ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከመካነሰላም ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አባይ በር መቅደላ ከተማ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም በፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት በግፍ የተረሸኑ ወጣቶች!
ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ላይ ከባድ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል ተጎናፀፉ::

ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ ከመርጦ ወደ ወልድያ ከተማ ይጓዝ የነበረ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ አማየ ሚጫ በሚባል ቀጠና ደፈጣ በመያዝ በፈፀሙበት ጥቅት ኦራል ላይ የነበረውን ሙሉ ለሙሉ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በእግር ይጓዝ የነበረውን ከሙትና ቁስለኛ የተረፈውን ብትንትኑን በማውጣት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል::

በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ላይ የሚወሰደው እርምጃ በደፈጣ ጥቃት ረፍት በመንስስትና በማዋከብ እንዲማረር በማድረግ ሲያመች በመደበኛ ውጊያ በመደምሰስና በመማረክ ብሎም በማስኮብለል አገዛዙን የማፈራረሱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 1/2018 ዓ.ም
2🙏1
#የዘር_ማጽዳት_ጭፍጨፋው_ዛሬም_እንደቀጠለ_ነው!

ዛሬ ኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ምሥራቅ አርሲ፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠለታ ቅዱስ ገብርኤል በተባለ  አካባቢ ከጠዋቱ 3:00 ገደማ ሦስት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች (ኹለት ወንዶችና አንድ ሴት) በአውድማ ሥራ ላይ እህል እየወቁ ባሉበት በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። በርካቶች ታፍነው ተወስደዋል።

ከሰሞኑ ተቋቋመ የተባለው "አጣሪ ቡድን" ዛሬ ባወጣው መግለጫ በሃማኖታቸው ተመርጠው ዘር ማጽዳት/Genocide/ የሚፈጸምባቸውን አስተባብሎ ማውጣቱ እጅግ ያሳዘነን ተግባር ነው። ፓርቲያችን አኹንም ገለልተኛ ዓለም አቀፍ አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም በጥብቅ ያሳስባል።

እናት ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል በተለይ በአርሲ የሚፈጸምን ዘር ማጽዳትና ተደጋጋሚ ጭፍጨፋ በጽኑ ያወግዛል። በሃይማኖታቸው ተመርጠው እንደሞቱ ሲካዱ ገዳይን ማበረታታት በመኾኑ ይኽን ዓይነቱን እውነቱን የካደ አካሄድ ፈጽመን እናወግዛለን። ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሕዝብ በአንድነት ቆሞ ካልደረሰላቸው ለዘር እንደማይተርፉ ግልጽ እየኾነ መጥቷል። ፓርቲያችን ለሟቾችም እረፍተ ነፍስን ለአካባቢው ማኅበረሰብና ለወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ይመኛል።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ኅዳር ፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ. ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
👍2
ልጇን ያጣች እናት ወደ ፋኖ ገባች!!

የሴቷ አርበኛ ሳራ ትባላለች:: በምዕራብ ወሎ ግንባር ጃማ ወረዳ ደጎሎ ከተማ ውስጥ ነዋሪ ስትሆን ምግብ ቤት ከፍታ ቤተሰብ ስትመራ ኖራለች::

ፋኖ ሮቤል ካሳዬ የሚባለውን ልጇን የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት አስፋልት ላይ እየገተተ አሰቃይቶታል:: ነጋ ጠባ ልጇን ዘረኛው ሰራዊት ሲያሰቃይባት እና ከፍተኛ ድብደባ ፈጽሞበት ቁስለኛ አድርጎት በስተመጨረሻም 5 ወር ከ15 ቀን ጮሪሳ አስሮ የግፍ ግፍ ፈጽሞበት ሲያበቃ ለቆት ወደ ትውልዲ አካባቢው ከተመለሰ በኋላ ወደ ፋኖ ገብቶ ነበር:: በነገራችን

በዚያን ቅጽበት እስኪ ቢያንስ ቁስልህ ይዳን በማለት ዘመድ ወዳጅ ሲመክረው ከወላጅ እናቱ ጋር ስለውሳኔው በሚያወጋበት ወቅት እናቴ የልብ ቁስል ነው እንጅ የማይድነው ሰው የሚያየው የገላው ቁስልማ ቀላል ነው እንዳላት ታስታውሳለች:: ልቤ ቆስሏል ከእንግዲህ እነሱን እስከ ሞት ድረስ መዋጋት ነው ያለብኝ ብሏታል::

በዚህ ውሳኔው መሰረት በጃማ ግንባር የሚንቀሳቀሰውን የፋኖ ኃይል ተቀላቅሎ በፊታውራሪነት ታግሏል::

ፋኖ ሮቤል ሞትን የማይፈራ ጀግና ታጋይ እንደነበር ጓዶቹ ይመሰክራሉ::

ሞት አይፈሬው ፋኖ ሮቤል በጃማ ግንባር ማሞ ቆላ (ወደ ሸክፍ መሄጃው ላይ) በተደረገ ትንቅንቅ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ካደረሰ በኋላ አንድ ጥይት ስትቀረው ራሱን ማጥፋቱን ነው ለማረጋገጥ የቻልኩት::

እኔ ለእናንተ እጄን አልሰጥም ብሎ ራሱን አጠፋ ያሉት ጓዶቹ ፋኖ ሮቤል እጅግ በጣም ደፋር መሆኑን ነው የመሰከሩት::

በጣም ልቤን የነካኝ ነገር ቢኖር ፋኖ ሮቤል ለእናቱ ይህ ፎቶ ማልቀሻ ይሆንሻል ብሎ አሳጥቦ ግድግዳ ላይ መስቀሉን ሲነግሩኝ ነው:: ሞትን አልፈራም የወጣሁት ልሞት ነው ይል የነበረው ጀግናው ወንድማችን ወላጅ እናትን የደጎሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች ከማፅናናት ይልቅ ይሄኔ ልጅሽ የመንግስት ሚሊሻ ቢሆን ኖሮ በካሳ መልኩ ብር ታፍሽ ነበር ይሏት እንደነበርም ነው የሰማሁት:: እሷ ግን እንኳንም ለአማራ ህዝብ ጠላት ሆኖ ታሪኩን እና ታሪኬን ያላበላሸ እንጅ ልጄን በገንዘብ የምሸጥ ሆዳም አይደለሁም እንዳውም እኔም ለአማራ እሞታለሁ ብላ ጠብመንጃ ነከሰች::

አሁን ላይ የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር ፊታውራሪ ናት!!

በድል ይመልስሽ እህትዋ:: የወንድማችንንም ነፍስ ይማርልን!
🙏3👍1
ሰበር ዜና ‼️

በአዲስ አበባ ከለገጣፎ አቅራቢያ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ 12 የመከላከያ አባላት መገደላቸው ተሰማ! በመከላከያ ካምፕ ውስጥ በተነሳ የእርስ በእርስ ውጊያ የአገዛዙ ወታደሮች እርስ በእርስ ተጫርሰዋል ነው የተባለው!

በካምፕ ውስጥ በነበረው የእርስ በእርስ ውጊያ 12 ወታደሮች ሲገደሉ አንድ የቡናና ሻይ ቁርስቤት ሰራተኛም በተኩስ ልውውጥ መሀል መገደሏ ተነግሯል ! የእርስ በእርስ ውጊያው የተደረገው ዛሬ ከሰአት ሲሆን ወደ ወሎ ዛሬ ትሄዳላችሁ ተብለው የነበሩ የ94ኛ ክፍለጦር ወታደሮች በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት የኦሮሚያ ልዩሀይል እና ሚሊሻ ወደ ካምፑ በመግባት የመከላከያ ዩኒፎርም እየለበሱ ከነሱ ጋር መቀላቀል ሲጀምሩ ይሄ ለምን ይሆናል የመከላከያን ስም እያጎደፍን ነው ይህን አንቀበልም ያሉ ወታደሮች መረሸናቸውን ተከትሎ ሲሆን የሚሰራው ህገወጥ ስራ ሳያንስ ጓዶቻችንን እንዴት ትረሽናላችሁ በሚል የእርስ በእርስ ውጊያ የተደረገ ሲሆን ለ1 ሰአት እርስ በእርስ ተታኩሰዋል ነው የተባለው። በዚህም 12 ወታደር ሲሞት የቆሰሉም ብዙ ናቸው። ተኩሱን ለማስቆም ከፍተኛ ጀነራሎች ወደቦታው በፍጥነት የሄዱ ሲሆን ተኩሱን አረጋግተው አሁን ተቃውሞ ያስነሱትን ወደ ወታደራዊ እስርቤት እያጋዟቸው ነው ተብሏል !
🙏3👍1
💪ሰበር መረጃ💪

ከወልድያ በቅርብ ርቀት አማየ ሚጫ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት አንድ ኦራል ሙሉ የአገዛዙ ወታደር ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል!

ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ ከመርጦ ወደ ወልድያ ከተማ ይጓዝ የነበረ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ አማየ ሚጫ በሚባል ቀጠና ደፈጣ በመያዝ በፈፀሙበት ጥቅት ኦራል ላይ የነበረውን ሙሉ ለሙሉ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በእግር ይጓዝ የነበረውን ከሙትና ቁስለኛ የተረፈውን ብትንትኑን በማውጣት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል ሲል የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ላይ የሚወሰደው እርምጃ በደፈጣ ጥቃት ረፍት በመንስስትና በማዋከብ እንዲማረር በማድረግ ሲያመች በመደበኛ ውጊያ በመደምሰስና በመማረክ ብሎም በማስኮብለል አገዛዙን የማፈራረሱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያለው ዕዙ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለጣቢያችን በላከው መረጃ።
4🙏1
ምኒልክ ዕዝ የአደረጃጀት ዜና!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጁ እያሱ ኮር ራሱን እንደ ንስር ማንቆሪያውን እና ጥፍሩን አድሶ ላባውን ቀይሮ በአዲስ አደረጃጀት በአዲስ ስያሜ እና በአዲስ የድል መንፈስ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የአመራር ሪፎርም በማድረግ ብቅ ብሏል፡፡

ትግሉን እና ዘመኑን መዋጀት ለምናደርገው ረጅም እና ፈታኝ የትግል ጉዞ ትልቅ ስንቅ እና ጡንቻ እንደሚሆን ግልፅና የማይካድ ሃቅ ነው።

የልጅ እያሱ ኮር ከፍተኛ የኮር አመራርን ጨምሮ በውስጡ የሚገኙቱን

** ራንቦ ክፍለ ጦር
** ቤተ አማራ ክፍለ ጦር
** ራስ አሊ ክፍለ ጦር
** የጁ ክፍለ ጦር ከሻለቃ መሪ በላይ ያሉ አመራሮችን ትግል በሚፈልገው ደረጃ በጥልቀት በማወያየት እና በማገማገም ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት እና ለችግሮቹ የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ጉባዔውን አጠናቋል፡፡

ጉባዔው በታቀደው መሠረት ግለቱን ጠብቆ እንዲሄድ ከድርጅት በመጡ የወታደራዊ እና የፖለቲካ ክንፍ አመራሮች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡

በስፍራው በተገኙት የድርጅቱ የዘመቻ መምሪያ ሃላፊው አርበኛ በለጠ ሸጋውን (ተራራው) ን ጨምሮ የድርጅቱ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ እና ምክትል ሃላፊ የሆኑት አበበ ቀዮ እና አሰፋ መሰለ (አሳምነው) በተገኙበት ጉባዔ እጅግ ድንቅ እና ለቀጠናው አስተማሪ የሆነ ሪፎርም ለመስራት ተችሏል፡፡

በሪፎርሙ ከኮር አመራርን ጨምሮ የክፍለ ጦር አመራር ለውጥ ከማድረግ ጀምሮ አራቱን ነባር ክፍለ ጦሮች መጠሪያቸውን ስም ጭምር በመቀየር ሠራዊታቸውም አዲሱ አመራር በፈለገው ሂደት ተሰባጥሮ ወደ ሁሉት ግዙፍ ክፍለ ጦር እንዲታጠፉና መጠሪያ ስያሜያቸውም ወደ ቁጥር በመለወጥ የልጅ እያሱ ኮር 23ኛ እና 24ኛ ክፍለ ጦር እየተባሉ እንዲጠሩ ተወስኗል፡፡

በቀጠናው የመጀመሪያ የሆነውን እና ፈር ቀዳጅ የሆነውን የሠራዊት ውህደት እና የቁጥር ስያሜ ለሌሎችም አርአያ እንደሚሆን ታምኗል፡፡

በሪፎርሙ መሠረት የኮሩ ወታደራዊ ክንፍ ላይ ሠፊ ሪፎርም የተደረገ ሲሆን የቤተ አማራ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረው እንዳሻው ወታደራዊ አዛዥ ሆኖ ሲሾም የየጁ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረው ፶ አለቃ ሞላ አባተ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ በመሆን ኀላፊነታቸውን ተረክበዋል፡፡

አዲሱ መዋቀር

1 አርበኛ ሰለሞን አሊ ሰብሳቢ
2 አርበኛ እንዳሻ ጌታሁን ምክትል ሰብሳቢ እና ወታደራዊ አዛዥ
3 አርበኛ ሲሳይ አየለ (ሳተናው) ምክትል ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ኀላፊ
4 አርበኛ ፶ አለቃ ሞላ አባተ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ
5 አርበኛ ዳንኤል አስረስ አስተዳደር
6 አርበኛ ቦጋለ ሞሌ ምክትል አስተዳደር
7 አርበኛ ሽመልስ አወል ሎጅስቲክ
8 አርበኛ እርገት አያሌው ም/ሎጅስቲክ
9 አርበኛ ሱሃሊ ሸኩር ዘመቻ
10 አርበኛ ዳንኤል ዋጋው ህዝብ ግኑኝነት
11 አርበኛ መሃመድ ፈንታው ኦርድናንስ
12 አርበኛ አሰፋ አባተ የሰው ኀይል
13 አርበኛ ዮሃንስ ከልክሌ ፋይናንስ

በማድረግ ነባሩን እና አዲሱን አመራር በማጣመር ኮሩን በታላቅ ኀላፍነት ክብሩን እና ሞገሱን አሁን ካለው በላይ በማግዘፍ በጥበብ በማስተዋል እና በፍፁም አማራዊ ስነልቦና እንዲመሩ ቃለ መሃላ ጨምሮ አደራም ጭምር ተሰጥቷቸዋል፡፡

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 2/2018 ዓ.ም
🙏31
የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በሰከላ ወረዳ በንፁሀን እና በት/ት ተቋማትን ላይ የድሮን ጥቃት ፈፀመ!

የአገዛዙ አረመኔው ሰረዓት ህዳር 02/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት በሰከላ ወረዳ አጉት የመጀመሪያ ት/ቤትን በድሮን ጥቃት አንድ ንፁሀን ሴት ማቁሰሉን እና የአጉት ት/ቤትን ሙሉ በሙሉ ማውደሙ ተረጋግጦል።

በሁሉም ቦታ የምትገኙ የፋኖ ሀይሎች በሙሉ የአገዛዙ ሀይል ሽንፈቱ እየተቃረበ በመምጣቱ የሽንፈቱን ጥግ ንፁሀን በመጨፍጨፍ እና የት/ት ተቋማትን በድሮን እያወደመ ይገኛል።

በመሆኑም የዚህ አረመኔዊ አገዛዝ አፀያፊ ተግባሩ እንደቀጠለ ስለሆነ በሁሉም ቦታ የምትገኙ የፋኖ ሀይሎች እና የተከበረከው የአማራ ህዝብ ጥብቅ ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል።
💔3
ሁለት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዞ ጎንደሬ በጋሻዎችን ተቀላቀለ

የአማራ ክልል አድማ ብተና አባል የነበረው ዳዊት ሀብታሙ የተባለው ወጣት ሁለት ክላሽንኮቭ መሳሪያዎችን ይዞ በጀግንነት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል የሆነውን አፄ ፋሲለደስ ብርጌድ ተቀላቅሏል።

ዳዊት ሀብታሙ አዲስ ተመራቂ ሲሆን ከተመደበ ሁለት ሳምንት ሳይሞላው ከጠዳ ከተማ መገጭ ግድብ በለሊት ተነስቶ ዛሬ ህዳር 2/2018 ዓ/ም አማራ ህዝብ ላይ አልተኩስም በማለት የጓዱን መሳሪያ ጨምሮ በመያዝ ጎንደሬዎቹን በጀግንነት ተቀላቅሏል።

ወጣቱን የአድማ ብተና አባል የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ዘመቻ መሪ አርበኛ ሞላ ከፌ ፣ የገስጥና ይላቅ ሻለቃዎች አመራሮች በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።

ዳዊት ሀብታሙ "ወደ አድማ ብተና የገባውት መሳሪያ ለመታጠቅ ስለነበረ ሰልጥኘ አንድ ጥይት ህዝቤ ላይ ሳልተኩስ ምኖቴን ሁለት ክላሽ በማምጣት አሳክቻለሁ" ብሏል።

የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ዘመቻ መሪ አርበኛ ሞላ ከፌ የአድማ ብተና፣የመከላከያ፣ የሚኒሻ እና የፖሊስ አባላትን ጨምሮ እስካሁን በተለያየ ጊዜ ከ50 በላይ አባላት ክፍለ ጦራችን መርጠው የተቀላቀሉ ሲሆን እንደየ ምርጫቸው የሚታገሉ እየታገሉ የሚሸኙም የተሸኙ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሰላም ተቀላቅለዋል።
አርበኛ ሞላ ከፌ አክሎም የአድማ ብተና፣የመከላከያ፣ የሚኒሻ እና የፖሊስ አባላት አገዛዙ ፀሀይ እየጠለቀችበት ስለሆነ አሽከርነታቸውን አቁመው ህዝባቸውን መርጠው ህዝባዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ህዳር 2/2018 ዓም
🙏3
አማራነትን እንደ ወንጀል በቆጠረው የብልፅግና አገዛዝ ተይዘው ከሁለት ዓመታት በላይ በእስር ላይ የነበሩ የግፍ እስረኞች ከ13 ዓመት እስከ 23 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው!

የስርዓቱ አሻንጉሊት በመባል የሚታወቁት ፍርድ ቤቶች፡ እስረኞቹን ተደጋጋሚ የሆነ ፍትሕ አልባ ቀጠሮ በመስጠት ከሁለት ዓመታት በላይ ካመላለሷቸው በኋላ ነው ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም ባዋሉት ችሎት ብይኑን ያስተላለፉባቸው።

በምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉቴ ከተማ እና በሌሎች የዞኑ አከባቢዎች በአማራነታቸው ምክኒያት ለእስር ተዳርገው ነቀምት በሚገኘው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው ለዓመታት ሲከራከሩ የቆዩት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 13 ዓመት ከስድስት ወር እስከ 23 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት እንደተፈረደባቸው ታውቋል።

ከፍርደኞቹ መካከል የተወሰኑት በምርመራ ወቅት በተፈፀመባቸው ድብደባ የተነሳ ለከባድ የአካል ጉዳት መጋለጣቸውን ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት ለማረጋገጥ ችሏል።

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም ባዋለው ችሎት በሙሉቀን አንተነህ የክስ መዝገብ ስር ከሚገኙ ሦስት ንዑስ የክስ መዝገቦች መካከል አንዱ በሆነው በሰለሞን አሰፋ ክስ መዝገብ ተከሰው በእስር ላይ ሆነው ሲከራከሩ በቆዩ የአማራ ተወላጆ ላይ ፍርደ ገምድል የሆነ ብይን አስተላልፎባቸዋል።

በክስ መዝገቡ ከተከሰሱ 31 የአማራ ተወላጅ ተከሳሾች መካከል፡ 14ቱ ከሁለት ዓመታት በፊት ለእስር ከተዳረጉ በኋላ የዋስትና መብት ተነፍገው በማረሚያ ቤት የድብደባ መዓትና አይነት ሲፈፀምባቸው የቆዩ መሆናቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በችሎቱ፡ ከተከሳሾቹ መካከል 17ቱ በሌሉበት የእስር ፍርድ የተላለፈባቸው ሲሆን፡ ለእስር ከተዳረጉት 14 የአማራ ተወላጆች መካከል ሁለቱ በማረሚያ ቤት እንዳሉ በደረሰባቸው ድብደባ ምክኒያት ሕይወታቸው አልፏል፡ አንዱ ከመያዙ በፊት ከፀጥታ አካላት ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ ቆስሎ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ አልፏል ተብሎ ብይን ሳይተላለፍባቸው ቀርቷል።

በተጨማሪም በምርመራ ወቅት በተፈፀመባቸው ቶርች ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል የሚጠቀሱት ሦስቱ ተከሳሾች በነፃ የተሰናበቱ ሲሆን፡ ችሎቱ በስምንት ተከሳሾች ላይ 13 ዓመት ከስድስት ወር እስከ 23 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።

በዚህም፦
1ኛ፦ እሸቱ ከበደ 23 ዓመት
2ኛ፦ አበባው አድማሱ 23 ዓመት
3ኛ፦ ጌታቸው ሽፈራው 23 ዓመት
4ኛ፦ ሰለሞን አሰፋ 22 ዓመት
5ኛ፦ ጀማል ሲራጅ 14 ዓመት
6ኛ፦ አህመድ አያሌው 13 ዓመት ከ6 ወር
7ኛ፦ እንድሪስ ሀሰን 13 ዓመት ከ6 ወር
8ኛ፦ ስንታየሁ አዲስ 13 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል ነው ያሉት መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የግፍ ፍርደኞቹ ቤተሰቦች።

በችሎቱ የአማራ ተወላጅ እስረኞች ምንም አይነት መከላከያ እንዳያቀርቡ ታግደው ነበር የሚሉት ጣቢያችን ያነጋገራቸው የግፍ ፍርደኞቹ ቤተሰቦች፡ ከዚህ ቀደም በነበረው የክርክር ሂደት ላይም ፍርድ ቤቱ፡ የአገዛዙ ጠበቆች ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጋር እየተመሳጠሩ የሚያቀርቡትን ሀሰተኛ ማስረጃ ብቻ ነው ሲቀበል የቆየው ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል በርካታ የአማራ ተወላጆች አማራነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ በገፍ ታስረው በሚፈፀምባቸው ድብድባ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ሕይወታቸው ያልፋል።

በርካቶችም በተለይ የምስራቅ ወለጋ ዞን መቀመጫ በሆነችው ነቀምቴ ከተማ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን መቀመጫ በሆነችው ሻምቡ ከተማ ውስጥ ከሁለት ዓመታት በላይ ታስረው የሚገኙ ሲሆን፡ ከእስረኞቹ መካከል በምርመራ ወቅት በሚፈፀምባቸው ቶርች ጆሯቸው መስማት፣ አይናቸው ማየት እንዳቆመና ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስም እንደማይችሉ የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።
💔2