የአርበኛ ጌትነት መሳፍንትን መስዋዕትነት አስመልክቶ ከአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ የተላለፈ መልዕክት!
አርበኝነት በደም የሚወረስ የታሪክ ስንቃችን ነው። አርበኝነት ፈሪዎች የማይደርሱበት የጎበዞች መንበር ነው። አርበኝነት ከራስ በላይ ለአገርና ለህዝብ፤ ለታራክና ማንነት የሚዋደቁ የተመረጡ ዋጋ የሚከፍሉበት ህያው የታሪክ ገፃችን ነው።
እኛ አማራ ነን ስንል። ከአገር ሰሪው ታላቁ የአማራ ህዝብ አብራክ ስለወጣን ብቻ ሳይሆን እነዚያ ጥቁር ሰው መሆኑን በክንዳቸው ለዓለም ያስተማሩት አርበኞች የግብር ልጆች መሆናችንን በተግባር በማሳየት ነው።
አርበኝነት የትውልድ ቅብብል ውጤት ነው ስንል በእኛ ዘመን ከፊት ምሳሌ የምናደርገው የትግል አባታችን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ነው።
አባታችን የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን አደራ በብረት ትግል ከተቀበሉ ቀዳሚ አርበኞች አንዱ ናቸው።
የአማራ ህዝብ የተቃጣበትን መዋቅራዊ ጥቃት ለመመከት የሀሳብ ትግል ያደረጉት፣ አንቂያችን አደራጃችን ፕሮፌሰር አሥራት የትግል ራዕያቸው በዘመናቸው ባይሳካም። ከሀሳብ ትግል ወደ ነፍጥ ትግል የገባው አማራ የፕሮፌሰር አሥራትን አደራ በመቀበል ነው።
ታላቁ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ በአማራዊ ብሄርተኝነት፣ "አማራ ነኝ" ብለው ቀድመው ነፍጥ ካነሱት አንዱና ቀዳሚው ናቸው።
ከ 30 ዓመታት በላይ አማራ ነኝ ብለው በመታገል ለኛ ትውልድ የሞራልም የተግባር መምህር ሆነውናል።
በዚህ ሳይወሰኑ መላ ቤተሰባቸውን በአማራ የኀልውና ትግል ላይ አሰልፈው፣ ታሪክ በወርቃማ ቀለም የሚፅፈው ገድል እየሰሩ ነው።
የአማራ ህዝብን የታሪክ እጥፋት በሚወስነው በዚህ የትግል ታሪክ መላ ቤተሰቡ በትግል ሜዳ ተሰልፎ በሚከፍለው ዋጋ፣ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት መስዋዕት መሆኑን የሰማሁት በከባድ ሐዘን ነው።
ለኛ ለታጋዮች ሞት ለአማራ ህዝብ ህልውና መረጋገጥ የምንከፈለው የመጨረሻው ስጦታችን ቢሆንም፣ አርበኛ ጌትነት ዕድሜው ለትግል ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ያለእረፍት ከአባቱ ጎን ተሰልፎ የከፈለው ዋጋና ከዚህም በላይ የሚጠበቅበት ታጋይ መሆኑን ስናስብ ህልፈቱ ከባድ ሐዘን ፈጥሮብናል።
ቢሆንም በዚህ መራር ዋጋ እየተከፈለበት ባለ ትግል የ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት እና ሌሎች ሰማዕታት የትግል አደራ ከግብ ለማድረስ የትግል ቃል ኪዳናችንን እናድሳለን።
ትግላችን እስከቀራኒዮ ነውና በእኛ መስዋዕትነት ታላቁን የአማራ ህዝብ ለዘላቂ ድል እናበቃዋለን።
በመጨረሻም ለድርጅታችን አፋብኃ የበላይ ጠባቂ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ፣ ቤተሰቦቹ፣ እና መላው የትግል ጓዶቹ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል አሳምነው ዕዝ ሰብሳቢ አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ
ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም

❤3💔1
አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር በአገዛዙ ጡት ቆራጭ ሰራዊት ላይ እርምጃ ወሰደ!!
የአገዛዙ ስርዓት ከምንጊዜውም በላይ እራሱን ለማትረፍ ከላይ ታች በሚረግጥበት ወቅት የፋኖ የቅንጂት ውጊያ ደግሞ ልዩነት ፈጣሪ አድርጎት ጠላት አንገቱን እንዲደፋ አድርጎታል። ላለፍት ሁለት ወራት በቀንም በሌትም እረፍት አልባ እንቅስቃሴ በማድረግ አንድም ግቡን ያላሳከው ይህ የግለሰብ ፍላጎት አስፈጻሚ ስብስብ አፈና ለመፈጸም ያልወረደው ቁልቁለት ያልወጣው ዳገት አለ ማለት አይቻልም።
ሆኖም የመዋጋት ሞራሉ ከጊዜ ወደጊዜ እየተዳከመ የመጣው ይህ ኃይል የፋኖን የመዋጋት አቅም መስበር ተስኖት በሁሉም አውደ ውጊያዎች ሽንፈትን እየተከናነበ ግማሹ በሞት ከፊሉ በምርኮ ቀሪው እጅ በመስጠት በመበታተን ላይ ነው። አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር በሁሉም ቀጠናዎች ላይ እልህ አስጨራሽ የትንቅንቅ ውጊያዎችን በማድረግ ዛሬም ለ 8:00 ሰዓታት የቆየ አውደ ውጊያ አሳልፏል።
የጠላት ኃይል ከዛጎች ተነስቶ በለሊት የአንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር አካል የሆነችውን ሻንበል አጥናፉ ብርጌድን ደንጓጥ ላይ ለማፈን ሙከራ አድርጎ ነበር። ነገር ግን እንዳሰበው ሳይሆን ባላሰበው መልኩ እራሱን በከበባ ውስጥ አግኝቶታል። ሻንበል አጥፉ ብጌድ በዋናዡ ሻለቃ ጌታሰው ቢራራ እተመራች የጠላትን ኃይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት መፈናፈኝ ሲያሳጡት ውለዋል። ታዲያ የመትረፍ እድሉ ዝቅተኛ መሆኑን የተረዳው ይህ የጠላት ኃይል ከክምር ድንጋይ ተጨማሪ አንድ ሬጅመት ቢላክለትም ከአንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር ፣ ከተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር እና ከኮሩ ጥምር ጦር በደንጓጥ ፣ ጎሃ ፣ እስላምቀብር ፣ፈላሺት ፣ ከአፋፍ መንደር እስከ ጎሃ ኪዳነ ምህረት ድረስ እጅግ ልብ እሚያሞቅ ቅንጅታዊ ውጊያ የታየበት ገጥሞት ውሏል ። በዚህ አውደ ውጊያ ጠላት :-
# 31 ሙት ጎሀ መድሀኒያለም ፣ፍላሽት ጎጥና ዶስካ ጌዎርጊስ ቀብሮ ሲወጣ እና ከ45 በላይ ቁስለኛ አስተናግዶ ተመልሷል።
# 13 ነፍስ ወከፍ ክላሽ እና በርካታ ተተኳሽ ገቢ ሆኗል።
በሌላኛው አውደ ውጊያ በትናትናው እለት ማለትም ህዳር 01/2018 ዓ.ም አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ጄኔራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦር በድል የታጀበ የሙሉ ቀን ውጊያ አድርጓል። ጠላት ተደጋጋሚ ሙከራውን ቢያደርግም አይበገሬዎቹ ትናትም እንደባለፉት ቀናቶች አሳፍረው መልሰውታል። ከየኳሳ እስከ ጃንባ በረሀ ሲባክን የዋለው ጠላት :-
# 18 ሙት
# 32 ቁስለኛውን ይዞ ወደ የኳሳ ዳግም ተመልሷል። ባለፉት ጊዜዓት በዋና አዛዡ ተሾመ ይመር ያልተሳካለት የአፈና እንቅስቃሴ ትናት በምክትል አዛዡ ኮረኔል ይርጋ አርአያ እየተመራ ገባው 64ኛ ክፍለ ጦር የለመደውን ሽንፈቱን ተከናንቦ ተመልሷል። በዚህ የተበሳጨው ጨፍጫፊ ስርዓት ሰላማዊ ሰዎችን ጭፍጨፏል በመፈጸም ዛሬም ከህዝብ የተነጠለ ግፈኛ ስርዓት መሆኑን ዳግም አሳይቷል። በግፍ የተጨፈጨፉ ንጹሀንን ስም ዝርዝርና መረጃ በማጠናከር ላይ እንገኛል በቀጣይ እምናሳውቅ ይሆናል።
ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል!!!

❤4🙏2
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ሲሆን ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ አንድ ስናይፐር እና አምስት ክላሽ ይዘው ምስራቅ አማራ ኮር አንድን ተቀላቅለዋል::
የሚዋጋበት አጀንዳ የሌለው የብልፅግና ሰራዊት አሁንም በሰሜን በኩል አዲስ ጦርነት ጀምሮ ሊያዋጋን ስለሆነና መምሪያም እየወረደ ስለሆነ ነው ኮብልለን ፋኖን የተቀላቀልነው ይላሉ አንድ ስናይፐርና አምስት ክላሽ ይዘው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር አንድን የተቀላቀሉ የሰራዊቱ አባላቶች::
በዚህም አንድ ስናይፐር ከሙሉ ትጥቁና ተተኳሹ ጋር እንዲሁም አምስት ክላሽ የወገብና የደረት ትጥቅ ከተተኳሽና የእጅ ቦምቦች በመያዝ ወደ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ተቀላቅለዋል::
በሌላ የተጋድሎ መረጃ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ እና የኮሩ ቃኝ በጋራ ሰሜን ወሎ ጊራና ዙሪያ ልዩ ስሙ ኮሎቦ ላይ በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃትና በወሰዱት እርምጃ አንድ ጓድ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግና ሁለት ክላሽም ጭምር በማንሳት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 3/2018 ዓ.ም

❤3🙏1
አራት የቪአይፒ (VIP) ጥበቃወች ፋኖን ተቀላቀሉ።
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦርን በዛሬው እለት ከወገናችን ጋር አንዋጋም በማለት ከአድማ ብተና ተቋም በመውጣት ፋኖን የተቀላቀሉት፦
1 መልካሙ አድኛው
2 አሸናፊ ጥጋቡ
3 እንዳለው አበበ
4 እሱባለው አቅነው የተባሉ ሲሆኑ ፦
➢ 04 ክላሽ
➢06 ቦንብ
➢03 የወገብ ትጥቅ
➢06 ካዝና
➢270 የክላሽ ተተኳሽ መሉ ትጥቃቸውን በመያዝ ወደ ወገኖቻቸው የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!

❤2🙏1
ከመብረቅ ክ/ጦር የተሰጠ የሃዘን መግለጫ
"በጓዳችን ድንገተኛ ሞት ልባችን ተሰብሯል ፤ ትከሻችንም ቀሏል !!"
ህዳር 02/2018 ዓ.ም የመብረቅ ክ/ጦር ልዩ ተወርዋሪ ብርጌድ አርኖ ጋርኖ በተባለችው ከተማ ላይ የፀጥታ ተግባርን በማከናወን ላይ በነበረበት ወቅት የጠላትን የእጅ አዙር ተልእኮ ሳያነግብ እንዳልቀረ በተጠረጠረ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት የመብረቅ ክ/ጦር ልዩ ተወርዋሪ ብርጌድ ዋና አዛዥ የሆነው አርበኛ መልካሙ ሞላ መስዋእትነት ከፍሏል።
ጀግናው ጓዳችን አርበኛ መልካሙ ሞላ ከመሪዎቹ የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ በቀናኢትና በታዛዥነት መስዋእትነት እስከከፈለበት ጊዜ ድረስ ሲፈጽምና ሲያስፈጽም ነበር።
ጓዳችን ትግሉ ከተጀመረ አንስቶ ከመብረቅ ክ/ጦር አመራሮችና አባላት ጋር በመሆን ሚካኤል ደብር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በጎንደር ሰማይ ስር የመጀመሪያውን ድሽቃ መማረክ የቻለ ክንዳችን ነበር።
የክ/ጦራችን ብልህና ጠንካራ አርበኛ መልካሙ ሞላ መስዋእትነት የተሰማንን ሃዘን እየገለጽን አርበኛ መልካሙ ሞላና ሌሎች እልፍ ጀግኖች አርበኞቻችን የከፈሉለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እንተጋለን።
➢ለወዳጅ ፣ ለቤተ ዘመዱ እንዲሁም ለትግል አጋሩ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ህዳር 4/2018 ዓ.ም

❤2🙏1💔1
በአፋብኃ በላይ ዕዝ ጠላት ተደመሰሰ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም ተማረኩ!!
የአፋብኃ በላይ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ከባ/ዳር ጎንደር መስመር በወታደራዊ አጀብ ሲጓጓዝ የነበረ ኮንቮይ ኃይል ላይ በተለያዩ ቦታዎች በሰነዘረው የተጠና ማጥቃት ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል።
አገዛዙ እየደረሰበት ያለውን ምት ለመቋቋም ያግዙኛል በሚል በግዳጅ የሰበሰበውን ግብስብስ ሰራዊት በተጨማሪነት ከባ/ዳር ጎንደር በማንቀሳቀስ ላይ ባለበት ከአዲዘመን ማክሰኝት በሚገኝ የመግደያ ቀጠና በማስገባት ብርቱ ምት ሊደርስበት ችሏል።
🔸 ህዳር 03/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ጀምሮ ከባህር ዳር ጎንደርና ከጎንደር ባህር ዳር በርካታ ቁጥር ያላቸው ሎጀስቲክና ሰራዊት የጫኑ ተሽከርካሪዎች በማንቀሳቀስ ላይ እያለ አርኖ ጋርኖ የተሰኘ ልዩ ቦታ እንደደረሰ የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አንድ አካል የሆነው ነብዩ አሳምነው ብርጌድ የአርኖ ጋርኖ ከፍተኛ ቦታዎችን በመጠቀም በጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ጉዳትን አድርሰዋል።
በጥቃቱም ቁጥሩ ለጊዜው በውል ያልተቻለ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።
የ5ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች በመሩት ውጊያ ከተመዘገበው አመርቂ ድል በተጨማሪ የጠላት ኃይል ተመልሶ መውጫ እንዳያገኝ በመዝጋት ሌላ ቀጠና ለተሰናዳ ደፈጣ ጠላት ተጋላጭ እንዲሆን ተደርጓል።
🔸ከአርኖ ጋርኖው ጥቃት አምልጠው ሰብሃ ገብርኤል የደረሰው የጠላት ሰራዊት በ5ኛ ኮር የመብረቅ ክ/ጦር አካል በሆነው ቁልቋል በር ብርጌድ አማካኝነት ለዳግም ጥቃት ተዳርጓል።አያሌዎችም ላይመለሱ ሲደመሰሱ ቀሪዎቹ አካላዊ ጉዳት ተከናንበው ሊያፈገፍጉ ተገደዋል።
ድንገተኛ ጥቃት የገጠመው ጠላት የአስር አለቅነት ማእረግ ያለው ጌታሁን ወርቁ የተባለ አመራሩን እስከነ ሙሉ ትጥቁ አስማርኳል።
በክንደ ፈርጣማዎቹ ፋኖዎች የደረሰበትን አሰቃቂ ምት መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን አርሶ አደሮችና በህፃናት ላይ የበቀል በትሩን አሳርፏል። በዚህም የንፁሃን ጥቃት አንድ የ9 ዓመት ህፃንን ጨምሮ ስምንት ንፁሃን ወገኖችን የዓብይ አገዛዝ ታጣቂዎች በግፍ ረሽነዋል።
🔸ከአርኖ ጋርኖ እስከ ሰብሃ ገብርኤል የፋኖዎችን መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም አቅቶት በንጹሃን አማሮች ላይ የበቀል ጥሙን አወራርዶ ወደ ጎንደር በመፈርጠጥ ላይ እያለ ፈረንጅ ውሃ ከተባለው ቦታ ላይ የጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ንስር ብርጌድና ራስ አሞራው ውብነህ ብርጌዶች በደፈጣ ስልት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ሲቀጠቅጡት አምሽተዋል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት እያጀበ ይዟቸው ከቦታው ያደረሳቸውን 3 ተሽከርካሪዎች ከጫኑት ስንቅና ትጥቅ ጋር የተማረከ ሲሆን ብዙ ቁጥር ያለው ኃይሉ ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ህዳር 04/2018 ዓ.ም

🙏3
"እራበን፣ ህፃናት ልጆቻችን ምግብ ከቀመሱ ብዙ ቀናትን አስቆጥረዋል" ተፈናቃይ ወገኖች!
ከተፈናቃዮቹ መካከል አንዳንዶች፡ የሚቀመስ ባለመኖሩ የልጆቻቸውን "የራበኝ" ድምፅ መስማት አቅቷቸው እራሳቸውን በገመድ አንቀው ማጥፋታቸው ነው የተነገረው።
ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ከአራቱም የወለጋ ዞኖች እንዲሁም ከምዕራብ ሸዋ ዞን በማንነታቸው ምክኒያት ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ ላይ ተጠልለው ከሚገኙ ወገኖች መካከል በርካቶች በረሃብ ምክኒያት ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።
"የሚላስ የሚቀመስ የለም፡ አይደለም እኛ አዋቂዎቹ ይቅርና ህፃናት ልጆቻችን ምግብ ከቀመሱ ብዙ ቀናትን አስቆጥረዋል" ነው ያሉት ተፈናቃዮቹ።
ከ2017 ዓ/ም ሚያዝያና ግንቦት ወራት ወዲህ ምንም አይነት እርዳታ እንዳልቀረበላቸው የገለፁት ተፈናቃይ ወገኖቻችን፡ "እባካችሁ በነፍሳችን ድረሱልን" ሲሉ ተማፅኖ አቅርበዋል።
ብዛታቸው ከ600 በላይ እንደሆነና በማሻ ከተማ በስድስት ካምፕ ተጠልለው እንደሚገኙ ነው መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮቹ የገለፁት።
"ከሰባትና ስምንት ወራት በፊት ይመጣ የነበረው የእርዳታ እህል ለምግብነት መዋል የማይችል፡ የነቀዘና የተበላሸ ነበር፡ አሁን ላይ እሱም ቢሆን ከተቋረጠብን መንፈቅ በላይ ሆኖታል" ሲሉ ለጣቢያችን የገለፁት ተፈናቃዮቹ፡ "እርቦናል፡ በረሃብ ምክኒያት ሕይወቱ የሚያልፈው ተፈናቃይ ቁጥር ከቀን ወደቀን ጨምሯል፣ አንዳንዶች የልጆቻቸውን <የራበኝ> ድምፅ መስማት አቅቷቸው እራሳቸውን በገመድ አንቀው እያጠፉ ነው" ሲሉ ቃል በቃል ተናግረዋል።
ከተፈናቃዮቹ መካከል ሰርቶ ማደር የሚችሉት ከዓመታት በፊት ካምፑን ለቀው ለስራ ወደ ተለያዩ አከባቢዎች የተበተኑ ሲሆን፡ አሁን ላይ በወረዳው በስድስት ካምፕ ተጠልለው ከሚገኙት ከ600 በላይ ተፈናቃዮች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት፡ ለአቅመ ስራ ያልደረሱ ታዳጊዎችና ህፃናት(በጥቃቱ እናትና አባታቸውን ያጡ የቲሞች)፣ አረጋውያን፣ በደረሰባቸው አሰቃቂ ጥቃት አካል ጉዳተኛ የሆኑና በጥቃቱ የተነሳ ለአዕምሮ ህመም የተጋለጡ መሆናቸውን ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
@መረብ ሚዲያ

💔2