ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለህዝብ እርዳታ የመጣ ገንዘብ በወረዳ የብልጽግና አመራሮች መዘረፉ ታወቀ!
    
በደቡብ ጎንደር ዞን በመና መቀጣዋ ወረዳ ህዝብን ለመርዳት በሚል ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የመጣ የእርዳ ገንዘብ በበልጽግና አመራሮች እየመዘበረ የግል ኪሳቸውን እያደለቡበት መሆኑ ታውቋል።
     
ከመዘበሩ የአገዛዙ አመራሮች መካከል
1 - ምስጋናው ሆነ ➢ የመቀጣዋ አስተዳዳሪ የነበረ በሚስቱና በራሱ  ከ2 መቶ ሺ ብር በላይ ዘርፏል።

2 - አሰፋ ➢ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ 230 ሺ ብር ዘርፏል።

3 - በርየ ደምሴ ➢የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ 200 ሺ  ብር በሚስቱና በራሱ መዝብረዋል።

4 - አደራጀው ጌትነት ➢ የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ
              
ለልማት የመጣን የህዝብ አፈር መዳበሪያ በይፋ በመሸጥ  ድብረታቦር ላይ በ12 ሚሊዮን ብር የመኖሪያ አፓርትማ / ቅንጡ መኖሪያ ቤት / ገዝቷል።
   
ከዚህም ጋር ተያይዞ በምስራቅ በለሳ ወረዳም በሴፍትኔት ስም የሚመጣን የእርዳታ ገንዘብ ለብልጽግና ወታደራዊ መሪዎች እጅ መንሻ እየተጠቀሙበት እንደሆነም ታውቋል።
   
በዋነኛነት ይህን የእርዳታ ገንዘብ ከታለመለት ዓላማ ውጭ ተግባር ላይ እንዲውል እያደረጉት ያለው የወረዳ አስተዳዳሪዎች መሆናቸው ታውቋል።
     
ይህ የእርዳታ ገንዘብ የሚሰጥበት ዓላማም ወረዳችንን አንድም የፋኖ አባል በከተማችን ተኩስ እንዳይከፍት ነቅታችሁ ጠብቁልን የሚል የእጅ መንሻ እንደሆነም ተገልጿል።
     
እጅ መንሻው ከተሰጣቸው ወታደራዊ መኮንንኖች መካከል ማዘዣ ጣቢያዋን ደጎማ ላይ ያደረገችው 57ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮሎኔል ኃይሉ ግንባር ቀደም ሆኖ ይጠቀሳል።
           
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ  ኃላፊ
                                    አብነት ሞላ    
                             ህዳር 18 /2018 ዓ.ም
💔1
ጎንደር ብርጌድ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የመጣ የአብይ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ መመለሱ ተገለጸ!
       
ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም የግዙፉ ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አብራክ የሆነው ጎንደር ብርጌድ አባላት ከምንዝሮ እስከ አርሴማ ባለው ሰፊ ቀጠና የቅኝት ተግባርን በመከወን ላይ እያሉ  የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ከጠዳ ከተማ ተነስቶ ከቀኑ 7:00 ላይ በጎንደሬዎቹ ፋኖዎች ላይ ተኩስ የከፈተ ሲሆን ነበልባሎዎቹም አፋጣኝ የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ የጠላትን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።

          በውጊያውም
            05 እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል።
           07  ቁስለኛ መሆናቸው ታውቋል።
ጠላት ይዞት የመጣው ግብስብስ ኃይል ሙትና ቁስለኛ ስለሆነበት ተደናግጦ በመጣበት እግሩ ተመልሶ ብዙም ሳይቆይ ጠዳ ከተማ ገብቷል።

          ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
          አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ  ኃላፊ አብነት ሞላ    
               ህዳር 18 /2018 ዓ.ም
🙏2
ከፋኖ ደፈጣ ጥቃት ለማምለጥ በተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲሸሹ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከባድ የሆነ የተሽከርካሪ አደጋ መድረሱ ተሰማ!

በአደጋው፡ የዋድላ ወረዳ ሚኒሻ አስተባባሪ ኮማንደር ሰይድ ስጦታውና የመቶ አለቃ ማዕረግ ያለው አንድ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥን ጨምሮ 12 የአገዛዙ ወታደሮች ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።

ለዚህ ፀረ አማራ አገዛዝ ስርዓት ተላላኪ የሆኑ ባንዳዎችና ዙፋን ጠባቂ ወታደሮች በየእለቱ ከሚፈጃቸው የፋኖ አፈሙዝ በተጨማሪ የበደሉት ሕዝብ እምባ ጎርፍ ሆኖ ጠራርጎ እያጠፋቸው ነው።

የዋድላ ወረዳ ሚኒሻ አስተባባሪውን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች በበርካታ ሰራዊት ታጅበው እየተጓዙ ባለበት በቀጠናው የሚገኘው ፋኖ ደፈጣ ጥቃት ይፈፅምብናል በሚል ፍራቻ በፍጥነት ሲያሽከረክሩ ከባድ የተሽከርካሪ አደጋ እንደደረሰባቸው መረብ ሚዲያ ከአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስር የደጋው መብረቅ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በአደጋው የዋድላ ወረዳ ሚኒሻ አስተባባሪ ኮማንደር ሰይድ ስጦታውና የመቶ አለቃ ማዕረግ ያለው አንድ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥን ጨምሮ 12 የመከላከያ ሰራዊትና የሚኒሻ አባላት ሕይወታቸው ሲያልፍ፡ ስምንት ወታደሮች ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸው ታውቋል።

በፀረ አማራው አገዛዝ ኃይሎች ላይ አደጋው የደረሰው የዋድላ ወረዳ መቀመጫ ከሆነችው ከኮን ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ የዶጌት ሚካኤል በተባለ ቦታ ላይ መሆኑን መረብ ሚዲያ ከደጋው መብረቅ ኮር ለማረጋገጥ ችሏል።

የአደጋው መንስኤ፡ በቀጠናው የሚገኘው በቅርቡ በኮር ደረጃ የተዋቀረው በምኒክ ዕዝ ስር የደጋው መብረቅ ፋኖ የደፈጣ ጥቃት ይፈፅምብናል በሚል ፍራቻ በፍጥነት ሲያሽከረክሩ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፡ የአገዛዝ ኃይሎች በየእለቱ ከሚፈጃቸው የፋኖ አፈሙዝ በተጨማሪ የበደሉት ሕዝብ እምባ ጎርፍ ሆኖ ጠራርጎ እያጠፋቸው ነው ሲሉ ለመረብ ሚዲያ አስተያየታቸውን የሰጡ የአከባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
(ምስል፦ ከማህደር)
🙏2
ፋኖ ከትግሉ ጎን ለጎን የመሰረተ ልማት ስራወችን ድጋፍ እያደረገ ነው‼️

የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ
201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር የማህበረሰብ አነልግሎት ሰጭ ተግባራትን ጥበቃና ድጋፍ እያከናወነ ይገኛል።

ዛሬ ህዳር 17/2018 ዓ/ም በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ከአጉላች ገደብ ያለውን የጠጠር መንገድ ልዩ ጥበቃ በማድረግ የጥገና ስራ ያስጀመረ ሲሆን ብልፅግና አንዳንድ ሰርጎ ገቦችን በማደራጀት የመንገድ ስራው እንዲቋረጥ፣ ሹፌሮች አንዲገደሉ እና መኪኖች እንዲቃጠሉ ፀረ ልማት ቡድኖችን አዋቅሮ የመንገድ ስራውን ለማቋረጥ ሞክሯል።

   ይህ የፀረ-አማራና የፀረ ልማቱ ብልፅግና ስውር ክንፍ በመለየት የ74ኛ ክፍለጦር ፋኖወች እና የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ፀጥታ ዘርፍ አመራሮች አነፍንፈው አፍራሽ እና የብልፅግና ተላላኪዎችን አየለቀሙ በቁጥጥር ስር በማዋል የመንገድ ሠራተኞችን በማበረታታት እና ከጎናችሁ ነን በማለት ስራውን እንደደከናውን በትብብር እየሰራን እንገኛለን።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስአስተሳሰብ፣ አዲስተስፋ

የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዞብ ግንኙነት
ህዳር 18/2018 ዓ.ም
🙏1
ሰበር የድል ዜና!

ምኒልክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር 23ኛ ክ/ጦር በቀን 17/03/2018 ዓ/ም ጀምሮ በተጀመረውና ተጠናክሮ በቀጠለው ተጋድሎ በጊሸን እና አባላ ሰፍሮ የነበረዉ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ኛ ክ/ጦር የብልፅግናዉ አራጂ ቆራጭ ሰራዊት አዳሩን 23ኛ ክ/ጦር ወደ ምትንቀሳቀስበት ቀጠና ተጉዞ ወደ ደልባ ለመግባት ቢሞክርም ቀድመዉ በአናብስቶቹ እና በአይበገሬዎቹ በ23ኛ ክ/ጦር በወገን ኃይል ተብትቦ የተያዘ እና ስቦ በመስገባት ታክቲክ አይበገሬዎቹ የአሳምነዉ ግልገል የብልፅግናዉ ሠራዊት የአሞራ ሲሳይ ሁኖ አንዲቀር አድርጎታል።

ዉጊያዉ ከቀኑ 5:30ስዓት እስከ ምሽት 5:10 ስዓት የተካሄደ ሲሆን የመጣዉ የአብይ ሰራዊት ዘለህ ግባ በሚባል ሁኔታ ተስቦ እንድገባ ከተደረገ ቡኃላ መመለስ እንዳይችል አድርገዉ ከቀኝም ከግራም በአናብስቶቹ አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣ ዉሎል።

ነገር ግን በአለም የቱሪስት መስህብ ዉስጥ የምትታወቀው ጊሸን ደብረ ከርቤ ገዳም ዉስጥ ከትሞ የሚኖር አስነዋሪዉ የብልፅግና ሰራዊት ከገዳሙ ዉስጥ ሁኖ ሞርተር እያሰወነጨፈ ወደ ኋላ ለማዉጣት ቢሞክርም መዉጣት እንደመግባት ቀላል አይደለም እና የአብይ ሎሌዎች ብዙ የድሀ ልጆች ድንጋይ ተንተርሰዉ እስከ ወዳኛዉ እንደሸኙ አድርጓቸዋል።

በአዉደ ዉጊዉ የተገኙ ድሎች
1. ከ50 በላይ የተደመሰሰ እና ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ቁስለኛ
2. 650 የክላሽ ተተኳሽ
3. 450 የብሬን ተተኳሽ
4. 295 የድሽቃ ተተኳሾች ገቢ ሁኗል:: እንደሁም አንድ የጥላት ሀይል በአመራር ደረጃ አብሮ ተሰዉቶል።

ከ 4 መኪና በላይ ቁስለኛ ይዞ ወደ ደሴ ለመግባት ቢሞክርም በቀን 18/03/2018 የ 23ኛ ክ/ጦር ቃንኝ ቁስለኛ ይዞ እንዳይወጣ በድጋሚ ዚሃ ላይ ጥቁር አሰፍልቱን ዘግተዉ አነብስቶቹ እየገረፉት ነዉ።
እሬሳ እንኳን ማንሳት በማይችልበት ሁኔታ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ኮብልሎል።

የአለም የጦር ህግ በአስቀመጠዉ የሁለት ተፋላሚ ሀይሎች የማርኩትን የጥላት ሀይል በህግ አግባብ መያዝ የግድ ይላል እና እኛም የቆሰሉ የተሰዉ የተማረኩ የጥላት ሃይል የተሰዋዉን ማስቀበር የቆሰለዉ ህክምና እንዳገኝ የማድርግ ስራ እየሰራን እንገኘለን።

መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበር ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 18/2018 ዓ.ም
2🙏1
የፅናት ተምሳሌቱ አርበኛ አዲሴ አለምነዉ ጎንደር ካፈራቻቸዉ እንቁ መካከል ነዉ!!!

"በቅርብ አዉቀዋለሁ፣የቅርብ ጓደኛየም ጨምር ነዉ፣አዲሴ የቀጠናዉ የፋኖ ምሳሌ መሆን የሚችል ድንቅ አርበኛ ነዉ፣እዉነትን በዕሱ ልክ የተጋፈጠ የለም፣አንድ ቀን ከፀዳሉ ደሴ ጋር ቁጭ ብሎ ፀዳሉን ለስርቆት ነዉ የገባሀዉ ያለዉ ነገር አሁንም በዓምሮየ ዉስጥ አይጠፋም፣መላ የደራ፣የፎገራ፣የእስቴ፣የአንዳቤት ህዝብ የሚወደዉ ጀግና አርበኛ ነዉ።ሀሙሲት በመከላከያ ተወሮ ባለበት ወቅት ሳይፈራ የአገዛዙን ባለስልጣናት አንጠልጥሎ ያወጣበት መንገድ ሳስበዉ ይገርመኛል፣ለእኔ እሱን መሰል ጀግና አልተመለከትኩም፣ግን ይገፉታል፣ፀዳሉ ባቀናበረዉ ሴራ አዲሴ ጦሩን በትኑ እንዲሳደድ ተደርጓል አዝነናል ከፈቷናልም" ይላል የትግል አጋሩ።

አርበኛ አዲሴ ልጆቹ እና ሚስቱ ወደሚኖሩበት አዉሮፓ ለመሄድ በ2015 ዓ.ም ፕሮሰስ ጨርሶ የፋኖ ትግል ተጀመረ ሲባል ከቦሌ ኢንተርሻናል አዉሮፕላን ማረፊያ በረራ ሰርዞ የተመለሰ ጀግና ታጋይ ነዉ።ይህን ያደረገዉ ለአማራ ህዝብ ነዉ።በነገራችን ላይ ገፍተዉ ሲጥሉት የት ነዉ ያለ ብሎ የጠየቀ የለም፣ከጎኑም የተሰለፈ የለም፣እሱ ግን እዉነትን ተጋፍጦ ያሸነፈ፣በመከራ መሀል ያለፈ፣እንደ አለት የፀና እንደ ብረት የጠነከረ ስለመሆኑ ከጎጃም እስከ ጎንደር ያሉ የፋኖ አመራሮችም ሆነ አባላት ጥንቅቅ አድርገዉ ያዉቁታል፣ቤቱን ሽጦ ስናይፐር ገዝቶ ወደ ትግል የወጣ ቆራጥ አንበሳ ነዉ።

አሁን ያን ሁሉ ወጀብ አሸንፎ በዛዉ በፅናቱ ቀጥሏል።
በርታ አንበሳየ🙏🙏🙏🙏🙏
5🙏1
ዘመቻ ሙላት ንጉሴ በቀስተ ደመና ሻለቃ በድል ተጀምሯል!

ህዳር 19/2018 ዓ.ም

የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር አካል የሆነው የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ በዛሬው ዕለት በዘመቻ ሙላት ንጉሴ በደብረ ኤልያስ ከተማ ባደረገው ውጊያ በጡት ቆራጩ የመከላከያ ሠራዊት፣ በሚሊሻና አድማ ብተና ላይ ድልን ተቀዳጅቷል።

ውጊያው በደብረ ኤልያስ ከተማ ሆስፒታል፣ አዲሷ ቤተክርስቲያንና ትግል ፍሬ ጀርባ ላይ  የተደረገ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያለው አድማ ብተና፣ሚሊሻና መከላከያ ተደምስሷል።

የሌባ ስብስቡ የብልጽግና ቡድን ወራሪ ሠራዊቱን በማሰማራት የአርሶ አደሩን ሰብል እያወደመና እየዘረፈ ለሽፋኑም "ቀጠናዎችን አስሻለሁ፤ ፋኖንም በትኛለሁ" እያለ ዲስኩሩን በሚነፋበት ሰዓት ጀግኖቹ የቀስተ ደመና ክንደ ነበልባል ፋኖዎች ማዘዣው ላይ ገብተው በአናቱ ላይ ጨፍረውበት፤ ክምር ሬሳና ቁስለኛን አስታቅፈውት ወጥተዋል።

በጀግኖቹ ሜዳ የጀግኖቹን እሳታዊ ክንድ መቋቋም ያቃተውና በየዕለቱ ለበላይ አለቆቹ የውሸት ሪፖርት ማቅረብ የማይሰለቸው የሐሰት አባት የጥፋት አበጋዝ የሆነው የብልጽግና ሥርዓትና ወራሪ ሠራዊቱ ከሰሞኑ አዲስ ስምሪት በመውሰድ በገጠርማ አካባቢዎች ላይ አደረግሁት ባለው አሰሳ በስነ ልቡናው የሞተ የወራሪ ሠራዊቱን አስከሬን በየደረሰበት እያዝረከረከ በዋለበት ሳያድር በአደረበት ሳይውል ከመሄዱም በላይ ቀስተኞቹ በወሬ የሚፈታ ስነ ልቡናን የገነቡ ይመስል "ፋኖን በረሃ አስገብተነዋል" እያለ ወሬውን ሲጠርቅ ጀግኖቹ ደብረ ኤልያስ ከተማ ላይ በዛሬው ዕለት ተከስተው የጀግንነት ስርተው እየተገማሸሩ ተመልሰዋል።

በአመራሮቹ የውሸት ግንባታ የተሞላው ወራሪ ሠራዊትም ጀግኖቹን ከበረሃው ሲጠብቅ ማዘዣ ጣቢያው ላይ ገብተው በፈጠሩት መብረቃዊ ጥቃት ተደናብሮ እግሬ አውጭኙን ሲፈረጥጥ አርፍዷል።

የጓዳችንን የአርበኛ ሙላት ንጉሴን ደምም በእጥፉ እጥፍ መልሰናል።

በውጊያውም
~ 10 አድማ ብተናና ሚሊሻ ቆስሏል
~ በርካታ ቁጥር ያለው ባንዳ ሚሊሻ፣ አድማ ብተናና ጡት ቆራጭ መከላከያ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል
~ 05 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ተማርኳል

ዘመቻ ሙላት ንጉሴ ይቀጥላል...

ድል ለአማራ ፋኖ!
ዘላለማዊ ክብር ለትግላችን ሰማዕታት!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
👍3
በአምባሰል ወረዳ ከግሸን እስከ ደልባ ድረስ በተደረ ውጊያ አንድ አመራርን ጨምሮ ከ50 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ!

በቀጠናው በዙ23ና በሞርተር እንዲሁም በሌሎች ከባባድ መሣሪያዎች ታግዞ ጥቃት ከፍቶ የነበረው በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር የ45 ክ/ጦር ሰራዊት፡ ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ መቋቋም አቅቶት ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ውድመትን ተከናንቦ ወደ መጣበት መፈርጠጡ ተገልጿል።

ከህዳር 17/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ዛሬዋ እለት በጠላት ላይ የፀረ ማጥቃት እርምጃውን በመውሰድ ድል የተቀዳጁት በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የ23 ክ/ጦር አባላት መሆናቸውን ከኮሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ተችሏል።

በአውደ ውጊያው አንድ አመራርን ጨምሮ ከ50 በላይ የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ኃይል ደግሞ ቁስለኛ መደረጉን ኮሩ አስታውቋል።

በተጨማሪም 1ሺ 395 የድሽቃና የብሬን እንዲሁም የክላሽ ተተኳሽ በፋኖ መማረኩ ነው የተገለፀው።

የጠላት ኃይል በውጊያው የቆሰሉበትን ወታደሮች በአራት ተሽከርካሪ ጭኖ ወደ ደሴ ለመውሰድ ቢሞክርም ነገር ግን፡ በፋኖ ቃኝ አባላት ዚሀ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ተቆርጦ ከባድ ጉዳትን ያስተናገደ ሲሆን፡ በርካታ ቁስለኛ ወታደሮችም ተማርከዋል።

የፋኖ አባላቱ ለተማረኩ የጠላት ወታደሮች የሕክምና አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን፡ በውጊያው የተገደሉ የጠላት አስ*ከ*ሬንን ደግሞ ስርዓተ ቀብራቸውን እየፈፀሙ ማርፈዳቸውን በሚኒሊክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር በህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለጣቢያችን በላከው መረጃ አስታውቋል።

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏1
አሳዛኝ ዜና፡ 11 ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች በምሥራቅ አርሲ ተገደሉ

ቀን: ሕዳር 18/2018 ዓ.ም
በምሥራቅ አርሲ ዞን፣ እንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ በቀቅሳ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አሥራ አንድ (11) ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች መገደላቸውን የአደባባይ ሚዲያ ምንጮች አስታውቀዋል።

መቼ ተገደሉ? ሕዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ተረጋግጧል።
ከመገደላቸው በፊት: ክርስቲያኖቹ በነፍሰ ገዳዮቹ ታግተው እንደተወሰዱ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ይህ እጅግ አሳዛኝ ድርጊት ነው። ለተጎዱት ቤተሰቦች እና ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን መጽናናትን እንመኛለን።

ዝርዝር መረጃዎች እንደደረሱን ተጨማሪ ዘገባ እናቀርባለን።
💔1
የቢቡኝ ወረዳ ጊዜያዊመንግስት ህዝባዊ ውይይት እንደቀጠለ ነው።

የአፋብሃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር የቢቡኝ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት በቢቡኝ ወረዳ ዋበል ከተማ ቀበሌ የሚገኙ የኋላ ደጀን ህዝባችን ጋር ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ ህገ-ወጥ ግንባታንና የመሬት ወረራ፣ የቀበሌ ፀጥታና የቀበሌ መሰረተ ልማት ስራዎችን በተመለከተ የኋላ ደጀኑ ህዝባችን በቅርብ ቀን በተዋቀረው የጊዜያዊ መንግስት አደረጃጀቶች በመካተት የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ላይ ዛሬም እንደትላንቱ እንዲሳተፍ ተደረጓል ብሏል ክፍለ ጦሩ።

በቢቡኝ ወረዳ የዋበል ቀበሌ ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት በማካሄድ የተመረጡት አመራሮች ቃለ-መሐላ በመፈፀምና በውይይት በማድረግ የአማራ ህዝብ ወቅታዊ የትግል እንቅስቃሴ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ሰፊ የፖለቲካ ግንዛቤ ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የዋበል ቀበሌ ማህበርሰቡ የሚያምንባቸው ሰዎችን ሙርጦ አደረጃጀቶች ተዋቅሯል ብሏል ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት።
🙏1
#በምዕራብ_ሐረርጌ_የታፈነው_ጩኸት_እና_በአርሲ_የቀጠለው_ዘር_ፍጅት!

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ጭሮ ወረዳ፣ ላሎ ጉዶ ቀበሌ፣  ኢፈ ባስ(ifabaas) በምትባል የገጠር መንደር ውስጥ በኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 እልፌ ተስፋ ወሌ የሚባሉ እናት በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። በዚኹ ቀበሌና በአጎራባች ቀበሌዎች ያብዶ ሸንበቆ፣ ረብሱ፣ ሼክ አደም፣ ሉጎ በርካታ ሃይማኖትና ማንነትን ማዕከል ያደረጉ ጭፍጨፋዎች የሚካሄዱባቸው ናቸው። ብንናገርም ሰሚ የለም። ሕዝቡና ሚዲያውም እኛን ረስቶናል ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በምሬትና በፍርኃት ተውጠው።

በወረዳው በቅርቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት የኾኑ ተፈሪ መንገሻ ከነ ባለቤቱ ቀለሟ በለጠ ጋር፣ ባለው መንገሻ፣ አሳምነው አባይነህ የተባሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በአሰቃቂ ኹኔታ በስለትና በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል፤ በርካቶችም ቆስለዋል። ግድያውን የሚፈጽመው በአካባቢው ሰዎች አጠራር ኦነግ ሸኔ(ራሱን ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ኃይል) ነው።

ይኽን መረጃ እያጣራን ባለንበት አፍታ በአርሲ ዞን በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ በቀቅሳ ቀበሌ በአጨዳ ላይ የነበሩ ከ19 በላይ ገበሬዎች ኅዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ታፍነው መወሰዳቸውን ከቦታው ለማረጋገጥ ችለናል። በዚኹ አካባቢ በቅርቡ ወንድማማቾችን ጨምሮ ሦስት ንጹሓን እንደተገደሉ ይታወሳል።

እናት ፓርቲ በምዕራብ ሐረርጌ ባሉ በርካታ ቀብሌዎች በጥንቃቄ ተደብቆ የሚካሄድውን ጭፍጨፋና እገታ፤ እንዲኹም በአርሲ እየተካሄደ ያለውን ዘር ፍጅት በጽኑ እናወግዛለን፤ የታገቱትም ያለምንም ቅድመ ኹኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ኅዳር ፲፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
1💔1
ፋኖ ጠላትን ስቦ በመምታት የውጊያ ስልት ባደረገው ማጥቃት ድል መቀዳጀቱን አስታወቀ!

በምስራቅ አማራ ቀጠና በደላንታና በአምባሰል ወረዳ አዋሳኝ ልዩ ስሙ ተሬ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ጠላትን ስቦ በምታት የውጊያ ስልት ፋኖ ባደረገው ማጥቃት፡ በርካታ የብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ በቅርቡ በኮር ደረጃ ከተዋቀረበት እለት ጀምሮ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በጠላት ላይ ከባባድ ጥቃቶችን በመሠንዘር ታላላቅ ድሎችን እየተቀዳጀ የሚገኘው የደጋው መብረቅ ኮር፡ ትናንት ህዳር 18/2018 ዓ/ም ከረፋድ ጀምሮ እስከ አመሻሹ በተሬ ቀጠና ባደረገው ተጋድሎ በጠላት ላይ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ችሏል።

በትናቱ ውጊያ ፋኖ የጠላትን ኃይል ወደ ተሬ ቀጠና ስቦ ካስገባው በኋላ ነው መውጫ መግቢያውን በመዝጋት ማጥቃት የጀመረው የተባለ ሲሆን፡ በዚህም በርካታ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ ቀሪዎቹ ደግሞ የወደቁ ጓዶቻቸውን ሳያነሱ ወደ ተንታ ወረዳ መፈርጠጣቸውን መረብ ሚዲያ ከደጋው መብረቅ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።

በተሬ ቀጠና በርካታ የጠላት አ*ስ*ከ*ሬ*ን በየአርሶ አደሩ ማሣ ወድቆ እንደሚገኝም ነው የተገለፀው።
1🙏1