ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.33K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አሩሲ አቦምሳ ሐይፋ ዳገት!

"ወዲያው ከዋናው መንገድ ራቅ ብለው ወደ ጫካ ይዘዋቸው እንደገቡ ተከታታይ የሩምታ ተኩስ ሰምተናል። ምናልባት የተወሰኑትን ሳይጨፈጭፏቸው አይቀርም።

አውቶብሱ በታጣቂዎች መንገድ ተዘግቶበት ቆመ። ወዲያው ታጣቂዎች ወደ አውቶብሱ ገብተው በኦሮሞኛ ሁሉም ተሳፋሪ እንዲወርድ አዘዙ ። ጭምብል አለባበሳቸው መሣሪያ አያያዛቸው አልባሳት አለባበሳቸው ከቴሌቪዥን የምናያቸውን የአልሸባብ ታጣቂዎች ይመስላሉ።

ወዲያው አማራ ኦርቶዶክስ የሆናችሁ በዚህ በቀኝ በኩል ተሰለፉ አሉ። ኦሮሞ የሆናችሁ በግራ ተሰለፉ አሉ።

ወዲያው ቆጠራ አድርገው ኦሮሞዎች ወደ አውቶብስ ገብታችሁ ጉዞ ቀጥሉ አሉ። እኛ ጉዞ እንደጀመርን 31 አማራ ኦርቶዶክሶችን ከሐይፋ ዳገት ወደ ጫካ ይዘዋቸው ገቡ።

.. ወዲያው ከዋናው መንገድ ራቅ ብለው ወደ ጫካ ይዘዋቸው እንደገቡ ተከታታይ የሩምታ ተኩስ ሰምተናል። ምናልባት የተወሰኑትን ሳይጨፈጭፏቸው አይቀርም።

እኔ ኦሮሞ ነኝ ብዬ በግራ በኩል ተሰልፌ ወደ አቦምሳ ገባሁ።

እስከአሁን ልቤ ሐይፋ ዳገት ታግተው ከተወሰዱት ዘመዶቼ ጋር ነው። እነማን ተጨፍጭፈዋል! እነማን ተረፈዋል! ሰቀቀን ላይ ነኝ።

ሰው ላይ የተተኮሰ ጥይትና አየር ላይ የተተኮሰ ጥይት ድምፁ ይለያያል። በእርግጠኝነት የሩምታ ተኩሱ አየር ላይ አይደለም።

በሰው ገላ ላይ ነው ያረፈው። ምነው ዕዛው በቀኝ ተሰልፌ አማራ ኦርቶዶክስ ነኝ ብዬ መከራውን ብቀበል እላለሁ።"

ኅዳር 6/2018 ዓ.ም ከናዝሬት ወደ አቦምሳ ሲጓዙ ሐይፋ የተባለ ቦታ 31 አማራ ኦርቶዶክሶች ታግተው ተወስደዋል። ከዚያ እገታ የተረፈ ሰው ቀጥታ የላከው መልዕክት ነው።

ዕገታው ሲፈፀም ዓለሙ ስሜ ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ኢብራሂም ከድር አቦምሳ ከተማ ሕዝብ ሰብስበው ሠላም ነው በሉ የጠላት ወሬ ነው በሉ የብልጽግና ጉዞ አይቆምም እያሉ ምናባዊ ብልጽግና ይሰብኩ ነበር!

ኅዳር 7/2018  ዓ.ም
@በለጠ ካሣ
2💔1
የአርበኛ ዋሴ ከበደ የህይወት እና የትግል ታሪክ!

"ጀግና ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!"

አርበኛ ዋሴ ከበደ የትውልድ ቦታው የራያ ቆቦ አርበት ልዩ ስሙ ቀጋይ አቦ የተባለ ቦታ ነው:: የ1ኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው ተወልዶ ባደገበት አገሩ የተማረ ሲሆን የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱንም ቆቦ ሃይስኩል ጨርሶ በኋላም በመምህርነት ተመርቋል::

አርበኛ ዋሴ ከበደ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት በመምህርነት ሞያ ሃገሩንና ወገኑን ያገለገለ የነበረ  ሲሆን 2013 ዓ.ም በጀመረው የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በነበረው ጥሪ ወደ ማሰልጠኛ ገብቶ ተመርቆ የአማራ ልዩ ሃይልን ተቀላቅሎ ታግሏል::

አርበኛ ዋሴ ከበደ በሰሜኑ ጦርነት የአማራ ልዩ ሃይል የቴዎድሮስ ክፍለጦር አር ፒ ጅ እና ብሬን ተኳሽ ሆኖ የታገለ ሲሆን በወቅቱ በነበረው ከፍተኛ ሴራና አሻጥር በመማረር ነፃ ሆኖ ህዝቡን ለማገልገልና ለመታገል ሲል ከልዩ ሃይሉ በመውጣት በትውልድ አካባቢው ወጣቶችን በማደራጀትና በማስታጠቅ ወደ ሽምቅ ውጊያ በመግባት በርካታ ጀብዶችን ፈፅሟል::

ከጥር 2013 ዓ.ም ድል በኋላም በይፋ ምስራቅ አማራ ፋኖን ተቀላቅሎ የቀድሞው የዞብል አምባ ብርጌድ አባል ሆኖ ሲታገልና ሲያታግል ቆይቷል:: በታሪካዊው የበላጎ ድልም የቀድሞው የዞብል አምባ ብርጌድ አባል ሆኖ ታሪክ ሰርቶ አልፏል::

አርበኛ ዋሴ ከበደ ከሰሜኑ ጦርነት በደቡብ አፍሪካው የፕሪቶሪያ ስምምነትና ድራማ መጠናቀቅ በኋላ ምስራቅ አማራ ፋኖ የአማራን ህዝብ ህልውና በትጥቅ ትግል ለማረጋገጥ ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም በረሃ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ሰራዊቱን እንደ አዲስ በማሰባሰብ በማደራጀትና በማስታጠቅ ጉልህ ሚና ተጫውቷል::

አርበኛ ዋሴ ከበደ ሰራዊት ከማሰባሰብ ከማደራጀትና ከማስታጠቅ ባሻገር ዞብል አምባ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃ ሻምበል መሪ ዘመቻ እና የሻለቃዋ አመራር ሆኖ በበርካታ ግንባሮች በርካታ ጀብዶችን በመፈፀም ብሎም ቆቦ ከተማ ድረስ ዘልቆ እየገባ ባንዳ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድና በማፅዳትም የሚስተካከለው አልነበረም::

በመቀጠልም አርበኛ ዋሴ ከበደ የዞብል አምባ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃን እየመራ በራያ በየጁ በአምባሰልና በተለያዩ የቤተ-አማራ ግንባሮች በርካታ ድሎችን የተጎናፀፈ ሲሆን መስከረም 26/2016 ዓ.ም ቆቦ ከተማ ሆርማት እና መጋቢት 3/2016 ዓ.ም አምባሰል አካባቢ ሁለት ጊዜ የቆሰለና በፅናት የታገለ ጀግና ነበር::

አርበኛ ዋሴ ከበደ በዞብል አምባ ክፍለጦር ሻለቃ እየመራ ባስመዘገበው ድልና ከፍተኛ አፈፃፃም ምክንያት ወደ ዞብል አምባ ክፍለጦር አመራርነት በኋላም ባለው ከፍተኛ ውጊያን የማንበብና የማዋጋት አቅም የክፍለጦር ዘመቻ ሆኖ የመራ ሲሆን በቅርብ ጊዜም የምስራቅ አማራ ኮር 2 ምክትል ዘመቻ መሪ ሆኖ እስከመመረጥ የደረሰ ጀግና አርበኛ ነበር::

በመጨረሻም አርበኛ ዋሴ ከበደ ምኒልክ ዕዝ ባወጀውና ከመስከረም 14-30/2018 ዓ.ም በቆየው በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የምስራቅ አማራ ኮር ሁለት ምክትል ዘመቻ አመራር ሆኖ በርካታ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናፅፎ ከዘመቻው መገባደድ ማግስት የጠላትን ከባድ የማጥቃት ዘመቻ በመመከት ተኩለሽ ግንባር ከቆቦ ከተማ ቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠበለት የተባለ ቦታ ላይ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም በክብር መስዋዕትነትን ተቀብሏል::    

በመጨረሻም እኛ የትግል ጓዶቹ አርበኛው ጓዳችን መስዋዕትነት የከፈለበትን አላማ ከግብ እናደርሳለን የህዝባችንን ህልውና እናረጋግጣለን!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የትግል ጓዶቹ ከትግሉ ሜዳ!
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 7/2018 ዓ.ም
💔2
የአፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት የ206ኛ ከፊያለው ደሴ ኮር አምበሳው ጋይንት ክፍለጦር አስቻለው ደሴ ብርጌድ ምልምል የፋኖ ሰላጠኞችን ለወራቶች አሰልጥኖ በዛሬውለት አስመርቋል!!
መሰልጠን መደራጀት መታጠቅ መደራጀት የፋኖ ትግል መርህ ነውና በርቱ
ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
🙏5🔥1
ከምንጃር ሸንኮራ ወደ በረኸት ወረዳ ሬሽን ሲያንቀሳቅሱ በነበሩ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ላይ ከባድ የደፈጣ ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል!

በጥቃቱ ሁለት ተሽከርካሪ ሙሉ ሰራዊት ከነ ተሽከርካሪው መውደሙ ታውቋል!

በደቡብ አማራ ቀጠና ከምንጃር ሸንኮራ ወደ በረኸት ወረዳ ሬሽን ሲያንቀሳቅሱ በነበሩ፡ አገዛዙ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ሲል የሚያሞካሻቸው ህፃን ደፋሪ የ104ኛ ክ/ጦር የኮማንዶ አባላት ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት ሁለት ተሽከርካሪ ሙሉ ሰራዊት ከነ ተሽከርካሪው መውደሙን መረብ ሚዲያ ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ስር ከሚገኘው ከነበልባል ክፍለጦ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ህዳር 06/2018 ዓ/ም ሲሆን፡ በጠላት ላይ መራር ክንዳቸውን በማሳረፍ ድሉን የተቀዳጁት ደግሞ በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክ/ጦር ስር የሚገኙት የጄነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ አባላት መሆናቸው ታውቋል።

ወታደራዊ ሬሽኑን ሲያንቀሳቅሱ ከነበሩ ተሽከርካሪዎች መካከል ሁለቱ ተሽከርካሪዎች በላያቸው ላይ ተሳፍረውባቸው እስከነበሩ ኮማንዶዎች ዶግ አመድ መደረጋቸውን ከክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ተችሏል።

የፀረ አማራውና ፀረ ሰላሙ ዐብይ አህመድ ተላላኪ ወታደሩ ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋቋም ሲያቅተው፡ በያዘው ከባድ መሣሪያ የእውር ድንብሩን በመተኮስ በአከባቢው የሚገኙ የአርሶአደሮችን መኖሪያ ቤትና አዝመራን ሲደበድብ መዋሉ ታውቋል።
🙏3
ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተሳተፈበት የህዝብ መድረክ በታሪካዊቷ ማጀቴ ከተማ ተካሔደ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር በታሪካዊቷ ማጀቴ ከታማ ከሊቅ እክከ ደቂቅ የዕዙ አመራሮችና የዓፄ ዘራዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የህዝብ መድረክ ተካሔዷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ የአማራ ክፍሎች የአብይ አህመድ እና የእሱ ደናቁርቶቹ ናለትም የብአዴን ካድሪዎች በአንድም በሌላም ያልሰሩት ያግፍና የጥፋት አይነት የለም። እንዳለመታደል ሆኖ አማራ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ አሁን ሳይሆን የተጀመረው ከ1960ቹ ጀመሮ ነበር ይላል የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዋና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ፋኖ ያሬድ አስናቀ ። ሆኖም ማጀቴ በተደጋጋሚ  ከአጎራባች የኦሮሞ ልዩ ዞን በእየ ቀኑ ትንኮሳዎች እየተነሱ ማህበረሰባችን አላግባብ ሲንገላታ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሃቅ ነው።

በመድረኩም አርበኛ ፋኖ ያሬድ አስናቀ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዋና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ፤አበበ ፀጋዬ የአሳምነው ዕዝ የሃብት አሰባሳቢ መምሪ፤ ደረሰ ታደስ የአሳምነው ዕዝ አደርጃጅት መምሪያ እንዲሁም ተስፋማሪያም ታፈሰ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና ፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ በተገኙበት ለማህበረሰቡ ሰፋያ ያለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ያለው ቁመናን በተመልከተ ከአመራሮቹ ግንዛቤ በመስጠት ህዝቡም አንኳር አንኳር የሚባሉ ነጥቦችን በተለይም የህዘብ አደረጃጀት ከብአዴን ጀመሮ የሚመጣው መንግስት እንዲሁም አማራ ጠሉ ብልፅግና በእራሱ ለአሰራር በሚመቸው መንገድ ይመርጥ ስለነበር እኛ እንድሉን ሰጣችሁን የሚሆነን የምናምንበት የእራሳችን መሪዎች በእናንተ በልጆቻችን እንድንመርጥ ሃሳባችንን በነፃነት እንድንግልፅ ስላደረጋችሁን ከምንም በላይ ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ለድርጅታችሁንና ለእናንተ ክብርና ምስጋ ይገባል በርቱ አማራ ማለት ለዚህች ውድ ሃገር ዋልታና ማገር ነው አንድነታችሁ ለአገዛዙ የውድቀት ምዕራፍ ነው በማለት ከማህበረሰቡ አንኳር ነጥቦች ተነስተዋል።

በመጨረሻም ከአራት ስዓት በላይ በወሰደው የህዝብ መድረክ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አሁን ላይ ኃይሉን በደንብ አዘምኖ ወደ ፊት በመግስገስ ላይ ስላለ በተለይም ማህበረሰቡ እራሱን ማደራጀት አለብት ያ ማለት ህዝብ ማለት ፋኖ ነው ፋኖ ማለትም ደግሞ ህዝብ ነው ስለዚህ ከትግሉ ጎን ለጎን የማህበረሰብ አደረጃጅት መፍጠር ለህብረተሰቡ ወቁቱን ያማከለነ ነው ስለዚህ በዚህም የቀበሌ መዋቅር አደረጃጅት በመፍጠርና የተመረጡት አመራሮች ለማህበረሰቡ በታማኝና በሃቀኝነት ለመስረታ የሙስሊም እና የኦርቶዶክስ አባቶች ቃለ መሀላ በመፈፀም አደረጃጀት ተሰርቷል።

መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ ነው
🙏4
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
‎   
   ህዳር 07/ዐ3/2018 ዓ.ም
🙏4
በወሎ ግንባር የ 14 ዓመቱ ታዳጊ አስገራሚ ገጠመኝ

የሚሊሻው ልጅ የአባቱን ትጥቅ ከቤት ከተኛበት አንስቶ ወደ ፋኖ የተቀላቀለው የ14 አመቱ ብላቴና #ግዛው_ማርየ_አዘነው የተባለው ታዳጊ ልጅ የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ የሆነውን አባቱን ከቤት በተኛበት መሳሪያውን በማንሳት ፅሀይ መውጫ ልዩ ቦታው ተንበኮ አካባቢ የምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር ጋር በሜሄድ አስረከበ::

የልጁ ቁርጠኝነት ያስደነቀው የኮር1 ምክትል ወታደራዊ አዛዠ እና የአሳምነው ክ/ ጦር ሀላፊ አርበኛ ጌታሁን ሲሳይ( ግጠም አለኝ) ለልጁ ማበረታቻ እንዲሆን ሁለት እግራ ስናይቶ ክላሽ ሸልሞታል !
🙏3