ምስል:- መሃል ላይ ያለው አስተኩአሽ : የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ፋኖ ታዘበው ሻንበል
🙏2
~ በደብረ ኤልያስ ከተማ የበርካታ ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲፈርስ ሀገር አፍራሹ የብልጽግና ስብስብ ወስኗል።
በስሁት የፖለቲካ ትርክት ሰክሮ አማራን ከነሁለንተናው ለማጥፋት ደፋ ቀና ለሚለው የኦሕዴድ መር ሥርዓት የሚያጎበድደው የአማራ ካድሬ ለምስር ወጥና ለርካሽ ስልጣን ሲል የገዛ ሕቡን ለጨፍጫፊዎቹ በማመቻቸትና የእኩያንን ዓላማ ተፈጻሚ በማድረግ በአማራ ሕዝብ ታሪክ የማይረሳው ግፍና መከራን እያደረሰ ይገኛል።
ከነዚህም መካከል "በመልካም አንገት ላይ እንቅርት እንዲሉ" ሁለንተናዊ ልዕልናና ኃያልነትን አስተባብራ በኖረችና ባለችዋ በደብረ ኤልያስ ከተማ የተወሸቀው ጸረ ሕዝቡ የብልጽግና ስብስብ ይገኝበታል።
ከተማውን ከወረረበት ዕለት ጀምሮ በንጹሐን ላይ የመከራ ቀንበር ሲያወርድ የከረመው ገዳይ ስብስብ ዛሬ ደግሞ ሌላ ጆሮን ጭው የሚያደርግ የጥፋት ዜናን ለደብረ ኤልያስ ከተማ ነዋሪዎች አሰምቷል።
ይህም በፋል(FAL) የመንገድ ተቋራጭ በሚሰራው ሀገር አቋራጭ መንገድ ምክንያት ቤታቸው ከሙዛ ጀምሮ እሰከ አበሸብ በግምት በ3KM ርዝመት ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ያለምንም የካሳ ክፍያ ቤታቸውን እንዲነሱ ነው ዛቻ አዘል ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው።
በወቅቱ (ከ3 ዓመት በፊት) ለባለ ቤቶቹ የካሳ ክፍያ ጸድቆላቸው በሚፈጸምበት ወቅት በፈነዳው የፋኖ አብዮት ሥራው በመቋረጡ ምክንያት የካሳ ክፍያ የቀረ ሲሆን ዛሬ ግን እንዳዲስ ውሳኔዎች ተገልብጠው ያለምንም ካሳ አፍርሰው እንዲነሱ ተነግሯቸዋል።
ቅሬታ ያቀረቡ የከተማው ነዋሪዎችም "አርፋችሁ ተቀመጡ ምንም አይነት ቅሬታም ሆነ ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፤ እንኳን ቤታችሁ ይቅርና እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤ የማታርፉ ከሆነ እናንተንም እናፈርሳችኋለን..." በማለት ነዋሪዎችን አንገታቸውን አስደፍተው መልሰዋቸዋል።
የብልጽግናው ሌባ ስብስብ ይህንን የክህደት ተግባር የፈጸመውም የተለመደ የዘረፋ ተግባሩን ለመፈጸም ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው! የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ ወረዳውን ሙሉ በመሉ ከተቆጣጠረበት ከሐምሌ 27/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ1 ዓመት ከ6 ወር ያክል ራሳቸውን የወረዳው አመራር አድርገው በመሰየም ደብረ ማርቆስ ከተማ የተወሸቁ ሆዳም ባንዳዎች ያለምንም መምሪያ በአየር ላይ እየተወራረደ ከ9000,000 (ዘጠኝ ሚሊዮን) ብር በላይ ተበልቶ በመገኘቱ ሁሉም የብልጽግና ካድሬዎች ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተው ሰንብተዋል።
ይህንንም የተበላ ገንዘብ ለማካካስ የካሳ ክፍያውን ወደ ራሳቸው በማዞር ካሳ ጸድቆላቸው ነገር ግን የመንገድ ተቋራጩ ስራ በማቆሙ ምክንያት ክፍያ ያልተፈጸመላቸው የቤት ባለይዞታዎች ያለምንም የካሳ ክፍያ ቤታቸውን አፍርሰው እንዲነሱ ዛቻ የተሞላበት መምሪያ አውርደዋል።
ይህ ስብስብ አስቀድሞም የደብረ ኤልያስንና ማቻክል ወረዳዎችን ለማገናኘት ጌደብ ወንዝ ሊሰራ ከታቀደው የድልድይ ማሰሪያ ገንዘብ በመቀበል ይህንን የተዘረፈ ገንዘብ ለመሙላት አስቦ እንደነበርም መረጃዎች ደርሰውናል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
ክብር ለሕዝባችን!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

⚖⚖⚖⚖=ሞዐ ችሎት=⚖⚖⚖⚖⚖
በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሕዳር 16/2018 የቀረቡ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች የችሎት ውሎ መረጃ
አማራነትን እንደ ወንጀል በፈረጀው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በተለያዩ መዝገቦች በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች ፍ/ቤት ቀርበዋል።
አማራነትን እንደ ወንጀል በፈረጀው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በተለያዩ መዝገቦች በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች ሕዳር 16/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።
በችሎት ከተገኙት መካከልም:-
(1)~ በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ :-
በሕመም ምክንያት በተደጋጋሚ ችሎት እየተገኘ ካልሆነው ከአማረ መለሰ በስተቀር የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ፣ የተከበሩ ክርስቲያን ታደለ እና የተከበሩ ዶ/ር ካሳ ተሻገርን ጨምሮ 15 በቂሊንጦ ማ/ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ተገኝተዋል።
መዝገቡ የተቀጠረው ዐቃቤ ሕግ ከመጋረጃ በስተጀርባ አስመስክረዋለሁ ያለውን አንድ ምስክር አቅርቦ እንዲያስመስክር በሚል ነበር።
ይሁን እንጅ የፌደራል ፖሊስ ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ አማራ ክልል ሄዷል የተባለውን ምስክር በኔት ወርክ እና በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለማቅረብ አለመቻሉን በደብዳቤ መግለጹን አሳውቋል።
በመሆኑም አለ የተባለው የኔት ወርክ እና የክልሉ የፀጥታ ችግር በቂ ምክንያት በመሆኑ ምስክሩን ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ዕቃቤ ሕግ ችሎቱን ጠይቋል።
የ0ቃቤ ሕግ መከራከሪያ በተከሳሾች ጠበቆች በኩል ጠንከር ያለ ተቃውሞ ገጥሞታል ፤ በግራ ቀኙ መካከልም አጭር ክርክር ተደርጓል።
በጠበቆች በኩል የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 94 እና 124 'ን በመጥቀስ ዐቃቤ ሕግ ስነ ስርዓታዊ ባልሆነ መልኩ ተጨማሪ ጊዜ እየጠየቀ ነው ፤ የኔት ወርክ እና የፀጥታ ችግር የሚለው ቀጠሮ ለማስቀጠር በቂ ምክንያት አይደለም ፤ ልዩ ጥበቃ እየተደገለት ያለ ምስክር መሆኑ ተገልጾ ነበር ፤ በቂ ትጋት አላሳየም ፤ ተከሳሾች ከታሰሩ 2 ዓመት ከ5 ወር ሆኗቸዋል በመሆኑም የተሰጠው ጊዜ በቂ ስለነበር ዐቃቤ ሕግ ምስክሩን የማሰማት መብቱ ይታለፍልን በሚል ተጠይቋል።
የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩላቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አማራ ክልል እየተንቀሳቀሱ ሰላም ነው እያሉን ባለበት ሁኔታ አንድ ምስክር ለማምጣት የፀጥታ ችግር አለ የሚለው ተቀባይነት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱም የዕቃቤ ሕግን መከራከሪያ በመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ ለታህሳስ 8/2018
ሰጥቷል።
በተካሳሾች በኩል በቂሊንጦ ማ/ቤት ከፍ/ቤት ትዕዛዝ በኋላ መሻሻል ሊያሳይ ሲገባው ችግሮቹ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆኑ እየባሰባቸው መሆኑን ገልፀዋል ፤ በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ላይ እየተፈፀመ ያለው ማንነት ተኮር ስድብ ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ ብሶበታል ፤ የፍ/ቤት ትዕዛዝ እየተከበረ አይደለም ፤ ክልከላው ፣ ጭቆናው ፣ ወከባው በዝቷል ፤ ፌደራል ፖሊስ እስካሁን ያጣራው ነገር የለም ፤ ደህንነታችን አደጋ ላይ ነው የሚሉና ሌሎች ችግሮችንም በመዘርዘር ያሉበት የአያያዝ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን በመጥቀስ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
(2)~ በእነ ሰለሞን ፍቃዱ ጣሴ መዝገብ:-
ተከሳሾች በቻሎት የተገኙ ሲሆን መዝገቡ የተቀጠረው ዐቃቤ ሕግ አለኝ ያለውን የተሰተካከለ የሲዲ ማስረጃ ይዞ እንዲቀርብ በሚል ነበር።
በእለቱም ዐቃቤ ሕግ የተስተካከለ ያለውን ሲዲ ይዞ መምጣቱን ቢገልጽም በጠበቆች በኩል ሲሞከር ግን የማይነበብ ፣ የማይደመጥ እና የማይሰራ በመሆኑ 0ቃቤ ሕግን በባለሙያ አስተካክለህ መስጠት ያንተ ኃላፊነት ነው በማለት በድጋሜ የተስተካከለውን ሲዲ ይዞ እንዲቀርብ በማለት ፍ/ቤቱ ለታህሳስ 1/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶታል።
(3)~ በእነ እሱባለው አስማማው መዝገብ:-
እሱባለው አስማማው እና ከበደ ንጉሴ የተባሉ አዲስ የሽብር ተከሳሾች በችሎት የተገኙ ሲሆን የክስ መቃወሚያቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ለሕዳር 30/2018 ተቀጥረዋል።
(4)~ ተስፋዬ ከበደ :-
ተከሳሹ አሉኝ ያላቸውን 11 የመከላከያ ምስክሮችን እንዲያሰማ በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ነው በችሎት የተገኘው።
ይሁን እንጅ በዳኛ ትዕዛዝ አሰጣጥ ላይ ነበረ በተባለው ክፍተት ተከሳሽ ተስፋዬ ከበደ ከሙያ ምስክሮች ጋር ሆኖ የዐቃቤ ሕግን የሰነድ ማስረጃ ባለማዳመጡ እና ከዝዋይ ያሉ ምስክሮቹ አለመምጣታቸውን በመጥቀስ ረዘም ያለ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።
ፍ/ቤቱም ዳግሞ የተስተከከለ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ በመግለፅ ለመጋቢት 17 እና 18 ቀጠሮ ይዞለታል።
ተስፋዬ ማ/ቤቱ ኃይሉን / ጉልበቱን እያሳየን ነው ፤ በማመልከቻዬ ላይ እንኳ ማህተም አልመታም በማለቱ ነው ያለማህተም ደብዳቤ ይዤ የወጣት ሲል ተናግሯል።
በተመሳሳይ ኤግዚቢት ሳይደረግ በፌደራል ፖሊስ እጅ የሚገኙ መፅሃፍት እና የተለያዩ ዶክመንቶች እንዲመለሱለትም ጠይቋል።
ፍ/ቤቱም ፌደራል ፖሊስ የተከሳሽ ንብረትን ማ/ቤት ድረስ ውስዶ እንዲሰጠው ትዕዛዝ ሰጥቷል።
(5)~ አበባው ነገሰ አለኽኝ :-
ተከሳሹ ጥቅምት 28/2018 በነበረው ችሎት ቀደም ሲል በምርመራ ቦታ እየተገኙ ሲደበድቡት የነበሩ 2 የፖሊስ አባላት እንዲመሰክሩበት ተደርጓል።
ይህን ተከትሎ የተከሳሽ ጠበቆች የሰነድ አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ በሚል ነበር ለሕዳር 16/2018 ቀጠሮ የተያዘው።
ነገር ግን በጠበቆች በኩል አጭር ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው በመጠየቁ ሀሳባቸው በችሎቱ ተቀባይነት በማግኘቱ ለሕዳር 25/2018 ተቀጥረዋል፡፡
(6)~ ንብረት ሕብስት :-
በእለቱ ተከሳሽ በጠበቃው በኩል የክስ መቃወሚያውን ይዞ ቀርቧል።
የክርክር ሂደቱን ለማስቀጠልም ለታህሳስ 1/2018 ቀጠሮ ተይዟል።
#ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ!
ህዳር 16/2018 ዓ.ም
ሞዐ ሚዲያ
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
⚖🗣

❤3🔥1
ማቻከል!
አንድ የኮረኔል ማዕረግ ያለው ሬጅመንት አዛዥ ተደምስሷል!
(አስከሬን ወደቤቱ ሲላክ ማንነቱ የሚረጋገጥ ይሆናል)
ለሳምታት የቆየው እልህ አስጨራሽ ውጊያ ቅዳምን ከተማን ማስለቀቅ ተችሏል።
የማቻክል በላይ ዘለቀ ሻለቆችን ለማፈን አረመኔው አገዛዝ ሰራዊቱን በማሰባሰብ ጥቅምት 26/2018 ጀምሮ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት ለማድረግ ሞክሯል።
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛክፍለጦር የበላይ ዘለቀ ሻለቆች ባደረጉት የመልሶ ማጥቃት ውጊያ የኮረኔል ማዕረግ ያለው ሬጅመንት አዛዥ በመጨመር በርካታ የጠላት ሃይል ተደምስሷል።
ቁስለኞቹን በሶስት ጭነት መኪና እና በአንድ አምቡላንስ ማውጣቱን አረጋግጠናል።
በዚህ አውደ ውጊያ የበላይ ዘለቀን ልጆች መቋቋም ያቃተው ጡት ቆራጭ ብልት ቆራጭ ምላስ ቆራጭ ሰራዊት ቅዳምን ከተማን በመልቀቅ ወደ አማኑኤል ከተማ ተመልሷል።
ከፍተኛ ምት ያስተናገደው የአረመኔው አገዛዝ የተደመሰሱ አባሎቹን #በጅምላ ቀብሯቸው ፈርጥጧል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

👍2
ፀረ ዐምሓራ ኃይሎች ኤዲት የተደረጉ ምስሎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የሚሰሩትን የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ተመልከቱ!
እራሳቸው ባዘጋጁት ሰው አሰቃቂውን ድርጊት ፈፀሙ... ከዚያም ሰሞኑን አለም አቀፍ ትኩረት ያገኘውን የአማራ ሕዝብን እልቂት ለመሸፈን አጀንዳ አድርገው አቀረቡት።
የድራማው ዳይሬክተር ቀሽም ሆኖ ነጥብ አስጣላቸው።
ሰሞኑን አለም አቀፍ ትኩረት ያገኘውን የአማራን ሕዝብ እልቂት ለመሸፋፈን ሲሉ የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ እጁን ሰጠን በሚል ያሳወቁትን ገለሰብ አሰቃቂውን ድርጊት አስፈፀሙና አጀንዳ አደረጉት።
ከዚያም ግለሰቡ "የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ እጁን ሰጠን" ብላችሁን አልነበር ወይ?...የሚል ተጠይቅ ሲቀርብባቸው ደግሞ ድርጊቱን ድሮ ነው የፈፀመው በሚል ሌላ ውሸት ጀመረዋል። ድሮ መቼ?...ዘግናኙ ድጊት የተፈፀመበት ግለሰብ ሰሞኑን ነዋ? ድሮ መቼ?
የሚያሳዝነው ደግሞ አክራሪ ኦርቶዶክስ ጠል ኃይሎች ተደርበው፡ እራሳቸው ድጊቱን እንዲፈፅም ያስደረጉትን ግለሰብ ግንባሩ ላይ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም <መስቀል> ስለው ቤተክርስቲያኗንም ለመምታት ሌላ የሐሰት መረጃ ስርጭት ላይ ናቸው።
ሌላ ማስረጃም ለትወና ዝግጅት ሲያደርጉና ሲወያዩ የሚያሳየውም ምስል ወጥቶ የሚያደርጉትን አሳጥቷቸዋል::
በሰው ልጅ ፍጡር ላይ ይህንን ያክል ጭካኔ ከቶ እንደምን ሆነላቸው ካልን ምክንያቱም አውሬነትን የተላበሱ ወራሪዎች ናቸውና ነው መልሱ

❤2👍1
የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ የመረጃና ደህንነት ሰው ቆቦ ከተማ ላይ እርምጃ ተወሰደበት::
የቆቦ ከተማ መረጃ እና ደህንነት የሆነው የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ ሰው አቶ ጥጋቡ ደርቤ ከነ አጃቢዎቹ በሰማዕቶቹ ጀግኖች በነ አርበኛ አለሙ ገብሩ በነ አርበኛ ዋሴ ከበደ በነ አርበኛ ፍሬው አለና እና ሌሎች አርበኞች ልጆች በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች ወደማይቀረው ተሽኝቷል::
ከአማራ ህዝብ ተፈጥሮ ከፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ጋር በመተባበር የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ የኖረው ሆድ አደሩ አቶ ጥጋቡ ደርቤ ከነ አጃቢዎቹ ህዳር 16/2018 ዓ.ም ምሽት ቆቦ ከተማ ላይ በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች እርምጃ ተውስዶበታል:: በቀጣይም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 17/2018 ዓ.ም

ከሲቪል ሰርቫንት ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ!
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛክ/ጦር በቢቡኝ ወረዳ ከሚገኙ መምህራኖች እና የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች ጋር ሰፊ ውይይት ማካሄዱን ከኮሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ተችሏል።
በውይይቱ፡ ለሕዝቡ አገልግሎት የሚሰጡ ማንኛቸውም የመንግስት ሰራተኞች ከየትኛውም የፓለቲካ እሳቤና አላማ እራሳቸውን ነፃ አድርገው እንዲሰሩ ሀሳብ ተነስቶ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል ኮሩ በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል ባወጣው መረጃ