ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ሌላ ሰበር የአደረጃጀት ዜና

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ምስረታ ተጠናቀቀ። ላለፉት ተከታታይ ቀናት ማለትም ከጥቅምት14 ቀን 2018 ዓ.ም አስከ ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ምዕራፎች ሲካሄድ የቆየው የ206ኛ ኮር አካል የሆኑትን የ14ኛ፣ 24ኛ እና 34ኛ ክፍለ ጦርሮችን የመመስረት ሂደት አካታች እና አሳታፊ ውይይቶችንና ውሳኔዎችን በማሳረፍ እንዲሁም ደግሞ የክፍለ ጦር እና የሻለቃ አመራሮችን በመመደብ ጭምር ተጠናቅቋል።

በዛሬው ዕለት ማለትም ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም የ206ኛ ኮር የምስረታ መርሃ ግብር በይፋ  የተጠናቀቀ ሲሆን የ14ኛ፣24ኛ እና 34ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች በጋራ በተገኙበት መድረክ ላይ በከፍተኛ የድርጅቱ እና የኮሩ አመራሮች አማካኝነት ወደፊት ሊተገበሩ የሚገቡ የሥራ መመሪያዎች እና አቅጣጫዎች ለክፍለ ጦር አመራሮች ተሰጥቷል። በመርሃ ግብሩ ላይም የስናን አባጅሜ ብርጌድ እና የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ላለፉት ዓመታት ያደረጉትን ተጋድሎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከድርጅታችን አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በተያያዘም አስር አለቃ አለሙ ባንተይርጋ የተባለ የ60 ዓመት ሽማግሌ የፋኖ አባል ብቻውን 8 የጠላትን ሃይል በመደምሰስ ላሳየው ጀብዱ በድርጅታችን በኩል ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር!!
1
በመካነሰላም ዙሪያ ወረዳ በተደረገ ተጋድሎ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ኛ ክ/ጦር ሰራዊት ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት ታወቀ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጌታሰው አስረስ ብርጌድ፡ በመካነሰላም ዙሪያ ወረዳ ዛሬ ጥቅምት 30/2018 ዓ/ም በወሰደው እርምጃ ታላቅ ድል መጎናፀፉን የዕዙ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ አስታዉቋል።

በዚህም በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኙ የአንድ ጋንታ አባላት ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ፡ በክፍለጦሯ ላይ ተጨማሪ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል ነው ያለው ዕዙ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለጣቢያችን በላከው መረጃ።

ከፋኖ ጋር የእጅ በእጅ ውጊያ ማድረግ ያልቻለው የጠላት ኃይል በወረዳው በታዳጊዋ መቅደላ ከተማ የእሁድ ገበያ እየተገበያዩ በነበሩ ገበያተኞች ላይ የከባድ መሣሪያ ጥቃት በመፈፀም አምስት ንፁኋኖችን ሲገድል በርካቶችን ማቁሰሉ ታውቋል።
1
አፋብኃ ከውጊያ ጎን ለጎን አዲሱ ትውልድ የነፃነት ጥሙን በደሙ ለመቁረጥ ይሰበሰባል፣ ፣ ይደራጃል ፣ ይሰለጥናል ፣ ይታጠቃል ፣ ጠላቱን ታግሎ ያሸንፋል።

የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክ/ጦ ጀብደኛው ግዮን ብርጌድ ለአምስት ለወራት ያሰለጠናቸውን ልዩ የኮማንዶ አባላትን አስመርቋል።

በፕሮግራሙም የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ ም/ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ መቶ አለቃ ማርቆስ አሞኘ እና በተዋረድ በተለያዬ ኃላፊነት ያላቸው የዕዝ አመራሮች፣ የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክ/ጦር ወታደራዊ አዛዥ አምሳ አለቃ ደሞዝ ግርማ፣ የክፍለ ጦር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ መቶ አለቃ መለሰ አይናለም፣ የግዮን ብርጌድ ሰብሳቢ አምሳ አለቃ ተፈራ እንዲሁም የከቡሬ ዳሞት እና የአረንዛው ዳሞት ብርጌድ አመራሮች ታድመዋል::
1
አርበኝነት በጀግኖች መስዕዋትነት የደም ቀለም የሚከተብ ህያው የኪዳን ብራና ነው

ከአፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ የተላለፈ የሀዘን መግለጫ

ከጥንት ታሪካችን ከዛሬ ተግባራችን ከራስ በላይ ለሀገር ከራስ በላይ ለህዝብ በማስቀደም በላብ ተጠምቀን ደማችን አፍሰን አጥንታችን ከስክሰን አንጡራ ንብረት አባክነን በድልና በክብር ሀገር ፀንቶ እንደቆየና ዛሬም የህዝባችን ማንነታዊ ህልው ዕጣ አስቀጣይነት አርበኝነታችን መሆኑን እንገነዘባለን።

ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ አጅሬ የተሰኘች አነስተኛ ከተማ የጠላትን የእጅ አዙር ተልዕኮ ሳያነግቡ እንዳልቀረ በተጠረጠሩ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት የሰሜን አምባራስ ክ/ጦር አዛዥና የራስ አሞራው 3ኛ ኮር አስተዳደር ኃላፊ የሆነው ጀግናው አርበኛ ጌትነት መሳፍንት መስዕዋትነት ከፍሏል።

ከአስር ዓመት በላይ ከወላጅ አባቱ ከአይበገሬው አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ጋር በመሰለፍ የለጋነት ዕድሜውን ሁሉ በአርበኝነት በላቀ ወታደራዊ ብቃት በተሻለ ፖለቲካዊ ንቃት ፍዳ የገጠመውን የአማራ ህዝብ ለመታደግ አያሌ የጦር ግንባሮችን በድል የቋጨው ጌትነት መሳፍንት በተለያዩ ግንባር ተጋድሎዎች አምስት ጊዜ ቆስሎ የነበረ ቢሆንም ከቁስሉ ሳያገግም ፍልሚያ ተመልሶ እየተሰለፈ ሲሻው በክላሽ ሲሻው በብሬን ጠላትን እየገረፈ ድል ሲነሳ ኑሯል።

ወላጅ አባቱ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ፣አጎቱ መከተ ተስፉን፣ወንድሞቹ ሻምበል መሳፍንት፣ገብሬ መሳፍንትን ጨምሮ ከ30 በላይ ቤተሰቦቹ በነቂስ በተሰለፉበት የአስርት ዓመታት የአማራ ትግል የጨለማው ዘመን ፅልመት አለንልህ አማራ ብለው የተስፋ ጮራ ከፈነጠቁት ጀግና አርበኞች መካከል በለጋ ዕድሜያቸው የተሰለፉት ብላቴናዎች ጌትነት መሳፍንትና ሻምበል መሳፍንት እንደነበሩ ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ሀቅ ነው።

አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉ በድንገተኛ አጋጣሚ የህይወት መስዕዋትነት እስከከፈለበት ዕለት ድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በቀናነትና በጀግንነት የተሰጠውን ህዝባዊ ተልዕኮ ሁሉ ሲፈፅም ቆይቷል።

ከዚህ ቀደም በርካታ ቤተዘመድ በትግል መስዕዋትነት ያጣው የምንጊዜም ወደር የለሽ ጀግና አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የአብራኩ ክፋይ የሆኑትን ልጆቹን አርበኛ ገብሬ መሳፍንትና አርበኛ ጌትነት መሳፍንት በማጣቱ እንዲሁም የዕዛችን ጠንካራ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት መስዕዋትነት የተሰማንን ልባዊ ሀዘን እየገለፅን
አርበኝነት በጀግኖች መስዕዋትነት የደም ቀለም የሚከተብ ህያው የኪዳን ብራና ነውና አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉ እና ሌሎች እልፍ ጀግና አርበኞቻችን ዓላማ ግብ ለማድረስ ከመቸውም ጊዜ በላይ በብስለትና በቁርጠኝነት እንተጋለን።

ለወዳጅ ቤተ ዘመድ መፅናናቱን እንመኛለን!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም
አርበኝነት በጀግኖች መስዕዋትነት የደም ቀለም የሚከተብ ህያው የኪዳን ብራና ነው!!

1💔1
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ( ሸማቂው ኮማንዶ )
በተለያዩ ከተሞች እየወጡ ስላሉ የመሬት ሊዝ ጨረታን አስመልክቶ ከአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ!

አማራን በአማራ ማውደምና ማጥፋት በሚል ፋሽስታዊ እሳቤ አማራንና የአማራን ሁሉ በሆድ አደር የአማራ ሚሊሻ፣ የአማራ ፖሊስ፣ የአማራ አድማ ብተና እና መከላከያ፤ በስልጣን መስተፋቅርና በሆዳቸው የወደቁ የአማራ ካድሬዎችን በመጠቀም በአማራ ላይ ጦርነት ከከፈተ ዓመታት ተቆጥረዋል።

ሰልቃጩ የአብይ አህመድ አገዛዝ አማራን ለማውደም ከሚከተለው አሠራር የአማራን አንጡራ ሃብት በመጠቀም አማራን መውጋት ሲሆን ለዚህ እኩይ ሥራው ግንባር ቀደም ተባባሪዎች እነዚህ የብልጽግና ስርዓት ደንገጡር ካድሬዎች እና የአማራ ሆድ አደር የጸጥታ አካላት ናቸው።

በክልሉ ውስጥ የሚገኝ የከተማ መሬት ደግሞ አገዛዙ ለዕኩይ ሥራው ተባባሪዎቹ ለሆኑት ከሃዲ ግለሰቦችና ማህበራት በሊዝ ስም የሚቸበችበው ሃብት ነው። ይሄንን አስመልክቶ ፋኖ ግልጽ የሆነ ማስገንዘቢያዎችንና ማስጠንቀቂያዎችን በተደጋጋሚ ለህዝብ ሲያድርስ ቆይቷል። ከሀምሌ 1 / 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የተፈጸመ የመሬት ሊዝ ግዥ በፋኖ ፊት እንደማይጸና (ለአማራ ሕዝብ እንደሚመለስ ማለትም እንደሚወረስ) እና እንደውም ለዚህ አውዳሚ ስርዓት ተባባሪነት ስለሆነ በወንጀል የምንጠይቅ መሆኑን በተደጋጋሚ አስጠንቅቀናል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በደሴ፣ በኮምቦልቻ እና በቆቦ በተለይም በወልደያ ከተማ ይሄው የመሬት ሽያጭ ተጠናክሮ መቀጠሉን በዕዛችን የመረጃና ደህንነት ክፍል ማረጋገጥ ችለናል።

የወልዲያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ከጥቅምት 12 እስከ 25/2018 ዓ.ም. ድረስ የቆየ የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ ያወጣ ቢሆንም ብዙሃኑ ሕዝባችን በዚህ ጨረታ ሊሳተፍ አልቻለም። በዚህ የሕዝባችን ንቃት በእጅጉ ደስ ብሎናል። ይሁን እንጂ አማራ ሆነው ሳለ ፀረ አማራ በመሆን ከአብይ አህመድ ስርዓት ጋር በመተባበር በአማራ ሕዝብ መቃብር ላይ ለመበልጸግ የሚናፍቁ ጥቂት የስርዓቱ የጥቅም ተጋሪዎች አሉ። ስለሆነም የወልድያ ከተማ ሆድ አደር ካድሬዎች በድጋሚ ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 2/2018 ዓ.ም. የመሬት ጨረታውን አራዝመው የሃጢያታቸው ተጋሪዎችን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የወልድያ ከተማ ባንዳዎች ከወልድያ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ወረድ ብሎ የሚገኘውን የአረጋውያን ማሕበር መሬት (መሰረት የወጣለትን ህጋዊ ይዞታ) የዚሁ የሊዝ ሽያጭ አካል በማድረግ ለጨረታ አቅርበውታል። አረጋውያን ማህበሩ ከ160 በላይ አረጋዊ አባላትን ያቀፈ ማህበር ነው።ይሁን እንጂ አረጋዊ ማህበሩ ህጋዊ ይዞታቸው ስለሆነ ባቀረቡት ቅሬታ 5 የማህበሩ ኮሚቴዎች በወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ተብዬው በባንዳው ዱባለ አብራሬ ትዕዛዝ ለእስር ተዳርገዋል። በዱባለ አብራሬ የታሰሩት የአረጋውያን ማህበርሩ ኮሚቴዎች አበበ ዳውድ (ሰብስቢ)፣ ሰፊው አማረ (የኮሚቴ አባል)፣ ምስጋናው ወርቁ (የኮሚቴ አባል)፣ ይማም መሃመድ (የኮሚቴ አባል) እና ሌሎችም ይገኙበታል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በዚህ የሊዝ ጨረታ ከገዳዩ የአብይ አህመድ ስርዓት ጋር ለመተባበር ላቀዳችሁ ሁሉ እንደወትሮው ወገናዊ ምክሩን ለማድረስ ይወዳል። ነገር ግን ለፋኖ ትዕዛዝ አሻፈረኝ ብሎ አማራን ሳላጠፋ አላርፍም በማለት በመደበኛና በኢ-መደበኛ ቅጥረኛ ሰራዊቱ አማራን በክልሉና በኦሮሚያ ውስጥ ለሚጨፈጭፍ የብልጽግና ስርዓት ተባባሪ የሚሆን ካለ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል።

በመጨረሻም በዛሬው ዕለት ለወልደያ ከተማ አስተዳደር ያወጣነው መግለጫ ለሁሉም ከተማ አስተዳደሮችና የወረዳ አስተዳደሮች እንደሚያገልግል እየገለጽን፣ ይሄን መመሪያ ጥሶ በተገኘ ሻጭም ሆነ ገዥ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እያሳወቅን፣ ከአገዛዙ ጋር ሽርክና የገባችሁ አካላት በሙሉ ገንዘባችሁን ከማባከን ወይም ከመበላት እንድታድኑ እያስታወስን፣ ይሄን መመሪያ ተላልፎ ከአገዛዙ ጋር የተሰለፈ ሁሉ ከአማራ ሕዝብ ነጻነት ማግስት የገዛችሁት መሬት ለሕዝብ፣ እናንተም በሕግ ተጠያቂ እንደምትሆኑ ማሳወቅ እንወዳለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ
ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም
1