ከራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የተላለፈ የትግል ጥሪ ‼️
ጤና ይስጥልኝ!
ሰውም ኢትዮጵያዊም ያልሆነውን ጭራቅ ከሕዝባችንና ከሀገራችን አናት ላይ አንስተን ማንነታችንን አክብረን እና አስከብረን የምንኖርበትን ስርአት ለመገንባት በጋራ እንነሳ!
የአማራ ሕዝብ በተፈፀመበት እና አሁንም እየተፈፀመበት ባለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምክንያት እራሱን ለማዳን እያደረገ ባለው ተጋድሎ አኩሪ ድሎችን ተጎናፅፏል። ሊያጠፉት እስከ አፍንጫቸው ታጥቀው የመጡትን ጠላቶቹን በታላቅ ወኔ እና ጀግንነት እየተፋለመ በያሉበት እየደመሰሰ፣ እራሱን እያደራጀ፣ ከጠላት የማረከውን እየታጠቀ ህልውናውን ለማስከበርና የወዲፊቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር በመተባበር በጋራ ለመወሰን ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል።
እኛ አማራዎች በእያንዳንዱ ቀን ከምናደርገው የጦር ሜዳ ፍልሚያ ጎን ለጎን እራሳችንን የማሰልጠን፣የማስታጠቅ እና የማደራጀት ስራችንን ያለ አንዳች መዘናጋት አጠናክረን እንቀጥላለን። አደረጃጀቶቻችንም የተናበበና የተቀነባበረ አመራር ለመስጠት በሚያስችለን መልኩ ለማሰባሰብ የምናደርገውን ጥረት በጥሩ መንገድ በትጋት እየሰራን ነው። ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ሀይሎች ጋር የምናደርገውን የትግል አጋርነት እና ቅርርብ መልክ ለማስያዝ የአማራ ፋኖ በከፍተኛ ትጋት እየሰራ ነው።
አማራ እራሱን እየተከላከለ በትጥቅ እና በአደረጃጀት ሀይሉን እያጠናከረ ከሌሎች ኢትዮጵያን ሀይሎች ጋር ትግሉን አስተባብሮ በድል ለመቋጨት የሚያደርገው ትንቅንቅ እንደተጠበቀ ሆኖ በከተሞች የሚኖረው ሕዝብ ግን የአረመኔው የአብይ አገዛዝ ዋና ገፈት ቀማሽ ሆኖ እያለ በእጁ ብዙ ሊጠቀምበት የሚችል የትግል ግብአት እና ሀይል ቢኖረውም እስካሁን በተደረገው ትግል ላይ የትጥቅ ትግሉን በመጠኑ ከመደገፍ ባለፈ በተገቢው ሁኔታ የትግሉን ጊዜ እና መስዕዋትነት ለማሳጠር በተቀናጀ መንገድ አልተነቃነቀም።
በዛሬዋ የአብይ አህመድ አረመኔያዊ አገዛዝ ኢትዮጵያ በከተሞች ለሚኖረው ሕዝብ በሰላም ወጥቶ መግባት ብርቅ ነው። ያለ ጉቦ ጉዳይ ማስፈፀም የማይታሰብ ሆኗል። ልጆቹን ለሚገድልበት ገንዘብ ለማሰባሰብ ሕዝባችንን አጥንቱን እየጋጠው ነው። በኑሮ ውድነት ሰቅዞ እያሰቃየው ነው። ከትግል መነሻችን ጀምሮ በተደጋጋሚ እንደገለፅነው የአማራ ሕዝብ ህልውና የሚጠበቀውና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነውን አገዛዝ ከነግሳንግሱ መቅበር የሚቻለው ሁሉንም የትግል ስልቶች በተገቢው ቦታ እና ጊዜ በተጠና እና በታቀደ መንገድ አቀናጅቶ እና አዋህዶ በመምራት እንደሆነ ላፍታም መዘንጋት የለበትም።
የኢትዮጵያ ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ አረመኔው አብይ አህመድ በትጥቅ የሚፋለሙትን ጀግኖች ለማጥፋት ሴራ የሚጎነጉንበት፣ስንቅና ትጥቅ የሚያገኝበት፣የወንበዴ እና የዘር አጥፊ መደበቂያ ዋሻ መሆኑ በአፋጣኝ ማክተም አለበት። በመሆኑም በከተሞች የሚኖረው ሕዝባችን ነባራዊ ሁኔታው በሚፈቅደው የትግል አይነት ሁሉ እምቢተኝነትን በማፋፋም አረመኔውን ስርአት ለመንቀል በቆራጥነት እንዲነሳ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ የከተማ ትግላችንን በልዩ ሁኔታ የሚከታተል እና የሚያስተባብር የስራ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ተገቢውን አመራር እንደሚሰጥ እናሳውቃለን።
ድል ለአማራ ሕዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
አዲስ ትውልድ፤ አዲስ አስሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ህዳር 6/2018 ዓ.ም
አርበኛ ዘመነ ካሴ

❤3
የአርበኛ አለሙ ገብሩ የህይወት እና የትግል ታሪክ!
"ጀግና ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!"
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የምስራቅ አማራ ኮር 2 ወታደራዊ ዋና አዛዥ አርበኛ አለሙ ገብሩ የትውልድ ቦታው ራያ ቆቦ ዞብል ነው::
አርበኛ አለሙ ገብሩ እንደ ማንኛውም የአማራ ልጅ ቤተሰቡን በተለያየ ስራ እያገዘ ያደገና በኋላም ለወግ ለማዕረግ በቅቶ አግብቶ የወለደና የሁለት ልጆች አባት የነበረ ነው::
አርበኛ አለሙ ገብሩ እንደ ሌሎች ጓዶቹ ሁሉ ኑሮን ለማሸነፍና የተሻለ ደረጃ ለመድረስ ወደ አረብ ሃገር ሳውዲ አረቢያ በመሄድ ሰርቶ ያለፈለትና ወደ ሃገሩ ተመልሶ ትዳሩን እየመራ ይኖር የነበረ ጀግና ነው::
አርበኛ አለሙ ገብሩ 2013 ዓ.ም በፈነዳው የሰሜኑ ጦርነት ጊዜ የነበረውን ጥሪ በመቀበል የዘመተ ሲሆን በወቅቱ ጠላትን ራስ ምታት በመሆን ከመደበኛው የመንግስት መከላከያ ሰራዊት በላይ ጠላት ጣርማ በር ደርሶ ራያ ላይ በደፈጣ አስቸግሮት የነበረው የዞብል ግንባር ሰራዊት አባልና ግንባር ቀደም አመራር ነበር::
በራያ ዞብል ግንባር ከነበረው የቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖ ክንፍ ጎን ለጎን ይታገል የነበረው ግዙፍ የወገን ሃይል ህዝባዊ ሰራዊት ግንባር ቀደም አመራር በመሆን በሽምቅ ውጊያ ጠላትን እስከ ራያ አላማጣ ዘልቀው በመግባት ራስ ምታት በመሆን ለተጎናፀፉት ትልቅ ድል ጉልህ ሚና ተጫውቷል::
ከ2013 ዓ.ም ድል በኋላ አርበኛ አርበኛ አለሙ ገብሩና ጓዶቹ ሲመሩት የነበረው ህዝባዊ ሰራዊት ቆቦ ከተማ ላይ የቀድሞውን ምስራቅ አማራ ፋኖ የተቀላቀለ ሲሆን በወቅቱ ብርጌድ የነበረውን ዞብል አምባ ብርጌድ ምክትል አዛዥና የአመራር አባል ሆኖም ታሪካዊውን የበላጎ ምሽግ ደምስሷል::
ከበላጎው ታሪካዊ ድል በኋላም የምስራቅ አማራ ፋኖ የጦር ሰፈር ወደነበረው ራያ ቆቦና አካባቢው በመመለስ ላይቀሬው የህልውና የትጥቅ ትግል ከፍተኛ ዝግጅት ይደረግ ስለነበር ምስራቅ አማራ ፋኖ የአገዛዙ ሹማምንቶችና ከፍተኛ የመከላከያ ጀኔራሎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች የሃገር ሽማግሌዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተገኙበት ታላቅ ተሃድሶ አድርጎ ፀረ-ወያኔ ትግሉን ደመደመ::
በመቀጠልም አርበኛ አለሙ ገብሩ የህልውና ትጥቅ ትግሉን አርበኛ ኮማንዶ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ችቦ ለኩሶ ካስጀመረበት ዕለት ጀምሮ ሰራዊቱን ዳግም በማሰባሰብ በማደራጀትና በማስታጠቅ ብሎም በመምራት በራያ በየጁ በላስታ በአምባሰልና ሌሎች የቤተ-አማራ ቀጠናዎች ብርድና ሃሩሩ ረሃብና ጥማቱ ደጋውና ቆላው ሳይበግረው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለህልውና ትግሉ ከፍተኛ የሚባል አስተዋጽኦ አበርክቷል::
አርበኛ አለሙ ገብሩ በወቅቱ ምስራቅ አማራ ፋኖ በጠላትና በውስጥ ባንዳዎች ገጥሞት የነበረውን የመበተን አደጋ በመቋቋምና እናት ሆና ሌሎች አሃዶችን ዳግም እስከ መውለድና እስከማደራጀት ብሎም ለዛሬ እስከማብቃት የደረሰችውን ዞብል አምባ ክፍለጦር 1ኛ ሻለቃ እየመራ በኋላም ክፍለጦሩን በመምራት በታሪክ የተመዘገበ ደማቅ ገድል ፈፅሟል::
አርበኛ አለሙ ገብሩ ዞብል አምባ ክፍለጦርን እየመራ ትግሉን ትልቅ ደረጃ ካደረሱ ጀግና የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ተርታ የተሰለፈ ሲሆን ምኒልክ ዕዝ አደረጃጀቱን አዘምኖ ወደ ኮር አደረጃጀት ሲሻገር የምስራቅ አማራ ኮር 2 ወታደራዊ ዋና አዛዥ ሆኖ ትግሉን ከዛሬ በማድረስ የሚጠበቅበትን ተወጥቶ አልፏል::
በመጨረሻም አርበኛ አለሙ ገብሩ ምኒልክ ዕዝ ባወጀውና ከመስከረም 14-30/2018 ዓ.ም በቆየው በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ምስራቅ አማራ ኮር ሁለትን እየመራ በርካታ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናፅፎ ከዘመቻው መገባደድ ማግስት የጠላትን ከባድ የማጥቃት ዘመቻ በመመከት ተኩለሽ ግንባር ከቆቦ ከተማ ቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠበለት የተባለ ቦታ ላይ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም በክብር መስዋዕትነትን ተቀብሏል::
በመጨረሻም እኛ የትግል ጓዶቹ አርበኛው ጓዳችን መስዋዕትነት የከፈለበትን አላማ ከግብ እናደርሳለን የህዝባችንን ህልውና እናረጋግጣለን!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የትግል ጓዶቹ ከትግሉ ሜዳ!
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 7/2018 ዓ.ም

❤2💔1
አሩሲ አቦምሳ ሐይፋ ዳገት!
"ወዲያው ከዋናው መንገድ ራቅ ብለው ወደ ጫካ ይዘዋቸው እንደገቡ ተከታታይ የሩምታ ተኩስ ሰምተናል። ምናልባት የተወሰኑትን ሳይጨፈጭፏቸው አይቀርም።
አውቶብሱ በታጣቂዎች መንገድ ተዘግቶበት ቆመ። ወዲያው ታጣቂዎች ወደ አውቶብሱ ገብተው በኦሮሞኛ ሁሉም ተሳፋሪ እንዲወርድ አዘዙ ። ጭምብል አለባበሳቸው መሣሪያ አያያዛቸው አልባሳት አለባበሳቸው ከቴሌቪዥን የምናያቸውን የአልሸባብ ታጣቂዎች ይመስላሉ።
ወዲያው አማራ ኦርቶዶክስ የሆናችሁ በዚህ በቀኝ በኩል ተሰለፉ አሉ። ኦሮሞ የሆናችሁ በግራ ተሰለፉ አሉ።
ወዲያው ቆጠራ አድርገው ኦሮሞዎች ወደ አውቶብስ ገብታችሁ ጉዞ ቀጥሉ አሉ። እኛ ጉዞ እንደጀመርን 31 አማራ ኦርቶዶክሶችን ከሐይፋ ዳገት ወደ ጫካ ይዘዋቸው ገቡ።
.. ወዲያው ከዋናው መንገድ ራቅ ብለው ወደ ጫካ ይዘዋቸው እንደገቡ ተከታታይ የሩምታ ተኩስ ሰምተናል። ምናልባት የተወሰኑትን ሳይጨፈጭፏቸው አይቀርም።
እኔ ኦሮሞ ነኝ ብዬ በግራ በኩል ተሰልፌ ወደ አቦምሳ ገባሁ።
እስከአሁን ልቤ ሐይፋ ዳገት ታግተው ከተወሰዱት ዘመዶቼ ጋር ነው። እነማን ተጨፍጭፈዋል! እነማን ተረፈዋል! ሰቀቀን ላይ ነኝ።
ሰው ላይ የተተኮሰ ጥይትና አየር ላይ የተተኮሰ ጥይት ድምፁ ይለያያል። በእርግጠኝነት የሩምታ ተኩሱ አየር ላይ አይደለም።
በሰው ገላ ላይ ነው ያረፈው። ምነው ዕዛው በቀኝ ተሰልፌ አማራ ኦርቶዶክስ ነኝ ብዬ መከራውን ብቀበል እላለሁ።"
ኅዳር 6/2018 ዓ.ም ከናዝሬት ወደ አቦምሳ ሲጓዙ ሐይፋ የተባለ ቦታ 31 አማራ ኦርቶዶክሶች ታግተው ተወስደዋል። ከዚያ እገታ የተረፈ ሰው ቀጥታ የላከው መልዕክት ነው።
ዕገታው ሲፈፀም ዓለሙ ስሜ ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ኢብራሂም ከድር አቦምሳ ከተማ ሕዝብ ሰብስበው ሠላም ነው በሉ የጠላት ወሬ ነው በሉ የብልጽግና ጉዞ አይቆምም እያሉ ምናባዊ ብልጽግና ይሰብኩ ነበር!
ኅዳር 7/2018 ዓ.ም
@በለጠ ካሣ

የአርበኛ ዋሴ ከበደ የህይወት እና የትግል ታሪክ!
"ጀግና ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!"
አርበኛ ዋሴ ከበደ የትውልድ ቦታው የራያ ቆቦ አርበት ልዩ ስሙ ቀጋይ አቦ የተባለ ቦታ ነው:: የ1ኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው ተወልዶ ባደገበት አገሩ የተማረ ሲሆን የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱንም ቆቦ ሃይስኩል ጨርሶ በኋላም በመምህርነት ተመርቋል::
አርበኛ ዋሴ ከበደ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት በመምህርነት ሞያ ሃገሩንና ወገኑን ያገለገለ የነበረ ሲሆን 2013 ዓ.ም በጀመረው የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በነበረው ጥሪ ወደ ማሰልጠኛ ገብቶ ተመርቆ የአማራ ልዩ ሃይልን ተቀላቅሎ ታግሏል::
አርበኛ ዋሴ ከበደ በሰሜኑ ጦርነት የአማራ ልዩ ሃይል የቴዎድሮስ ክፍለጦር አር ፒ ጅ እና ብሬን ተኳሽ ሆኖ የታገለ ሲሆን በወቅቱ በነበረው ከፍተኛ ሴራና አሻጥር በመማረር ነፃ ሆኖ ህዝቡን ለማገልገልና ለመታገል ሲል ከልዩ ሃይሉ በመውጣት በትውልድ አካባቢው ወጣቶችን በማደራጀትና በማስታጠቅ ወደ ሽምቅ ውጊያ በመግባት በርካታ ጀብዶችን ፈፅሟል::
ከጥር 2013 ዓ.ም ድል በኋላም በይፋ ምስራቅ አማራ ፋኖን ተቀላቅሎ የቀድሞው የዞብል አምባ ብርጌድ አባል ሆኖ ሲታገልና ሲያታግል ቆይቷል:: በታሪካዊው የበላጎ ድልም የቀድሞው የዞብል አምባ ብርጌድ አባል ሆኖ ታሪክ ሰርቶ አልፏል::
አርበኛ ዋሴ ከበደ ከሰሜኑ ጦርነት በደቡብ አፍሪካው የፕሪቶሪያ ስምምነትና ድራማ መጠናቀቅ በኋላ ምስራቅ አማራ ፋኖ የአማራን ህዝብ ህልውና በትጥቅ ትግል ለማረጋገጥ ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም በረሃ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ሰራዊቱን እንደ አዲስ በማሰባሰብ በማደራጀትና በማስታጠቅ ጉልህ ሚና ተጫውቷል::
አርበኛ ዋሴ ከበደ ሰራዊት ከማሰባሰብ ከማደራጀትና ከማስታጠቅ ባሻገር ዞብል አምባ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃ ሻምበል መሪ ዘመቻ እና የሻለቃዋ አመራር ሆኖ በበርካታ ግንባሮች በርካታ ጀብዶችን በመፈፀም ብሎም ቆቦ ከተማ ድረስ ዘልቆ እየገባ ባንዳ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድና በማፅዳትም የሚስተካከለው አልነበረም::
በመቀጠልም አርበኛ ዋሴ ከበደ የዞብል አምባ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃን እየመራ በራያ በየጁ በአምባሰልና በተለያዩ የቤተ-አማራ ግንባሮች በርካታ ድሎችን የተጎናፀፈ ሲሆን መስከረም 26/2016 ዓ.ም ቆቦ ከተማ ሆርማት እና መጋቢት 3/2016 ዓ.ም አምባሰል አካባቢ ሁለት ጊዜ የቆሰለና በፅናት የታገለ ጀግና ነበር::
አርበኛ ዋሴ ከበደ በዞብል አምባ ክፍለጦር ሻለቃ እየመራ ባስመዘገበው ድልና ከፍተኛ አፈፃፃም ምክንያት ወደ ዞብል አምባ ክፍለጦር አመራርነት በኋላም ባለው ከፍተኛ ውጊያን የማንበብና የማዋጋት አቅም የክፍለጦር ዘመቻ ሆኖ የመራ ሲሆን በቅርብ ጊዜም የምስራቅ አማራ ኮር 2 ምክትል ዘመቻ መሪ ሆኖ እስከመመረጥ የደረሰ ጀግና አርበኛ ነበር::
በመጨረሻም አርበኛ ዋሴ ከበደ ምኒልክ ዕዝ ባወጀውና ከመስከረም 14-30/2018 ዓ.ም በቆየው በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የምስራቅ አማራ ኮር ሁለት ምክትል ዘመቻ አመራር ሆኖ በርካታ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናፅፎ ከዘመቻው መገባደድ ማግስት የጠላትን ከባድ የማጥቃት ዘመቻ በመመከት ተኩለሽ ግንባር ከቆቦ ከተማ ቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠበለት የተባለ ቦታ ላይ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም በክብር መስዋዕትነትን ተቀብሏል::

💔2
የአፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት የ206ኛ ከፊያለው ደሴ ኮር አምበሳው ጋይንት ክፍለጦር አስቻለው ደሴ ብርጌድ ምልምል የፋኖ ሰላጠኞችን ለወራቶች አሰልጥኖ በዛሬውለት አስመርቋል!!
መሰልጠን መደራጀት መታጠቅ መደራጀት የፋኖ ትግል መርህ ነውና በርቱ✊
ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ

🙏5🔥1
ከምንጃር ሸንኮራ ወደ በረኸት ወረዳ ሬሽን ሲያንቀሳቅሱ በነበሩ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ላይ ከባድ የደፈጣ ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል!
በጥቃቱ ሁለት ተሽከርካሪ ሙሉ ሰራዊት ከነ ተሽከርካሪው መውደሙ ታውቋል!
በደቡብ አማራ ቀጠና ከምንጃር ሸንኮራ ወደ በረኸት ወረዳ ሬሽን ሲያንቀሳቅሱ በነበሩ፡ አገዛዙ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ሲል የሚያሞካሻቸው ህፃን ደፋሪ የ104ኛ ክ/ጦር የኮማንዶ አባላት ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት ሁለት ተሽከርካሪ ሙሉ ሰራዊት ከነ ተሽከርካሪው መውደሙን መረብ ሚዲያ ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ስር ከሚገኘው ከነበልባል ክፍለጦ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ህዳር 06/2018 ዓ/ም ሲሆን፡ በጠላት ላይ መራር ክንዳቸውን በማሳረፍ ድሉን የተቀዳጁት ደግሞ በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክ/ጦር ስር የሚገኙት የጄነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ አባላት መሆናቸው ታውቋል።
ወታደራዊ ሬሽኑን ሲያንቀሳቅሱ ከነበሩ ተሽከርካሪዎች መካከል ሁለቱ ተሽከርካሪዎች በላያቸው ላይ ተሳፍረውባቸው እስከነበሩ ኮማንዶዎች ዶግ አመድ መደረጋቸውን ከክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ተችሏል።
የፀረ አማራውና ፀረ ሰላሙ ዐብይ አህመድ ተላላኪ ወታደሩ ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋቋም ሲያቅተው፡ በያዘው ከባድ መሣሪያ የእውር ድንብሩን በመተኮስ በአከባቢው የሚገኙ የአርሶአደሮችን መኖሪያ ቤትና አዝመራን ሲደበድብ መዋሉ ታውቋል።

🙏3
ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተሳተፈበት የህዝብ መድረክ በታሪካዊቷ ማጀቴ ከተማ ተካሔደ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር በታሪካዊቷ ማጀቴ ከታማ ከሊቅ እክከ ደቂቅ የዕዙ አመራሮችና የዓፄ ዘራዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የህዝብ መድረክ ተካሔዷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ የአማራ ክፍሎች የአብይ አህመድ እና የእሱ ደናቁርቶቹ ናለትም የብአዴን ካድሪዎች በአንድም በሌላም ያልሰሩት ያግፍና የጥፋት አይነት የለም። እንዳለመታደል ሆኖ አማራ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ አሁን ሳይሆን የተጀመረው ከ1960ቹ ጀመሮ ነበር ይላል የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዋና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ፋኖ ያሬድ አስናቀ ። ሆኖም ማጀቴ በተደጋጋሚ ከአጎራባች የኦሮሞ ልዩ ዞን በእየ ቀኑ ትንኮሳዎች እየተነሱ ማህበረሰባችን አላግባብ ሲንገላታ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሃቅ ነው።
በመድረኩም አርበኛ ፋኖ ያሬድ አስናቀ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዋና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ፤አበበ ፀጋዬ የአሳምነው ዕዝ የሃብት አሰባሳቢ መምሪ፤ ደረሰ ታደስ የአሳምነው ዕዝ አደርጃጅት መምሪያ እንዲሁም ተስፋማሪያም ታፈሰ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና ፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ በተገኙበት ለማህበረሰቡ ሰፋያ ያለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ያለው ቁመናን በተመልከተ ከአመራሮቹ ግንዛቤ በመስጠት ህዝቡም አንኳር አንኳር የሚባሉ ነጥቦችን በተለይም የህዘብ አደረጃጀት ከብአዴን ጀመሮ የሚመጣው መንግስት እንዲሁም አማራ ጠሉ ብልፅግና በእራሱ ለአሰራር በሚመቸው መንገድ ይመርጥ ስለነበር እኛ እንድሉን ሰጣችሁን የሚሆነን የምናምንበት የእራሳችን መሪዎች በእናንተ በልጆቻችን እንድንመርጥ ሃሳባችንን በነፃነት እንድንግልፅ ስላደረጋችሁን ከምንም በላይ ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ለድርጅታችሁንና ለእናንተ ክብርና ምስጋ ይገባል በርቱ አማራ ማለት ለዚህች ውድ ሃገር ዋልታና ማገር ነው አንድነታችሁ ለአገዛዙ የውድቀት ምዕራፍ ነው በማለት ከማህበረሰቡ አንኳር ነጥቦች ተነስተዋል።
በመጨረሻም ከአራት ስዓት በላይ በወሰደው የህዝብ መድረክ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አሁን ላይ ኃይሉን በደንብ አዘምኖ ወደ ፊት በመግስገስ ላይ ስላለ በተለይም ማህበረሰቡ እራሱን ማደራጀት አለብት ያ ማለት ህዝብ ማለት ፋኖ ነው ፋኖ ማለትም ደግሞ ህዝብ ነው ስለዚህ ከትግሉ ጎን ለጎን የማህበረሰብ አደረጃጅት መፍጠር ለህብረተሰቡ ወቁቱን ያማከለነ ነው ስለዚህ በዚህም የቀበሌ መዋቅር አደረጃጅት በመፍጠርና የተመረጡት አመራሮች ለማህበረሰቡ በታማኝና በሃቀኝነት ለመስረታ የሙስሊም እና የኦርቶዶክስ አባቶች ቃለ መሀላ በመፈፀም አደረጃጀት ተሰርቷል።
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ ነው

🙏4
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ህዳር 07/ዐ3/2018 ዓ.ም