ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
📝የፋኖ ደጋፊ ተብለው ከቤተክርስቲያን ተባረሩ

👉የኔታ ተስፋ ማርያም ይባላሉ አራት አይና ሊቅ የጎንደር ፊት ሚካኤል ከሰላሳ ሁለት አመት በላይ ያገለገሉ ፣ በርካታ ሊቃውንትን ያፈሩ ታላቅ አባት ናቸው።

👉 የድጓም መህምር፣ የሐድስ ኪዳን ፣ ትርጓሜ መህምር ናቸው ባህታዊ ሥጋ ባፋቸው ገብቶ አያውቅም መጠጥ ምን እንደሆነ አያውቁም የሚኖሩት መቃብር ቤት ነው

👉የቤተ ክርስቲያኑ መምህር እና አስተዳዳሪ ናቸው ፣ መነኩሴ ሆነው አንድ ቀን እንኳን እንደ መነኩሴ ቀሚስ ለብሰው ቆብ አጥልቀው ለሰው አይታዩም፦

👉 በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ለሰው ልጅ በህይዎታቸው የሚያስተምሩ የሕይወት መምህር ጭምር ናቸው ፦

👉ታዲያ የማይከላዊ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዮሐንስ በውጭው ሲኖዶስ በአቡነ መርቆሬዎስ የተሾሙ ፣ሥራ አስኪያጃቸው አባ ዮሴፍ የብልጽግና የቁም ተጠሪ እና ካድሬ እንደሆኑ የመረጃ ምንጮቻችን ይናገራሉ ፣ ሊቀ ጳጳሱም ጉዳዩን በጥልቀት ሳይመረምሩ ፣ ከሥራ አስኪያጁ ጋር በመሆን ከቤተክርስቲያን እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ፦

👉 የፋኖ ደገፊ ፣ ቤተክርስቲያኑን የፋኖ አደረጉ ተብለው ከቤተ ክርስቲያን በሰባት (7) ፖሊስ ተባረው በአሁኑ ጊዜ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጊቢ እንዳይገቡ ተደርገው አቤቱታ እንዳያቀርቡ በስቃይ በችግር ውስጥ እንደሚገኙ የመረጃ ምንጮቻችን መረጃውን አድርሰውናል ፦

🙏 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ፣ ካህናት አገልጋዮች እና ምዕመናኑ በሙሉ ድምፅ ሊሆናቸው ይገባል ።
🔥2💔1
206ኛ ኮር ደጀን ላይ የተጠና ኦፕሬሽን ካደረገ በኋላ በከተማው የመሸገው የአረመኔው ሰራዊት ፍርስርሱ እየወጣ ነው።

ም/ኢንስፔክተሩን ጨምሮ በተደመሰሱበት ኦፕሬሽን የተደናገጠው ጠላት ፍርስርሱ እየወጣ ከ30 በላይ ሚኒሻዎች የከዱ ሲሆን ይህንን መቋቋም አልቻልክም በሚል ምክንያት አሰተዳደር ፀጥታ የነበረው ዳኘ ደነቀው ዘብጥያ ካወረዱት በኋላ ከኃላፊነቱ ተነስቷል።

  ይህን ተከትሎ ትርምሱን መቋቋም ያልቻለው የደጀን ካድሪ  ውጥረት ውስጥ ሲገኝ ፈርሰው ከከዱ የጠላት ኃይሎች መካከል
1) በላይ አየለ
2) ንፁህ ግዛቸው
3) አባትህ ሙንየ
4) ሀብቴ ታደለ
5) ከፌ ሙንየ
6) ፀሀይነህ ማናየ
7) ሀውልቱ አያሌው
8) ብርሌው ብሬ
9) ተሜ አበባው
10) እንደግ ጤናው
11) ደመቀ ሙሉ 
12) አሳቤ ተዋዶ
13) ብርሌው አሻግሬ 
14) ጌታቸው አብነህ
15) ቀስቅስ አስማረ
16) ጐዴ አድማሱ
17) ደጓላ ማናየ
18) አማረ መንገሻ
19) ተሾመ አዳነ
20) ደባስ አባተ
21) ጥላሁን ዘውዱ
22) ጌትሽ ደመቀ
23) ደመላሽ ደርሰህ
24) አላምኔ አወቀ
25) ብዙነህ ግዜ
26) ስላምሰው አሻግሬ 
27) አላምረው ማማሩ
28) ማሟሽ ደሳለኝ
29) ይደግ አደመ
30) ምስና አፍራሽ
31) ተመስገን ውዱ
32) በልስቲ ሀብታሙ ፣መሆናቸው  ተረጋግጧል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
1🙏1
ሰበር ዜና!

ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ መርጦ ከተማ በጨለማ ሰርጎ በመግባት የፋሽስቱ አራዊት ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችን በመደምሰስና በመማረክ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ ጉባላፍቶ ወረዳ መርጦ ከተማ መሽጎ ካለው የብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ህዳር 17/2018 ዓ.ም ሌሊት ሰርገው በመግባት አራት አጃቢዎቻቸውን በሳንጃ በመግደል እንዲሁም አንድ ሻምበል መሪ እና አንድ የክፍለጦር ሃኪም በመማረክ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ሻለቃዋ የሌሊት ጥቃቱን የፈፀመችው ያለምንም የጥይት ተኩስ ሲሆን የከፍተኛ አመራሮቹን አጃቢዎች ቀድመው በማስወገድ አመራሮቹን ከሶስት ጥቁር ክላሽና ሙሉ ትጥቁ ጋር በመማረክ የተሳካ ስራ ሰርተው ወጥተዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 18/2018 ዓ.ም
🙏2
ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለጦር አምባሰል ጊሼን ላይ ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ::

ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለጦር ከአምባሰል ጊሼን አካባቢ ወደ አምባሰል ጅብጎዶ ለማጥቃት የመጣ የፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግና በጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አምባሰል ጊሼን ቤተክርስቲያን ውስጥ በብዛት መሽጎ ያለ ሲሆን ከዛ በመነሳት በቅርብ ርቀት ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለጦር ወዳለችበት ጅብጎዶ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ንስሮቹ ባግባቡ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ ብሎም ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ወደ መጣበት ምሽጉ መልሰውታል::

በዚህ የተበሳጨው የጠላት ሰራዊት እንደተለመደው ህዝብ ወደሚበዛበት አካባቢ ወደ ከተማ ሞርተር በማስወንጨፍ ትምህርት ቤት እና ባካባቢው ባሉ መንደሮች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 18/2018 ዓ.ም

https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏2
ጧሪ የሌላት እናቴን ትቼ ጫካ የገባሁት የአማራ ህዝብ ጭቆና አንገብግቦኝ ነው!
በብዙ ግንባር ከፍተኛ ጀብድ የፈፀመችው እንስቷ ከልጇ ጋር ዛሬም አፋብኃ በላይ ዕዝ በጦር ግንባር ሰራዊት እየመራች ትገኛለች።

ጀግኒት አርበኛ ታድላ ስማቸው

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን
👌❤️🔥💪


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏2
በታሪክም ይሁን በአሁናዊ ኹነት የድርጅትን ዓላማ የሚደግፉ እየመሰሉ፣ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለጠላት የፕሮፓጋንዳ ማሽን የሚውል መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦች ይኖራሉ። በርግጥ አንዳንዶቹ የጠላትን ተልዕኮ በመሸከም double agent የሆኑም ይኖራሉ።

ያም ሆነ ይኽ፤ ለድርጅታችን ደጋፊዎች እና አባላት ስለሚዲያ አጠቃቅም ይችን መልዕክት እነሆኝ ማለት ወደድን!


እንደሚታወቀው ዛሬ የምንታገለው በጠመንጃ አፈሙዝ ብቻ አይደለም፤ ትልቁና ወሳኙ ትግል ያለው በማኅበራዊ ሚዲያ  ላይ'ም ነው። ጠላት ሁላችንንም እያየን ነው። ስልቱም ደግሞ ግልጽ ነው። እኛን በራሳችን ማዳከም።

የእኛን ማንነት ለብሰውና ደጋፊ መስለው ጥርጣሬንና መከፋፈልን  የሚፈጥሩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት፤ ጠላት የሚጠቀመ ስልት ነው። በስሜት ተገፋፍተን ወይም በቂ መረጃ ሳይኖረን የምንጽፋቸውን ድክመቶቻችንን፣ ሚስጥራዊ መረጃዎቻችንን እና የውስጥ ቅራኔዎቻችንን፣ ጠላት ለራሱ ፕሮፓጋንዳ በማዋል ይጠቀምባቸዋል።

ስለሆነም፤ እያንዳንዱ ጽሑፍና አስተያየት "የጦር መሣሪያ ነው" ማሰብ ያስፈልጋል። መሣሪያን ወደ ራስ ማዞር ደም ውጤቱ የታወቀ ነው።  ስለዚኽ እነሆ የልጅ ምክር፦

1. መረጃን ማረጋገጥ እና መገደብ

ምንጭዎን ይፈትሹ። አንድ መረጃን ከማጋራትዎ በፊት በይፋዊ የድርጅት ምንጮች የተረጋገጠ መሆኑን ያረጋግጡ። ያልተረጋገጡ ወሬዎችና ግምቶች የጠላት የስንኩል መሣሪያ  ናቸው።

የውስጥ መረጃን አያጋሩ። የድርጅቱ የሥራ አመራር፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች፣ የገንዘብ ሁኔታዎች ወይም የውስጥ ስብሰባዎች በተመለከተ ያልተፈቀደ ማንኛውንም መረጃ በግል መልዕክቶችም ቢሆን ማውራት "ከድርጅት ክህደት" አይተናነስም።

2. ስሜትን መቆጣጠርና በጥበብ ምላሽ መስጠት 

በስሜት አይገፉ! ጠላት ሁልጊዜ የሚያበሳጩና የሚያስቆጡ አስተያየቶችን ይጥልብናል። ዋናው ዓላማቸው አንዱ ደጋፊ ከሌላው ጋር እንዲጣላና ለጠላት የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የሚሆን የውስጥ ቅራኔ በአደባባይ እንዲወጣ ማድረግ ነው።

በየትኛውም መንገድ ዘውትር የትግሉን ዓላማ ብቻ ያንጸባርቁ። በትግላችን ውስጥ ዋናው ነገር የግል ውርርድ ወይም ክርክር አይደለም፤ የትግሉ ትልቅ ጉዳይ "የትግሉ ዓላማ" ነው። ጽሑፍዎ ሁሉ "ስለ መጪው ብሩህ ተስፋ እና ስለ ድርጅታችን መርሆችና ግብ" ብቻ ይሁን።

3. ጠላትን ማጋለጥ 

የጠላት ደጋፊዎችን በመለየትሐሰተኛ መረጃዎችን በስፋት የሚያሰራጩና ግልጽ የሆነ የጠላት አቋም ያላቸውን አካውንቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ሕግጋት መሠረት ሪፖርት ማድረግ (Report) እንጂ ከእነሱ ጋር ክርክር ውስጥ በመግባት  ጊዜና ጉልበትዎን ማባከን አያስፈልግም።

እንደአጠቃላይ፤ ማኅበራዊ ሚዲያ የጦር ሜዳ ነው። በግዴለሽነት የሚጻፍ አንድ ቃል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል። እያንዳንዱ ደጋፊ የድርጅቱ የመረጃና የደህንነት አካል ነኝ ብሎ ማመን አለበት። በአንድነት ቆመን፣ በንቃትና በጥንቃቄ ጠላትን በመረጃም ጭምር እናስወግደዋለን!

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ

አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
👍1
የብልፅግና ግፍ እና መከራ!!!

አሳዛኝ መረጃ
በጠገዴ ወረዳ ገጠራማ ስፍራ በ4 የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተደፈረችዉ የ55 ዓመት እድሜ ያላት እናት መረጃ እንዳታወጣ ህክምና መከልከሏን ተከትሎ በዛሬዉ ዕለት ራሷን ማጥፋቷ ተሰምቷል።


https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
በታሪክም ይሁን በአሁናዊ ኹነት የድርጅትን ዓላማ የሚደግፉ እየመሰሉ፣ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለጠላት የፕሮፓጋንዳ ማሽን የሚውል መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦች ይኖራሉ። በርግጥ አንዳንዶቹ የጠላትን ተልዕኮ በመሸከም double agent የሆኑም ይኖራሉ።

ያም ሆነ ይኽ፤ ለድርጅታችን ደጋፊዎች እና አባላት ስለሚዲያ አጠቃቅም ይችን መልዕክት እነሆኝ ማለት ወደድን!


እንደሚታወቀው ዛሬ የምንታገለው በጠመንጃ አፈሙዝ ብቻ አይደለም፤ ትልቁና ወሳኙ ትግል ያለው በማኅበራዊ ሚዲያ  ላይ'ም ነው። ጠላት ሁላችንንም እያየን ነው። ስልቱም ደግሞ ግልጽ ነው። እኛን በራሳችን ማዳከም።

የእኛን ማንነት ለብሰውና ደጋፊ መስለው ጥርጣሬንና መከፋፈልን  የሚፈጥሩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት፤ ጠላት የሚጠቀመ ስልት ነው። በስሜት ተገፋፍተን ወይም በቂ መረጃ ሳይኖረን የምንጽፋቸውን ድክመቶቻችንን፣ ሚስጥራዊ መረጃዎቻችንን እና የውስጥ ቅራኔዎቻችንን፣ ጠላት ለራሱ ፕሮፓጋንዳ በማዋል ይጠቀምባቸዋል።

ስለሆነም፤ እያንዳንዱ ጽሑፍና አስተያየት "የጦር መሣሪያ ነው" ማሰብ ያስፈልጋል። መሣሪያን ወደ ራስ ማዞር ደም ውጤቱ የታወቀ ነው።  ስለዚኽ እነሆ የልጅ ምክር፦

1. መረጃን ማረጋገጥ እና መገደብ

ምንጭዎን ይፈትሹ። አንድ መረጃን ከማጋራትዎ በፊት በይፋዊ የድርጅት ምንጮች የተረጋገጠ መሆኑን ያረጋግጡ። ያልተረጋገጡ ወሬዎችና ግምቶች የጠላት የስንኩል መሣሪያ  ናቸው።

የውስጥ መረጃን አያጋሩ። የድርጅቱ የሥራ አመራር፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች፣ የገንዘብ ሁኔታዎች ወይም የውስጥ ስብሰባዎች በተመለከተ ያልተፈቀደ ማንኛውንም መረጃ በግል መልዕክቶችም ቢሆን ማውራት "ከድርጅት ክህደት" አይተናነስም።

2. ስሜትን መቆጣጠርና በጥበብ ምላሽ መስጠት 

በስሜት አይገፉ! ጠላት ሁልጊዜ የሚያበሳጩና የሚያስቆጡ አስተያየቶችን ይጥልብናል። ዋናው ዓላማቸው አንዱ ደጋፊ ከሌላው ጋር እንዲጣላና ለጠላት የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የሚሆን የውስጥ ቅራኔ በአደባባይ እንዲወጣ ማድረግ ነው።

በየትኛውም መንገድ ዘውትር የትግሉን ዓላማ ብቻ ያንጸባርቁ። በትግላችን ውስጥ ዋናው ነገር የግል ውርርድ ወይም ክርክር አይደለም፤ የትግሉ ትልቅ ጉዳይ "የትግሉ ዓላማ" ነው። ጽሑፍዎ ሁሉ "ስለ መጪው ብሩህ ተስፋ እና ስለ ድርጅታችን መርሆችና ግብ" ብቻ ይሁን።

3. ጠላትን ማጋለጥ 

የጠላት ደጋፊዎችን በመለየትሐሰተኛ መረጃዎችን በስፋት የሚያሰራጩና ግልጽ የሆነ የጠላት አቋም ያላቸውን አካውንቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ሕግጋት መሠረት ሪፖርት ማድረግ (Report) እንጂ ከእነሱ ጋር ክርክር ውስጥ በመግባት  ጊዜና ጉልበትዎን ማባከን አያስፈልግም።

እንደአጠቃላይ፤ ማኅበራዊ ሚዲያ የጦር ሜዳ ነው። በግዴለሽነት የሚጻፍ አንድ ቃል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል። እያንዳንዱ ደጋፊ የድርጅቱ የመረጃና የደህንነት አካል ነኝ ብሎ ማመን አለበት። በአንድነት ቆመን፣ በንቃትና በጥንቃቄ ጠላትን በመረጃም ጭምር እናስወግደዋለን!

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ

አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
👍2
ቴዎድሮስ ዕዝ በመተከል የማምቡክ ከተማ ሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊ ላይ እርምጃ ሲወስድ፡ በተመሣሣይ ምኒልክ ዕዝ ደግሞ የአልብኮ ወረዳ ብልፅግና አመራሮች ላይ ከባድ እርምጃ መውሰዱን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ ፋኖዎች
በመተከል የማምቡክ ከተማ ሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ለሚሳን ጨምሮ በርካታ የአድማ ብተና አባላትን ሲገድሉ ሦስት ወታደሮችን ደግሞ መማረካቸው ታውቋል።

በምስራቅ አማራ ቀጠና ደግሞ የምኒልክ ዕዝ ፋኖዎች የአልብኮ ወረዳ መቀመጫ የሆነችው ሳልመኔ ከተማ ዘልቀው በመግባት የወረዳውና የከተማ አስተዳደሩ ብልፅግና አመራሮች ላይ በፈፀሙት ጥቃት በርካቶችን ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ችለዋል።

https://t.me/gfmn21
🙏2
ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለህዝብ እርዳታ የመጣ ገንዘብ በወረዳ የብልጽግና አመራሮች መዘረፉ ታወቀ!
    
በደቡብ ጎንደር ዞን በመና መቀጣዋ ወረዳ ህዝብን ለመርዳት በሚል ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የመጣ የእርዳ ገንዘብ በበልጽግና አመራሮች እየመዘበረ የግል ኪሳቸውን እያደለቡበት መሆኑ ታውቋል።
     
ከመዘበሩ የአገዛዙ አመራሮች መካከል
1 - ምስጋናው ሆነ ➢ የመቀጣዋ አስተዳዳሪ የነበረ በሚስቱና በራሱ  ከ2 መቶ ሺ ብር በላይ ዘርፏል።

2 - አሰፋ ➢ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ 230 ሺ ብር ዘርፏል።

3 - በርየ ደምሴ ➢የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ 200 ሺ  ብር በሚስቱና በራሱ መዝብረዋል።

4 - አደራጀው ጌትነት ➢ የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ
              
ለልማት የመጣን የህዝብ አፈር መዳበሪያ በይፋ በመሸጥ  ድብረታቦር ላይ በ12 ሚሊዮን ብር የመኖሪያ አፓርትማ / ቅንጡ መኖሪያ ቤት / ገዝቷል።
   
ከዚህም ጋር ተያይዞ በምስራቅ በለሳ ወረዳም በሴፍትኔት ስም የሚመጣን የእርዳታ ገንዘብ ለብልጽግና ወታደራዊ መሪዎች እጅ መንሻ እየተጠቀሙበት እንደሆነም ታውቋል።
   
በዋነኛነት ይህን የእርዳታ ገንዘብ ከታለመለት ዓላማ ውጭ ተግባር ላይ እንዲውል እያደረጉት ያለው የወረዳ አስተዳዳሪዎች መሆናቸው ታውቋል።
     
ይህ የእርዳታ ገንዘብ የሚሰጥበት ዓላማም ወረዳችንን አንድም የፋኖ አባል በከተማችን ተኩስ እንዳይከፍት ነቅታችሁ ጠብቁልን የሚል የእጅ መንሻ እንደሆነም ተገልጿል።
     
እጅ መንሻው ከተሰጣቸው ወታደራዊ መኮንንኖች መካከል ማዘዣ ጣቢያዋን ደጎማ ላይ ያደረገችው 57ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮሎኔል ኃይሉ ግንባር ቀደም ሆኖ ይጠቀሳል።
           
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ  ኃላፊ
                                    አብነት ሞላ    
                             ህዳር 18 /2018 ዓ.ም
💔1
ጎንደር ብርጌድ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የመጣ የአብይ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ መመለሱ ተገለጸ!
       
ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም የግዙፉ ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አብራክ የሆነው ጎንደር ብርጌድ አባላት ከምንዝሮ እስከ አርሴማ ባለው ሰፊ ቀጠና የቅኝት ተግባርን በመከወን ላይ እያሉ  የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ከጠዳ ከተማ ተነስቶ ከቀኑ 7:00 ላይ በጎንደሬዎቹ ፋኖዎች ላይ ተኩስ የከፈተ ሲሆን ነበልባሎዎቹም አፋጣኝ የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ የጠላትን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።

          በውጊያውም
            05 እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል።
           07  ቁስለኛ መሆናቸው ታውቋል።
ጠላት ይዞት የመጣው ግብስብስ ኃይል ሙትና ቁስለኛ ስለሆነበት ተደናግጦ በመጣበት እግሩ ተመልሶ ብዙም ሳይቆይ ጠዳ ከተማ ገብቷል።

          ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
          አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ  ኃላፊ አብነት ሞላ    
               ህዳር 18 /2018 ዓ.ም
🙏2
ከፋኖ ደፈጣ ጥቃት ለማምለጥ በተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲሸሹ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከባድ የሆነ የተሽከርካሪ አደጋ መድረሱ ተሰማ!

በአደጋው፡ የዋድላ ወረዳ ሚኒሻ አስተባባሪ ኮማንደር ሰይድ ስጦታውና የመቶ አለቃ ማዕረግ ያለው አንድ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥን ጨምሮ 12 የአገዛዙ ወታደሮች ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።

ለዚህ ፀረ አማራ አገዛዝ ስርዓት ተላላኪ የሆኑ ባንዳዎችና ዙፋን ጠባቂ ወታደሮች በየእለቱ ከሚፈጃቸው የፋኖ አፈሙዝ በተጨማሪ የበደሉት ሕዝብ እምባ ጎርፍ ሆኖ ጠራርጎ እያጠፋቸው ነው።

የዋድላ ወረዳ ሚኒሻ አስተባባሪውን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች በበርካታ ሰራዊት ታጅበው እየተጓዙ ባለበት በቀጠናው የሚገኘው ፋኖ ደፈጣ ጥቃት ይፈፅምብናል በሚል ፍራቻ በፍጥነት ሲያሽከረክሩ ከባድ የተሽከርካሪ አደጋ እንደደረሰባቸው መረብ ሚዲያ ከአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስር የደጋው መብረቅ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በአደጋው የዋድላ ወረዳ ሚኒሻ አስተባባሪ ኮማንደር ሰይድ ስጦታውና የመቶ አለቃ ማዕረግ ያለው አንድ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥን ጨምሮ 12 የመከላከያ ሰራዊትና የሚኒሻ አባላት ሕይወታቸው ሲያልፍ፡ ስምንት ወታደሮች ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸው ታውቋል።

በፀረ አማራው አገዛዝ ኃይሎች ላይ አደጋው የደረሰው የዋድላ ወረዳ መቀመጫ ከሆነችው ከኮን ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ የዶጌት ሚካኤል በተባለ ቦታ ላይ መሆኑን መረብ ሚዲያ ከደጋው መብረቅ ኮር ለማረጋገጥ ችሏል።

የአደጋው መንስኤ፡ በቀጠናው የሚገኘው በቅርቡ በኮር ደረጃ የተዋቀረው በምኒክ ዕዝ ስር የደጋው መብረቅ ፋኖ የደፈጣ ጥቃት ይፈፅምብናል በሚል ፍራቻ በፍጥነት ሲያሽከረክሩ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፡ የአገዛዝ ኃይሎች በየእለቱ ከሚፈጃቸው የፋኖ አፈሙዝ በተጨማሪ የበደሉት ሕዝብ እምባ ጎርፍ ሆኖ ጠራርጎ እያጠፋቸው ነው ሲሉ ለመረብ ሚዲያ አስተያየታቸውን የሰጡ የአከባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
(ምስል፦ ከማህደር)
🙏2
ፋኖ ከትግሉ ጎን ለጎን የመሰረተ ልማት ስራወችን ድጋፍ እያደረገ ነው‼️

የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ
201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር የማህበረሰብ አነልግሎት ሰጭ ተግባራትን ጥበቃና ድጋፍ እያከናወነ ይገኛል።

ዛሬ ህዳር 17/2018 ዓ/ም በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ከአጉላች ገደብ ያለውን የጠጠር መንገድ ልዩ ጥበቃ በማድረግ የጥገና ስራ ያስጀመረ ሲሆን ብልፅግና አንዳንድ ሰርጎ ገቦችን በማደራጀት የመንገድ ስራው እንዲቋረጥ፣ ሹፌሮች አንዲገደሉ እና መኪኖች እንዲቃጠሉ ፀረ ልማት ቡድኖችን አዋቅሮ የመንገድ ስራውን ለማቋረጥ ሞክሯል።

   ይህ የፀረ-አማራና የፀረ ልማቱ ብልፅግና ስውር ክንፍ በመለየት የ74ኛ ክፍለጦር ፋኖወች እና የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ፀጥታ ዘርፍ አመራሮች አነፍንፈው አፍራሽ እና የብልፅግና ተላላኪዎችን አየለቀሙ በቁጥጥር ስር በማዋል የመንገድ ሠራተኞችን በማበረታታት እና ከጎናችሁ ነን በማለት ስራውን እንደደከናውን በትብብር እየሰራን እንገኛለን።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስአስተሳሰብ፣ አዲስተስፋ

የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዞብ ግንኙነት
ህዳር 18/2018 ዓ.ም
🙏1