ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አማራነትን እንደ ወንጀል በቆጠረው የብልፅግና አገዛዝ ተይዘው ከሁለት ዓመታት በላይ በእስር ላይ የነበሩ የግፍ እስረኞች ከ13 ዓመት እስከ 23 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው!

የስርዓቱ አሻንጉሊት በመባል የሚታወቁት ፍርድ ቤቶች፡ እስረኞቹን ተደጋጋሚ የሆነ ፍትሕ አልባ ቀጠሮ በመስጠት ከሁለት ዓመታት በላይ ካመላለሷቸው በኋላ ነው ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም ባዋሉት ችሎት ብይኑን ያስተላለፉባቸው።

በምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉቴ ከተማ እና በሌሎች የዞኑ አከባቢዎች በአማራነታቸው ምክኒያት ለእስር ተዳርገው ነቀምት በሚገኘው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው ለዓመታት ሲከራከሩ የቆዩት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 13 ዓመት ከስድስት ወር እስከ 23 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት እንደተፈረደባቸው ታውቋል።

ከፍርደኞቹ መካከል የተወሰኑት በምርመራ ወቅት በተፈፀመባቸው ድብደባ የተነሳ ለከባድ የአካል ጉዳት መጋለጣቸውን ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት ለማረጋገጥ ችሏል።

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም ባዋለው ችሎት በሙሉቀን አንተነህ የክስ መዝገብ ስር ከሚገኙ ሦስት ንዑስ የክስ መዝገቦች መካከል አንዱ በሆነው በሰለሞን አሰፋ ክስ መዝገብ ተከሰው በእስር ላይ ሆነው ሲከራከሩ በቆዩ የአማራ ተወላጆ ላይ ፍርደ ገምድል የሆነ ብይን አስተላልፎባቸዋል።

በክስ መዝገቡ ከተከሰሱ 31 የአማራ ተወላጅ ተከሳሾች መካከል፡ 14ቱ ከሁለት ዓመታት በፊት ለእስር ከተዳረጉ በኋላ የዋስትና መብት ተነፍገው በማረሚያ ቤት የድብደባ መዓትና አይነት ሲፈፀምባቸው የቆዩ መሆናቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በችሎቱ፡ ከተከሳሾቹ መካከል 17ቱ በሌሉበት የእስር ፍርድ የተላለፈባቸው ሲሆን፡ ለእስር ከተዳረጉት 14 የአማራ ተወላጆች መካከል ሁለቱ በማረሚያ ቤት እንዳሉ በደረሰባቸው ድብደባ ምክኒያት ሕይወታቸው አልፏል፡ አንዱ ከመያዙ በፊት ከፀጥታ አካላት ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ ቆስሎ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ አልፏል ተብሎ ብይን ሳይተላለፍባቸው ቀርቷል።

በተጨማሪም በምርመራ ወቅት በተፈፀመባቸው ቶርች ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል የሚጠቀሱት ሦስቱ ተከሳሾች በነፃ የተሰናበቱ ሲሆን፡ ችሎቱ በስምንት ተከሳሾች ላይ 13 ዓመት ከስድስት ወር እስከ 23 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።

በዚህም፦
1ኛ፦ እሸቱ ከበደ 23 ዓመት
2ኛ፦ አበባው አድማሱ 23 ዓመት
3ኛ፦ ጌታቸው ሽፈራው 23 ዓመት
4ኛ፦ ሰለሞን አሰፋ 22 ዓመት
5ኛ፦ ጀማል ሲራጅ 14 ዓመት
6ኛ፦ አህመድ አያሌው 13 ዓመት ከ6 ወር
7ኛ፦ እንድሪስ ሀሰን 13 ዓመት ከ6 ወር
8ኛ፦ ስንታየሁ አዲስ 13 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል ነው ያሉት መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የግፍ ፍርደኞቹ ቤተሰቦች።

በችሎቱ የአማራ ተወላጅ እስረኞች ምንም አይነት መከላከያ እንዳያቀርቡ ታግደው ነበር የሚሉት ጣቢያችን ያነጋገራቸው የግፍ ፍርደኞቹ ቤተሰቦች፡ ከዚህ ቀደም በነበረው የክርክር ሂደት ላይም ፍርድ ቤቱ፡ የአገዛዙ ጠበቆች ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጋር እየተመሳጠሩ የሚያቀርቡትን ሀሰተኛ ማስረጃ ብቻ ነው ሲቀበል የቆየው ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል በርካታ የአማራ ተወላጆች አማራነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ በገፍ ታስረው በሚፈፀምባቸው ድብድባ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ሕይወታቸው ያልፋል።

በርካቶችም በተለይ የምስራቅ ወለጋ ዞን መቀመጫ በሆነችው ነቀምቴ ከተማ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን መቀመጫ በሆነችው ሻምቡ ከተማ ውስጥ ከሁለት ዓመታት በላይ ታስረው የሚገኙ ሲሆን፡ ከእስረኞቹ መካከል በምርመራ ወቅት በሚፈፀምባቸው ቶርች ጆሯቸው መስማት፣ አይናቸው ማየት እንዳቆመና ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስም እንደማይችሉ የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።
💔2
⚫️#አሳዛኝ_ዜና‼️
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ ከ10 በላይ ንፁሀን አርሶ አደሮች በጡት ቆራጩ  የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሀይል ስራ ላይ እንዳሉ በወጡበት ተገድለዋል ።

አርሶ አደሮቹ  የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የሚንቀሳቀስበት ቀጠና ነዋሪ ሲሆኑ በዚህ አካባቢ የጀግኖች ፋኖዎቻችን  ምትና ሀይል በተደጋጋሚ መቋቋም ያቃተው ሆድ አደሩ የብልፅግና ሰራዊት ዛሬም የበቀል በትሩን  እንደተለመደው ንፁሀን ላይ በማሳረፍ  የደረሰ ሰብልላቸውን በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አርሶአደሮችን በጥይት ገድሏቸዋል ።

ይህ አማራ ጠል የሆነው የብልፅግና መንግስት ተብየው በቀጠናው ምንም ጦርነት ባልነበረበት ሰዓት ሆን ብሎ አልሞና አቅዶ አርሶአደሮችን በመግደል ዛሬም አማራን ከምድረ ገፅ የማጥፋት ስራውን ቀጥሎበታል።

ከተገደሉት ንፁሀን አርሶ አደሮች መካከል ጥቂቶቹ
1; አቶ ሞላ ደርብ ዕድሜ 56 ቀበሌ ሚጦ
2;  አቶ ይርዳው ዘመነ ዕድሜ 28 ቀበሌ ሚጦ
3; ወጣት እያያለም ውዱ ዕድሜ 16 ቀበሌ ሚጦ
4; አስማረ በላይ ዕድሜ 38 ቀበሌ ጭልፋ ወንዝ
5; አለምነህ ቀኔ ዕድሜ 60 ቀበሌ ጭልፋ ወንዝ
6; ድረስ ፀሐይ ዕድሜ 62 ቀበሌ ጭልፋ ወንዝ
7; መልካሙ አለሙ  ቁስለኛ ጭልፋ ወንዝ
8; ታደሰ ይግዛው ቁስለኛ ቀበሌ ሚጦ
9; አዋጅ በላይ ቁስለኛ ቀበሌ ሚጦ ሲሆኑ  እንዲሁም  ወ/ሮ ካሳየ ያለው የተባለች እናታችን ሳንቃ ጥቅም ቀበሌ የፋኖ አገርነው እናት ሰባት ልጆችን ያለ አባት ስታሳድግበት የነበረው ቤቷ  ሙሉ በሙሉ በእሳት እንዲወድም በማድረግ ከእነ ልጆቿ ሜዳ ላይ እንድትወድቅ አድርገዋል።
በአጠቃላይ በዚህ ጭፍጨፋ በርካታ የቁም እንስሳትን በመግደል እና ንብረታቸውን ሽጠው የገዙትን የጦር መሳሪያ ጭምር በመቀማት  አርሶአሮችን ለከፍተኛ የሆነ ሰባዊ፣ ቁሳዊና ስነ- ልቦናዊ ጉዳት አድርሶባቸዋል ።

ስለሆነም የሰባዊ መብት ተሟጋች ቦታው ድረስ በአካል በመገኘት ጉዳዩን አጣርተው ለአለማቀፋ ማህበረሰብና መንግስታት ይህ አምባገነን የሆነው የአገዛዙ ስርዓት በእየ ጊዜው ምን ያህል የገዛ ዜጎቹን እየፈጀ እንደሆነ እንዲያውቁልንና እንዲያሳውቁልን ጥሪ እናቀርባለን።

ለሟቾች ነብሳቸውን በአፀደ ገነት እንዲያሳርፍልን  ቤተሰቦች ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን ።

  ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!!
©አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
💔4
የአርበኛ ጌትነት መሳፍንትን መስዋዕትነት አስመልክቶ ከዋርካው ምሬ ወዳጆ የተላለፈ መልዕክት!

ዘመናትን ተሻግሮ የመጣውን የአማራ ህዝብ ግፍና በደል ለማስቆም ህዝቡንና መላ ቤተሰቡን አስተባብሮ ሲታገል የኖረው የትግል አባታችን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ዛሬም የዘመናት ግፉ ወደ ዘር ማጥፋት አድጎ የህልውና አደጋ ውስጥ የገባውን የአማራ ህዝብ ለመታደግ እየተደረገ ባለው ተጋድሎ ከባድ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል::

በዚህ መራር ዋጋ እየተከፈለበት ባለ ትግል ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ አጅሬ የተሰኘች ታዳጊ ከተማ የሰሜን አምባራስ ክፍለጦር አዛዥና የራስ አሞራው 3ኛ ኮር አስተዳደር ሃላፊ የሆነው አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉ መስዋዕትነት የከፈለ ሲሆን በዚህም ከባድ ሃዘን እንደተሰማኝ ለመግለፅ እወዳለሁ::

ትግላችን እስከቀራኒዮና አባታችን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ እስከ ቤተሰብዎ ለአማራ ሕዝብ በደማቅ የደም ቀለም እየተጻፈ ነውና ትውልድ በጀግንነትና ለአማራ ሕዝብ የተከፈለ እውነተኛ አማራነት ነውና ለእሱ በግሌ አመሰግናለሁ ማለት እወዳለሁ። ይህ መስዋዕትነት የአንድ ጀግና መስዋዕትነት ብቻ ሳይሆን ለአማራነት ዋጋ መክፈል ምን ማለት እንደሆነ በሕይወት እያሉ ህያው ምስክር ነዎት!

የአማራ ፋኖ የጀመረውን የህልውና ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል፣ የወንድማችን አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉና በአውደ ውጊያ በወደቁ ጀግኖቻችን ዘመቻ አውጀን የአብይ አህመድን አገዛዝ ድባቅ እንደምንመታው ወደ ድልና ነጻነትም እንደምንሸጋገር ከምስራቅ አማራ ቀጠና ሁኜ ይሄን መልዕክት ሳስተላልፍ በታላቅ ቁርጠኝነትና ቁጭት ሁኜ መሆኔን መግለጽ እፈልጋለሁ።

በመጨረሻም ለአርበኛ መሳፍንት ተስፉ፣ ቤተሰቦቹ፣ እና መላው የትግል ጓዶቹ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል እና የምኒልክ ዕዝ ሰብሳቢ ዋርካው ምሬ ወዳጆ
3💔1
ህዳር 1/2018 ዓ.ም ላሊበላ የተከሰተው ምንድን ነው?

ሎሌው አረጋ ከበደና ስብስቡ በላሊበላ በተፈፀመባቸው ያልጠበቁት ከባድ ጥቃት ያሰቡትን ሳያሳኩ ወደ ምሽጋቸው ባህርዳር ተመልሰዋል::

ከኦሮሚያ ብልፅግና ጋር በመተባበር የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው አረጋ ከበደና ስብስቡ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ያለው አለቃቸው አብይ አህመድ የሰጣቸውን ተልዕኮ ይዘው ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ የተጓዙ ሲሆን ትናትና ህዳር 1/2018 ዓ.ም ረፋድ ላሊበላ አየር መንገድ ከደረሰ በኋላ ጥቃት ተፈፅሞበታል::

አቶ አረጋ ከበደ እና የክልሉ ልዑካን ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃና የክፍለ ጦሩ ሜካናይዝድ በጋራ በመሆን ህዳር 1/2018 ዓ.ም ከጧቱ 2:30 እስከ ረፋዱ 3:30 ድረስ በወሰዱት እርምጃ ነው::

ጥቃቱ የክልሉ ፕሬዝዳንት ነኝ የሚሉት አረጋ ከበደ እና ግብረ አበሮቹ ከባህርዳር ኤርፖርት በመነሳት ላሊበላ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ወደ ላሊበላ ከተማ በማቅናት ላይ እያሉ ሹምሽሃ አየር ማረፊያ አጠገብ ልዩ ስሙ በርታ በተባለ ቦታ ድንገተኛና የተጠና ልዩ የሽምቅ ኦፕሬሽን ነው::

በዚህም ሎሌዎቹ አቶ አረጋ ከበደና ግብረአበሮቹ ከአምላካቸው አብይ አህመድ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ሳይፈፅሙ በከባድ ፍርሃትና ድንጋጤ ውስጥ ሆነው ወደ ባህርዳር ተመልሰዋል:: በጥቃቱ ከአስር በላይ ቀይ ቦኔት ለባሽ አጃቢዎቻቸው የተደመሰሱ ሲሆን የተወሰኑ ቁስለኞችም ነበሩ::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 2/2018 ዓ.ም
5💔1
የአገዛዙ ብልፅግና ገመና ተጋለጠ!!!!

በጎንደር ቋራ ወስድኩት ባለዉ የድሮን ጥቃት የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አመራሮችን ገደልኩኝ በሚል በልሳናቱ በኩል ማስራጨቱ ይታወሳል።

ተገደሉ፣ተደመሰሱ የተባሉት የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አመራሮች ሰራዊቱን እየመሩ፣እያደራጁ በስራ ላይ መገኘታቸዉ እና መታየታቸዉ የአገዛዙን ገመና አጋልጠዋል።

ተገደሉ በሚል በወቅቱ ዜና ያሰራጩት የአገዛዙ ልሳናት ጀግኖቹን የቲዎድሮስ ልጆች በጀግንነት ስራቸዉን እየከወኑ ሲመለከቱ የሚደበቁበት መጋረጃ፣የሚገቡበት ጉድጓድ አተዋል።

በዝርዝር እንመለስበታለን!!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
👍71
የተለያዩ ሀገራት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል አርሲ ለተጨፈጨፉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ድምፃቸዉን አሰሙ!!

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን በአገዛዙ ብልፅግና መንግስት በኩል በተጠና መልኩ በጀምላ ለተጨፈጨፉ የኦርቶዶክስ ተዎህዶ እምነት ተከታዮች  የኔፕል ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች፣የአርመኑ ፓትርያርክ እና የሀገሪቱ የኦሮቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና የሌሎችም ሀገራት የእምነቱ ተከታዮች ድምፃቸዉን አሰምተዋል።

በአርሲ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ ተዎህዶ እና የአማራ ብሄር ተዎላጆች በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል ።

የሀገሪቱ ምስለኔ አገዛዝ ብልፅግና ጨፍጨፋዉን ለማስተባበል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወደ ስፍረዉ ቢልክም ተቋሙ ከጨፍጫፊዎቹ በባሰ መልኩ መላ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን ያሳዘነ መግለጫ አዉጥቷል።

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጫ እንደ ተጨማሪ ጥቃት ሊወሰድ የሚችል ነው ተብሏል!!

ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ አርሲ ዞን “በጥቅምት ወር ብቻ ከ25 በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

ይሁን እንጂ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን የተፈፀመው ጥቃት "ሃይማኖት እና ዘር ሳይለይ የተፈፀመ ነዉ ማለቱ ተቋሙ በጉዳዩ ላይ እጁን ሳያስገባ እንዳልቀረ ተነግሯል።

አጣሪ ኮሚቴው በምስራቅ አርሲ"በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የሰዎች መገደል፣ መታጋት እና የንብረት ውድመት መከሰቱን ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ጉዳት ከደረሰባቸው ወገኖች መረጃ ማግኘቱን" የገለፀ ቢሆንም መረጃዉ የተሰበሰዉ ግን ጉዳቱ ከደረሰባቸዉ ሰዎች እንዳልሆነ ግሎባል ፋኖ ሚዲያ ከቦታዉ ማረጋገጥ ችሏል።

ተቋሙ "የተገደሉት ሰዎች እንዲሁም የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ያጋጠማቸው ዜጎች የአንድ የሃይማኖት ተከታይ እና አገልጋዮች አለመሆናቸውን" ጠቅሶ፤ "ሃይማኖት እና ዘር ሳይለይ ግድያና ጥቃት እንደተፈጸመ ቢገልፅም ከሙቱት ዉስጥ ስንት የኦርቶዶክስ፣ስንት የእስልምና እንዲሁም ስንት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እንደተገደሉ በአሀዝ ደረጃ አላስቀመጠም።ይህ ደግሞ ተቋሙ ያቀረበዉ መረጃ ዉሸት መሆኑን እና ጉዳቱ ከደረሰባቸዉ ሰዎች ጋር እንዳልተገናኘም ከጥቃቱ ያመለጡ እና የተጎጂ ቤተሰቦች ለጣቢያችን ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የተፈጠረውን ችግር እንዲያጣራ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ተውካዮችን ያካተተ አንድ ግብረ ኃይል አቋቁሞ ችግር ወደ ተከሰተባቸው ወረዳዎች ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ/ም ማሰማራቱን የሚታወስ ቢሆንም ተመርጠዉ ወደ ቦታዉ ያቀኑት ተወካዮች ግን በብልፅግናዉ አገዛዝ የፖለቲካ ዉክልና ያላቸዉ እና በጥቃቱ እጃቸዉ ያለባቸዉ እንዲሁም ለሆዳቸዉ ያደሩ መሆናቸዉ ተረጋግጧል።

በተጨማሪም በአርሲ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ቢገደሉም ተቋሙ ግን 25 ብቻ ናቸዉ የተገደሉት ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል።

ጥቃቱ አሁንም ያላባራ ሲሆን በትናንትነዉ ዕለት በምስራቅ አርሲ ዞን የ10 ዓመት ህጻንን ጨምሮ 3 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸዉ ሌላ ተኩሳትን ፈጥሯል።

ትናንት ህዳር 01 -2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን፡ አሰኮ ወረዳ በጡሌ ቢዮ ቀበሌ፤ ጠለታ አከባቢ በአውድማ ላይ እህል እየወቁ ያሉ 3 የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች በጥይት ተደብድበው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደልዋል።

የ10 ዓመት ህጻን የሆነውን ጻድቃኔ ሠራዊት ጨምሮ ጥላሁን ቦጌ እና ኢዮብ እጅግ የተባሉ ምዕመናንን የግድያው ሰለባ መሆናቸውን ከአከባቢው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

ምን እንደምናደርግ ግራ ገብቶናል። ለማን አቤት ይባል ? ማንንስ እንክሰስ ፤ማንስ መፍትሄ ይስጠን፤ማንስ ያስጠልለን ?ብለዉ የጮሁ እነዚህ ምስኪን ወገኖቻችን በኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኩል የተሰረዉ የሀሰት ትርክት ዳግም ከሀዘን ላይ ሀዘን ደርቦብናል ሲሉ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ጥቃቱ በካቶሊክ ማህበረሰብ ላይም ያነጣጠረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ድርጊቱን በጽኑ አውግዟል።
ጉባኤው ባወጣው መግለጫ፣ "በምዕራብ ሐረርጌ በቅድስት ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ካቶሊኮች መሞታቸውንና ንብረት መቃጠሉን" በመጥቀስ፣ ይህ "ኢሰብዓዊ ድርጊት" መሆኑን ገልጿል። ጳጳሳቱ መንግስት "የዜጎችን ሰላምና ደህንነት እንዲያስከብር" እና አስፈላጊውን ህግ የማስከበር ስራ እንዲሰራ አሳስበዋል።

ለጥቃቶቹ ተጠያቂነትን በተመለከተ የተለያዩ አካላት የተጠቀሱ ሲሆን፣ "የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA)" በተወሰኑ ጥቃቶች እጁ እንዳለበት አንዳንዶች ቢጠቅሱም፣ የቀድሞው የቡድኑ የፖለቲካ ክንፍ በበኩሉ "በሲቪሎች ላይ ለሚደርሰው ግፍ" መንግስትን ተጠያቂ አድርጓል። ይሁን እንጂ በሀረርጌ የተፈፀመዉ ጥቃት በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች መሆኑን ከጥቃቱ የተረፉ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ተናግረዋል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
የፋኖ ድምፅ!!!
4