ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
=ሞዐ ችሎት=

በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሕዳር 16/2018 የቀረቡ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች የችሎት ውሎ መረጃ

አማራነትን እንደ ወንጀል በፈረጀው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በተለያዩ መዝገቦች በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች ፍ/ቤት ቀርበዋል።

አማራነትን እንደ ወንጀል በፈረጀው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በተለያዩ መዝገቦች በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች ሕዳር 16/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።

በችሎት ከተገኙት መካከልም:-

(1)~ በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ :-

በሕመም ምክንያት በተደጋጋሚ ችሎት እየተገኘ ካልሆነው ከአማረ መለሰ በስተቀር የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ፣ የተከበሩ ክርስቲያን ታደለ እና የተከበሩ ዶ/ር ካሳ ተሻገርን ጨምሮ 15 በቂሊንጦ ማ/ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ተገኝተዋል።

መዝገቡ የተቀጠረው ዐቃቤ ሕግ ከመጋረጃ በስተጀርባ አስመስክረዋለሁ ያለውን አንድ ምስክር አቅርቦ እንዲያስመስክር በሚል ነበር።

ይሁን እንጅ የፌደራል ፖሊስ ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ አማራ ክልል ሄዷል የተባለውን ምስክር በኔት ወርክ እና በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለማቅረብ አለመቻሉን በደብዳቤ መግለጹን አሳውቋል።

በመሆኑም አለ የተባለው የኔት ወርክ እና የክልሉ የፀጥታ ችግር በቂ ምክንያት በመሆኑ ምስክሩን ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ዕቃቤ ሕግ ችሎቱን ጠይቋል።

የ0ቃቤ ሕግ መከራከሪያ በተከሳሾች ጠበቆች በኩል ጠንከር ያለ ተቃውሞ ገጥሞታል ፤ በግራ ቀኙ መካከልም አጭር ክርክር ተደርጓል።

በጠበቆች በኩል የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 94 እና 124 'ን በመጥቀስ ዐቃቤ ሕግ ስነ ስርዓታዊ ባልሆነ መልኩ ተጨማሪ ጊዜ እየጠየቀ ነው ፤ የኔት ወርክ እና የፀጥታ ችግር የሚለው ቀጠሮ ለማስቀጠር በቂ ምክንያት አይደለም ፤ ልዩ ጥበቃ እየተደገለት ያለ ምስክር መሆኑ ተገልጾ ነበር ፤ በቂ ትጋት አላሳየም ፤ ተከሳሾች ከታሰሩ 2 ዓመት ከ5 ወር ሆኗቸዋል በመሆኑም የተሰጠው ጊዜ በቂ ስለነበር ዐቃቤ ሕግ ምስክሩን የማሰማት መብቱ ይታለፍልን በሚል ተጠይቋል።

የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩላቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አማራ ክልል እየተንቀሳቀሱ ሰላም ነው እያሉን ባለበት ሁኔታ አንድ ምስክር ለማምጣት የፀጥታ ችግር አለ የሚለው ተቀባይነት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱም የዕቃቤ ሕግን መከራከሪያ በመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ ለታህሳስ 8/2018
ሰጥቷል።

በተካሳሾች በኩል በቂሊንጦ ማ/ቤት ከፍ/ቤት ትዕዛዝ በኋላ መሻሻል ሊያሳይ ሲገባው ችግሮቹ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆኑ እየባሰባቸው መሆኑን ገልፀዋል ፤ በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ላይ እየተፈፀመ ያለው ማንነት ተኮር ስድብ ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ ብሶበታል ፤ የፍ/ቤት ትዕዛዝ እየተከበረ አይደለም ፤ ክልከላው ፣ ጭቆናው ፣ ወከባው  በዝቷል ፤ ፌደራል ፖሊስ እስካሁን ያጣራው ነገር የለም ፤ ደህንነታችን አደጋ ላይ ነው የሚሉና ሌሎች ችግሮችንም በመዘርዘር ያሉበት የአያያዝ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን በመጥቀስ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

(2)~ በእነ ሰለሞን ፍቃዱ ጣሴ መዝገብ:-

ተከሳሾች በቻሎት የተገኙ ሲሆን መዝገቡ የተቀጠረው ዐቃቤ ሕግ አለኝ ያለውን የተሰተካከለ የሲዲ ማስረጃ ይዞ እንዲቀርብ በሚል ነበር።

በእለቱም ዐቃቤ ሕግ የተስተካከለ ያለውን ሲዲ ይዞ መምጣቱን ቢገልጽም በጠበቆች በኩል ሲሞከር ግን የማይነበብ ፣ የማይደመጥ እና የማይሰራ በመሆኑ  0ቃቤ ሕግን በባለሙያ አስተካክለህ መስጠት ያንተ ኃላፊነት ነው በማለት በድጋሜ የተስተካከለውን ሲዲ ይዞ እንዲቀርብ በማለት ፍ/ቤቱ ለታህሳስ 1/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶታል።

(3)~ በእነ እሱባለው አስማማው መዝገብ:-

እሱባለው አስማማው እና ከበደ ንጉሴ የተባሉ አዲስ የሽብር ተከሳሾች በችሎት የተገኙ ሲሆን የክስ መቃወሚያቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ለሕዳር 30/2018 ተቀጥረዋል።

(4)~ ተስፋዬ ከበደ :-

ተከሳሹ አሉኝ ያላቸውን 11 የመከላከያ ምስክሮችን እንዲያሰማ በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ነው በችሎት የተገኘው።

ይሁን እንጅ በዳኛ ትዕዛዝ አሰጣጥ ላይ ነበረ በተባለው ክፍተት ተከሳሽ ተስፋዬ ከበደ ከሙያ ምስክሮች ጋር ሆኖ የዐቃቤ ሕግን የሰነድ ማስረጃ ባለማዳመጡ እና ከዝዋይ ያሉ ምስክሮቹ አለመምጣታቸውን በመጥቀስ ረዘም ያለ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ፍ/ቤቱም ዳግሞ የተስተከከለ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ በመግለፅ ለመጋቢት 17 እና 18 ቀጠሮ ይዞለታል።

ተስፋዬ ማ/ቤቱ ኃይሉን / ጉልበቱን እያሳየን ነው ፤ በማመልከቻዬ ላይ እንኳ ማህተም አልመታም በማለቱ ነው ያለማህተም ደብዳቤ ይዤ የወጣት ሲል ተናግሯል።

በተመሳሳይ ኤግዚቢት ሳይደረግ በፌደራል ፖሊስ እጅ የሚገኙ መፅሃፍት እና የተለያዩ ዶክመንቶች እንዲመለሱለትም ጠይቋል።

ፍ/ቤቱም ፌደራል ፖሊስ የተከሳሽ ንብረትን ማ/ቤት ድረስ ውስዶ እንዲሰጠው ትዕዛዝ ሰጥቷል።

(5)~ አበባው ነገሰ አለኽኝ :-

ተከሳሹ ጥቅምት 28/2018 በነበረው ችሎት ቀደም ሲል በምርመራ ቦታ እየተገኙ ሲደበድቡት የነበሩ 2 የፖሊስ አባላት እንዲመሰክሩበት ተደርጓል።

ይህን ተከትሎ የተከሳሽ ጠበቆች የሰነድ አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ በሚል ነበር ለሕዳር 16/2018 ቀጠሮ የተያዘው።

ነገር ግን በጠበቆች በኩል አጭር ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው በመጠየቁ ሀሳባቸው በችሎቱ ተቀባይነት በማግኘቱ ለሕዳር 25/2018 ተቀጥረዋል፡፡

(6)~ ንብረት ሕብስት :-

በእለቱ ተከሳሽ በጠበቃው በኩል የክስ መቃወሚያውን ይዞ ቀርቧል።

የክርክር ሂደቱን ለማስቀጠልም ለታህሳስ 1/2018 ቀጠሮ ተይዟል።

#ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ!
ህዳር 16/2018 ዓ.ም
ሞዐ ሚዲያ
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
🗣
3🔥1
ማቻከል!

አንድ የኮረኔል ማዕረግ ያለው ሬጅመንት አዛዥ ተደምስሷል!
(አስከሬን ወደቤቱ ሲላክ ማንነቱ የሚረጋገጥ ይሆናል)

‎ለሳምታት የቆየው እልህ አስጨራሽ ውጊያ ቅዳምን ከተማን ማስለቀቅ ተችሏል።

‎የማቻክል በላይ ዘለቀ ሻለቆችን ለማፈን አረመኔው አገዛዝ ሰራዊቱን በማሰባሰብ ጥቅምት 26/2018 ጀምሮ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት ለማድረግ ሞክሯል።

‎የአፋብኃ ቴዎድሮስ  ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛክፍለጦር የበላይ ዘለቀ ሻለቆች ባደረጉት የመልሶ ማጥቃት ውጊያ የኮረኔል ማዕረግ ያለው ሬጅመንት አዛዥ በመጨመር በርካታ የጠላት ሃይል ተደምስሷል።
‎ ቁስለኞቹን በሶስት ጭነት መኪና እና በአንድ አምቡላንስ ማውጣቱን አረጋግጠናል።

‎በዚህ አውደ ውጊያ የበላይ ዘለቀን ልጆች መቋቋም ያቃተው ጡት ቆራጭ ብልት ቆራጭ ምላስ ቆራጭ  ሰራዊት ቅዳምን ከተማን በመልቀቅ ወደ አማኑኤል  ከተማ ተመልሷል።

‎ከፍተኛ ምት ያስተናገደው የአረመኔው አገዛዝ የተደመሰሱ አባሎቹን #በጅምላ ቀብሯቸው ፈርጥጧል።


‎አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!

አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

         ህዳር 16/2018 ዓ.ም
👍2
ፀረ ዐምሓራ ኃይሎች ኤዲት የተደረጉ ምስሎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የሚሰሩትን የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ተመልከቱ!

እራሳቸው ባዘጋጁት ሰው አሰቃቂውን ድርጊት ፈፀሙ... ከዚያም ሰሞኑን አለም አቀፍ ትኩረት ያገኘውን የአማራ ሕዝብን እልቂት ለመሸፈን አጀንዳ አድርገው አቀረቡት።

የድራማው ዳይሬክተር ቀሽም ሆኖ ነጥብ አስጣላቸው።

ሰሞኑን አለም አቀፍ ትኩረት ያገኘውን የአማራን ሕዝብ እልቂት ለመሸፋፈን ሲሉ የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ እጁን ሰጠን በሚል ያሳወቁትን ገለሰብ አሰቃቂውን ድርጊት አስፈፀሙና አጀንዳ አደረጉት።

ከዚያም ግለሰቡ "የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ እጁን ሰጠን" ብላችሁን አልነበር ወይ?...የሚል ተጠይቅ ሲቀርብባቸው ደግሞ ድርጊቱን ድሮ ነው የፈፀመው በሚል ሌላ ውሸት ጀመረዋል። ድሮ መቼ?...ዘግናኙ ድጊት የተፈፀመበት ግለሰብ ሰሞኑን ነዋ? ድሮ መቼ?

የሚያሳዝነው ደግሞ አክራሪ ኦርቶዶክስ ጠል ኃይሎች ተደርበው፡ እራሳቸው ድጊቱን እንዲፈፅም ያስደረጉትን ግለሰብ ግንባሩ ላይ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም <መስቀል> ስለው ቤተክርስቲያኗንም ለመምታት ሌላ የሐሰት መረጃ ስርጭት ላይ ናቸው።

ሌላ ማስረጃም ለትወና ዝግጅት ሲያደርጉና ሲወያዩ የሚያሳየውም ምስል ወጥቶ የሚያደርጉትን አሳጥቷቸዋል::

በሰው ልጅ ፍጡር ላይ ይህንን ያክል ጭካኔ ከቶ እንደምን ሆነላቸው ካልን ምክንያቱም አውሬነትን የተላበሱ ወራሪዎች ናቸውና ነው መልሱ
2👍1
የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ የመረጃና ደህንነት ሰው ቆቦ ከተማ ላይ እርምጃ ተወሰደበት::

የቆቦ ከተማ መረጃ እና ደህንነት የሆነው የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ ሰው አቶ ጥጋቡ ደርቤ ከነ አጃቢዎቹ በሰማዕቶቹ ጀግኖች በነ አርበኛ አለሙ ገብሩ በነ አርበኛ ዋሴ ከበደ በነ አርበኛ ፍሬው አለና እና ሌሎች አርበኞች ልጆች በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች ወደማይቀረው ተሽኝቷል::

ከአማራ ህዝብ ተፈጥሮ ከፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ጋር በመተባበር የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ የኖረው ሆድ አደሩ አቶ ጥጋቡ ደርቤ ከነ አጃቢዎቹ ህዳር 16/2018 ዓ.ም ምሽት ቆቦ ከተማ ላይ በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች እርምጃ ተውስዶበታል:: በቀጣይም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 17/2018 ዓ.ም
ከሲቪል ሰርቫንት ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ!

‎በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛክ/ጦር በቢቡኝ ወረዳ ከሚገኙ መምህራኖች እና የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች ጋር ሰፊ ውይይት ማካሄዱን ከኮሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ተችሏል።

‎በውይይቱ፡ ለሕዝቡ አገልግሎት የሚሰጡ ማንኛቸውም የመንግስት ሰራተኞች ከየትኛውም የፓለቲካ እሳቤና አላማ እራሳቸውን ነፃ አድርገው እንዲሰሩ ሀሳብ ተነስቶ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል ኮሩ በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል ባወጣው መረጃ
👍2
በጎጃም የአገዛዙ ሰራዊት የጀምላ መቃብር!!!!!!

ጠላት እሬሳውን በጅምላ ቀበረ።

በርካታ ቁጥር ያለው ሀይል በመያዝ ወደ ግራ ቅዳምን የተንቀሳቀሰው በደረሰበት ተከታታይ ምት በርካታ ሃይሉን አጧል። በደረሰበት ምት ግራቅዳምንን ለቆ ሲወጣ በርካታ የጅምላ መቃብሮችን ማግኘቱን ማህበረሰቡ አሳውቋል።

ፋኖ የተኮሰው ጥይት መሬት ላይ እንደማይወድቅ አረጋግጠናል ሲሉ በማዕረግ የተገደሉትን ደግሞ ጭኖ መውሰዱንም የአካባቢው ማህበረሰብ ገልጿል።
👍3
የአገዛዙ ብልፅግና ጥምር ጦር በአርሶአደሩ ሀብትና ንብረት ላይ ዘረፋ ሲፈፅም በፋኖ እርምጃ ተወሰደበት!!!

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ሰላምሰዉ ሻለቃ ዘረፋ በተሰማረዉ የአገዛዙ ብልፅግና ጥምር ጦር ላይ እርምጃ መዉሰዷን ክፍለጦሩ አስታዉቋል።

በከሰም ሀገረማሪያም ኮርማሽ ቀጠና ሳልማን ቀበሌ የገበዉ የአገዛዙ ጡት ቆራጭ ወንበዴ ቡድን የአርሶአደሩን ሀብትና ንብረት በመዝረፋ ላይ እያለ የሀለማሪያም ማሞ አናብስቶች ፈጥነዉ በመድረስ ቅፅበታዉ እርምጃ ወስደዉበታል።

የአገዛዙ ጥምር ጦር ማር፣ቅቤ እና ሌሎችንም የአርሶአደሩን ሀብት እና ንብረት ዘርፎ ወደ መጣበት የተመለሰ ሲሆን የደረሰበት የጉዳት መጠን በዉል አልታወቀም።

በተያያዘ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ሰላም ሰዉ ሻለቃ ከአዉደዉጊያ ጎን ለጎን  የታድሶ ፕሮግራም ያደረገች ሲሆን ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በመገምገም እና በማስተካከል የቀጣይ የስራ አቅጣጫውችን በማስቀመጥ የታድሶ ፕሮግራሙን በተሳካ ሁኔታ አጠናቃለች።


በፕሮግራሙ ስነስርዓት  ላይ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር የሀይለማሪያም  ማሞ ክ/ጦር ም/ኦፕሬሽናል ኃላፊ ደፋሩ ተ/ሚካኤል፣የሀይለማሪያም ማሞ ክ/ጦ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ መምህር ሔኖክ ጌትየ እና የሃይለማርያም  ማሞ ክ/ጦር ዘመቻ መምሪያ ሀለፊ ዋሴ ማንጉዳይ ተገኝተዋል ሲል የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መረጀዉን አድርሶናል።

የግሎባል ፋኖ ሚዲያ የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!
https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
🙏41
የብልፅግናዉ አገዛዝ በአማራ አክልል የተለያዩ አካባቢዎች የድሮን ቅኝት ሲያደርግ መዋሉ ተገለፀ።

ላለፉት ሁለት አመታት በአማራ ክልል ሁሉን አቀፍ ጦርነት የከፈተዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ በፋኖ ከፍተኛ ምትን ሲያስተናግድ መክረሙ ይታወቃል።የእግረኛ ሰራዊቱትን፣የኮማንዶ ሀይሉን፣መካናይዝዱን እና አየር ኃይሉን በመጠቀም በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት የከፈተው የብልፅግናዉ መንግስት የፋኖ ኃይሎችን ባሰበዉ እና ባቀደዉ ልክ ማሸነፍ አልቻለም።

ሁሉንም አቅሙን ተጠቅሞ ፋኖን ማሸነፍ ያቃተዉ አገዛዙ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ድጋፍ በተደረገለት ገንዘብ የአጥፍቶ ጠፊ ድሮን ወደ ሀገር ዉስጥ ማስገባቱ ተረጋግጧል።

እነዚህ ድሮኖችን ለመጠቀም ዛሬ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የድሮን ቅኝት ሲያደርግ ዉሏል።

በሶስት ቦታዎች የድሮን ጣቢያ የተከለዉ አገዛዙ ዛሬ ሁሉም የድሮን ጣቢያዎች ስራ ላይ መዋላቸዉን የውስጥ ምንጫችን ከደብረዘይት የድሮን ስታፍ ማዕከል መረጀዉን አድርሶናል።

መነሻቸዉን ከደብረዘይት ያደረጉ ሶስት ድሮኖች የሸዋ ቆላማ አካባቢዎችን እና የደቡብ ምዕራብ ወሎ አካባቢዎችን አሰሳ ሲያደርጉ መዋላቸዉን ምንጫችን ገልፆልናል።

ሌላኛው ከባህርዳር መነሻቸዉን ያደረጉ ሁለት ድሮኖች የምዕራብ ጎጃምን እና ባህርዳር ዙሪያን እንዲሁም የጎንደርን አብዛኛውን ክፍል ያካለለ የድሮን አሰሳ አድርገዋል ብሏል።

አፋር ሰመራ መነሻቸዉን ያደረጉ ሁለት ድሮኖች ደግሞ የትግራይን፣የአፋርን እና የአማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ቅኝት አድርገዋል።በራያ አካባቢ ተደጋጋሚ የድሮን ቅኝት የተደረገ ሲሆን በአፋር እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢም ተደጋጋሚ የድሮን ቅኝት መደረጉን ነዉ ምንጫችን ከዋናው መስሪያቤት ያደረሰን።

የፋኖ አመራሮችን ኢላማ ያደረገ የድሮን አሰሳ በአዲስ ሊጀመር እንደሆነ ጨምሮ የገለፀልን ምንጫችን ሁሉም የፋኖ አመራሮች አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸዉ ሀሳቡን አጋርቶናል።

የድሮን ጥቃቱ የሚፈፀመው በዘፈቀ በመሆኑ ማህበረሰቡም በተቻለ መጠን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲል የዉስጥ ምንጫችን መልዕክት አስተላልፏል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ
የፋኖ ድምፅ!!!

የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ
https://t.me/+APfg2ZKNKrhhMTlk
👍4