ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሰበር አሳዝኝ ዜና‼️

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን፡ አሰኮ ወረዳ በጡሌ ቢዮ ቀበሌ፤ ጠለታ አከባቢ 3 የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ ።

በምሥራቅ አርሲ ዞን፡ አሰኮ ወረዳ በጡሌ ቢዮ ቀበሌ፤ በቀን 01/3/2018 ዓ.ም ልዩ ቦታው ጠለታ ገብርኤል ደብር በተባለ  አከባቢ፤ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ፤ ሶስት ኦርቶዶክሳውያን በአውድማ ላይ እህል እየወቁ ሳሉ በጥይት ተደብድበው በግፍ ተገድለዋል ።

በዚህ ጨካኝና አረመኔ የኦነግ ሸኔ ቡድን እና በአስጨፍጫፊው ብልፅግና መራሹ መንግሥት፤ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች እና አማራ ስለሆኑ ብቻ ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል ። በዚህም፤ ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ፤

➣ ጥላሁን ቦጌ
➣ እዮብ እጅጉ ፡ እንዱሁም፤
#የ_10_ዓመት_ህፃን ልጅ፡ ፃድቃኔ ሰራዊቱ
የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን እና አማራ ግለሰቦች በዘግናኝ ሁኔታ እና  በግፍ ተገድለዋል ።

- የአከባቢውን ግፍና ሰቆቃ ገፈት-ቀማሾችን ነዋሪዎችን ለማነጋገር ሞክረናል፤ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል "በዚህ አገዛዝ ለብዙ አመታት እየተገደለን ፥ እተፈናቀልን ፥ እየታፈንን ፥ እየታረድን...እንገኛለን... 'ፍትህ' በሌለበት 'ፍትህ...ፍትህ...' ብለን ጮኸን ነበር፤ ነገር ግን አሁን የገባን እራሱ "መንግሥት ነኝ..." የሚለው አካል ነው የሚጨፈጭፈን ፥ የሚያስጨፈጭፈን..." ቀጥለውም "እኛ በአርሲ አከባቢ የምንኖር ኦርቶዶክሳውያን እና አማራዎች እንደ ዜጋ ተነጥለን ስለምንገደል፤ የዓለም መንግሥት  ሆይ አንድ መፍትሄ ሊያመጣልን ይገባል..." ሲሉ ነው ለከሰም ሚዲያ አቤቶታቸውን ያቀረቡት ።

ዘገባው፦ የአበባየሁ ሰይፈ ነው ።
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ የአውደ ውጊያ ሽንፈቱን መቀበል ሲያቅተው ንፁሃን ወጣቶች ላይ ነፃ እርምጃ መውሰዱንና ባደባባይ በግፍ መረሸኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል!

ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና መካነሰላም ከተማ ዙሪያ በኢንጅነር ደሳለኝ ክፍለጦር የደረሰበትን ሽንፈት መቋቋም ሲያቅተው ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘው በተለምዶ አባይ በር እየተባለች በምትጠራው መቅደላ ከተማ አምስት ንፁሃን ወጣቶች ላይ ነፃ እርምጃ በመውሰድ በግፍ አስፓልት ላይ ባደባባይ ረሽኗል::

በግፍ የተረሸኑት ወጣቶች ስም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው፦

1. ይታገስ አረጋ
2. መቻል ደርብ
3. እሸቱ ብሬ
4. ስመኘው ጥጋቡ
5. ሀብቴ አቢ ታመነ ሲሆኑ ሁሉም የአንድ ሰፈር የመቅደላ ከተማ ልጆች ናቸው።

ይህ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ፀረ-አማራ ተግባር ከክልሉ ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ በሰፊው ሲፈፀም የነበረ ያለና ታግለን ካላሸነፍነውና ካላስቆምነው ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ዘር ማጥፋት ዛሬ በሁሉም አማራ በር ላይ እያንኳኳ ያለ የእልቂት ድግስ ነው::

ስለሆነም የአማራ ህዝብ ሆይ በተለይ የአማራ ወጣቶች ጠላቶቻችን ሞት እልቂት ደግሰው ሞታችንን መዋቅራዊና ህገ-መንግስታዊ አድርገው የህዝባችን የጅምላ ሞት ቁጥር ሆኖ እንዲለመድ በማድረግ አማራው ሃይማኖት መንግስትና አገር አልባ እንዲሆን ተግተው ቀን ተሌት እየሰሩ ነውና አንተም ሞትህን እቤትህ ቁጭ ብለህ እያየኸው ከምትቀበለው ታግለህ ገዳይህን ገለህ ሞትህን እንድታስቆምና ሁለንተናዊ ህልውናህን እንድታረጋግጥ ዛሬም ባለመታከትና ፍፁም ተስፋ ባለመቁረጥ ጥሪያችንን እናቀርብልሃለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 1/2018 ዓ.ም
ለደብረ ኤልያስ ወረዳ መምህራንና የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ!!!

እነሆ ይህ ጡት ቆራጭ ኦሆዴድ መራሹ የብልፅግና ቡድን በአማራው ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውንና ሊፈጽመው ያቀደውን ሁለንተናዊ ጥፋት በደንብ ተረድታችሁ እያሳያችሁ ላለው ቁርጠኝነት ከልብ እናመሰግናለን።

ሆኖም በቀን 29/02/2018 ዓ.ም "የሚሉሽን በሰማሽ ገቢያ ባልወጣሽ" እንደሚባለዉ:ደብረ ኤልያስ ከተማ ውስጥ ተወሽቆ የሚገኘው የኦህዴድ አሽከሩ ጡት ቆራጩ የብልጽግና ስብስብ ከበላዮቹ የተሰጠውን የውሸትና የማታለያ ዘባተሎውን  ይነዛ ዘንድ "የውጭ ባዕዳዎች የውስጥ ባንዳዎች"ብሎ እየቀዣበረ በሰበሰባችሁ ሰዓት ያሳያችሁት ቁርጠኝነት አሰደስቶናል።

በዚሁ ስብሰባም "የግድ ሀሳብ መስጠት አለባችሁ"እያሉ ሲሳደቡ መዋላቸውን በውስጥ አርበኞቻችን በኩል ደርሶናል።

ከመሠረቱ በእውነት ሳይሆን በማስመሰል ተግባር የተሽሞነሞነው ይህ የጥፋት ስብስብ በእውነት አርበኞች አሁን ላይ መቃብራዊ ማንነቱ እየተገለጠ የውጩን መንቆጥቆጥ የሚያስንቅ ውሳጣዊ ጉስቁልናው እየተገለጠ ነው። በዚህ ስብሰባም የሆነው ይህ ነው።

ስለሆነም በአማራው ላይ የሚደርሰው ግፍና መከራ ያከትም ዘንድ ይህንን ግፈኛ አማራ ጠል  የብልፅግና  ቡድን በአንድነት ነቅለን እንድንጥል የተለመደውን የእምቢተኝነት አማራዊ ስነ ልቦናችሁን አጠንክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ቀኜ የውስጥ አርበኞቻችንም የምትሰሩት ስራ የሚየያስመሰግን ስኬታማ ነውና በርቱልን!!!
     

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!!!

በቴዎድሮስ ዕዝ በ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ
2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!

ፋኖ በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች ህዝባዊ መድረኮች እንደቀጠሉ ናቸው!
ህዳር 01/2018 ዓ.ም

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በተቆጣጠራቸው የላስታ ወረዳ ቀበሌዎች መካከል 02 ቀበሌ ብልባላ ገጠሩ የወልደንጉስ ህዝቦች ጋር የክፍለ ጦሩ አመራሮች ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም ጥልቅ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ የተካሄደው የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ አርበኛ ፋኖ አውራሪስ ደረሰና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ሲሆን ህዝቡም ሃሳቡን በነፃነት የገለፀበት ከአመራሮቹም በቂ ምላሽ የተሰጠበት መሆኑን ከህዝቡ በተገኙ አስተያየቶች ተረጋግጧል።

ህዝቡም ፋኖ ከመምጣቱ በፊት ሰብላችን ይበላና ይወድም ነበር፣የከብቶቻችን መዋያ ጥብቅ ስፍራዎች በህገወጥ በነፍስ ወከፍ ደኖች እየተጨፈጨፉ ለእርሻ ስራ ይውሉ ነበር፣ሌቦችና ወንበዴዎች በዝተው ነበር፣ህዝቡ በነፃነት ማሳ ውሎ አይመጣም ነበር፣በአጠቃላይ ህዝቡ በስጋትና በፍራቻ ቆፈን ውስጥ ይኖር ነበር ነገር ግን ፋኖ ከመጣ ወዲህ ነፃነታችንን አግኝተናል ስራዎችን እየሰራችሁ ነው የቀሩ ስራዎች ካሉ እነዛን በቶሎ ስሩና አስተካክሉልን ትግሉን እኛም እንደግፈዋለን ከጎናችሁ ነን በማለት ህዝቡ ለፋኖ ድጋፉን ችሮታል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ የፀዳው አመረ መረጃውን አድርሷል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 01/ 2018 ዓ.ም
🙏1
ሰበር ዜና

አረጋ ከበደ (ቀንዳውጣ ) ከፋኖ ጥይት ለጥቂት በማምለጥ ነፍሳቸውን አሽትተው ፈረጠጡ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር የተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃና የክፍለ ጦሩ ሜካናይዝድ በጋራ በመሆን ህዳር 01/2018 ዓ.ም ከጧቱ 2:30 እስከ ረፋዱ 3:30 ሰዓት በወሰዱት ጥቃት የክልሉ ፕሬዝዳንት ነኝ የሚሉት አረጋ ከበደ (ቀንድ አውጣ) ከባህርዳር ኤርፖርት በመነሳት ላሊበላ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ወደ ላሊበላ ከተማ በማቅናት ላይ እያሉ ሹምሽሃ አየር ማረፊያ አጠገብ ልዩ ስሙ በርታ በተባለ ቦታ ድንገተኛና የተጠና ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

በተወሰደባቸውም መብረቃዊ ጥቃት ከ10 በላይ ቀይ ቦኔት ለባሽ አጃቢዎቻቸው የተደመሰሱባቸው ሲሆን ፕሬዝዳንቱም ለጥቂት ከፋኖ በትር እንዳመለጡና ከአየር ማረፊያው ቅርብ ስለነበሩ መንገድ ቀይረው በሌላ አቅጣጫ እንደፈረጠጡ ታውቋል።

አገዛዙ ብልፅግና የመጨረሻው ህቅታ ላይ እንደሚገኝና የአለባብሰው ቢያርሱ የአዳራሽ ዲስኩር ህዝቡን እንደማያደናግረው ብሎም የፋኖ የድል ችቦና የአማራ ህዝብ ሰቆቃ የሚያበቃበት ዘመን እውን እየሆነ መምጣቱን የተከዜ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ ገልፀዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ኢንጅነር አማረ ካሳ መረጃውን አድርሷል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 01/ 2018 ዓ.ም
🙏1
ከመካነሰላም ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አባይ በር መቅደላ ከተማ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም በፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት በግፍ የተረሸኑ ወጣቶች!
ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ላይ ከባድ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል ተጎናፀፉ::

ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ ከመርጦ ወደ ወልድያ ከተማ ይጓዝ የነበረ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ አማየ ሚጫ በሚባል ቀጠና ደፈጣ በመያዝ በፈፀሙበት ጥቅት ኦራል ላይ የነበረውን ሙሉ ለሙሉ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በእግር ይጓዝ የነበረውን ከሙትና ቁስለኛ የተረፈውን ብትንትኑን በማውጣት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል::

በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ላይ የሚወሰደው እርምጃ በደፈጣ ጥቃት ረፍት በመንስስትና በማዋከብ እንዲማረር በማድረግ ሲያመች በመደበኛ ውጊያ በመደምሰስና በመማረክ ብሎም በማስኮብለል አገዛዙን የማፈራረሱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 1/2018 ዓ.ም
2🙏1
#የዘር_ማጽዳት_ጭፍጨፋው_ዛሬም_እንደቀጠለ_ነው!

ዛሬ ኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ምሥራቅ አርሲ፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠለታ ቅዱስ ገብርኤል በተባለ  አካባቢ ከጠዋቱ 3:00 ገደማ ሦስት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች (ኹለት ወንዶችና አንድ ሴት) በአውድማ ሥራ ላይ እህል እየወቁ ባሉበት በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። በርካቶች ታፍነው ተወስደዋል።

ከሰሞኑ ተቋቋመ የተባለው "አጣሪ ቡድን" ዛሬ ባወጣው መግለጫ በሃማኖታቸው ተመርጠው ዘር ማጽዳት/Genocide/ የሚፈጸምባቸውን አስተባብሎ ማውጣቱ እጅግ ያሳዘነን ተግባር ነው። ፓርቲያችን አኹንም ገለልተኛ ዓለም አቀፍ አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም በጥብቅ ያሳስባል።

እናት ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል በተለይ በአርሲ የሚፈጸምን ዘር ማጽዳትና ተደጋጋሚ ጭፍጨፋ በጽኑ ያወግዛል። በሃይማኖታቸው ተመርጠው እንደሞቱ ሲካዱ ገዳይን ማበረታታት በመኾኑ ይኽን ዓይነቱን እውነቱን የካደ አካሄድ ፈጽመን እናወግዛለን። ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሕዝብ በአንድነት ቆሞ ካልደረሰላቸው ለዘር እንደማይተርፉ ግልጽ እየኾነ መጥቷል። ፓርቲያችን ለሟቾችም እረፍተ ነፍስን ለአካባቢው ማኅበረሰብና ለወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ይመኛል።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ኅዳር ፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ. ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
👍2