተና አዛዥን ጨምሮ አንድ አይሱዝ ሙሉ የአገዛዙ ኮማንዶ ተደመሰሰ።

‎በአንኮበር ወረዳ አልዩ አምባ ከተማ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር  ሰር የሚገኙት ጣይቱ ክፍለጦር እና ወንዱ አስቻለው ደሴ ክፍለጦር በተውጣጡ ሻለቆች በተደረገ ፍልሚያ በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: በአንኮበር እና አልዩ አምባ ከተማ መካከል የምትገኝ ልዩ ቦታው ጥድ አምባ የሚባል ቦታ ላይ ለዕገዛ የመጣ የአገዛዙ ኮማንዶ አንድ አይሱዝ ሙሉ ተደምስሷል።

‎በተጨማሪ በአልዩ አምባ ከተማ በተደረገው ፍልሚያ የአድማ ብተና አዛዥ የሆነው አማረ የተባለ ፀረ አማራ የአገዛዙ ቀኝ እጅ በጀግኖቹ እርሳስ ከባድ ጉዳት ደርሶበት በከፍተኛ  ህክምና ላይ ይገኛል።

‎እንዲሁም አንድ የአድማ ብተና የሻምበል አመራር  በአናብስቶቹ አፈሙዝ በደረሰበት ምት አንገቱ ላይ ተመቶ በሒወት እና በሞት መካከል እንዳለ ለማረጋገጥ ተችሏል።
በተጨማሪም  የአድማ ብተና ተመራጭ የሆኑ የቡድን መሳሪያ ተኳሾች አንድ የስናይፕር እና የብሬን ተኳሾች ከነመሳሪያቸው በወገን ጦር በቦንብ ጋይተዋል።

‎ጥድ አምባ የምትባል ቦታ ላይ  አንድ አይሱዝ ሙሉ ከተደመሰሰው ውጭ በተጨማሪ በአልዩ አምባ ከተማ በነበረው ፍልሚያ  ከጠላት በኩል በውስጥ በደረሰን መረጃ መሰረት 13 የአገዛዙ ጥምር ጦር እስከወዲያኛው የተሸኙ ሲሆን 18 የሚሆኑ ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል።

በአውደውጊያው ‎7 ነፍስ ወከፍ መሳሪያ : 554 የብሬንና የክላሽ ተተኳሽ : 2 የብሬን ሸንሸል እና 4 የክላሽ ካዝና ተማርኩአል::

‎በአጠቃላይ በነበረው በአውደ ውጊያው የመሀመድ ቢሆነኝ ኮር የኮሩ ቃኝዎችም ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል።

‎@ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
1🙏1
ምስራቅ አማራ ኮር 2 ታጠቅ ክፍለጦር ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ ላይ ድል ተጎናፀፉ::

ምስራቅ አማራ ኮር 2 ታጠቅ ክፍለጦር ወዳለችበት ቀጠና ህዳር 19/2018 ዓ.ም ከመርሳ ከተማ እና ኒኒ በር በመነሳት ማጥቃት ያደረገ ጠላት ጋር ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

የጠላት ሃይል ከመርሳ ከተማ እና ኒኒ በር በሁለት አቅጣጫ ለማጥቃት እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን ታጠቅ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃ ጠዶት ሚካኤል ላይ ደፈጣ ይዘው በመጠበቅ በርካታ ሃይል ላይ ያላሰበው ጥቃት በማድረስ ሙትና ቁስለኛውን ይዙ እንዲመለስና ወደ መጣበት ምሽጉ እንዲገባ አድርገው ድል ተጎናፅፈዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 19/2018 ዓ.ም
🙏1
በወልዲያ ወጣቱ እየታፈሰ ነው! የቆሎ ተማሪዎች ሳይቀሩ በቤተክርስቲያን እየታፈሱ ነው! ለማምለጥ ሲሞክሩ ይመታሉ። ዛሬ ጧት 2 የቆሎ ተማሪወች በምኒሻ ተመትተው መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል!

እንመለስበታለን###

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
💔1
በልማት ስራ ላይ በነበሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥካት ተከፍቶ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መገደላቸዉ ተሰምቷል።

ሀገር ጠሉ የአብይ አህሐድ ቡድን ሰራዊት በመንገድ ስራ ላይ በነበሩ ሰላማዊ ዜጎች ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን በጥቃቱም ስድስት ተገድለዉ በርካቶች ደግሞ አካላዊ ጉዳት አስተናግደዋል ተብሏል።

አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ኃይል ለልማት በወጣ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው የአማራ ጠሉ አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ በመንገድ ጠረጋ ልማት በተሰማራ ሕዝብ ላይ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት መካናይዝድና የቡድን መሳሪያ በመጠቀም በስድስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል::

በዚህም ፋሽስቱ የአብይ አህመድ አገዛዝ ሕዝብ ጠል ፣ ልማት ጠል ፣ ማንነት ጠልና ፍፁም ሰብዓዊነትም የሌለው መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
የይርጋ ሲሳይ ሌቦች በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

አገዛዙ ብልፅግና ያሰማራቸው የአድማ ብተና ሌቦች በዘረፋ ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

በደቡብ ጎንደር ቀጠና የተሰማሩ የአገዛዙ ተልዕኮ ፈፃሚ ሌቦች በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ፩ኛ ኮር ቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተነግሯል።

ሰው በማገት፣አስገድዶ በመድፈር፣አሽከርካሪዎች
ን በማገት እና በመግደል ወንጀል ላይ የተሰማሩ የብአዴን አጀንዳ ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተደረገባቸዉ ይገኛሉ።

በአገዛዙ ብልፅግና የተሰማሩ የአድማ ብተና እና የሚኒሻ አባላት የፋኖን ልብስ አልብሶ ወደ ቀጠናው እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ በማህበረሰቡ ላይ ዘረፋ እንዲፈፅሙ ግዳጅ ስለመሰጠታቸዉ መናገራቸዉን ኮሩ አስታዉቋል።

ትናንት ህዳር 19/2018 ዓ.ም በደራ ወረዳ የአገዛዙ ጥምር ጦር ሰራዊት እየተተራመሰ ባለበት ቀጠና አገዛዙ ያሰማራቸው #ሁለት_የአድማ_ብተና አባላት አስፓልት ላይ የህዝብ መኪና በማስቆም ስልክን ፣ገንዘብ፣የእጅ ቀለበት ሳይቀር እየቀሙ በነበረበት ሰአት የሚጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር የጣና ገላውዲዎስ ክፍለጦር በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

አናብስቶች በልዩ ኦፕሬሽን ወሮበላዎችን ያለምንም ተኩስ እስከ ዘረፉት ንብረት ስልክ እና ሙሉ ትጥቃቸው በመማረክ በቁጥጥር ስር አውለዋል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አስታዉቋል።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
💔1
የ206ኛ ኮር አደረጃጀት ዘርፍ መምሪያ የመልሶ ማደራጀት ተግባሩን በተቀላጠፈ ሁኔታ እየፈፀመ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ህዳር 20/2018 ዓ.ም

የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ መዋቅርን በማሻሻል ሰራዊቱን ለተሻለ ግዳጅ እያበቃ ሲሆን በመልሶ ማደራጀት ተግባሩ ትኩረት ሰጦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው 206ኛ ኮር በስሩ ያሉ ክ/ጦሮችን በማደራጀት ሰራዊቱን በጠንካራ ሻለቆች እያዋቀረ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን አጠቃሎ በአዲስ የተደራጀው ጊዜያዊ መንግስት በኮሩ ቀጠናዎች ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ቢሮ በመክፈት አገልግሎት መጀመሩን ያረጋገጠው የ206ኛ ኮር አደረጃጀት መምሪያ የተሰጠውን ድርጅታዊ ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግሯል።

ኮሩ የስራ ስምሪት ወስዶ ከተንቀሳቀሰ ጀምሮ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ያወሳው መምሪያው 24ኛ ክ/ጦርን በመልሶ ማደራጀት ተግባሩ ሙሉለሙሉ ያዋቀረ ሲሆን የክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስን ጨምሮ ቀጠናውን ሸፍነው የሚንቀሳቀሱ ጠንካራ ሻለቆችን በማደራጀት ክ/ጦሩ የሚሰጠውን ግዳጅ በብቃት ለመወጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ አክሎ ገልጿል።

ከመልሶ ማደራጀት ትግበራው ጎን ለጎን ከአካባቢው ማህበረሰብ ፣ከሀገር ሽማግሌዎች፣ሴቶችና ነጋዴዎች እንዲሁም ከመላው ሰራዊቱ ጋር አስቀድሞ ውይይት ያደረገው 206ኛ ኮር ግዳጆችን በብቃት ለመወጣት የማህበረሰቡ ተሳትፎ አይነተኛ ሚና እንደነበረው የ206ኛ ኮር አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ ፲አለቃ ደርሳችሁ አትንኩት ከ206ኛ ኮር የሚዲያ ክፍል ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
👍21