ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!

የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት ንፁሃንና እንስሳትን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ !

ህዳር 05/2018ዓ.ም

የአገዛዙ ብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጨፍጫፊ ሰራዊት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ላስታ ወረዳ 04 ቀበሌ ሳርዝና ልዩ ስሟ ወምበርኮ ማርያም ከምትባል ደብር እህል በመዉቃት ላይ ያሉ ንፁሃንን ላሊበላ ከተማ ልዩ ስሙ ሁለት ቁጥር ከሚባለው ቦታ በመሆን በዘፈቀደ ሞርተር 120 ወደ ንፁሃን በመተኮስ የአንድ ቤተሰብ ልጆች
1. ህፃን ወርቅየ ጌታቸው ዕድሜ=15 ወዲያውኑ አውድማው ላይ ሲሞት
2. ህፃን ደባሽ ጌታቸው ዕድሜ=8 ቀኝ እጁ የተቆረጠ እንዲሁም
3. የልጆቹ አባት አቶ ጌታቸው መለሰ ዕድሜ=46 በከባድ ሁኔታ የቆሰለ
4. ሰባት ከብቶች ወዲያውኑ ሲሞቱ
5. አውድማው ላይና በዙሪያው የነበረ ሦስት ክምር እህል ከ30 ኩንታል በላይ የሚገመት እህል ወድሟል።

የብልፅግና ወራሪ ሰራዊት ግብረ ሰዶም የሚፈፅም፣ህፃናትን የሚያርድ፣ንፁሃንን የሚረሽን በመድፍ አረር የሚቆላ፣አራጅ፣ደፋሪ ፀረ አማራ በመሆኑ በህዝባዊ ማዕበልና እምቢተኝነት ለአንዴና ለመጨረሻ ተባብረን እናስወግደው ሲሉ የጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ሃምሳ አለቃ ጌታየ ተፈሪ ጥሪ አስተላልፈዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጄ/ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ ፋኖ ሽፈራው አለልኝ መረጃውን አድርሷል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 05/ 2018 ዓ.ም
4💔2
የወንበዴ ስርዓት : የብልፅግና የደናቁርት አመራር : የደቦ ፍርድ ውጤት!

ይህ ሰው ጨካኝ ሆኖ የሰው ነፍስ አላጠፋም። በውንብድና ተግባር ተሰማርቶ አልያም ዘርፎ አይደለም፣ የሰው ሚስትም አልቀማም። እኔ እንደሰማሁት ከሆነም ልጁ በጨዋነቱ የሚወቀስም አልነበረም። የአከባቢው ሰዎችም እንዲሁ ነው የሚሉት። ምስኪን ነው።

ይህን የጭካኔ ጥግ፣ የግፍ ግፍ የፈፀሙበት ጉልበተኞች በወቅቱ በተፈጠረ ፀብም አልነበረም። በዚህ ልክ ማሰብ እንዲሳናቸው ያደረጋቸው የቆየ ነገር፣ ያደረ እና የከራረመ ቂም ይዘው መሆኑ ነው። የሰማሁት ይህንኑ ነው። የተባልኩትም እንዲሁ።

በ2009 ዓም ላይ ቤቴን አቃጥለሃል፣ ንብረቴን አውድመሃል ነው መነሻቸው። ይህን ብለው ቂማቸውን በግፍ ማወራረድ የፈለጉት ግለሰብ አቶ ብርሃኑ በቀለ የሚሰኙ እና በዲላ ዙሪ የአንዲዳ ቀበሌ ነዋሪም ናቸው።

ነሃሴ 24 2016 ዓ/ም አቶ ብርሃኑ በቀለ ተባባሪ ጓደኞቹን ይዞ ወጣት ደሳለኝ ማርያምን ወዳለበት መኖሪያ ቤት በማቅናት ያገኙታል። ይዘውትም ተረባርበውበት አዋክበውና አንገላተው ልብሱን ቀዳደው አውልቀው፣ እጆቹን በገመድ ጠፈሩት። እርቃኑን እንደሆነም ወደ ገበያ ለሽያጭ እንደሚነዱት ከ*ብ**ት እየጎተቱት፣ በአለንጋም እየገረፉት፣ በካሜራዎቻቸው እየቀረፁት እና ፎቶ እያነሱት፣ በሰው እያሳቁበት፣ እየተዘባበቱበት፣ ከኦቲልቾ እስከ አንዲዳ ድረስ ህዝብ እየተመለከታቸው፣ አንድም ተዉ፣ በህግ አምላክ፣ እባካችሁን እረፉ. . የሚላቸው ሳይኖር ህጉም፣ እግዜሩም፣ ሰዉም፣ ባህልም የሚጠየፈውን የነውር እና የጭካኔ ጥግ የሆነ ድርጊታቸውን በአደባባይ እየፈፀሙ፣ እንዲሁ ደጋግመው እየገረፉት፣ ባሰሩት ገመድ እየጎተቱት ለአንዲዳ ፖሊስ አስረክበውታል።

በወቅቱ የነበረው ፖሊስም ደሳለኝን እርቃኑን በገመድ ታስሮ ሲያየው ጥቂት እንኳን አልደነገጠም። "አስገቡት !!" ነበር ያለው። አዎን አስገቡት ከማለት ውጪ ለምን እንዲህ አደረጋችሁ ብሎ እንኳን አልጠየቃቸውም። ወጣቱ ምስኪን ደሳለኝም አንድ የሚረዳው፣ አንድ እንኳን የሚሟገትለት፣ አይዞህ የሚለው ሳይኖር ይህን ሁሉ ግፍ ተቀበለ። ምሬትን አጣጥሞ ቀመሰ። ጭካኔን እስከ ጥጉ ድረስ ያውም ሲፈፀምበት አየ። ሀፍረተ ስጋውን በእራፊ ጨርቅ እንኳ አልሸፈኑትም ነበር።

ከዚህ ሁሉ ስቃይ እና እስር በኋላም እንዲህ ሆነ።

ፖሊስ ነፃ ነህ ብሎት ካሰናበተው ቀን በኋላ ይህ ምስኪን ወጣት ደሳለኝ ማርያም የገባበት አልታወቀም።
ወላጅ አባቱ አቶ ማርያም ጎበና ከኦሮሚያ ክልል ሻኪሶ ወረዳ ሆነው፣ ለዲላ ከተማ አስተዳደር እና ለሚመለከተው ሁሉ ብለው በፃፉት ደብዳቤ

"ልጄን አጣሁት። ስራ ይሆናል ብለን ብንጠባበቀው ድምፁ ጠፋብን። ኋላ ላይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እርቃኑን በገመድ አስረው ሲያሰቃዩት የሚያሳይ ፎቶ ተለቆ ያዩ ሰዎች ነገሩን። ለዲላ ከተማ ፖሊስ ባመለክት ከሶስት ወር ያለፈ ክስ አንቀበልም አሉኝ። ቢያንስ የልጄን መኖርም መሞትም ባውቅ ብዬ አልሆነልኝም። ፖሊስ እንኳን ለፍትህ ደጁን ዘጋብኝ" የሚል ይዘት ያለው ነው።

እንግዲህ ይህ የሆነው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ አስተዳደር ስር ነው። እንደሰማሁት ከሆነም የዲላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ፣ ጉዳዩን ይዘውት የነበሩት መርማሪ ፖሊሶች በጉርሻ ተደልለው ነገሩ ተድበስብሶ እንዲቀር አድርገውታል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ እና የዲላ ከተማ ፖሊስ ስለዚህ በሰው ልጅ ላይ ስለተፈፀመ ግፍ በቂ እና የተጣራ መረጃ እንዲሰጥ እናድርግ።

ይሄን ሁሉ ግፍ የፈፀሙት ጉልበተኞች እና ተባባሪ የህግ አካላቶች እንዲጠየቁ ማድረግ አለብን።

ምን የሚባል ኋላ ቀርነት፣ ምን የሚባል ጭካኔ፣ ምን የሚባል ከሰውነት መሸሽ እንደሆነም ይንገሩን። በየጊዜው የምንሰማው ዜና ሁሉ እውነት መንግስት ያለበት ሀገር ላይ ነን ?! ከማስባልም እያለፈ ነው።

እባካችሁ ይህን አፀያፊ ነውር መስማት ያለበት ሁሉ ጋር እንዲደርስ ሼር አድርጉት።

Cc Minase Wako Gudeta
5
የደጋው መብረቅ ኮር ከወቄታ እስከ ፍላቂት ባለው ቀጠና በርካታ የጥላት ሃይል በመደምሰስ ድል ተጎናፀፈ::

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለ ጦር በጥላት ላይ በወሰደችው ከፍተኛ ጥቃት በመቄት ወረዳ ታይቶ የማይታወቅ ታሪክ ሰራች።

ከማለዳው 4:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት አንድ ሰዓት በዘለቀው እልክ አስጨራሽ አውደ ውጊያ ከወቄታ እስከ ፍላቂት ቀጠናውን ዘርግቶ ሲለበለብ ውሎ ያመሸው የጥላት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተደመሰሰ።
የፋሽስቱ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛውን በስምንት ፓትሮል ሲያጎጉዝ የዋለ ሲሆን ሶስት ፓትሮል ሙት፤አምስት ፓትሮሎች ቁስለኛን ጭነው ሲያመላልሱ ውለዋል።የጥላት ጥምር ሰራዊት ተብየው ጣረሞቱን አፋጥኖ ሞቱን ተረክቧል።

ከአፍንጫው ዳር ሞትን እያነፈነፈ ያለው ስርአት በመቄት ወረዳ በግስላዎቹ ሞትን እድጎርሳት ተደርጓል። የደጋው መብረቅ ኮር የፋሽስቱን ሰራዊት ከመሀል አስገብቶ ቅንድብ ቅንድቡን በመቀንደሽ ወደማይቀረው አለሙ እየሸኘው ለምስጥ ሲሳይ አድርጎታል። ፎክሮና ፎግሮ አማራ ክልል የገባው የጥላት ሰራዊት እና በሆዱ የተገዛው ባንዳ በአንሻ ክፍለ ጦር አመርቂ አሸኛኜት ተደርጎለታል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለ ጦር
ህዳር 5/2018 ዓ.ም
🙏4👍1
ሁለት የሀገር በቀል ጥቁሩ ፋሽስት ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ተደመሰሱ!
አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለጦር በትናንትናው አውደ ውጊያ የአድማበትን ሁለት ከፍተኛ አመራር ተደምስሰዋል

ህዳር 5/2018 ዓ/ም ከወቂታ እስከ ፍላቂት በነበረው አውደ ውጊያ የጥላት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ መደምሰሱን የዘገብን ሲሆን። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአማራን ህዝብ በከርሳቸው ፍጆታ የሸጡ አብርሀምና ጌታቸው የተባሉ የአድማበትን የውህድ ምክትል አዛዥ እና ከፍተኛ አመራር በአውደ ውጊያው ተደምስሰዋል። የቀብር ስርዓታቸው ዛሬ ህዳር 6/2018 ዓ/ም እደሚፈፀምም ያገኘነው መረጃ ያሳውቃል።

የሶስት ሻለቃ ውህድ ምክትል አዛዥ የሆነው ጌታቸው የሚባል ባንዳ በትናንትናው እለት አውደ ውጊያው ላይ ሲሸኝ፤አብርሀም የሚባለው ከፍተኛ አመራር ግን ከባድ ቁስለኛ ሆኖ ወደ ሆስፒታል ቢገባም የአብይ አህመድ የከርስ መሙያ ብር ህቅታውን ሊታደጋት አልተቻለውም ነበር።በባንዳነት ህዝባቸውን ክደው ለፋሽስቱ ሲያጎበድዱ የነበሩት ሁለቱም ወደ አምላካቸው ተሸኝተዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለ ጦር
ህዳር 6/2018 ዓ.ም
🙏31
የድል ዜና

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ  ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የበፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር ድልን ተቀናጀ!

በትላንትናው ዕለት በቀን 05/03/2018 የአብይ አህመድ አገዛዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር አናብስቶች አሉበት ወደ ተባለው ቀጠና የጠላት ኃይል ዘልቆ በመግባት ከበባ ለማድረግ ቢሞክርም በክንደ ነበልባሎች ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።

በመሆኑም ጠላት በሰፊው ከጉንዶ መስቀል በመነሳት ከግራኝ ሙቀጫ እስከ ሀንቁ ባለው ቀጠና  ከስድስት ስዓት  በላይ የወሰደ ውጊያ በማድርግ  የጡት ቆራጩ ኃይል ሶስት መኪና አስከሬን በመያዝ አይቀጡ ቅጣት በመቀጣት እንዲሁም የበፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር  ትግስት ይርሳው ብርጌድ በማከፍታ ቀጭኔ ቀጠና በአደረጉት ውጊያ በጠላት ላይ ከፍታኛ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

በመሆኑም የአብይ አህመድ ተላላኪ ባንዳና ወራዳ መከላከያ በዚህ አካባቢ ፋኖን አጠፋለሁ በማለት በዘጠኝ ሪጅመት በሜካናይዝድ የታገዘ ውጊያ ቢያደርግም በአሳምነው አናብስቶች ከጥዋቱ አስራ አንድ ስዓት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት በመደበኛ ውጊያ ሲዋጉት ውለዋል።  እንደለመደው አሁን የማህበረሰብ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት በሞሆኑ አማራን ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ ስልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ በደራ አማራ ያላደረገው ያልሰራው ስራ የለም ነገር ግን ጀግኖች የአማራ እናት የወለደቻቸው የበፍቃዱ  በላይ ክፍለ ጦር በአስደማሚ ሁኔታ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድልን ተቀናጅተዋል።

አማራ በታሪክ ጀምሮ ያልጨረሰው የትግል ምዕራፍ የለም አባቶቻችን ብዙ ጥበብን፣ ፅናትን፣ አይበገሬነትን አስተምረውን አልፈዋል። እኛም የአባቶቻችን ፈለግ ተከትለን በጥበብ፣ በፅናትና በአሸናፊነት መንገድ የጀመርነውን የአማራን ህዝብ ከመጥፋት የህልውና አዳጋ የማዳንን ሂደት በማይታመን ፍጥነት ወደ ፊት እየገሰገሰ በጠላት ላይ የበላይነት በመውሰድ ዳር ለማድረስ ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን ።

መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  ፩ኛ ኮር  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ ነው።

" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
     አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ  የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል

ህዳር 06/03//2018 ዓ.ም
🙏3
ተሪ የስርዓቱ መቃብር ደሴት ሆናለች!
ፅናት ክፍለ ጦርና 23ኛ ክፍለ ጦር ቃኞች የስርዓቱን አመራር ደመሰሱ!

አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለጦር እና ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር የሻለቃ ቃኝዎች በጥምረት የብልፅግናና አከርካሪ ተሪ በረሀ ላይ ሰበሩ!!

በፓትሮል አራት የመከላከያ አመራሮች ሲንቀሳቀሱ በአራቱም አመራሮች ላይ በተወሰደባቸው እርምጃ ተደምስሰዋል።የሚፈረጥጡባት ፓትሮልም እንደ አለቆቿ እርምጃ ተወስዶባታል።

ህዳር 6/2018 ዓ/ም ከደላንታ እና ከተንታ ወረዳ መነሻውን አድርጎ ሲቀሳቀስ በነበረው የፋሽስቱ ሰራዊት ላይ ፋኖዎች በወሰዱት ጠንካራ ኦፕሬሽን ሙትና ቁስለኛ አደረጉት። ከአራቱ ከፍተኛ አመራሮች በተጨማሪ በርካታ የስርዓቱ ወታደሮች የተሪ ጅብ እራት ተደርገዋል። ከተማንና ህዝብን ምሽግ አድርጎ ሲማግጥ የነበረው የፋሽስቱ ሰራዊት ጭር ባለው የተሪ በረሀ ተቀጥቅጧል።

ራሱን ብልፅግና እያለ የሚጠራው ጨፍጫፊው ስርዓት በአራቱም አቅጣጫ በቆፈረው ምሽጉ እየተቀበረ ይገኛል። ቆሎ ለናፈቀው ህዝብ የድሮን ቦብ የሚያዘበው ስርዓት ቃጠሎ ቤት ላይ ዘላ እደገባች እንቁራሪት ጣረሞት ላይ የሚገኘው የመድፍም ሆነ የድሮን አጀብ የፍርሀቱና የሞቱን መላዕክት ሊያስተጓጉሉለት አልተቻላቸውም።


መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር እና የልጅ እያሱ ኮር ጥምር ቃኞች!!
ህዳር 6/2018 ዓ.ም
🙏3
ድርጅታዊ ተልዕኮን በብቃት መወጣት ተቀዳሚ ተግባሩ መሆኑን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ም ምዕራብ አማራ ቀጠና የ206ኛ ኮር አስታወቀ።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ በመልሶ ማደራጀት ከተቋቋሙ 5(አምስት) ኮሮች መካከል የሚገኘው 206ኛ ኮር በተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ የተሰጠውን ድርጅታዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት በደጀን፣ ስናን ሉማሜና ጎዛምን ወረዳዎች በአደረጋቸው ተጋድሎዎች በርካታ ወታደራዊ ድሎች ያስመዘገበ ሲሆን ከ70 በላይ የጦር መሳሪያ፣ጥይት ፣ሁለት ብሬን፣ በመማረክ የጠላት መገልገያ ሁለት ተሽከርካሪዎችን በማጋየት 4(አራት) የመቶ እና የሻለቃ ማዕረግተኛ የጦር አመራሮች ሁለት የፓለቲካ አመራር እንዲሁም በርካታ ሚኒሻና ፖሊስ መደምሰስ መቻሉን ኮሩ ገልጿል።

የመልሶ ማደራጀቱን ተግባር አርያ በመሆን እየተገበረ የሚገኘው 206ኛ ኮር በስሩ ያሉ ክ/ጦሮችን እና ሻለቆችን ከማደራጀት ጎን ለጎን የጊዚያዊ መንግስት ስርዓትና መዋቅር በፍጥነት እየተተከለ እንደሚገኝም አክሎ ገልጿል።

የጋራ አመራርነትንና የቡድን ስራን መርህ አድርገው አድርገው ዝርዝር ተግባራትን በሚፈፅሙ አመራሮች የተደራጀው 206ኛ ኮር የቀጠናውን ትግል ከፍ ለማድረግ የሚያስችል መዋቅር በመዘርጋት ድርጅታዊ ተልዕኮን በብቃት መወጣት የኮሩ ተቀዳሚ ተግባር ይሆናል ሲል የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር አስታውቋል።  ለዚህም ማሳያ የሚሆኑ ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን በደጀን እና ሉማሜ የተፈፀሙ ጀብዶች ተጠቃሽ ናቸው ሲል ኮሩ አክሎ ገልጿል።

የአፋብኃ ቲዎድሮስ ዕዝ ህዝብ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት!!
👍3
"ጀግና ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!"

የአርበኛ ፍሬው አለና የህይወት እና የትግል ታሪክ!

አርበኛ ፍሬው አለና የትውልድ ቦታ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ነው:: የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ቆቦ ከተማ ሚሊኒየም ት/ቤት እና ቆቦ ሃይስኩል ተምሯል::

ወጣቱ አርበኛ ፍሬው አለና የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ፊቱን ወደ ግል ስራ በማዞር የግል ስራዎችን ይሰራ የነበረ ሲሆን ባለ ትዳርና የሁለት ልጆች አባትም ነበር::

አርበኛ ፍሬው አለና በ2013 ዓ.ም የተቀሰቀሰውን የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ ፋኖን በመቀልቀል የዞብል አምባ ክፍለጦር አባል በመሆን በርካታ ተጋድሎዎችን በማድረግ ስሙን በታሪክ መዝገብ አስፍሯል::

የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነትና ድራማ መጠናቀቅ ማግስት የአማራ ህዝብ የዘመናት ጥያቄዎች በብልፅግናው አገዛዝ በኃይል መታፈን ጋር ተያይዞ ፋኖ ወደ ለየለት የፖለቲካ ት ጥቅ ትግል መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን አርበኛ ፍሬው አለና ቆቦ ከተማ በህቡ እየተንቀሳቀሰ ስውር ድርጊያዎችን በመፈፀም ትግሉን ቀጠለ::

አርበኛ ፍሬው አለና የፋሽስቱ አገዛዝ ሰዎች እስከሚጠረጥሩና እስከሚነቁበት ድረስ ከአንድ አመት በላይ ጊዜ ቆቦ ከተማ በህቡ በመንቀሳቀስ በርካታ ተጋድሎዎችን በማድረግና ጀብዶችን በመፈፀም ከተማውንና ግንባር ያለውን ፋኖ ድልድይ ሆኖ በማገናኘት የትግሉን ሚዛን በመጠበቅ ጉልህ ሚና ተጫውቷል:: በነበረው ተጋድሎም ቆስሎ ታክሞ ብዙም ሳያገግም ተመልሶ ወደ ትግሉ ገብቷል:: በዚህ ጊዜም ከተማ ውስጥ በፋሽስቱ አገዛዝ መካከል ሆኖ ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በመተባበር ከ50 በላይ ክላሾችን ከብልፅግና ሰዎች በመሰብሰብ ፋኖን አስታጥቋል::

አርበኛ ፍሬው አለና ከስውር ድርጊያው በመውጣት ወደ መደበኛው የግንባር ተጋድሎ በመቀላቀል የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን በመቀላቀል የክፍለጦር ዘመቻ መሪ በመሆን በበርካታ የቤተ-አማራ አካባቢዎችና ግንባሮች የጠላትን አንገት ያስደፋ የወገንን አንገት ቀጥ ያደረጉ ድሎችን ተጎናጽፏል::

አርበኛ ፍሬው አለና ምኒልክ ዕዝ ባወጀውና ከመስከረም 14-30/2018 ዓ.ም በቆየው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የዕዙ ልዩ ዘመቻ አሃድ የሆነውን ክፍለጦር ዘመቻ መሪ ሆኖ በርካታ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናፅፎ ከዘመቻው መገባደድ በኋላ የነበረውን የጠላት ከባድ ማጥቃት በመመከት ተኩለሽ ግንባር በነበረ ትንቅንቅና ተጋድሎ ከቆቦ ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠበለት የተባለ ቦታ ላይ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ለአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ነፃነት ሲል መስዋዕትነት ከፍሎ አልፏል::

በመጨረሻም እኛ የትግል ጓዶቹ ወጣቱ አርበኛ ፋኖ ፍሬው አለና የተሰዋለትን የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ለድልና ነፃነት እናበቃለን!
የትግል ጓዶቹ ከትግሉ ሜዳ!
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ
💔3