ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ህዳር 1/2018 ዓ.ም ላሊበላ የተከሰተው ምንድን ነው?

ሎሌው አረጋ ከበደና ስብስቡ በላሊበላ በተፈፀመባቸው ያልጠበቁት ከባድ ጥቃት ያሰቡትን ሳያሳኩ ወደ ምሽጋቸው ባህርዳር ተመልሰዋል::

ከኦሮሚያ ብልፅግና ጋር በመተባበር የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው አረጋ ከበደና ስብስቡ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ያለው አለቃቸው አብይ አህመድ የሰጣቸውን ተልዕኮ ይዘው ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ የተጓዙ ሲሆን ትናትና ህዳር 1/2018 ዓ.ም ረፋድ ላሊበላ አየር መንገድ ከደረሰ በኋላ ጥቃት ተፈፅሞበታል::

አቶ አረጋ ከበደ እና የክልሉ ልዑካን ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃና የክፍለ ጦሩ ሜካናይዝድ በጋራ በመሆን ህዳር 1/2018 ዓ.ም ከጧቱ 2:30 እስከ ረፋዱ 3:30 ድረስ በወሰዱት እርምጃ ነው::

ጥቃቱ የክልሉ ፕሬዝዳንት ነኝ የሚሉት አረጋ ከበደ እና ግብረ አበሮቹ ከባህርዳር ኤርፖርት በመነሳት ላሊበላ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ወደ ላሊበላ ከተማ በማቅናት ላይ እያሉ ሹምሽሃ አየር ማረፊያ አጠገብ ልዩ ስሙ በርታ በተባለ ቦታ ድንገተኛና የተጠና ልዩ የሽምቅ ኦፕሬሽን ነው::

በዚህም ሎሌዎቹ አቶ አረጋ ከበደና ግብረአበሮቹ ከአምላካቸው አብይ አህመድ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ሳይፈፅሙ በከባድ ፍርሃትና ድንጋጤ ውስጥ ሆነው ወደ ባህርዳር ተመልሰዋል:: በጥቃቱ ከአስር በላይ ቀይ ቦኔት ለባሽ አጃቢዎቻቸው የተደመሰሱ ሲሆን የተወሰኑ ቁስለኞችም ነበሩ::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 2/2018 ዓ.ም
5💔1
የአገዛዙ ብልፅግና ገመና ተጋለጠ!!!!

በጎንደር ቋራ ወስድኩት ባለዉ የድሮን ጥቃት የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አመራሮችን ገደልኩኝ በሚል በልሳናቱ በኩል ማስራጨቱ ይታወሳል።

ተገደሉ፣ተደመሰሱ የተባሉት የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አመራሮች ሰራዊቱን እየመሩ፣እያደራጁ በስራ ላይ መገኘታቸዉ እና መታየታቸዉ የአገዛዙን ገመና አጋልጠዋል።

ተገደሉ በሚል በወቅቱ ዜና ያሰራጩት የአገዛዙ ልሳናት ጀግኖቹን የቲዎድሮስ ልጆች በጀግንነት ስራቸዉን እየከወኑ ሲመለከቱ የሚደበቁበት መጋረጃ፣የሚገቡበት ጉድጓድ አተዋል።

በዝርዝር እንመለስበታለን!!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
👍71
የተለያዩ ሀገራት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል አርሲ ለተጨፈጨፉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ድምፃቸዉን አሰሙ!!

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን በአገዛዙ ብልፅግና መንግስት በኩል በተጠና መልኩ በጀምላ ለተጨፈጨፉ የኦርቶዶክስ ተዎህዶ እምነት ተከታዮች  የኔፕል ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች፣የአርመኑ ፓትርያርክ እና የሀገሪቱ የኦሮቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና የሌሎችም ሀገራት የእምነቱ ተከታዮች ድምፃቸዉን አሰምተዋል።

በአርሲ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ ተዎህዶ እና የአማራ ብሄር ተዎላጆች በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል ።

የሀገሪቱ ምስለኔ አገዛዝ ብልፅግና ጨፍጨፋዉን ለማስተባበል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወደ ስፍረዉ ቢልክም ተቋሙ ከጨፍጫፊዎቹ በባሰ መልኩ መላ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን ያሳዘነ መግለጫ አዉጥቷል።

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጫ እንደ ተጨማሪ ጥቃት ሊወሰድ የሚችል ነው ተብሏል!!

ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ አርሲ ዞን “በጥቅምት ወር ብቻ ከ25 በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

ይሁን እንጂ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን የተፈፀመው ጥቃት "ሃይማኖት እና ዘር ሳይለይ የተፈፀመ ነዉ ማለቱ ተቋሙ በጉዳዩ ላይ እጁን ሳያስገባ እንዳልቀረ ተነግሯል።

አጣሪ ኮሚቴው በምስራቅ አርሲ"በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የሰዎች መገደል፣ መታጋት እና የንብረት ውድመት መከሰቱን ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ጉዳት ከደረሰባቸው ወገኖች መረጃ ማግኘቱን" የገለፀ ቢሆንም መረጃዉ የተሰበሰዉ ግን ጉዳቱ ከደረሰባቸዉ ሰዎች እንዳልሆነ ግሎባል ፋኖ ሚዲያ ከቦታዉ ማረጋገጥ ችሏል።

ተቋሙ "የተገደሉት ሰዎች እንዲሁም የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ያጋጠማቸው ዜጎች የአንድ የሃይማኖት ተከታይ እና አገልጋዮች አለመሆናቸውን" ጠቅሶ፤ "ሃይማኖት እና ዘር ሳይለይ ግድያና ጥቃት እንደተፈጸመ ቢገልፅም ከሙቱት ዉስጥ ስንት የኦርቶዶክስ፣ስንት የእስልምና እንዲሁም ስንት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እንደተገደሉ በአሀዝ ደረጃ አላስቀመጠም።ይህ ደግሞ ተቋሙ ያቀረበዉ መረጃ ዉሸት መሆኑን እና ጉዳቱ ከደረሰባቸዉ ሰዎች ጋር እንዳልተገናኘም ከጥቃቱ ያመለጡ እና የተጎጂ ቤተሰቦች ለጣቢያችን ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የተፈጠረውን ችግር እንዲያጣራ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ተውካዮችን ያካተተ አንድ ግብረ ኃይል አቋቁሞ ችግር ወደ ተከሰተባቸው ወረዳዎች ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ/ም ማሰማራቱን የሚታወስ ቢሆንም ተመርጠዉ ወደ ቦታዉ ያቀኑት ተወካዮች ግን በብልፅግናዉ አገዛዝ የፖለቲካ ዉክልና ያላቸዉ እና በጥቃቱ እጃቸዉ ያለባቸዉ እንዲሁም ለሆዳቸዉ ያደሩ መሆናቸዉ ተረጋግጧል።

በተጨማሪም በአርሲ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ቢገደሉም ተቋሙ ግን 25 ብቻ ናቸዉ የተገደሉት ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል።

ጥቃቱ አሁንም ያላባራ ሲሆን በትናንትነዉ ዕለት በምስራቅ አርሲ ዞን የ10 ዓመት ህጻንን ጨምሮ 3 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸዉ ሌላ ተኩሳትን ፈጥሯል።

ትናንት ህዳር 01 -2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን፡ አሰኮ ወረዳ በጡሌ ቢዮ ቀበሌ፤ ጠለታ አከባቢ በአውድማ ላይ እህል እየወቁ ያሉ 3 የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች በጥይት ተደብድበው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደልዋል።

የ10 ዓመት ህጻን የሆነውን ጻድቃኔ ሠራዊት ጨምሮ ጥላሁን ቦጌ እና ኢዮብ እጅግ የተባሉ ምዕመናንን የግድያው ሰለባ መሆናቸውን ከአከባቢው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

ምን እንደምናደርግ ግራ ገብቶናል። ለማን አቤት ይባል ? ማንንስ እንክሰስ ፤ማንስ መፍትሄ ይስጠን፤ማንስ ያስጠልለን ?ብለዉ የጮሁ እነዚህ ምስኪን ወገኖቻችን በኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኩል የተሰረዉ የሀሰት ትርክት ዳግም ከሀዘን ላይ ሀዘን ደርቦብናል ሲሉ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ጥቃቱ በካቶሊክ ማህበረሰብ ላይም ያነጣጠረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ድርጊቱን በጽኑ አውግዟል።
ጉባኤው ባወጣው መግለጫ፣ "በምዕራብ ሐረርጌ በቅድስት ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ካቶሊኮች መሞታቸውንና ንብረት መቃጠሉን" በመጥቀስ፣ ይህ "ኢሰብዓዊ ድርጊት" መሆኑን ገልጿል። ጳጳሳቱ መንግስት "የዜጎችን ሰላምና ደህንነት እንዲያስከብር" እና አስፈላጊውን ህግ የማስከበር ስራ እንዲሰራ አሳስበዋል።

ለጥቃቶቹ ተጠያቂነትን በተመለከተ የተለያዩ አካላት የተጠቀሱ ሲሆን፣ "የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA)" በተወሰኑ ጥቃቶች እጁ እንዳለበት አንዳንዶች ቢጠቅሱም፣ የቀድሞው የቡድኑ የፖለቲካ ክንፍ በበኩሉ "በሲቪሎች ላይ ለሚደርሰው ግፍ" መንግስትን ተጠያቂ አድርጓል። ይሁን እንጂ በሀረርጌ የተፈፀመዉ ጥቃት በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች መሆኑን ከጥቃቱ የተረፉ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ተናግረዋል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
የፋኖ ድምፅ!!!
4
የድል ብስራት ዜና አድራሹ : የጋራ ቤት ቀያሹ : የነሃብቴ ወንድም : መልከመልካም ገራገርና ጨዋታ አዋቂው : ደግሞ ቆፍጣና ፊታውራሪ #አርበኛ_ዮሐንስ_ንጉሡ የበላይ እዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ

አገዛዙ : የውሸት ፋብሪካው የአብይ አህመድ ጦር ገደልኩ ሲል ጭራሽ በግርማሞገስ ኩም አድርጎ ተከስቷል

ባለህበት በድላድራጊነት ወደፊት ትገሰግስ ዘንድ ተመኝተናል
የአርበኛ ጌትነት መሳፍንትን መስዋዕትነት አስመልክቶ ከአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ  የተላለፈ  መልዕክት!

አርበኝነት በደም የሚወረስ የታሪክ ስንቃችን ነው። አርበኝነት ፈሪዎች የማይደርሱበት የጎበዞች መንበር ነው። አርበኝነት ከራስ በላይ ለአገርና ለህዝብ፤ ለታራክና ማንነት የሚዋደቁ የተመረጡ ዋጋ የሚከፍሉበት ህያው የታሪክ ገፃችን ነው።

እኛ አማራ ነን ስንል። ከአገር ሰሪው ታላቁ የአማራ ህዝብ አብራክ ስለወጣን ብቻ ሳይሆን እነዚያ ጥቁር ሰው መሆኑን በክንዳቸው ለዓለም ያስተማሩት አርበኞች የግብር ልጆች መሆናችንን በተግባር በማሳየት ነው።

አርበኝነት የትውልድ ቅብብል ውጤት ነው ስንል በእኛ ዘመን ከፊት ምሳሌ የምናደርገው የትግል አባታችን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ነው።

አባታችን የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን አደራ በብረት ትግል ከተቀበሉ ቀዳሚ አርበኞች አንዱ ናቸው።

የአማራ ህዝብ የተቃጣበትን መዋቅራዊ ጥቃት ለመመከት የሀሳብ ትግል ያደረጉት፣ አንቂያችን አደራጃችን ፕሮፌሰር አሥራት የትግል ራዕያቸው በዘመናቸው ባይሳካም። ከሀሳብ ትግል ወደ ነፍጥ ትግል የገባው አማራ የፕሮፌሰር አሥራትን አደራ በመቀበል ነው።

ታላቁ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ በአማራዊ ብሄርተኝነት፣ "አማራ ነኝ" ብለው ቀድመው ነፍጥ ካነሱት አንዱና ቀዳሚው ናቸው።

ከ 30 ዓመታት በላይ አማራ ነኝ ብለው በመታገል ለኛ ትውልድ የሞራልም የተግባር መምህር ሆነውናል።

በዚህ ሳይወሰኑ መላ ቤተሰባቸውን በአማራ የኀልውና ትግል ላይ አሰልፈው፣ ታሪክ በወርቃማ ቀለም የሚፅፈው ገድል እየሰሩ ነው።

የአማራ ህዝብን የታሪክ እጥፋት በሚወስነው በዚህ የትግል ታሪክ መላ ቤተሰቡ በትግል ሜዳ ተሰልፎ በሚከፍለው ዋጋ፣ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት መስዋዕት መሆኑን የሰማሁት በከባድ ሐዘን ነው።

ለኛ ለታጋዮች ሞት ለአማራ ህዝብ ህልውና መረጋገጥ  የምንከፈለው የመጨረሻው ስጦታችን ቢሆንም፣ አርበኛ ጌትነት ዕድሜው ለትግል ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ያለእረፍት ከአባቱ ጎን ተሰልፎ የከፈለው ዋጋና ከዚህም በላይ የሚጠበቅበት ታጋይ መሆኑን ስናስብ ህልፈቱ ከባድ ሐዘን ፈጥሮብናል።


ቢሆንም በዚህ መራር ዋጋ እየተከፈለበት ባለ ትግል የ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት እና ሌሎች ሰማዕታት የትግል አደራ ከግብ ለማድረስ የትግል ቃል ኪዳናችንን እናድሳለን።

ትግላችን እስከቀራኒዮ ነውና በእኛ መስዋዕትነት ታላቁን የአማራ ህዝብ ለዘላቂ ድል  እናበቃዋለን።


በመጨረሻም ለድርጅታችን አፋብኃ የበላይ ጠባቂ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ፣ ቤተሰቦቹ፣ እና መላው የትግል ጓዶቹ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል  አሳምነው  ዕዝ ሰብሳቢ አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ

ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም
2