ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአገዛዙ ብልፅግና ጥምር ጦር በአርሶአደሩ ሀብትና ንብረት ላይ ዘረፋ ሲፈፅም በፋኖ እርምጃ ተወሰደበት!!!

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ሰላምሰዉ ሻለቃ ዘረፋ በተሰማረዉ የአገዛዙ ብልፅግና ጥምር ጦር ላይ እርምጃ መዉሰዷን ክፍለጦሩ አስታዉቋል።

በከሰም ሀገረማሪያም ኮርማሽ ቀጠና ሳልማን ቀበሌ የገበዉ የአገዛዙ ጡት ቆራጭ ወንበዴ ቡድን የአርሶአደሩን ሀብትና ንብረት በመዝረፋ ላይ እያለ የሀለማሪያም ማሞ አናብስቶች ፈጥነዉ በመድረስ ቅፅበታዉ እርምጃ ወስደዉበታል።

የአገዛዙ ጥምር ጦር ማር፣ቅቤ እና ሌሎችንም የአርሶአደሩን ሀብት እና ንብረት ዘርፎ ወደ መጣበት የተመለሰ ሲሆን የደረሰበት የጉዳት መጠን በዉል አልታወቀም።

በተያያዘ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ሰላም ሰዉ ሻለቃ ከአዉደዉጊያ ጎን ለጎን  የታድሶ ፕሮግራም ያደረገች ሲሆን ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በመገምገም እና በማስተካከል የቀጣይ የስራ አቅጣጫውችን በማስቀመጥ የታድሶ ፕሮግራሙን በተሳካ ሁኔታ አጠናቃለች።


በፕሮግራሙ ስነስርዓት  ላይ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር የሀይለማሪያም  ማሞ ክ/ጦር ም/ኦፕሬሽናል ኃላፊ ደፋሩ ተ/ሚካኤል፣የሀይለማሪያም ማሞ ክ/ጦ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ መምህር ሔኖክ ጌትየ እና የሃይለማርያም  ማሞ ክ/ጦር ዘመቻ መምሪያ ሀለፊ ዋሴ ማንጉዳይ ተገኝተዋል ሲል የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መረጀዉን አድርሶናል።

የግሎባል ፋኖ ሚዲያ የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!
https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏41
የብልፅግናዉ አገዛዝ በአማራ አክልል የተለያዩ አካባቢዎች የድሮን ቅኝት ሲያደርግ መዋሉ ተገለፀ።

ላለፉት ሁለት አመታት በአማራ ክልል ሁሉን አቀፍ ጦርነት የከፈተዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ በፋኖ ከፍተኛ ምትን ሲያስተናግድ መክረሙ ይታወቃል።የእግረኛ ሰራዊቱትን፣የኮማንዶ ሀይሉን፣መካናይዝዱን እና አየር ኃይሉን በመጠቀም በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት የከፈተው የብልፅግናዉ መንግስት የፋኖ ኃይሎችን ባሰበዉ እና ባቀደዉ ልክ ማሸነፍ አልቻለም።

ሁሉንም አቅሙን ተጠቅሞ ፋኖን ማሸነፍ ያቃተዉ አገዛዙ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ድጋፍ በተደረገለት ገንዘብ የአጥፍቶ ጠፊ ድሮን ወደ ሀገር ዉስጥ ማስገባቱ ተረጋግጧል።

እነዚህ ድሮኖችን ለመጠቀም ዛሬ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የድሮን ቅኝት ሲያደርግ ዉሏል።

በሶስት ቦታዎች የድሮን ጣቢያ የተከለዉ አገዛዙ ዛሬ ሁሉም የድሮን ጣቢያዎች ስራ ላይ መዋላቸዉን የውስጥ ምንጫችን ከደብረዘይት የድሮን ስታፍ ማዕከል መረጀዉን አድርሶናል።

መነሻቸዉን ከደብረዘይት ያደረጉ ሶስት ድሮኖች የሸዋ ቆላማ አካባቢዎችን እና የደቡብ ምዕራብ ወሎ አካባቢዎችን አሰሳ ሲያደርጉ መዋላቸዉን ምንጫችን ገልፆልናል።

ሌላኛው ከባህርዳር መነሻቸዉን ያደረጉ ሁለት ድሮኖች የምዕራብ ጎጃምን እና ባህርዳር ዙሪያን እንዲሁም የጎንደርን አብዛኛውን ክፍል ያካለለ የድሮን አሰሳ አድርገዋል ብሏል።

አፋር ሰመራ መነሻቸዉን ያደረጉ ሁለት ድሮኖች ደግሞ የትግራይን፣የአፋርን እና የአማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ቅኝት አድርገዋል።በራያ አካባቢ ተደጋጋሚ የድሮን ቅኝት የተደረገ ሲሆን በአፋር እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢም ተደጋጋሚ የድሮን ቅኝት መደረጉን ነዉ ምንጫችን ከዋናው መስሪያቤት ያደረሰን።

የፋኖ አመራሮችን ኢላማ ያደረገ የድሮን አሰሳ በአዲስ ሊጀመር እንደሆነ ጨምሮ የገለፀልን ምንጫችን ሁሉም የፋኖ አመራሮች አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸዉ ሀሳቡን አጋርቶናል።

የድሮን ጥቃቱ የሚፈፀመው በዘፈቀ በመሆኑ ማህበረሰቡም በተቻለ መጠን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲል የዉስጥ ምንጫችን መልዕክት አስተላልፏል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ
የፋኖ ድምፅ!!!

የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ
https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
👍4
የድል ዜና!

መተከል የማምቡክ ከተማ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ #ደረጀ ለሚሳ ላይ እርምጃ ተወስዷል!

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሻለቃ በሰሩት ኦፕሬሽን መተከል ክፍለ ሀገር፣ ፓዊ ወረዳ መንደር 34 ቀበሌ በሰሩት ኦፕሬሽን የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት አባላትን መግደል ሲቻል በርካቶችን ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።

እንዲሁም በዛሬዉ እለት በቀን 17/03/2018 ዓ.ም ከወርቅ ሜዳ ወደ ፓዊ ከተማ በባጃጅ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 3 የአድማ ብተና አባላት በቁጥጥር ስር ዉለዋል።
እነሱም:-
1.ገኔ ሽታሁን
2.ተሻለ አረጋ
3.ደርበዉ አስማረ

በሌላ ዜና የቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሻለቃ አባል የሆነ ጀግና ፋኖ መተከል ክፍለ ሀገር ዳንጉር ወረዳ ማቡክ ከተማ ሰርጎ በመግባት :- የማምቡክ ከተማ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ #ደረጀ ለሚሳን ጨምሮ 2 የአድማ ብተና አባላትን መግደል ሲችል 2 አድማ በተናን በማቁሰል በድል ተመልሷል።

በተመሳሳይ ዜና
የሚሊሻ ተቋሙን የማፍረስ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

ሰፊ የሆነ የውስጥ ለውስጥ ስራ በመስራት ወንድሞቻችን የመሰብሰብ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር እና 54ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።

1- እሱባለው ደረጀው
2- ዘሩ ባየ ..ሚሊሻ ከቢቸና የዕድኃከተማ
3- አሌክስ ይሁን 34 ዙር ምልምል ፓሊስ ከሰዴ ወረዳ
4- መሌ ባሰ ...ሚሊሻ ከጎንቻ ሲሶእነሴ

አሁንም አልመሸም ወደ ቀድሞ ማንነታቹህ ተመለሱ ትጥቃቹህን በመያዝ መታገል ትችላላቹህ መታገል ለማይፈልግ ደግሞ መብታቹህ የተከበረ መሆኑን ተቋሙ ሀላፊነት ይወስድላቹሀል።

@አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
             
👍42
የብልፅግና ሰራዊት ሁለት የቡድን መሳሪያ እና ሁለት ክላሽ በመያዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦርን ተቀላቀሉ::

የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት የ104ኛ ኮር 16ኛ ክፍለጦር አባላቶች አንድ ስናይፐር አንድ ብሬን እና ሁለት ክላሽ በመያዝ አገዛዙን በቃን በማለት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::

አገዛዙን በአውደ ውጊያ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ የማፍረሱ እና ከህዝባችን ጫንቃ ብሎም ከሃገራችን ለማስወገድና ለመደምሰስ የሚደረገው ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 17/2018 ዓ.ም
👍31👎1
ግዙፉ ላስታ አሳመነዉ ኮር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር በዛሬዉ ዕለት ከ35 በላይ የአገዛዙ ሰራዊትን በመደምሰስና ከ40 በላይ የሚሆኑ የአገዛዙ ሰራዊትን በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፏል :

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳመነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆኑት እሸት ክፍለ ጦር ፣ ወባንተ አባተ ክፍለ ጦር ፣ በመደራጀት ላይ ያለው አሃድ ራስ አንችም፣ እንዲሁም ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በጋራ መናበብ ባደረጉት አውደ ዉጊያ ከ35 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ40 በላይ ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል።

የአገዛዙ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ65ኛ ክፍለ ጦር እና የ61ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት መነሻውን ከላስታ ወረዳ ሽምሽሃ ቀበሌ (ላሊበላ አየር ማረፊያ) ከተማ በማድረግ የእሸት  ክፍለ ጦርን አፍናለሁ በሚል አጉል ምኞት ወደ  ገለሶት ቀበሌ በመጓዝ  ላይ እንዳለ ክፍለ ጦሩ ቀድሞ በደረሰው መረጃ መሠረት ከኮራችን ክንፎች ከሆኑ ሌሎች ክፍለ ጦሮች እና ብርጌዶች ጋር በመናበብ በጠላት ላይ ኪሳራ አድርሰዉበታል።

በዚህም ዉጊያ ላይ እሸት ክፍለ ጦር በልዩ ስሙ እገርፋ፣ ተካይ መንደር ፣ማዶ ራንባ ተብሎ እሚጠራዉን ቦታ ሸፍና የተዋጋች ሲሆን ዉባንተ አባተ ክፍለ ጦር ፣ራስ አንችም ክ/ጦር ፣ነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ በጥምረት በመሆን ከላሊበላ ከተማ ወደ ጋሸና እሚወስደዉን አስፓልት መንገድ በተለምዶ በርታ፣   ግራኝ አንባ፣ ቻይና ካንፕ ድረስ በመዘርጋት ጠላትን ሲያረግፉት ዉለዋል።

ህዳር 17/3/2018 ዓ/ም ከ ቀኑ 5:00  ሰዓት እስከ አመሻሽ 9:30 ከአራት ሰዓት በላይ በፈጀ ትንቅንቅ ከ35 በላይ የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ40 በላይ ቆስለኛ ማድረግም ተችሏል።

በዚህ አውደ ዉጊያ ጠላት የእሽት ክፍለ ጦርን ለማፈን አቅዶ የመጣ ቢሆንም ባላሰበውና ባልጠበቀው መንገድ ራሱ ታፍኖ በወገን ክንድ ሲቀጠቀጥ ውሎ ወደ መጣበት ሽምሽሃ ቀበሌ (ላሊበላ አየር ማረፊያ) ፈርጥጦ ተመልሷል።

በዚህም ወጊያ ጠላት ሽምሽሃ ቀበሌ ኪኒሸር ከሚባል ቦታ ላይ 120 ሞርተር አጥምዶ በሚወረዉረዉ ቅንቡላ እርፋ እና ተካይ መንደር አካባቢ በንፁሃን ዜጎች ላይ አካላዊ እና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል።

በትላንትናዉ ዕለትም የዚሁ ኮር አካል የሆነችዉ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በአገዛዙ ሰራዊት ላይ አካላዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን መዘገባችን ይታወቃል።

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ  ፋኖ ደረበ መኮንን!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ
ህዳር 17/3/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና

የፋሽስቱ መከላከያ መቶ አለቃ ጨምሮ የሚንሻ አስተባባሪው እርምጃ ተወሰደባቸው:: ባንዳዎች እና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ ላይ ከባድና የማያዳግም እርምጃ የመውሰዱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ባንዳ ጥቁሩ ፋሽስት ሎሌ እና በርካታ የሚኒሻና የመከላከያ ሰራዊቶች ተሸኝተዋል። የአማራ ሳር ቅጠሉ ምድር ሰማዩ ሁሉ ጥላትን እየተፋለመው ይገኛል።

ህዳር 17/2018 ዓ/ም በዋድላ ወረዳ የሚኒሻ አስተባባሪና ኮማንደር የሆነው ሰይድ ስጦታው እና አምስትየሚኒሻ አባል እድሁም የፋሽስቱ መከላከያ መቶ አለቃና ሰባት የመከላከያ ሰራዊቶች የሞቱ ሲሆን፤ 5 ሚኒሻ እና 3 መከላከያዎችም ቁስለኛ ሆነዋል። ኮን የዶጌት ሚካኤል በተባለ ቦታ ላይ በመኪና ተጭነው ሲጓጓዙ ተሽከርካሪው ተገልብጦ ወደማይቀረው ዓለም ተጉዘዋል።

ኮማንደር ሰይድ በዋድላ ወረዳ የሚታወቅበት ከስሙ በላይ ቀድሞ የሚጠራበት የአማራን ንፁሀን በመግደል፣ በመዝረፍና በመጨፍጨፍ እድሁም ሴቶችን አስገድዶ በመድፈር ነበር። ሰይድ የፋሽስቱ አብይ አህመድ ታማኝ ተላላኪ ሲሆን የአማራ ህዝብ ግንባር ቀደም ጥላት ሆኖ ሌባ ጎማ ተጭኖት እስኪሞት ድረስ አፀያፊ ተግባሩን ይፈፅም ነበር። ፋሽስቱ በሰጠው ስልጣን የግል ቂምበቀል የሚዎጣበት የፋሽስቱ ደጀንነትን ተጠቅሞ እደነበር ታሪኩ ይናገራል።

የሰይድ የባንዳነት የታሪክ ፍፃሜ የተደመደመው እስከ ከርሰ ምድር በዘለቀው የሎሌነት ተግባሩ ሆኗል። ከፊደልና ከትምህርት ታቅቦ የተፈጠረው ሰይድ ከመቃብሩ ላይ ከሚጫነው ሸክም በላይ ያልነጠፈ የባንዳነት ታሪኩ ሰባተኛ መሬትን ሰርስሮ የተነጠፈ ጥቁር የታሪክ ባለቤት ፈፃሚም ነበር።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 17/2018 ዓ.ም
3🙏1
ከስቦ ማስከዳት ወደ ቀንድሾ መውጣት !!

ዘመን ተሾመ ይባላል በዳንግላ ከተማ ራሱን ሰላም አስከባሪ እያለ የሚጠራው ቡድን አባል ነበር። ብልፅግና ከግዜ ወደ ግዜ ፀረ ህዝብነቱ እየጨመረ ስለመጣ የቡድኑን አመራር መልካሙ አለኸኝ የተባለ የሚኒሻ አመራር አስወግዶ መሳሪያውን በመያዝ በቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል።

የቴሌግራም ገፃችን ይኸዳጁ
https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
2👍1
እዉነተኛ ስራ በመተከል ዳንጉር ወረዳ ማንቡክ በጀግኖቹ የበላይ ዘለቀ ልጆች ተሰርቷል።

በመተከል ዳንጉር ወረዳ ማምቡክ ከተማ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደረጀ ለሚሳ የሰሞኑን የንፁሐን አማራ ጭፍጨ*ፋ እንዲፈፀም ትዕዛዝ ሲሰጥ የነበረው አው*ሬ ዛሬ በቆንጆዎቹ ተሸኝቷል


የቴሌግራም ገፃችን ይኸዳጁ
https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏2
💔#አሳዛኝ መረጃ 😭
እስኪ በአንድ በብልፅግና ለተሰራ ድራማ ያን ያህል ስታላዝኑ የነበርችሁ አስመሳዮች ዛሬ እስኪ እንያችሁ ብልፅግናን አውግዙ 😡😡😡

የአብይ አሕመድ ጨፍጫፊ ጡት ቆራጭ አራዊት ሰራዊት ትናንት ሲያካሂድ በነበረው የዘር ጭፍጨፋ በመራቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ገብሮ ቀበሌ ልዩ ቦታው ይማኔ በተባለ ቦታ የሶስት ንፁሃን ታዳጊዎችን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ጥላቸዋል።
ትናንት ከቀኑ10:30 ጀምሮ ባደርገው አማራን የማጥፋት የበቀል ድርጊት አንድ የአስራ ሶስት 13 አመት ልጅ እና ሁለት ከ15 አመት የማይበልጡ ወጣቶችን እረሽኗል
1,ዳምጠው አወቀ
2,ተምየ ወርቅነህ
3,ውድየ ዘለቀ
ከነዚህ በተጨማሪ ለግዜው ስማቸው በዝርዝር ያልደረሰን 6ንፁሃን ማሕበረሰብ ከባድ ጉዳት እንዳደረሰባቸው ከበታው መረጃውን አደርሰውናል። በተጨማሪ አምስት 5 የአርሶአደር በሮችን ገሏል የጭካኔ ጥጉን እና የፀረ አማራነቱን የበቀል ጥሙን ተዋቶባቸው ሂዷል ።

ይሔ ፀረ አማራ ጨፍጫፊ ጡት ቆራጭ ቡድን ለአማራ ለሰው ሳይሆ ለንብረቱም እረሕራሔ እንደለለው የለት ከለት ተግባሩ አረጋግጧል በመሆኑም ሕዝባችን ልጆቹንም ንበረቱንም እያጠፋበት የሚገኘውን ጨፍጫፊ ቡድን አምርሮ ሊታገለው ይገባል ይሕ ዘረኛ እና በቀልተኛ የኦነግ ሼኔ ምልስ አራጅ ቡድን አማራውን ጧሪ አልባ አዛውንት እና ወላጅ አልባ ሕፃናት በማድረግ የአማራን ዘር እያጠፋ ይገኛል ።

ለሞቱት ነብስ ይማር 😭

ለእናት ለአባቶቻቸው፣ ለእህት ወንድሞቻችው፣ ለዘመድ አዝማዱ መፅናናትን እንመኛለን ።

ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ሕዝብ

ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ አፄ ዘረ ያዕቆብ ፩ ኮር በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ ሕዝብ ግንኘነት
3