ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በተለያዩ ከተሞች እየወጡ ስላሉ የመሬት ሊዝ ጨረታን አስመልክቶ ከአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ!

አማራን በአማራ ማውደምና ማጥፋት በሚል ፋሽስታዊ እሳቤ አማራንና የአማራን ሁሉ በሆድ አደር የአማራ ሚሊሻ፣ የአማራ ፖሊስ፣ የአማራ አድማ ብተና እና መከላከያ፤ በስልጣን መስተፋቅርና በሆዳቸው የወደቁ የአማራ ካድሬዎችን በመጠቀም በአማራ ላይ ጦርነት ከከፈተ ዓመታት ተቆጥረዋል።

ሰልቃጩ የአብይ አህመድ አገዛዝ አማራን ለማውደም ከሚከተለው አሠራር የአማራን አንጡራ ሃብት በመጠቀም አማራን መውጋት ሲሆን ለዚህ እኩይ ሥራው ግንባር ቀደም ተባባሪዎች እነዚህ የብልጽግና ስርዓት ደንገጡር ካድሬዎች እና የአማራ ሆድ አደር የጸጥታ አካላት ናቸው።

በክልሉ ውስጥ የሚገኝ የከተማ መሬት ደግሞ አገዛዙ ለዕኩይ ሥራው ተባባሪዎቹ ለሆኑት ከሃዲ ግለሰቦችና ማህበራት በሊዝ ስም የሚቸበችበው ሃብት ነው። ይሄንን አስመልክቶ ፋኖ ግልጽ የሆነ ማስገንዘቢያዎችንና ማስጠንቀቂያዎችን በተደጋጋሚ ለህዝብ ሲያድርስ ቆይቷል። ከሀምሌ 1 / 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የተፈጸመ የመሬት ሊዝ ግዥ በፋኖ ፊት እንደማይጸና (ለአማራ ሕዝብ እንደሚመለስ ማለትም እንደሚወረስ) እና እንደውም ለዚህ አውዳሚ ስርዓት ተባባሪነት ስለሆነ በወንጀል የምንጠይቅ መሆኑን በተደጋጋሚ አስጠንቅቀናል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በደሴ፣ በኮምቦልቻ እና በቆቦ በተለይም በወልደያ ከተማ ይሄው የመሬት ሽያጭ ተጠናክሮ መቀጠሉን በዕዛችን የመረጃና ደህንነት ክፍል ማረጋገጥ ችለናል።

የወልዲያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ከጥቅምት 12 እስከ 25/2018 ዓ.ም. ድረስ የቆየ የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ ያወጣ ቢሆንም ብዙሃኑ ሕዝባችን በዚህ ጨረታ ሊሳተፍ አልቻለም። በዚህ የሕዝባችን ንቃት በእጅጉ ደስ ብሎናል። ይሁን እንጂ አማራ ሆነው ሳለ ፀረ አማራ በመሆን ከአብይ አህመድ ስርዓት ጋር በመተባበር በአማራ ሕዝብ መቃብር ላይ ለመበልጸግ የሚናፍቁ ጥቂት የስርዓቱ የጥቅም ተጋሪዎች አሉ። ስለሆነም የወልድያ ከተማ ሆድ አደር ካድሬዎች በድጋሚ ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 2/2018 ዓ.ም. የመሬት ጨረታውን አራዝመው የሃጢያታቸው ተጋሪዎችን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የወልድያ ከተማ ባንዳዎች ከወልድያ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ወረድ ብሎ የሚገኘውን የአረጋውያን ማሕበር መሬት (መሰረት የወጣለትን ህጋዊ ይዞታ) የዚሁ የሊዝ ሽያጭ አካል በማድረግ ለጨረታ አቅርበውታል። አረጋውያን ማህበሩ ከ160 በላይ አረጋዊ አባላትን ያቀፈ ማህበር ነው።ይሁን እንጂ አረጋዊ ማህበሩ ህጋዊ ይዞታቸው ስለሆነ ባቀረቡት ቅሬታ 5 የማህበሩ ኮሚቴዎች በወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ተብዬው በባንዳው ዱባለ አብራሬ ትዕዛዝ ለእስር ተዳርገዋል። በዱባለ አብራሬ የታሰሩት የአረጋውያን ማህበርሩ ኮሚቴዎች አበበ ዳውድ (ሰብስቢ)፣ ሰፊው አማረ (የኮሚቴ አባል)፣ ምስጋናው ወርቁ (የኮሚቴ አባል)፣ ይማም መሃመድ (የኮሚቴ አባል) እና ሌሎችም ይገኙበታል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በዚህ የሊዝ ጨረታ ከገዳዩ የአብይ አህመድ ስርዓት ጋር ለመተባበር ላቀዳችሁ ሁሉ እንደወትሮው ወገናዊ ምክሩን ለማድረስ ይወዳል። ነገር ግን ለፋኖ ትዕዛዝ አሻፈረኝ ብሎ አማራን ሳላጠፋ አላርፍም በማለት በመደበኛና በኢ-መደበኛ ቅጥረኛ ሰራዊቱ አማራን በክልሉና በኦሮሚያ ውስጥ ለሚጨፈጭፍ የብልጽግና ስርዓት ተባባሪ የሚሆን ካለ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል።

በመጨረሻም በዛሬው ዕለት ለወልደያ ከተማ አስተዳደር ያወጣነው መግለጫ ለሁሉም ከተማ አስተዳደሮችና የወረዳ አስተዳደሮች እንደሚያገልግል እየገለጽን፣ ይሄን መመሪያ ጥሶ በተገኘ ሻጭም ሆነ ገዥ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እያሳወቅን፣ ከአገዛዙ ጋር ሽርክና የገባችሁ አካላት በሙሉ ገንዘባችሁን ከማባከን ወይም ከመበላት እንድታድኑ እያስታወስን፣ ይሄን መመሪያ ተላልፎ ከአገዛዙ ጋር የተሰለፈ ሁሉ ከአማራ ሕዝብ ነጻነት ማግስት የገዛችሁት መሬት ለሕዝብ፣ እናንተም በሕግ ተጠያቂ እንደምትሆኑ ማሳወቅ እንወዳለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ
ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም
1
አስደማሚው : ብቁ የፋኖ ኮማንዶ ሃይል!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮዝ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር የግዮን ብርጌድ ልዩ ኮማንዶ ተመራቂዎች።
🙏3
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!

የማህበረሰቡን የንፁህ መጠጥ ዉኃ ችግር የሚቀርፍ የውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ!

ህዳር 01/2018 ዓ.ም

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጄኔራል ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር በተቆጣጠራቸው ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ቀበሌዎች አንዱ የሆነው የ09 ቀበሌ ላልኪው ታዳጊ ከተማ ለረጅም ዓመታት የማህበረሰቡ ችግርና ዕጥረት የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውኃ አገልግሎት የቀረፈ የውኃ ፕሮጀክት የኮሩና የክፍለ ጦሩ አመራሮች እንዲሁም የወረዳው ወታደራዊ ሲቪል አስተዳደር፣የግብረ ሰናዩ ድርጅት አመራሮችና ማህበረሰቡ በተገኙበት የውኃ ፕሮጀክቱ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም ተመርቋል።

ይህ ፕሮጀክት ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ7 ነጥብ 5ሚሊዮን ብር የተሰራ ሲሆን ፕሮጀክቱ ተሰርቶ እስኪጠናቀቅም ክፍለ ጦሩ አስፈላጊውን ጥበቃና ድጋፍ እንዲሁም የወረዳው ወታደራዊ ሲቪል መዋቅር ህብረተሰቡን በማስተባበር በጉልበት እንዲሁም እንደ ጠጠር፣ድንጋይና አሸዋ ያሉ ግብዓቶችን በማቅረብ በትብብር በሦስት ወር አጭር ጊዜ ውስጥ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ መደረጉና ተመርቆ ለማህበረሰቡ፣ለትምህርት ቤት እንዲሁም ለጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ይህ በሶላር የሚሰራ የውኃ ፕሮጀክት ከ1500 በላይ አባውራና እማውራዎችን እንደሚያስጠቅም ታውቋል።

በመጨረሻም ኮሩ በተቆጣጠራቸውና በሚንቀሳቀስባቸው ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዞንና ሰሜን ወሎ ዞን ወረዳዎች መሰል የማህበረሰብ እንደ ንፁህ መጠጥ ውኃ አገልግሎት ዕጥረት ድርቅና ወረርሽኝ ችግሮችን እንድትቀርፉልን ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጥሪ እያስተላለፍን አስፈላጊውን ጥበቃና ከለላ፣የሰው ኃይል ጉልበትና የቁሳቁስ ድጋፍ ምቹ ሁኔታዎችን እንፈጥራለን ሲሉ የኮሩ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አርበኛ ፋኖ አለምነው መብራቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 01/ 2018 ዓ.ም
🙏1
ሰበር አሳዝኝ ዜና‼️

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን፡ አሰኮ ወረዳ በጡሌ ቢዮ ቀበሌ፤ ጠለታ አከባቢ 3 የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ ።

በምሥራቅ አርሲ ዞን፡ አሰኮ ወረዳ በጡሌ ቢዮ ቀበሌ፤ በቀን 01/3/2018 ዓ.ም ልዩ ቦታው ጠለታ ገብርኤል ደብር በተባለ  አከባቢ፤ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ፤ ሶስት ኦርቶዶክሳውያን በአውድማ ላይ እህል እየወቁ ሳሉ በጥይት ተደብድበው በግፍ ተገድለዋል ።

በዚህ ጨካኝና አረመኔ የኦነግ ሸኔ ቡድን እና በአስጨፍጫፊው ብልፅግና መራሹ መንግሥት፤ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች እና አማራ ስለሆኑ ብቻ ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል ። በዚህም፤ ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ፤

➣ ጥላሁን ቦጌ
➣ እዮብ እጅጉ ፡ እንዱሁም፤
#የ_10_ዓመት_ህፃን ልጅ፡ ፃድቃኔ ሰራዊቱ
የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን እና አማራ ግለሰቦች በዘግናኝ ሁኔታ እና  በግፍ ተገድለዋል ።

- የአከባቢውን ግፍና ሰቆቃ ገፈት-ቀማሾችን ነዋሪዎችን ለማነጋገር ሞክረናል፤ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል "በዚህ አገዛዝ ለብዙ አመታት እየተገደለን ፥ እተፈናቀልን ፥ እየታፈንን ፥ እየታረድን...እንገኛለን... 'ፍትህ' በሌለበት 'ፍትህ...ፍትህ...' ብለን ጮኸን ነበር፤ ነገር ግን አሁን የገባን እራሱ "መንግሥት ነኝ..." የሚለው አካል ነው የሚጨፈጭፈን ፥ የሚያስጨፈጭፈን..." ቀጥለውም "እኛ በአርሲ አከባቢ የምንኖር ኦርቶዶክሳውያን እና አማራዎች እንደ ዜጋ ተነጥለን ስለምንገደል፤ የዓለም መንግሥት  ሆይ አንድ መፍትሄ ሊያመጣልን ይገባል..." ሲሉ ነው ለከሰም ሚዲያ አቤቶታቸውን ያቀረቡት ።

ዘገባው፦ የአበባየሁ ሰይፈ ነው ።
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ የአውደ ውጊያ ሽንፈቱን መቀበል ሲያቅተው ንፁሃን ወጣቶች ላይ ነፃ እርምጃ መውሰዱንና ባደባባይ በግፍ መረሸኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል!

ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና መካነሰላም ከተማ ዙሪያ በኢንጅነር ደሳለኝ ክፍለጦር የደረሰበትን ሽንፈት መቋቋም ሲያቅተው ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘው በተለምዶ አባይ በር እየተባለች በምትጠራው መቅደላ ከተማ አምስት ንፁሃን ወጣቶች ላይ ነፃ እርምጃ በመውሰድ በግፍ አስፓልት ላይ ባደባባይ ረሽኗል::

በግፍ የተረሸኑት ወጣቶች ስም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው፦

1. ይታገስ አረጋ
2. መቻል ደርብ
3. እሸቱ ብሬ
4. ስመኘው ጥጋቡ
5. ሀብቴ አቢ ታመነ ሲሆኑ ሁሉም የአንድ ሰፈር የመቅደላ ከተማ ልጆች ናቸው።

ይህ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ፀረ-አማራ ተግባር ከክልሉ ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ በሰፊው ሲፈፀም የነበረ ያለና ታግለን ካላሸነፍነውና ካላስቆምነው ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ዘር ማጥፋት ዛሬ በሁሉም አማራ በር ላይ እያንኳኳ ያለ የእልቂት ድግስ ነው::

ስለሆነም የአማራ ህዝብ ሆይ በተለይ የአማራ ወጣቶች ጠላቶቻችን ሞት እልቂት ደግሰው ሞታችንን መዋቅራዊና ህገ-መንግስታዊ አድርገው የህዝባችን የጅምላ ሞት ቁጥር ሆኖ እንዲለመድ በማድረግ አማራው ሃይማኖት መንግስትና አገር አልባ እንዲሆን ተግተው ቀን ተሌት እየሰሩ ነውና አንተም ሞትህን እቤትህ ቁጭ ብለህ እያየኸው ከምትቀበለው ታግለህ ገዳይህን ገለህ ሞትህን እንድታስቆምና ሁለንተናዊ ህልውናህን እንድታረጋግጥ ዛሬም ባለመታከትና ፍፁም ተስፋ ባለመቁረጥ ጥሪያችንን እናቀርብልሃለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 1/2018 ዓ.ም
ለደብረ ኤልያስ ወረዳ መምህራንና የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ!!!

እነሆ ይህ ጡት ቆራጭ ኦሆዴድ መራሹ የብልፅግና ቡድን በአማራው ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውንና ሊፈጽመው ያቀደውን ሁለንተናዊ ጥፋት በደንብ ተረድታችሁ እያሳያችሁ ላለው ቁርጠኝነት ከልብ እናመሰግናለን።

ሆኖም በቀን 29/02/2018 ዓ.ም "የሚሉሽን በሰማሽ ገቢያ ባልወጣሽ" እንደሚባለዉ:ደብረ ኤልያስ ከተማ ውስጥ ተወሽቆ የሚገኘው የኦህዴድ አሽከሩ ጡት ቆራጩ የብልጽግና ስብስብ ከበላዮቹ የተሰጠውን የውሸትና የማታለያ ዘባተሎውን  ይነዛ ዘንድ "የውጭ ባዕዳዎች የውስጥ ባንዳዎች"ብሎ እየቀዣበረ በሰበሰባችሁ ሰዓት ያሳያችሁት ቁርጠኝነት አሰደስቶናል።

በዚሁ ስብሰባም "የግድ ሀሳብ መስጠት አለባችሁ"እያሉ ሲሳደቡ መዋላቸውን በውስጥ አርበኞቻችን በኩል ደርሶናል።

ከመሠረቱ በእውነት ሳይሆን በማስመሰል ተግባር የተሽሞነሞነው ይህ የጥፋት ስብስብ በእውነት አርበኞች አሁን ላይ መቃብራዊ ማንነቱ እየተገለጠ የውጩን መንቆጥቆጥ የሚያስንቅ ውሳጣዊ ጉስቁልናው እየተገለጠ ነው። በዚህ ስብሰባም የሆነው ይህ ነው።

ስለሆነም በአማራው ላይ የሚደርሰው ግፍና መከራ ያከትም ዘንድ ይህንን ግፈኛ አማራ ጠል  የብልፅግና  ቡድን በአንድነት ነቅለን እንድንጥል የተለመደውን የእምቢተኝነት አማራዊ ስነ ልቦናችሁን አጠንክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ቀኜ የውስጥ አርበኞቻችንም የምትሰሩት ስራ የሚየያስመሰግን ስኬታማ ነውና በርቱልን!!!
     

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!!!

በቴዎድሮስ ዕዝ በ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ
2